አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ብስጭቱ በረታ፣ ደሙ ፈላ፡፡ የሷ ድምጽ በከፊል ይሰማ ጀመር፤ ከምኔው ጀመሩ? የቅናት ስሜቱን መግራት አልቻለም፡፡ ራሱን ለመግዛት እና እርምጃ ለመውሰድ ደቂቃዎች ፈጀበት፡፡ በሩን በርግዶት ገባ፡፡ ሰውየው በድንጋጤ ፊቱን ወደደምሴ አዞረ፡፡
ደምሴ በሚመለከተው ነገር ግራ ተጋብቷል፡፡ ሰውየው በትራስ አፍኖ ሰላምን ጨርሷታል፡፡ ምን እየተካሔደ እንደሆነ ለማሰብ ጊዜ የለውም፡፡ ያቀባበለውን ሽጉጥ በሰውየው ደረት ላይ አነጣጥሮ ቃታውን ሳበ፡፡
#አማራጭ_ሁለት
አዲሱ የሰላም ፍቅረኛ ዛሬ አብሯት ሊያድር እንደሚፈልግ ነግሯታል፡፡ ሆኖም ሊዘገይ ስለሚችል እስከዛሬ የሚገናኙበት ሆቴል ውስጥ ክፍል ይዛ እንድትጠብቀው ነግሯታል፡፡
ሰላም አንዱ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላ ፍቅረኛዋን እየጠበቀችው ነው፡፡ ደምሴ እንዳይደውልባት ስልኳን አጥፍታዋለች፡፡ በሩ ተንኳኳ፡፡ ከፊል ራቁቷን ነች፡፡ ፍቅረኛዋ ሰዐት አክባሪ ነው፡፡ ልክ በነገራት ሰዓት ከች በማለቱ ተደስታ በሙሉ ፈገግታ በሩን ከፈተችለት፡፡
አዲሱ ፍቅረኛዋ ብቻውን አልነበረም፤ ደምሴ አብሮት አለ፡፡ ከፊት ለፊቷ የምታየው ነገር ሰውነቷን አራደው፡፡ ከፊል እርቃኗን እንዳያዩባት ለመደበቅም የፈለገች መሰለች፡፡ ከንፈሯ ተንቀጠቀጠ እንጂ መናገር አልቻለችም፡፡ እንግዶቿ ያለግብዣዋ ገብተው በሩን ዘጉት፡፡ ምክንያቷን ሳያዳምጡ፣ ለስሜቷም ሆነ ለምላሽዋ ሳይጨነቁ ሰማይ በሚበሳ ድምጽ እየተፈራረቁ አምባረቁባትና ሲበቃቸው ወጡ፡፡
ሁለቱንም ማጣት ያልፈለገችው ሰላም ከሁለት አንዱንም ከማጣት የበለጠ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማት፡፡
ወድ አንባብያን፡-
ምርጫችሁ የቱ ነው? የቱንም ብትመርጡ የምርጫችሁ ቅጣት ግዞተኛ መሆናችሁ እንደማይቀር ጸሃፊው ያስባል፤ ምርጫችሁ ያውጣችሁ!!!

እስቲ ምርጫችሁን 👉 @atronosebot ላይ አሳዉቁኝ
👍2