#ሀገሬ... 🇪🇹
:
:
በከባድ ንፋስና የዝናብ ሰዐት ትልልቅ ዛፎችን ዐይታችሁ ታውቃላችሁ ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፤ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ፤ "ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ...ካሁን አሁን ተገነደለ..." ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል።
ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፤ ቅጠሎቹ ባድነት ቢረግፉም፤ ግንዱን ብትመለከቱ ግን አይነቃነቅም።
ምክንያቱም ስር የሰደደ ነው።
ምክንያቱም መሬትን ቆንጥጦ ያየዘ ነው።
ምክንያቱም ጠንካራ ነው።
ምክንያቱም ግንድ ነው። እና...እኔ ፤ ሀገሬ ግንዱን ትመስለኛለች። ቅርንጫፎቹ መንግስታቷን። ቅጠሎቹ ደግሞ ማለዳ እንደ አዲስ በቅለው ማምሻውን እንደ አሮጌ የሚረግፉ ባለስልጣናቷን።
እና...
ሀገሬ ምን ጋኖች አልቀውባት በምንቸቶች ብትሞላ፤ ምን ለአንዱ በስንዝር ለሌላው በሄክታር ብትታደል፤ ዘወትር በእመቤት ወግ ባትኖር፤
በጭጋጋማ ቀናት ብትሸነፍም፣ በውርጭ ብትንዘፈዘፍም ፣ በብርቱ ንፍስ ብትናወጥም፣ በዶፍ ዝናብ ብትደበደብም
ሀገሬ ግንድ ናትና ንቅንቅ አትልም።
ዐውሎ ንፋስ በተነሳ ቁጥር ፣ ከባድ ዝናብ በጣለ ቁጥር፣ ትልቅ ዛፍ ሁሉ ቢወድቅ ዛፍ አይኖርም ነበር።
ነውጥ በተነሳ ጊዜ ሁሉ፣
ፈተና በበዛ ሰዓት ሁሉ፣
ሀገር የምትወድቅ ቢሆን ኖሮ #ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር።
#ኢትዮጵያ ግን ቅርንጫፍ ስላልሆነች በቀላሉ አትቀነጠስም።
ቅጠል ስላልሆነች እንደዋዛ አትረግፍም።
ይልቅስ ፣ ለዘላለም ስር እንደሰደደች ትኖራለች።
💚ኢትዮጵያ 💛ለዘላላም ❤️ትኑር
:
:
በከባድ ንፋስና የዝናብ ሰዐት ትልልቅ ዛፎችን ዐይታችሁ ታውቃላችሁ ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፤ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ፤ "ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ...ካሁን አሁን ተገነደለ..." ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል።
ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፤ ቅጠሎቹ ባድነት ቢረግፉም፤ ግንዱን ብትመለከቱ ግን አይነቃነቅም።
ምክንያቱም ስር የሰደደ ነው።
ምክንያቱም መሬትን ቆንጥጦ ያየዘ ነው።
ምክንያቱም ጠንካራ ነው።
ምክንያቱም ግንድ ነው። እና...እኔ ፤ ሀገሬ ግንዱን ትመስለኛለች። ቅርንጫፎቹ መንግስታቷን። ቅጠሎቹ ደግሞ ማለዳ እንደ አዲስ በቅለው ማምሻውን እንደ አሮጌ የሚረግፉ ባለስልጣናቷን።
እና...
ሀገሬ ምን ጋኖች አልቀውባት በምንቸቶች ብትሞላ፤ ምን ለአንዱ በስንዝር ለሌላው በሄክታር ብትታደል፤ ዘወትር በእመቤት ወግ ባትኖር፤
በጭጋጋማ ቀናት ብትሸነፍም፣ በውርጭ ብትንዘፈዘፍም ፣ በብርቱ ንፍስ ብትናወጥም፣ በዶፍ ዝናብ ብትደበደብም
ሀገሬ ግንድ ናትና ንቅንቅ አትልም።
ዐውሎ ንፋስ በተነሳ ቁጥር ፣ ከባድ ዝናብ በጣለ ቁጥር፣ ትልቅ ዛፍ ሁሉ ቢወድቅ ዛፍ አይኖርም ነበር።
ነውጥ በተነሳ ጊዜ ሁሉ፣
ፈተና በበዛ ሰዓት ሁሉ፣
ሀገር የምትወድቅ ቢሆን ኖሮ #ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር።
#ኢትዮጵያ ግን ቅርንጫፍ ስላልሆነች በቀላሉ አትቀነጠስም።
ቅጠል ስላልሆነች እንደዋዛ አትረግፍም።
ይልቅስ ፣ ለዘላለም ስር እንደሰደደች ትኖራለች።
💚ኢትዮጵያ 💛ለዘላላም ❤️ትኑር
#የወታደር_ልጅ_ነኝ
አባቴ ሃገሬን የሚመስለኝ፣
ሃገሬ ነብሴን የምትመስለኝ፣
ተነካች ሲሉኝ ነብሴን የሚያመኝ፣
ከሃገር ፈትል የተሸመንኩ
የሰንደቅ ፍቅር ያሳደገኝ፣
በኢትዮጵያ ጉዳይ ቀልድ የማላውቅ
የበረኸኛው ጀግና ልጅ ነኝ፡፡
#ኢትዮጵያ ማለት ለእኛ ቤት ...!
የነገራችን ማጠንጠኛ፣
የምኞታችን መዳረሻ፣
የቤተሰባችን አበይት ጉዳይ፣
የአባታችን ማስታወሻ
የማትታይ ኣባወራ
የፀሎታችን ማሳረጊያ፣
ሃገር ማለት አባታችን
አባት ማለት ኢትዮጵያ፡፡
አባቴ ማለት ያገሬ አምሳል፣
የማይታይ በአካል መጥቶ
በሃሳቤ ብቻ የሚሳል
ጠቁሮ የሚያምር እንደ አፈሯ፣
የማልጨብጠው እንደ አየሯ
ጠምቶት ሳስበው የምጠማ
ምንጮቿ ያስቡህ የሚያስብለኝ፣
እርቦት ስስለው በምናቤ
ቀጋዋ ያጥግብህ የሚያሰኘኝ፣
ደክሞት ይሆን? ብዬ ሳስብ
የዛፍ ጥላዋን ለእሱ የምመኝ፣
አባቴን ከሃገሬ ፀጋ
ነጥሎ ማሰብ የተሳነኝ፣
ኢትዮጵያ ሲባል አቤት የምል
የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
ወጥቶ አዳሪ ነው ከርታታ
እረፍት አያውቁም እግሮቹ፣
ድንበሯን ሲቃኙ ያድራሉ
አያንቀላፉም አይኖቹ፡፡
ፍራሽ አያውቅም ለእረፍቱ
አባቴ አሸዋ ልብሱ፣
የምቾቱ ነገር አይገደውም
አለት ነው ድንጋይ ትራሱ፡፡
ምን ቢጎሰቁል አካሉ በረሃብ ቢታጠፍ አንጀቱ፣
ወዙ ተመጥጦ ቢጠወልግ አመዳይ ቢመስል ፊቱ
የእግሮቹ ጣቶች አዝለው ውሃ ጀርባው ቢረሰርስ በላቡ፣
የሃገሩን ኪዳን ያኖረበት ሁሌም ፅኑ ነው ታማኝ ልቡ፡፡
አባቴ ሃገሬን የሚመስለኝ፣
ሃገሬ ነብሴን የምትመስለኝ፣
ተነካች ሲሉኝ ነብሴን የሚያመኝ፣
ከልብ ምቴ እኩል የማስባት
ከሷ ውጭ ማሰብ የተሳነኝ፣
በኢትዮጵያ ስም አፍ የፈታሁ
የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
አባቴ የበረሃው ፈርጥ የኔ አባት የሰውነት ጥግ፣
ሃገር ነች እምነት ማተቡ ሃቅ ነው ያሳየኝ ፈለግ፡፡
እስከ ሞት ለወደደው ህዝብ ዘብ ለቆመላት ሃገሩ፣
በደም ለለማች አፈሩ አጥንት ላጠራት ድንበሩ
ሺ ጊዜ ቢሰዋ የሚወድ ቃሉን በተግባር ያፀና፣
የኔ አባት ሃገር አፍቅሮ ልጁን የረሳኝ ሳተና፣
አባቴ ሰንደቁን ሊያቆም በረሃ የወደቀ ጀግና፣
እኔም የአባቴ ልጅ የገባኝ ውትድርና፣
አባቴ ካልሰጠኝ ጊዜ ለሃገር በሰጠው የምፅናና
በእንቶ ፈንቶ የማልበረግግ ሃቀኝነት ህግ የሆነኝ፣
በሃገሬ ጉዳይ ቀልድ የማላውቅ የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
አባቴ ሃገር ርስቱ ከርታታው አያርፌ እግሮቹ፣
ስትናፍቀው እናቴ ስንርበው እኛ ልጆቹ፣
ለሃገሩ ይነግራት ይሆናል ከሰንደቋ አርፈው አይኖቹ
እንጂማ ደግሞ ደጋግሞ የልጆቹ ልደት ቢመጣ፣
አባቴ ሃገር ነውና ወደ ቤታችን አይመጣ፡፡
በአል አውደ ዓመት ቢሆንም ገና ፋሲካ ሲከበር፣
አውቃለሁ አባቴ አይመጣም ለምጄው አይለኝም ቅር፡፡
ተምሬ ስመረቅ ይሁን ወይ ተሞሽሬ ለሰርጌ፣
አባቴን አልጠብቀውም አይመጣም ለወግ ማዕረጌ፡፡
ይልቅስ ለሰርጌ ድምቀት በተዘረጋው ባንዲራ፣
ያባቴን ምስል እየሳልኩ እቀበላለሁ ምርቃት
እረከባለሁ አደራ፡፡
የወታደር ልጅ ነኝና የአባቴ ምስል የሚነግረኝ
የሚመርቀኝ ምርቃት፣
‹‹ልጄ ሃገርሽን ውደጃት
ከትቢያት በማይለቅ ቀለም
ወታደር ለልጁ የሚያወርሰው
ከሃገር ፍቅር በቀር የለም” ::
እንዴት አልወዳት ሃገሬን
የነብሴን ደማቅ ንቅሳት፣
በሃዘንና ደስታዋ ውስጥ
የአባቴን እውነት የማይባት፣
አባቴ ማለት ኢትዮጵያ
ሃገሬ ደግሞ የኔ አባት፡፡
አባቴ ሃገሬን የሚመስለኝ፣
ሃገሬ ነብሴን የምትመስለኝ፣
ተነካች ሲሉኝ ነብሴን የሚያመኝ፤
የሀገሬ ፍቅር አቅል ያሳጣኝ
ያለ ሃገር ማሰብ የተሳነኝ
በኢትዮጵያ ስም አፍ የፈታሁ ፣
የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
🔘ሻለቃ /ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በሸለ🔘
መታሰቢያነቱ ለሃገር ዳርድንበር መከበር በጦር ግንባር ለተሰዋው አባቴ
፲/አ በቀለ ታደሰና ለወታደር ልጆች ሁሉ ይሁንልኝ፡፡
አባቴ ሃገሬን የሚመስለኝ፣
ሃገሬ ነብሴን የምትመስለኝ፣
ተነካች ሲሉኝ ነብሴን የሚያመኝ፣
ከሃገር ፈትል የተሸመንኩ
የሰንደቅ ፍቅር ያሳደገኝ፣
በኢትዮጵያ ጉዳይ ቀልድ የማላውቅ
የበረኸኛው ጀግና ልጅ ነኝ፡፡
#ኢትዮጵያ ማለት ለእኛ ቤት ...!
የነገራችን ማጠንጠኛ፣
የምኞታችን መዳረሻ፣
የቤተሰባችን አበይት ጉዳይ፣
የአባታችን ማስታወሻ
የማትታይ ኣባወራ
የፀሎታችን ማሳረጊያ፣
ሃገር ማለት አባታችን
አባት ማለት ኢትዮጵያ፡፡
አባቴ ማለት ያገሬ አምሳል፣
የማይታይ በአካል መጥቶ
በሃሳቤ ብቻ የሚሳል
ጠቁሮ የሚያምር እንደ አፈሯ፣
የማልጨብጠው እንደ አየሯ
ጠምቶት ሳስበው የምጠማ
ምንጮቿ ያስቡህ የሚያስብለኝ፣
እርቦት ስስለው በምናቤ
ቀጋዋ ያጥግብህ የሚያሰኘኝ፣
ደክሞት ይሆን? ብዬ ሳስብ
የዛፍ ጥላዋን ለእሱ የምመኝ፣
አባቴን ከሃገሬ ፀጋ
ነጥሎ ማሰብ የተሳነኝ፣
ኢትዮጵያ ሲባል አቤት የምል
የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
ወጥቶ አዳሪ ነው ከርታታ
እረፍት አያውቁም እግሮቹ፣
ድንበሯን ሲቃኙ ያድራሉ
አያንቀላፉም አይኖቹ፡፡
ፍራሽ አያውቅም ለእረፍቱ
አባቴ አሸዋ ልብሱ፣
የምቾቱ ነገር አይገደውም
አለት ነው ድንጋይ ትራሱ፡፡
ምን ቢጎሰቁል አካሉ በረሃብ ቢታጠፍ አንጀቱ፣
ወዙ ተመጥጦ ቢጠወልግ አመዳይ ቢመስል ፊቱ
የእግሮቹ ጣቶች አዝለው ውሃ ጀርባው ቢረሰርስ በላቡ፣
የሃገሩን ኪዳን ያኖረበት ሁሌም ፅኑ ነው ታማኝ ልቡ፡፡
አባቴ ሃገሬን የሚመስለኝ፣
ሃገሬ ነብሴን የምትመስለኝ፣
ተነካች ሲሉኝ ነብሴን የሚያመኝ፣
ከልብ ምቴ እኩል የማስባት
ከሷ ውጭ ማሰብ የተሳነኝ፣
በኢትዮጵያ ስም አፍ የፈታሁ
የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
አባቴ የበረሃው ፈርጥ የኔ አባት የሰውነት ጥግ፣
ሃገር ነች እምነት ማተቡ ሃቅ ነው ያሳየኝ ፈለግ፡፡
እስከ ሞት ለወደደው ህዝብ ዘብ ለቆመላት ሃገሩ፣
በደም ለለማች አፈሩ አጥንት ላጠራት ድንበሩ
ሺ ጊዜ ቢሰዋ የሚወድ ቃሉን በተግባር ያፀና፣
የኔ አባት ሃገር አፍቅሮ ልጁን የረሳኝ ሳተና፣
አባቴ ሰንደቁን ሊያቆም በረሃ የወደቀ ጀግና፣
እኔም የአባቴ ልጅ የገባኝ ውትድርና፣
አባቴ ካልሰጠኝ ጊዜ ለሃገር በሰጠው የምፅናና
በእንቶ ፈንቶ የማልበረግግ ሃቀኝነት ህግ የሆነኝ፣
በሃገሬ ጉዳይ ቀልድ የማላውቅ የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
አባቴ ሃገር ርስቱ ከርታታው አያርፌ እግሮቹ፣
ስትናፍቀው እናቴ ስንርበው እኛ ልጆቹ፣
ለሃገሩ ይነግራት ይሆናል ከሰንደቋ አርፈው አይኖቹ
እንጂማ ደግሞ ደጋግሞ የልጆቹ ልደት ቢመጣ፣
አባቴ ሃገር ነውና ወደ ቤታችን አይመጣ፡፡
በአል አውደ ዓመት ቢሆንም ገና ፋሲካ ሲከበር፣
አውቃለሁ አባቴ አይመጣም ለምጄው አይለኝም ቅር፡፡
ተምሬ ስመረቅ ይሁን ወይ ተሞሽሬ ለሰርጌ፣
አባቴን አልጠብቀውም አይመጣም ለወግ ማዕረጌ፡፡
ይልቅስ ለሰርጌ ድምቀት በተዘረጋው ባንዲራ፣
ያባቴን ምስል እየሳልኩ እቀበላለሁ ምርቃት
እረከባለሁ አደራ፡፡
የወታደር ልጅ ነኝና የአባቴ ምስል የሚነግረኝ
የሚመርቀኝ ምርቃት፣
‹‹ልጄ ሃገርሽን ውደጃት
ከትቢያት በማይለቅ ቀለም
ወታደር ለልጁ የሚያወርሰው
ከሃገር ፍቅር በቀር የለም” ::
እንዴት አልወዳት ሃገሬን
የነብሴን ደማቅ ንቅሳት፣
በሃዘንና ደስታዋ ውስጥ
የአባቴን እውነት የማይባት፣
አባቴ ማለት ኢትዮጵያ
ሃገሬ ደግሞ የኔ አባት፡፡
አባቴ ሃገሬን የሚመስለኝ፣
ሃገሬ ነብሴን የምትመስለኝ፣
ተነካች ሲሉኝ ነብሴን የሚያመኝ፤
የሀገሬ ፍቅር አቅል ያሳጣኝ
ያለ ሃገር ማሰብ የተሳነኝ
በኢትዮጵያ ስም አፍ የፈታሁ ፣
የጀግና ወታደር ልጅ ነኝ፡፡
🔘ሻለቃ /ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በሸለ🔘
መታሰቢያነቱ ለሃገር ዳርድንበር መከበር በጦር ግንባር ለተሰዋው አባቴ
፲/አ በቀለ ታደሰና ለወታደር ልጆች ሁሉ ይሁንልኝ፡፡
👍1