አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከኢንጅነር_ናዝራዊት_የተላከ

😥😥እናንተዉ ውለዱኝ😢


"በቅን አስተሳሰብ በገራገር ልቤ
የታሸገ ሻንጣ በስሜ አስመዝግቤ
እኔም እንደባሕራን የሞቴን ደብዳቤ
መልክቴን ለማድረስ ሳላየው አንብቤ

ተሰናበትኩና የሀገሬን ጓዳ
በእምነት ገሰገስኩ ወጣሁ በማለዳ

ከኢትዮጵያ አየር ከአፈሯ ስርቅ
ባየር ተሳፍሬ ስሔድ እሩቅ ምስራቅ
ምኞቴ ሊሳካ በደስታ ስቦርቅ

አውሮፕላን ወርዶ ከሀገረ ቻይና
በፍቅር ደርሼ በሰላም በጤና
ሀገሩን አፈሩን ባይኔ ሳላይ ገና
በኋላ በፊቴ ከበቡኝ መጡና

እጀግ ደነገጥኩኝ ሆዴም ተሸበረ
ከቶ ምን ወረደ ምንስ ተፈጠረ

በሴትነት መንፈስ በሰፍሳፋ አንጄቴ
ጨለማ ሲውጠኝ ጠፋኝ እኔነቴ

እራሴን ስፈልግ ራሴ ጠርጥሬ
ራሴን ስጠይቅ ራሴን መርምሬ

ናዝራዊት አይደለሁ ሌላ ሴት ነኝ እኔ
አደንዛዥ ዕፅ ሰቶ የላከኝ ወገኔ

መሞት መገደልን ካገሬ ሳላጣው
እንዴት ሞት ፍለጋ ወደቻይና መጣሁ?

እኔ ለመሆኔ ባይኖርም መረጃ
ለካስ እኔ ሳላውቅ ያገሬ ምድጃ

ውጭ ውጭ ብሎ ሸኝቶ የላከኝ
በሞት ብያኔ ነው ካገር ያሾለከኝ

እናማ ወገኔ የሀገሬ ዜጋ
እኔም ሳልሰቀል እንደ ፍየል ሥጋ

የታነቀችን ነብስ በብርቱ ፈልጉ
ድምጻችሁን ስጡኝ ሳትሳሱ ሳትነፍጉ

እኔ እንደባሕራን ነኝ ሞቴን ተሸካሚ
መላኩን ላኩልኝ ለህይወቴ ቋሚ

መላክ ፈልጉልኝ የሚታመን ቃሉ
ጦማር የሚለውጥ እፍ ብሎ በቃሉ

ሚካኤልን ጥሩት ገብርኤልን ላኩልኝ
የሞቴን ደብዳቤ የሠርግ ያድርጉልኝ

ዳንኤልን ጥሩት ባንድ ድምጽ ሁኑና
በረበናት ቅጣት እንዳትሞት ሶስና

ወገን ድምጽ ሰጠኝ ናፍቆቱ ከብዶኛል
ድምጽ ደምጽ የሚያሰኝ ስስት አድሮብኛል

እናቴ ብትወልደኝ ዘጠኝ ወር አርግዛ
ከናቴ ማሕጸን ወጥቼ እንደዋዛ
እንዳትቀር እናቴ ፎቶ ብቻ ይዛ

አዋቂ በእውቀቱ አማኝ በጸሎቱ
ሰው የሚፈጥርበት አሁን ነው ሰዐቱ

የሞት የልደቴን ቀን እየጠበኩኝ
ደግሞኛ ጽንስ ሁኜ ስለተረገዝኩኝ
ነብሴን ሳያጠፉት በጽንሴ ሳይጎዱኝ

እናንተ አምጣችሁ እናንተ ወለዱኝ"
15/7/2011

🔘በመምህር ኤፍሬም ተስፋ🔘

http://chng.it/YPY2Z4ZMfg
👍2