#ስትናፍቂኝ
:
ናፍቆት ያደመነው
የናፋቂሽ ውብ ፊት
ከ...ዝርጉ ሸራ ላይ .. በ'ሰማይ ተሰቅሎ
እንደ ሐምሌ ሠማይ
የ'ጭጋግን አድባር
ሲያላዝን ውሎ ያድራል .. በጉም ተከልሎ
ያ .. .. የ'ሐምሌ ሠማይ
በመብረቅ ብልጭታ
በ'ቅፅበት ድን'ፋታ
ፍጥረታቱን ሚያርድ .. ሚያርበደብደው
ስነግረው የነበር
የ'ትዝታዬን ጥግ
የናፍቆቴን መጠን .. መሸከም ከብዶት ነው
ብዬሽም አልነበር .. ?
.
(ደግሞሳ ..!)
.
ያው .. የ'ሐምሌ ሠማይ
.
በፅኑ ታመመ .. ህመሙም በረታ
ሀዘኑ ቅጥ ኣጣ .. ከ'ደስታ ተፋታ
ናፍቆት አጠላበት .. ጉጉት አደከመው
የ'ጨረቃ ፍካት
የፀሐይም ድምቀት ~ እያደረ ሸሸው
ብዬሽስ አልነበር .. ?
.
.
.
አይተሻል ሰማዩን
አይተሻል ስሜቱን
በ'ተሳለ ናፍቆት ~ ተወግቶ መውደቁን?
.
.
አይተሻል ህመሙን
አይተሻል አለሙን
ከ'ጀምበር ተፋቶ .. ፅልመቷን መውረሱን
.
(ታድያ ምነው ውዴ ..!)
.
ናፍቆትህ እስከ ምነው
ምን ያህል ይገዝፋል
ምን ያህል ይርቃል ..?
ብለሽ መጠየቅሽ
በ'ነገርኳት ብቻ
የሠማይዋ ጀምበር .. ስትጠልቅ እያየሽ
.
(ኣዬሽ!
በ'መናፈቅ አለም .. በ'መናፈቅ ምድር
የናፍቆትን ህመም
ማንም አያውቀውም .. ከ'ናፋቂው በቀር)
:
:
እናም ..
:
:
እገልፅበት ቃላት
አወራበት ሀሳብ .. ያጥረኛል ያጥረኛል
ብቻ ስትናፍቂኝ
እንደ ሐምሌ ሠማይ .. ያነጫንጨኛል
:
ናፍቆት ያደመነው
የናፋቂሽ ውብ ፊት
ከ...ዝርጉ ሸራ ላይ .. በ'ሰማይ ተሰቅሎ
እንደ ሐምሌ ሠማይ
የ'ጭጋግን አድባር
ሲያላዝን ውሎ ያድራል .. በጉም ተከልሎ
ያ .. .. የ'ሐምሌ ሠማይ
በመብረቅ ብልጭታ
በ'ቅፅበት ድን'ፋታ
ፍጥረታቱን ሚያርድ .. ሚያርበደብደው
ስነግረው የነበር
የ'ትዝታዬን ጥግ
የናፍቆቴን መጠን .. መሸከም ከብዶት ነው
ብዬሽም አልነበር .. ?
.
(ደግሞሳ ..!)
.
ያው .. የ'ሐምሌ ሠማይ
.
በፅኑ ታመመ .. ህመሙም በረታ
ሀዘኑ ቅጥ ኣጣ .. ከ'ደስታ ተፋታ
ናፍቆት አጠላበት .. ጉጉት አደከመው
የ'ጨረቃ ፍካት
የፀሐይም ድምቀት ~ እያደረ ሸሸው
ብዬሽስ አልነበር .. ?
.
.
.
አይተሻል ሰማዩን
አይተሻል ስሜቱን
በ'ተሳለ ናፍቆት ~ ተወግቶ መውደቁን?
.
.
አይተሻል ህመሙን
አይተሻል አለሙን
ከ'ጀምበር ተፋቶ .. ፅልመቷን መውረሱን
.
(ታድያ ምነው ውዴ ..!)
.
ናፍቆትህ እስከ ምነው
ምን ያህል ይገዝፋል
ምን ያህል ይርቃል ..?
ብለሽ መጠየቅሽ
በ'ነገርኳት ብቻ
የሠማይዋ ጀምበር .. ስትጠልቅ እያየሽ
.
(ኣዬሽ!
በ'መናፈቅ አለም .. በ'መናፈቅ ምድር
የናፍቆትን ህመም
ማንም አያውቀውም .. ከ'ናፋቂው በቀር)
:
:
እናም ..
:
:
እገልፅበት ቃላት
አወራበት ሀሳብ .. ያጥረኛል ያጥረኛል
ብቻ ስትናፍቂኝ
እንደ ሐምሌ ሠማይ .. ያነጫንጨኛል
👍1