ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Untitled one
While her bower eyes cry
In the middle of dark day
She weaves by the long day
She whisper to the blue sky
With the powerful word
But in her night the pain was obvious and clear
Her shadow was scare and fear
Not a single air was full of joy, Rather
The magic was visible in her tear
All her hope was inside the air
The sparkle day was off and gone
To the far and far away kingdom that won’t be visible to bee seen in trode❤️

May/2020
©Tina
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEwq0Pmw61GSm7UoKQ

https://tttttt.me/GitemSitem

#Tina’sview #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
የክፉ ሰው ምላስ*

ምሰሶው ተማግዶ ጎጆኣችን ነደደ
ውበት ትዝታው ላይ ፍም ሳት ወረደ
ጢሱ በአይን ሞላ ነበርን ሸፈነው
አሁን የቆምንበት ጥላሸት አመድ ነው ፡፡
ብለን ተክዘን ሳል
ካመዱ ላይ ቆመን
አንድ እውነት ገረመን
አንድ ሀቅ አመመን
እዚህ እኛ እውነት ላይ
እፍቅራችን ሞት ላይ
ነፋስ ስራው በዛ
ከአመዱ ቆንጥሮ ሰው ፊት እየነዛ ! ! !

©መቅደስ ሞገስ

#መቅደስ_ሞገስ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ግጥም ሲጥም 3 ተቃርባለች
ቅዳሜ፣ ጥር ፣ 2013

Gitem Sitem 3 is almost here
January 16, 2021

የአሁኑ 'ራስ' ማን ይመስላችኋል? (የምታውቁ🤫) እነማንንስ እናመጣለን? አብረን እንከታተል!



#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ # #artinaddis #poetry #poetrycommunity #poetrylovers #poetsinaddis
በአሁኑ የግጥም ሲጥም 'ራስ' ዲበኩሉ ጌታ ነው። 'የምድር ዘላለም' የተሰኘች ግሩም የግጥም ስብስብ መጽሐፍ አለችው!

ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።

https://tttttt.me/GitemSitem

በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም

የ'ራሱ'ንም የራሳቸውንም ግጥም ሊያቀርቡ እንዲሁም ዝግጅቱን ሊያጥሙ የተዘጋጁት ደግሞ እኚሁላችሁ !
መቅደስ ሞገስ፣ ምትኩ ምድሩ፣ ሊያ አበበ፣ ልዩ ናቃቸው፣ ኪሩቤል ዘርፉ (ድሬ)፣ አናንያ ተሾመ፣ ቲና በላይ፣ ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል፣ ቃልኪዳን (Everted), ሻሎም ደሳለኝ፣ አስታወሰኝ ረጋሳ (አስቱ) እና ሌሎችም

ትጉንጬ ካፌ እና ሬስቶራንት /Tigunche cafe and Resturant
ካዛንቺስ ኢሲኤ መንገድ ከእፎይ ፒዛ ጀርባ
Kazanchis ECA road behind Efoy Pizza

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
የፊታችን ቅዳሜ በግጥም ሲጥም 3 ላይ የአሁኑን 'ራስ' አጅበው ጥዑም ግጥም ከሚያቀርቡላችሁ ውስጥ ሁለቱ ፦ ምትኩ ምድሩ እና ቲና በላይ እንኋቸው!

ዛሬ ብሔራዊ ትያትር 11፡30 ጀምሮ ብትገኙ ደግሞ ምትኩ ምድሩን ለበጎ ዓላማ ግጥም እንካችሁ ሲል ታገኙታላችሁ።

https://tttttt.me/GitemSitem

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #ምትኩ_ምድሩ #ቲና_በላይ #poeticsaturdays #Dibekulu_Geta #Mitiku_Midru #Tina_Belay #artinaddis #poetry #poetrylovers
አበባ ናት
ለጋ ቀንበጥ
በአረንጓዴ ዘንግነቷ
ከሩቅ የምትታይ
ውሃን ነሷት የምራቃቸውን ጠብታ እንኳ ነፈጓት !
ጠደቀች
አፈር ነሷት የምትደላደለበት
ጠደቀች
በውበቷ አሰማመረቻቸው
በፍቅሯ አቅበጠበጠቻቸው
እስትንፋሷን እፍፍ ብላ ህይወት ዘራች
የመጣችው በምክንያት ነው
ልታኖር
ያላኖሯትን
ልታደላድል
የጎረበጧትን
ፍቅር ሆነችላቸው
ህይወት ሆነችላቸው
ውበት ሆነችላችው
ሲሆንላት ፈክታ ፍንድቅድቅ ብላ
ደሞ እየጠወለገች እየሞተችም
ጠደቀች
እየረገፈች ጠደቀች
ሞቷም ውበት ነው::
ትገርመኛለች !!!
እውነቷን ያሠረችበት ዘመኗ ግን ብዙም አይደል
አጃኢብ እላለሁ ሁሌም ሳስባት !

©መቅደስ ሞገስ

#Mekdes_Moges #መቅደስ_ሞገስ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ተማፅኖ

አንተ የማላውቅህ ኃያሉ ዳኝነት - ገናናው ዝግ ሠሚ
በማትለይበት ሁሉን ዐካል የሆነክ፤
ብርሃን ጨለማን ዳር ድንበር አስማሚ፤
አንት የተምኔት ዐለም - ንጉስ ምናቤ ሆይ . . .
[ከበፊት ያልታዬ - ያልነበረን ዘር ግንድ]
እባክህን ችረኝ!
[አዎን———-]
አንዲት ቅንጣት ነገር
ትንሽ ሚጢጥ ሥልጣን
ሰውን፣ ከእግዜር ሰይጣን - ከራሱም ለማስጣል።

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
We are so honored to have amazing poets like Kalkidan with us along side our headline poet Dibekulu Geta !!!

''I didn't grow up to be a poet because I loved the art. I am not a writer because I love spilling words. My writing experience never came from a loving place. It came from a place of need. A need to escape, to be alone, to feel out loud, to let go or to just talk to myself without labeling the process. I needed to talk to myself and listen to myself in return. I believe writing a single poem takes a lot of courage. It starts from revisiting your past and ends with acceptance, but a lot goes in between. There is a lot of feeling in there, from love to resent'' - Kalkidan

"poetic disruption through bold and uncensored self-expression''
-Everted

Check out her amazing poetry collection here at Everted https://tttttt.me/Everted

#Kalkidan #Everted #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
አዬ ሰው ጎስቋላ

አዎን...!

አውርተነው ነበር
ይህንን ሰውነት
ይህን የሞት እብለት!

ላይዙት ላይጥሉት
መሐላ እንዳለበት፤

ያው ሆነለት ያልነው
ገላ ላይ ሲያደርጉት
እንዶድም እድፍ ነው።

©ዲበኩሉ ጌታ

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ግጥማዊ ቅዳሜን የሚያውቁ ሁሉ ማርቆስንና ጥዑም ግጥሞቹን ያውቃሉ። የተማረው ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ቢሆንም የሳይንስም የኪነ ጥበብም ሰው መሆንን ከታደሉ ጥቂት ጸኃፍት አንዱ ነው - ባለ ብዙ ተሰጥዖም ነው። 'እናንንብብ፣ እንወያይ፣ ነጻ እንውጣ' በሚል በንባብ ዙሪያ የማሕበራዊ ሚድያውንና መተግበሪያን በመጠቀም ለጸኃፊዎችን አንባቢዎችም ዘመኑን የዋጀ ስራ ለመከወን የተነሳው የ'ንበብ' ባልደረባ ነው።

ግጥሞቹን በዚህ እዩበት 👉🏾 https://tttttt.me/thegreyspot

#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#ማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
1600 ኪሎሜትር ገደማን ከሐረር አዲስ አበባ ከአዲስ ደሞ አድዋ ድረስ በእግሩ የተጓዘው የዘመናችን አድዋ ዘማች የሆነው ውዱ አጣሚያችን 'የድሬደዋ ልጆች' መድረክን ከማሰናዳት ጀምሮ አምስት ዓመታትን የተሻገረ የመድረክ ልምድ አለው። አሁን ደሞ የሁለተኛ ዓመት የቲያትር ዳይሬክቲንግ ተማሪ ነው - ኪሩቤል ዘርፉ (ያይቆብ ነኝ አታላዩ)።

#ኪሩቤል_ዘርፉ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ሕይወት እና ሚዛን

አለመመጠን ሁለት ነወ
አንዱ ማነስ ሲሆን
ሌላው መብለጡ ነው።
...
ደማቁ ቀለም ምንግዜም ደማቅ ነው
ኮከቦች አገዙት ጨለማ ጋረደው፤
ነቃፊን ደጋፊን፣
ሁለቱን ወገን
ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መጠን
ይቻላል ማሳመን።
...
ያልታየ መልክህን፣ ጥረት ትጋትህን
ከኋላ ተነስቶ፣ ከፊት መውጣትህን
አይተናል፣ ለይተናል፤
ጀንበር ድል ፋናህን፤
አንተ ያልመጠንከው - ልቀህ በመሄድ ነው !!!

©ዲበኩሉ ጌታ

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
''ስለ ስልጣን አቀራረቡ በተመለከተ:- ገጣሚው ግጥምን የመወረብ፣ የመደነስ ችሎታዎቹ ድንቅ ያሰኙታል። ዝማሜውን ተከትሎ ቃል እያነሳ ሲያሻው እየደፋ ከፍ ሲል ቸብቸቦውን እያስቸበቸበ መረግዱን እያስመረገደ የግጥሙን ቆሌ ይካድማል ...''

ይህን ያለው የመጀመሪያው ኩነታችን 'ራስ' የዘንባባ መጽሐፍ ደራሲና ገጣሚ ምግባር ሲራጅ ነው። ይህ የተባለለት ደሞ የአሁኑን 'ራስ' ዲበኩሉ ጌታን አጅቦ እንደ አጋፋሪ የሚያጋፍርልን ተስፋ የተሰኘች የስነ ግጥም ስብስብ መጽሐፍ አሳትሞ ያስነበበን አስቱ ነው።


#አስቱ #አስታወሰኝ_ረጋሳ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጊዜው በሰጠነው በርካታ ስሙ ነጠቃ፣ after poetry፣ የእሳት ዳር ጨዋታ በተለይም ደግሞ ከ'እሁድ ሰዎች' በተወሰደ ቃል 'ንሸጣ' ካልነው ውስጥ ጨረፍታ ዜማ በ መንቢ. . .
ይህ የዝግጅታችን ክፍል በሚገባው መጠን ተሰንዶ ያልተገኙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ የበለጠ እንሰራለን ዋናውን ዝግጅትም 'እራሶቻችንን' በሚመጥን ከፍታ ለመዘገብ ይበልጥ እንተጋለን።

እስከአሁን የተገኛችሁ ከልባችሁ ለሰጣችሁን ሃሳብ ሁሉ ተመስገኑልን!!!

መሰናዶዋ በሚገባ ከመነሻቸው የሚዘከሩ ገጣሚዎችን እያወደሰች ወይም በ'ዚህ ዘመን' ቋንቋ እንድናሽቃብጥላቸው የሚያስገድዱንን፣ የዘመናችንን የስነ ግጥም መልክ በራሳቸው ቀለም የሚጽፉትን 'Headline Poets' ስራዎቻቸውን እያጋራች ለበርካቶችም የትውውቅ መንገድ እየሆነች ትቀጥላለች!

ኑ ተነጠቁ! ኑ ንጠቁ! ኑ ተነሸጡ!
...ንሸጣ ለተነሻጭ ብቻ እንጂ ለሁላችሁም ነው!

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ከመልካም በዓል ምኞት ጋር የወርኃ ታህሳስ የግጥም መጽሔትን ዘግየት ብለንም ቢሆን እንሆ አቅርበናል።
በቀጣይ መጽሔታችን የእናንተኑ ስራ እንጠብቃለን።
https://drive.google.com/file/d/1HushONVS9C8XU_xzalz55cis8Ol2KMK5/view?usp=drivesdk ገብታችሁ እዩልን፣ አውርዳችሁም የራሳችሁ ልታደርጉት ትችላላችሁ፣ አንብባችሁ ስታበቁ ግን አስተያየት አቀብሉን።

ግጥማቸውንና ምስሎቻቸውን እያቀበሉ ወሩን ላደመቁልን ሁሉ ምስጋና ይድረስ!!!

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥበብበአደባባይ #የግጥምመጽሔት
#gietmsitem #poeticsaturdays #artinaddis #poetrybooklet

Cover Sketch Credit: Moon'it
በዲበኩሉ ጌታ 'ራስ'ነት በምድር ዘላለም ቀዳሚነት ደምቆ እና ጥሞ ተጣጥሞ ያለፈው ግጥም ሲጥም 3 በጨረፍታ ይህን ይመስል ነበር። ከመደበኛ አጣሚዎቻችን በተጨማሪ በታዳሚነትም በአቅራቢነትም በድንገቴ ተገኝተው መሰናዶውን ካጣሙሉን ውስጥ ዮሐንስ ሃብተማርያም (ጨበሬው)፣ Kal's T (The Wordsmith) እና ማሕሌት ማይረጉን እንዲሁም የተገኛችሁትን ሁሉ ምስጋና ልናቀብላችሁ እንወዳለን።
ለተሻለ ከፍታ እየተጋን ነውና አሁንም ብርቱ እገዛችሁ አይለየን!

እስቲ ደሞ ቀጣዩን 'ራስ' ገምቱ. . . ማን ሊሆን ወይም ልትሆን ትችላለች?

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
የዓመቱን የመጀመሪያ ክፍት መድረክ ይዘንላችሁ መጣን!

እስቲ እንደ'ራሳችሁ፣ እንደ ልባችሁ፣ እንደ ስሜታችሁ፣ እንደ ቀለማችሁ፣ እንደ መልካችሁ እና እንደፈለጋችሁ ተሰየሙበት።

12 ሰዓት ላይ ምዝገባ እንጀምራለን የመጀመሪያ 20 ተመዝጋቢዎች ብቻ ቅድሚያ ያገኛሉ።

#ግጥምሲጥም #ግጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ኅብረቃል #ሽፍታ
👍2