አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ጉዳዩ #ልምድን_ስለመጻፍ

ይድረስ ለማፈቅርሽ..ይድረስ ለምወድሽ
ጠልተሽ ላባረርሽኝ..በገዛ ፈቃድሽ::
ቀድሞ ለነበርሽው..የፍቅር አቻዬ
በቅጡ ይጤንልኝ..ይህ ማመልከቻዬ::-
ጥረቴን..ልፋቴን..ድካሜን..ትጋቴን..
ለፍቅር እንደገበርኩ..ቀንና ሌሊቴን..
ችዬ ያካበትኩትን..የዘመናት ልምዴን..
ከልብ ማፍቀሬን..አጥብቄ መውደዴን..
...ንፁህ ሆኜ መኖሬን..
ፈጣሪን መፍራቴን..
...ፍጥረቱን ማክበሬን..
ልዩ ሐሴትእንዳለኝ..ማንም እማይቀማኝ..
እንደሆንኩኝ ታማኝ..እንደነበርኩ አማኝ..
ካሻሽ ወንጀለኛ..
ወይም ኃጢኃተኛ..
ሁሉንም ዘርዝረሽ..በይፋ አውጂልኝ
የሔዋን ዘር በሙሉ..ልምዴን እንዲያውቅልኝ
"ለሚመለከተው ሁሉ"
በሚል ዐብይ ርዕስ..ማስረጃ ጻፊልኝ::
ከሰላምታ ጋር
ያንቺው የፍቅር አጋር!!