❖♥እንኩዋን ለቅድስት #እናታችን_ማርያም_መግደላ
ዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❖♥
✝#ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት✝
ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ
"መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት
(ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:-
በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ
ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች
በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::
ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና
ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7
አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር::
በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና
ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::
በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት
የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም
ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት
አልዘገየችም::
ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ
ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ
መርጦ ተከታዩ አደረጋት::
ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች::
እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ
ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::
ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::
ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ
#መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ
ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን
ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::
እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም
ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር
አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን
አልፈራችም:: ጌታችንም #ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት
ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ
አደላት::
በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን
( #ሚካኤልና_ገብርኤልን ) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ
የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም"
አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::
ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ
መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት::
"ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን
ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::
#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ
ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን : #ትምሕርተ_ኅቡዓትን
ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ
ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ
አገልግሎት ነበራት::
ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን
ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን
ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ
የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ
ነበረች::
እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ
በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል::
እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ
ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ
ይመግባቸው ነበር::
እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም
የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን
#ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች::
ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና
ግርፋትን ታግሳለች::
በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን
መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን
ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ
በቀር) ያከብሯታል::
ዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❖♥
✝#ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት✝
ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ
"መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት
(ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:-
በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ
ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች
በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::
ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና
ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7
አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር::
በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና
ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::
በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት
የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም
ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት
አልዘገየችም::
ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ
ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ
መርጦ ተከታዩ አደረጋት::
ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች::
እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ
ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::
ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::
ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ
#መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ
ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን
ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::
እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም
ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር
አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን
አልፈራችም:: ጌታችንም #ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት
ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ
አደላት::
በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን
( #ሚካኤልና_ገብርኤልን ) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ
የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም"
አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::
ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ
መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት::
"ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን
ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::
#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ
ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን : #ትምሕርተ_ኅቡዓትን
ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ
ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ
አገልግሎት ነበራት::
ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን
ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን
ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ
የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ
ነበረች::
እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ
በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል::
እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ
ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ
ይመግባቸው ነበር::
እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም
የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን
#ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች::
ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና
ግርፋትን ታግሳለች::
በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን
መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን
ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ
በቀር) ያከብሯታል::
💚💛ነሐሴ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)
🌈ወርኀዊ በዓላት🌈
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ
#ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ::
ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን
ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_
ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል
የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ
ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ
እግር ልብስ ከፈኑት::"
(ዮሐ. 19:38)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ::
ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም
ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት
የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም
ከጫጉላዋ ይውጡ::"
(ኢዩ. 2:15)
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)
🌈ወርኀዊ በዓላት🌈
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ
#ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ::
ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን
ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_
ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል
የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ
ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ
እግር ልብስ ከፈኑት::"
(ዮሐ. 19:38)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ::
ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም
ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት
የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም
ከጫጉላዋ ይውጡ::"
(ኢዩ. 2:15)
💚💛ነሐሴ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)
🌿ወርኀዊ በዓላት🌿
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
"የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ #ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" (ዮሐ. 19:38)
"በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" (ኢዩ. 2:15)
@senkesar @senkesar
1.በአተ ጾመ ፍልሠታ
2.አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
3.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት
4.ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ
5.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት)
6.ቅድስት ሐና ነቢይት (ወለተ ፋኑኤል)
7.ደናግል ቅዱሳት (የንግስት ሶፍያ ልጆች)
🌿ወርኀዊ በዓላት🌿
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
"የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ #ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ #ጌታ_ኢየሱስ መጥቶ የነበረ #ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" (ዮሐ. 19:38)
"በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" (ኢዩ. 2:15)
@senkesar @senkesar