ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ጳጉሜን ፪
#እንኩዋን_ለቅዱስ #ቲቶ_ሐዋርያ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞
#ቅዱስ_ቲቶ_ሐዋርያ
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ
ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን
የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ
ዻውሎስ ከጻፋቸው 14 መልእክታት መካከል አንዷ
የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኩዋ
ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ዻውሎስም
በመልዕእክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል::
☞ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው?
ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን እስያ
ውስጥ: #ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው:: የዘር ሐረጉ
ከእሥራኤልም: ከጽርእም (ግሪክ ለማለት ነው)
ይወለዳል:: አካባቢው አምልኮተ እግዚአብሔር የጠፋበት
ስለሆነ እሱም: ቤተሰቦቹም የሚያመልኩት ከዋክብትን
ነበር::
መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው
ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ
ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን
ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት
ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ::
ቅዱሱ በወቅቱ ምንም እውነተኛውን ፈጣሪ አያምልክ
እንጂ በጠባዩ እጅግ ቅንና ደግ ነበር:: ምክንያቱን
ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ:
ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን
ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን
በራዕይ ተገለጠለት::
በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ!
ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው"
ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ::
የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም
ሊገባቸው አልቻለም::
ለተወሰነ ጊዜም ለጉዳዩ ምላሽ ሳያገኝለት በልቡ
እየተመላለሰ ኖረ:: ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ
#ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት
ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር
ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው"
ሲሉ ለቲቶ ነገሩት::
"ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን
ይፈወሳሉ:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ለምጻሞች
ይነጻሉ:: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው"
አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና
ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ::
እርሱ መሔድ ስላልተቻለው "ብልህ ጥበበኛ ሰው
ፈልጉልኝ" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ
በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን
"ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ
መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ" ብሎ ላከው::
ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ::
ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው::
1.ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ:
አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር
እንዳልሆነ ተረዳ::
2.ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና
እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: የግሪክ ፍልሥፍና
መነሻውም ሆነ መድረሻው ሥጋዊ ነው:: ጌታ ግን
በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ
ዘለዓለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ
ተጋደል" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት::
በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ
ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከ72ቱ # አርድእት ደመረው::
የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን
ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት::
ከዚህ በሁዋላ #ቅዱስ_ቲቶ ከጌታችን እግር ለ3
ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ:
በመላው እስያ ለ8 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::
#ቅዱስ_ዻውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ
መዝሙር ሆኖ ለ25 ዓመታት አስተምሯል::
ቅዱስ ዻውሎስ ሰማዕት ከሆነ በሁዋላ ደግሞ ወደ
#አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ
ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም
መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኩዋቸውም
በዚህች ቀን ዐርፏል::
✿አምላከ ቅዱስ ቲቶ መልካሙን የሕይወት ምሥጢር
ይግለጽልን:: ከሐዋርያውም በረከቱን ያድለን::