ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ማሕቶተ_ተዋሕዶ # ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ
ቅዱስ ያዕቆብ ከሊቀ ዻዻሱ
ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ
#ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል:: ምናልባትም ከሐዋርያው
#ቅዱስ_ዻውሎስ በሁዋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት
ቀዳሚ አባት ነው:: (በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብ
ማሰርን ያስተማረ አባትም ነው)
2ቱ (አባ ቴዎዶስዮስና ቅዱስ ያዕቆብ) ስለ ቀናች ሃይማኖት
ብዙ ስለ ደከሙ የዘመኑ ምዕመናን በስማቸው "
#ያዕቆባውያን እና #ቴዎዶስዮሳውያን " ተብለው
ተጠርተዋል:: አባ ቴዎዶስዮስ ግን ሲታሠር ሲፈታ: ሲሰደድ
ሲመለስ ብዙ ተሰቃየ::
ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ጠብቆ: ከተኩላ አፍ ታደገ::
በዚህች ቀንም ዐርፎ ተቀብሯል:: በፓትርያርክነት
ያገለገለባቸው ዘመናት 32 ዓመታት ሲሆኑ ከእነዚህ ዓመታት
28ቱ ያለቁት በስደትና በመከራ ነው::
#ቅድስት_ኄራኒ_ሐዋርያዊት_ሰማዕት
ይህቺ ቅድስት ወጣት መልክ ከደም ግባት: ምግባር
ከሃይማኖት: ስም ከመልካምነት የተባበረላት ሰማዕት
ናት:: #ኄራኒ ማለት "ሰላማዊት: የተወደደች" ማለት
ነው:: አንድም በጥሬው "ሰላምና ፍቅር" ማለት ነው::
ቅድስት ኄራኒ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ
እስያ የንጉሥ #ሉክያኖስ ልጅ ናት:: ከተወለደች ጀምሮ
ስለ ክርስትና ሰምታ አታውቅም:: ምክንያቱም አባቷ
ጣዖት አምላኪ ከመሆኑ ባለፈ ክርስቲያኖችን ይቀጣ ስለ
ነበር ነው::
ልጁን ማንም እንዳያገኛት ሲል ንጉሡ ለቅድስት ኄራኒ
ቤተ መንግስት ሠራላት:: ማንም እንዳይገባ በዙሪያው
12 አጥር አጠረበት:: ጣዖቶቹን እንድታጥን
አገልጋዮችንም ሾመላት::
ምናልባት አጥር ሰውን ሊከለክለው ይችላል::
#እግዚአብሔር ግን እግዚአብሔር ነውና ምንም
አይከለክለውም:: ጌታ ደግሞ ይህቺን ወጣት ለወንጌል
አገልግሎት ይፈልጋታል:: አንድ ቀን አባቷ: ልጁ ምሑር
እንድትሆንለት አለ የተባለ ሽማግሌ ፈላስፋ ቀጠረላት::
ጥበበ እግዚአብሔር ማለት ይሔ ነው:: አባቷ ይሕ
ሽማግሌ ማንን እንደሚያመልክ አልተረዳም:: አረጋዊው
እጅግ የተዋጣለት ክርስቲያን ነው:: ግን ማንም
አያውቅበትም:: አረጋዊው ቅድስት ኄራኒን ዝም ብሎ
ሊሰብካት አልወደደም::
መጀመሪያ በስነ ምግባር አነጻት:: ቀጥሎ ግን "ጌታ ሆይ! ጐዳናህን ምራት" እያለ ይጸልይላት ገባ:: ጌታችን ልመናውን ሰምቶታልና ቅድስቷ አንድ ቀን ግሩም ራዕይን
አየች::
እርሷ ለማዕድ ተቀምጣ ሳለ: የምሥራቅና የምዕራብ
መስኮቶቿም ተከፍተው ሳሉ: በምሥራቁ መስኮት ነጭ
ርግብ በአፏ የወይራ ዝንጣፊ (ቆጽለ ዘይት) ይዛ ገባችና
ማዕዷ ላይ አኑራው ሔደች:: እርሷን ተከትሎ ደግሞ
ንስር በአፉ አክሊል ይዞ ገብቶ ማዕዷ ላይ ጥሎት ሔደ::
በ3ኛው ግን ቁራ: እባብ በአፉ ይዞ በምዕራቡ መስኮት
ገብቶ ማዕዷ ላይ ጥሎት ወጣ:: ቅድስት ኄራኒ ያየችው
ራዕይ ቢጨንቃት ሽማግሌ መምሕሯን "ተርጉምልኝ"
አለችው::
እርሱም "ልጄ ሆይ! ለዘመናት ስጠብቀው የነበረ ምኞቴን ነው ጌታ ያሳየሽ:: የሕልምሽ ትርጉም እንዲህ ነው:- ነጭ ርግብ የመንፈስ ቀዱስ (የሃይማኖት) ምሳሌ
ናት:: የወይራ ዝንጣፊው ደግሞ #ማሕተመ_ጥምቀት
( #ሜሮን ) ነው:: ቁራ የክፉ ነገሥታት ምሳሌ ሲሆን
እባብ የመከራ ምሳሌ ነው::
ንስር ድል የመንሳት ምልክት ሲሆን አክሊል ደግሞ
የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ነው:: ልጄ! ክርስቲያን ሆነሽ
የሚደርስብሽን ሁሉ ጌታ አሳይቶሻል" ብሎ ተርጉሞላት
ተሰናበታት::
እርሷም ወደ ምሥራቅ ዙራ ጸለየች:- "የማላውቅህ
አምላክ ሆይ! ወደ እውነትህ ምራኝ" ስትል ለመነች::
በዚያች ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ አጽናናት::
የሚያጠምቃትም እንደሚልክላት ነገራት::
በዚያን ጊዜ አባቷ ገብቶ "ልጄ! ከመሣፍንቱ ላንዱ ልድርሽ ስለሆነ ምን ትያለሽ?" አላት:: "3 ቀን ስጠኝ" አለችውና ሰጣት:: ወደ ጣዖቶቹ ዕለቱኑ ወርዳ "ላግባ
ወይስ ይቅርብኝ?" አለቻቸው:: ከቀድሞም በወርቅ
የተለበጡ ድንጋዮች ናቸውና ዝም አሉ:: በሙሉ ቀጥቅጣ
ሰባብራቸው ተመለሰች::
በዘመኑ #ቅዱሳን_ሐዋርያት (በተለይ እነ
#ቅዱስ_ዻውሎስ ) በሕይወተ ሥጋ ነበሩና ከቅዱስ
ዻውሎስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ቤቷ እንደ ተዘጋ ገባ::
ክርስትናን ከጥንቱ እስከ ተፍጻሜቱ አስተምሮ አጠመቃት::
በ3ኛው ቀን አባቷ "ምን መከርሽ?" ቢላት "የእኔ ምክር
#መርዓተ_ክርስቶስ (ሰማያዊ ሙሽራ) መሆን ነው"
አለችው:: አባቷ ደነገጠ:: እጅግ ስለ ተናደደ ወደ
አደባባይ አውጥቶ: አስሮ መሬት ላይ ጣላትና በመቶ
የሚቆጠሩ ፈረሶች እንዲረግጧት አደረገ::
በወቅቱ ሰው የሚጠብቀው የአካሏን ቁርጥራጭ ነበር::
ነገር ግን ጌታ ከእርሷ ጋር ነበርና ልብሷ እንኩዋ ጭቃ
አልነካም:: አባቷ ንጉሥ ሉክያኖስና ሠራዊቱ ያዩትን
ማመን አልቻሉም:: ሁሉም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው
"ከክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" አሉ:: ቅድስት
ኄራኒ ምንም ሳትናገር ይህንን ሁሉ ሰው ማረከች::
ወዲያውም ንጉሡ መልእክተኛ ልኮ: የቅዱስ ዻውሎስ
ደቀ መዝሙርን አስጠርቶ: ከነ ቤተሰቦቹ ተጠመቀ::
የዚህን ዓለም ክብር ንቆም ንግሥናውን ተወ:: የጸሎት
ሰውም ሆነ:: የቅድስት ኄራኒ ተጋድሎ ግን ቀጠለ::
በአካባቢው የነበረ ንጉሥ መጥቶ የአባቷን መንግስት
ቀማ:: እርሷንም እጅግ አሰቃያት:: እርሱ አልፎ
አርማንዮስ የሚባል ንጉሥ እንዲሁ አሰቃያት:: እርሱም
አለፈ:: ከእርሱ ቀጥሎ የመጣው ንጉሥ ብዙ
መከራዎችን በእርሷ ላይ አደረሰ:: በጦርም ጐኗን ወግቶ
ገደላት::
ከጥቂት ሰዓታት በሁዋላ ግን ልክ ከእንቅልፉ
እንደሚነቃ ሰው ተነስታ ጠራችው:: በጣም ደንግጦ
"አምላክሽ አምላኬ ነው" ሲል አመነ:: ከ30,000 በላይ
ሠራዊቱን ይዞም ተጠመቀ::
ቅድስት ኄራኒ በቀረ ሕይወቷ በስብከተ ወንጌል እስያን
አድርሳለች:: ጌታ አብርቶላት: እርሷም አብርታ: እልፍ
ፍሬን አፍርታ: በዚህች ቀን ዐርፋለች:: የሐዋርያትንም:
የሰማዕታትንም አክሊል ተቀዳጅታለች::
ጳጉሜን ፪
#እንኩዋን_ለቅዱስ #ቲቶ_ሐዋርያ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞
#ቅዱስ_ቲቶ_ሐዋርያ
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ
ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን
የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ
ዻውሎስ ከጻፋቸው 14 መልእክታት መካከል አንዷ
የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኩዋ
ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ዻውሎስም
በመልዕእክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል::
☞ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው?
ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን እስያ
ውስጥ: #ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው:: የዘር ሐረጉ
ከእሥራኤልም: ከጽርእም (ግሪክ ለማለት ነው)
ይወለዳል:: አካባቢው አምልኮተ እግዚአብሔር የጠፋበት
ስለሆነ እሱም: ቤተሰቦቹም የሚያመልኩት ከዋክብትን
ነበር::
መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው
ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ
ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን
ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት
ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ::
ቅዱሱ በወቅቱ ምንም እውነተኛውን ፈጣሪ አያምልክ
እንጂ በጠባዩ እጅግ ቅንና ደግ ነበር:: ምክንያቱን
ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ:
ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን
ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን
በራዕይ ተገለጠለት::
በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ!
ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው"
ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ::
የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም
ሊገባቸው አልቻለም::
ለተወሰነ ጊዜም ለጉዳዩ ምላሽ ሳያገኝለት በልቡ
እየተመላለሰ ኖረ:: ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ
#ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት
ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር
ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው"
ሲሉ ለቲቶ ነገሩት::
"ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን
ይፈወሳሉ:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ለምጻሞች
ይነጻሉ:: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው"
አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና
ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ::
እርሱ መሔድ ስላልተቻለው "ብልህ ጥበበኛ ሰው
ፈልጉልኝ" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ
በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን
"ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ
መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ" ብሎ ላከው::
ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ::
ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው::
1.ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ:
አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር
እንዳልሆነ ተረዳ::
2.ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና
እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: የግሪክ ፍልሥፍና
መነሻውም ሆነ መድረሻው ሥጋዊ ነው:: ጌታ ግን
በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ
ዘለዓለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ
ተጋደል" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት::
በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ
ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከ72ቱ # አርድእት ደመረው::
የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን
ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት::
ከዚህ በሁዋላ #ቅዱስ_ቲቶ ከጌታችን እግር ለ3
ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ:
በመላው እስያ ለ8 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::
#ቅዱስ_ዻውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ
መዝሙር ሆኖ ለ25 ዓመታት አስተምሯል::
ቅዱስ ዻውሎስ ሰማዕት ከሆነ በሁዋላ ደግሞ ወደ
#አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ
ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም
መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኩዋቸውም
በዚህች ቀን ዐርፏል::
✿አምላከ ቅዱስ ቲቶ መልካሙን የሕይወት ምሥጢር
ይግለጽልን:: ከሐዋርያውም በረከቱን ያድለን::
🌼#ቅዱስ_ዻውሎስ_ሐዋርያ🌼
የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን?
¤ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ
ሰው ነው?
¤የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ?
¤ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን
መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::

#ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል
የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ
ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት
ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ
ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ::
ጨው ሆኖ አጣፈጠ::
ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን
(የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል
ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ:
በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ::
በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ25 ዓመታት
ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::

እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ:
በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል:: ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው::

#የቅዱስ_ዻውሎስ መጠሪያዎች:-
1.ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2. #ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3. #ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4. #ብርሃነ_ዓለም
5. #ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6. #የአሕዛብ_መምሕር
7. #መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8. #አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ)
9. #ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10. #መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11. #መርስ (ወደብ)
12. #ዛኅን (ጸጥታ)
13. #ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ)
14. #ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15. #ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . .
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን::
ከበረከታቸውም ያድለን::
@dn yordanos abebe
💚💛 ቅድስት ሣራ ብጽዕት💛❤️
አበው እናታችን ሣራን " #ቡርክተ_ማሕጸን " ይሏታል::
(የቅዱሱ ዘር የይስሐቅ እናት ናትና) በዚያውም ላይ የደጉ
ሰው የአብርሃም ሚስት ናት:: ልክ በዓለም ታሪክ "ከጠንካራና
ስኬታማ ወንዶች ጀርባ ጠንካራ ሴቶች አሉ" እንደሚባለው
ከአብርሃም አባታችን ስኬታማ የቅድስና ሕይወት ጀርባ
ብጽዕት ሣራ አለች::
ለአብርሃም አባታችን መጽሐፍ የተናገረው ክብር ሁሉ
ለቅድስት ሣራ ይገባታል:: አንድም ገንዘቧ ነው:: ቅድስቷ እናት
ደጉ አብርሃምን ያገባችው ገና በከላውዴዎን (በ2ቱ ወንዞች
መካከል) ሳለ ነው:: ገና ከልጅነቷ ጀምራ አብርሃምን "ጌታየ"
እያለች ታገለግለው እንደ ነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል::
(1ዼጥ. 3:5)
በዚህም ከብራበታለች: ገናበታለች እንጂ አልተጐዳችበትም::
አብርሃም ወደ ካራን ሲወጣ "ለምን?" አላላችም:: እንዲሁ
ለፈቃደ እግዚአብሔር ታዘዘች እንጂ:: በካራን ታራን ቀብረው:
በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ #ከነዓን ሲፈልሱም ቅድስት ሣራ
አልተቃወመችም::
ለፈጣሪዋ ትዕዛዝና ለባሏ ስትል ርስቷን: ሃገሯን: ዘመዶቿን
ሁሉ ትታ ሔዳለች:: ይሔውም በጐ ምናኔ ነው:: እናታችን ሳራ
በከነዓን የተመቸ ነገር አልገጠማትም:: ከአንዴም ሁለቴ
በረሃብና በድርቅ ምክንያት ወደ ግብጽ እና #ጌራራ ተሰደዋል::
በዚያም ፈርዖን "እነካለሁ" ቢል እግዚአብሔር ተቆጥቶ:
ፈርኦንንና ግብጽን በደዌ መታ:: በዚህም ክብረ ሣራን
ተመለከትን:: ከስደት መልስም በኬብሮን (በተመሳቀለ
መንገድ ላይ) ድንኩዋን ሠርተው የወጣ የወረደውን ሲያበሉ:
እንግዳ ሲቀበሉ ኑረዋል::
(ልብ በሉልኝ ይህን ትጋትና ደግነት ያሳየችውን ቅድስት ሣራን
ልናከብራት ይገባል)
እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው እንግዳ በመቀበል:
እግዚአብሔርን በማምለክ ነው:: ምንም እንኩዋ ማሕጸኗ
ለጊዜው ቢዘጋ ተስፋ አልቆረጠችም:: ለአብርሃምም ከአጋር እንዲወልድ ፈቃድ ሰጥታለች:: ዕድሜዋ 89 ዓመት በሆነ ጊዜ ሰይጣን እንግዳ እንዳይመጣ ለ3 ቀናት ቢያስቀርባቸው እንደ ባሏ እርሷም 3 ቀናትን ያለ ምግብ አሣልፋለች:: በ3ኛው ቀን ሥላሴን በቤቷ
አስተናግዳለች:: ስለ ክብሯም ከ3 መሥፈሪያ ዱቄት ለውሳ
ያዘጋጀችውን እንጐቻ ሥላሴ በልተውላታል:: (ምንም ሥላሴ
ምግብን ባይመገቡም)
የሥላሴ በዚያች ድንኩዋን ውስጥ መስተናገድ ታላቅ
ምሥጢር አለው:: ከግብዣው በሁዋላም እግዚአብሔር አለ:-
"አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ . . . እንዲሁ ከርሞ
እመለሳለሁ: ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች" አለው::
ያን ጊዜ ሣራ በውሳጤ ሐይመት (በድኩዋኑ ውስጥ) ሆና
ሰምታ ሣቀች:: ለምን ሳቀች ቢሉ:- እጅግ ደስ ቢላት! አንድም
ቢገርማት:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- ልጇ " #ይስሐቅ "
የተባለው "ለእናቱ ሣቅን: ደስታን ያመጣ" ለማለት ነውና::
ሥላሴም:- "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ: እንዘ ትብል
ዓዲየኑ እስከ ይእዜ: ወእግዚእየኑ ልሕቀ: ቦኑ ነገር ዘይሰዓኖ
ለእግዚአብሔር - ሣራን ምን አሳቃት? ለእግዚአብሔርስ
የሚሳነው ነገር አለን" ብለዋል::
ቅድስት ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳ በቀሪ ዘመኖቿ
በደስታ ኑራለች:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፋ:
አባታችን #አብርሃም ከታላቅ ሐዘን ጋር ቀብሯታል:: ሐዋርያው
#ቅዱስ_ዻውሎስ ብጽዕት ሣራን በበጐ ምሳሌ መስሏታል::
(ዕብ. 11:11)
💚💛ሐምሌ ፭💛❤️
✞እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ:
ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::

💚💛" ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት "💛❤️
የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው::

¤በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ

¤ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል:: ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: (ማቴ. 16:17, ዮሐ.
21:15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ
እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከ አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::

በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል::
እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::

ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው::."እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም"
አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ
ነበር::

#የቅዱስ_ዼጥሮስ መጠሪያዎች:-
1.ሊቀ ሐዋርያት
2.ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ)
3.መሠረተ ቤተ ክርስቲያን
4.ኰኩሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት)
5.አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ)

💚💛#ቅዱስ_ዻውሎስ_ሐዋርያ 💛❤️
የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን?

¤ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው?

¤የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ?

¤ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::

#ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት
ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ:: ጨው ሆኖ አጣፈጠ::

ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ:: በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::

እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል::.ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘ ማለት ነው::

የቅዱስ ዻውሎስ መጠሪያዎች:-
1.ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2.#ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3.#ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4.#ብርሃነ_ዓለም
5.#ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6.#የአሕዛብ_መምሕር
7.#መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8.#አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ)
9.#ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10.#መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11.#መርስ (ወደብ)
12.#ዛኅን (ጸጥታ)
13.#ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ)
14.#ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15.#ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . .

ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
From dn yordanos abebe

@senkesar @senkesar
💚💛ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት 💛❤️
እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::
@senkesar @senkesar