ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
አበባ ናት
ለጋ ቀንበጥ
በአረንጓዴ ዘንግነቷ
ከሩቅ የምትታይ
ውሃን ነሷት የምራቃቸውን ጠብታ እንኳ ነፈጓት !
ጠደቀች
አፈር ነሷት የምትደላደለበት
ጠደቀች
በውበቷ አሰማመረቻቸው
በፍቅሯ አቅበጠበጠቻቸው
እስትንፋሷን እፍፍ ብላ ህይወት ዘራች
የመጣችው በምክንያት ነው
ልታኖር
ያላኖሯትን
ልታደላድል
የጎረበጧትን
ፍቅር ሆነችላቸው
ህይወት ሆነችላቸው
ውበት ሆነችላችው
ሲሆንላት ፈክታ ፍንድቅድቅ ብላ
ደሞ እየጠወለገች እየሞተችም
ጠደቀች
እየረገፈች ጠደቀች
ሞቷም ውበት ነው::
ትገርመኛለች !!!
እውነቷን ያሠረችበት ዘመኗ ግን ብዙም አይደል
አጃኢብ እላለሁ ሁሌም ሳስባት !

©መቅደስ ሞገስ

#Mekdes_Moges #መቅደስ_ሞገስ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers