ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
The Human In Us

They think they have figured it out, Humans. They believe they have Deconstructed and traced back the universe and God himself to the origins.

Yet, look at them Enslaving others for a path of freedom. Creating chaos in the name of peace. Taking more lives in hopes they can reduce death...

All they do is Destroy themselves.

They gather in their circle of pity and mock another Circle of pity [So as I keep doing now..] They've made God Vulnerable, so lonely and insecure... smiling for the Heathen souls they killed and Getting angry at them for being happy.

They think they have figured it all out.
Yet all that's out there is contradiction.

In a world of change, I envy how some are willing to die for somethings that exist in just their minds.
But then I would die for You!
[Did I just contradicted my self?]

In the manner of contradiction God is more human than humans themselves!

https://tttttt.me/thegreyspot

©ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል
©Markos
©Fasika Kebede
ከፊል መልክሽ ዐይን ሸሽቶ
ግራጫ ላሁጫ ጠጉርሽ
ከሻሽ መሐል ሾልኮ ወጥቶ
እዛ ጥግ...
አንቺ
በግማሽ እየገባሺኝ
መረዳቴን በግማሽ መርሳት ልትረቺ

እያየሁሽ..
አስታወስሁኝ ዕለት
ከእቅፍሽ አንገቴ
ፀጉርሽ መሐል ፊቴ..
ነፍሴ ላይ ጠረንሽ
አንቺ - ዙሪያዬ
እኔ - ውስጥሽ....
መውደቅ ስንረታ ወድቀን
አሳላፊያችን ሲያልፈን

አስታወስሁ
ትዝ አለኝ

የረሳሁት ያልረሳኝ
ሳውቅሽ የማውቃት ሽበት
እንግዳ ነገር ትመስል
ከሌላው ዕለት ጎልታ ታይታኝ..

መቼ ማርጀት ጀመርሽ?
..

(ጠሩኝ
አልሽኝ..

ወዳሉበት
የምትወጃቸው
...ተ ከ ተ ል ሻ ቸ ው!

መንገድ ያህል ነገር
ያለስንብት
በእስትንፍስ ፍጥነት
ቶሎ
ጥድፍ
ክንፍ
አንዴ ተንፍሶ
መኖር ጨርሶ
...ቀድሞ ለመድረስ....
ጠሩኝ አልሽ
ጥድፍ
(አቤት እንደማለት...)
እፍፍፍፍፍ

ሸኘሁሽ ሄደሽ ከጨረስሽ...
መቼ ነበር ማርጀት የጀመርሽ?)

ከፊል አንቺ ጎኔ
ጠጉርሽ መሐል የኖረችን
አንዲት ሽበት እየቆጠርሁ
ጎንሽ እኔ..

ምን ያህል ዘመን እጅሽን ያዝሁ
ስንት ዕለታት ተቃቅፈናል?
ዘለዓለም ይሁን ሰከንድ
ከፍቅራችን በልጦ
ጊዜ እኛን ይመዝነናል?

ዛሬኣችን ላይ አድፍጦ ዕድሜን የተደገፈ
ጠጉርሽን እያየሁ በከፊልሽ ስደመም
መቃናችንን እየታከከ
ዘጠኝ ሞት መጣ ዘጠኝ ሞት አለፈ...

ትዝ አለኝ
እንግዳ ያላየሁት
እያየሁ የዘነጋሁት

ክንዴ መሐል ሆነሽ
ከኖርነው የበለጠ አዲስ
ረዥም ዕድሜ ወረሰሽ

መቼ አረጀሽ?

(...እዚያች
ከፊልሽ ያረፈችባት
እቅፌ መሐል የወደቅሽባት።
ወርደ ጠባብ መደብ ላይ ጥላ እየጣሉ
"አቤት" እና ስምሽ ተቀምጠዋል...

ያን 'ለት ዘጠኙ አለፈ
አሥርኛው ገባ...
ቤት ለእንግዳ!
በሚያልፍበት ቅጽበት
እንኳን ያልተረዱት
የሚያውቁት ይሆናል ባዳ

ደነቀኝ
እየፈካሽ ማርጀትሽ
መኖር ምልክትሽ
መዋቲ የመሆንሽ...

"አቤት!"
በእስትንፋስ ዕድሜ
ስትጀምሪ ማብቃትሽ
ያውም መንገድ ያህል ነገር
እስካሁን የነበርሽው መሄድሽን ነበር?

መቼ ጀመርሽ ማርጀቱን?
እፎይ!)

-----አስታወስሁ ያልሁሽ ትዝ ያለኝ
እንዲህ እየሆንሁ ነው!----

ከፊልሽ ካረፈበት መደብ
አንዱን ዕድሜ ብንተራሰው
እንግዳ ያላስተዋልሁት
እያየሁ የዘነጋሁት
ጠጉሬን ሽበት ወረሰው..

(ለግርምቴ ደግሞ ቀለሙ ያንቺን የሚመስል!)
ዕድሜዬን መቼ ኖርሁት
መምጫ ስጠብቅ እንጂ የሸበትሁት
አረጀሁ!

ቀትር - ጀንበር በፈካችበት
ጥላሽ ቤቴን ሞልቶታል
ከአንቺ ጋር የወሰደኝ
ዳግም ደጃፌን ይመታል...
(ምን ቀረው?)

ከፊልሽን መርታት ያቃተው ብርሃን ቤቴ ዘለቀ
(በሬን ማን ገፋው? ግባ! ቤት ለእንግዳ)
ግማሽ ጥላሽ ሞላኝ ከፊሌ ላይ ወደቀ!

አስታወስሁ ዕለት መዘንጋት ረሳሁ
(ከመ ጽጌ ረዳ መዓዛኪ ጥዑም
ዘያበርሆ ለጽልመት ገጽኪ ግሩም...
ዜማ ሆነሽ ፊቴ ሰፈፍሽ)
ተፈለቀቀ ከንፈርሽ
አሸበሸበ ከፊልሽ..
ስታዜሚ
ስትዜሚ
መዝሙርሽ ላይ ስሜን ሰማሁ
ከመኝታዬ ተራገፍሁ ከፊሌን ይዤ ተነሳሁ...

(እፎይ! በእስትንፋስ ዕድሜ

ልከ'ተልሽ!
ያውም
መንገድ ያህል ነገር
መጠበቄ መድረሴን ነበር!)

ተከተልሁሽ!

"አቤት ዓለሜ? ጠራሺኝ መሰል"


#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#𝖒𝖆𝖗𝖐 𝖔'𝖘
ግጥማዊ ቅዳሜን የሚያውቁ ሁሉ ማርቆስንና ጥዑም ግጥሞቹን ያውቃሉ። የተማረው ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ቢሆንም የሳይንስም የኪነ ጥበብም ሰው መሆንን ከታደሉ ጥቂት ጸኃፍት አንዱ ነው - ባለ ብዙ ተሰጥዖም ነው። 'እናንንብብ፣ እንወያይ፣ ነጻ እንውጣ' በሚል በንባብ ዙሪያ የማሕበራዊ ሚድያውንና መተግበሪያን በመጠቀም ለጸኃፊዎችን አንባቢዎችም ዘመኑን የዋጀ ስራ ለመከወን የተነሳው የ'ንበብ' ባልደረባ ነው።

ግጥሞቹን በዚህ እዩበት 👉🏾 https://tttttt.me/thegreyspot

#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#ማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
We perish as if we were never here.
May be now
May be later...
Nobody knows.
And the one thing we often do
Is die for a better cause.

We build up a lot just to let it go
We learn too much gibbrish
And spend the rest of our lives trying to unlearn it.

It's all a process of leaving behind and growing apart.

I, am growing apart from myself.
[After all the greatest war fought is, between man and himself.]

We Perish as If we never existed.
And we let go of those who leave
As if, we never notice them missing

We kill and dance,
We die and chant...
We smile as we perish.
It all lies on finding a purpopse..
A purpose, after achieving one.
A purpose after a purpose.
A purpose deconstractimg the first one..
Unlearning everything.

We live to draw lines and then spend time widening them
Or erasing the lines and limit ourselves with excessive freedom.

We let go of what we've been seeking desperately.

[If you ask me,
I would never die for anything,
I don't even get to live well for my self.

And to be honest death is overrated,
Cause the bravest thing you could do is live.]

We perish and be forgotten
In the roads of existence
We are walking towards Nothingness.

And knowing that might make see something,
Like all we can do is
Just live life for the sole purpose of living.

We perish and we know.
So we smile through it
Cause the bravest thing we could do,
Is live.

#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#To_the_oblivion
እሸሻለሁ! ከብዙ ነገር....

ከሞት እሸሻለሁ። መኖር ያስበረግገኛል።
ከማጣት እሸሻለሁ። ማግኘትን እሸሻለሁ።  እሷን እሸሻለሁ። ከእሷ መለየትን እሸሻለሁ።
አካል ለበስ ፍርሃት ነኝ። በመፈለግና ባለመፈለግ መሐል ሰፋሪ ነኝ። ምናልባትም መሸሽን መኖር ብዬ የያዝሁ.... ጉዞዬ ክብ መሆኑን አልታዘበውም። የምሸሸውን ዞሬ ከፊቴ ሲመራኝ አገኘዋለሁ። ወደሽሽቴ ጉያ ሮጣለሁ።
--------------------------------
የገፋሁት ገላዋ ከሩቅ ውልብልታው ይታየኛል። የሚታየኝ ጀርባዋ ይሁን ፊቷ አላውቅም። እየሄደች ይሁን እየመጣች እንጃ ..... ብቻ አያታለሁ። እርግጠኛ የምሆነው እሷነቷ ላይ ብቻ ነው። በፋናዋ የምለያት ናት።
ዝም ብዬ ሚራዧን እታዘባለሁ። ሌላ አይነት ሽሽት፤ ዝምታ! ስሜት አልባ መታዘብ። ፋናዋ ይቀርበኛል። በዝምታ ርቀዋለሁ። ይርቀኛል በዝምታ አቀርበዋለሁ። 
-------------------------------
የሽሽት ሥጋዊ ገጽታ ነኝ።
እሸሻለሁ!
ፖለቲካ ያንገሸግሸኛል። ።ኮሚዩኒዝም ሆነ ካፒታሊዝም ከኮረዳ እቅፍ ይልቃሉ? ከጠይም ሳቅ ይገዝፋሉ? የጥርሷ መገለጥ ከአብዮት ፍንዳታ በላይ ብርሃን ይፈልቅበታል። ከእዚህች ልጅ ፍቅር የሚበልጥ ሪቮሉሽን አለ? እንጃ... መጽሐፍቱ ከቨር ላይ ያለው ራሰ በራው ሠውዬ ያ ኢሊች ሌኒን የሚሉት ይህቺን የግራ ፖለቲካ ያልተጠመቀች ሣቅ ርዕዮተ ዓለሟ የሆነች ጠይም ሴት አያውቃትም።

ወደምንቀው ፖለቲካ በሽሽቴ ተጠለፌ እወድቃለሁ። ለማንቋሸሽ በማነባቸው ቀያይ እና ቡላማ የኮሚኒስት መጻሕፍት የጭቆና ተንታኝ እሆናለሁ። ግን አይነግሩኝም አየህ የድሃ ሀገር ፖለቲካ መሠረቱ ጭቆና እንደሆነ...! ከቨራቸውን አሳምረው ሽታቸው ወርቅ የሆነ እነዛ መጻሕፍት በምሸሸው ነገር እየተሳብሁ እንደሆነ... መፈለጌን እና አለመፈለጌን እያስተሳሰሩ ዳያሌቲክስ ቅብርጥሶ በሚል ትብታብ ሥር አሰማምረው ሲጽፉልኝ ይሄን አይነግሩኝም። ግን እንደነሱ ዳያሌክቲክስ ብናወራ እውነትም የምሸሸውን እየተከተልሁ ነው።
---------------------------------
እየሄደች እንደሆነ አስብና ልቤ ይፈራል። ልቤን እንዲሸኛት ስልከው አብሮ ይቀራል። የቁራ መላክተኛ ነው። ይዘሽ ነይ እንድላት ታክቲክ መሆኑ ነው። እንዴት ሠው በአንድ ገላ ሁለት ይሆናል! ትንሽዬ የራሴ ዳያሌክት ፈጠርሁ ማለት አይደል?
እያየኋት ይህቺን በውል የማትታየኝን ፊት ትሁን ጀርባ ፌርዌል እሰድላታለሁ።

Bella Ciao!
ደህና ሁኝ ውቢት!
----------------------------------------
መሸሼ አይቆምም!
ሕዝብ መሆን እሸሻለሁ። መቆዘም ወደሚመርጥ ባለትልልቅ ቡትሌ ድራፍት እና የፈረንጅ ካቲካላ ቤት እደበቃለሁ። ሶበር ሆኜ ያራቅሁትን ሕዝብነት ከእኔን መሰል ድንጉጥ ግለኞች ጋር ተቀላቅዬ የጠርሙስ ማሕበር እፈጥራለሁ።
ሌላ ሕዝብ!

ቺርስ! ግጭ! ስለፍርሃት እንጠጣ።
---------------------------------------
እሩቅ የማያት ፋና ምናልባትም ታክቷት የቆመች፤ ያቀፍኋት። ያቀፈችኝ። እሷ! የእስከለመይቴው ፍላጎቴ የዘለዓለም ሽሽቴ እየሄደች ነው! 
ብጠየቅ እንዳላጣት ነው የተውኋት ብዬ እዋሻለሁ።
ምናልባት ልክ እሆን ይሆናል። ዞሮ መሞት ካልቀረ አይነት ይህቺን ዕድሜ የሚሏትን ጳጉሜ ታህል ዘመኔን ባለመኖር መግፋት....! ተስፋን መጣል!

ፋናዋ አይንቀሳቀስም። ፊቴን አዙሬ ብራመድ እየሄደች የማያትን እየመጣች እንደማገኛት ከመንገዴ አውቃለሁ። የክብ ተጽዕኖ አለብኝ!
----------------------------
እሰናበታታለሁ!
ደህና ሁኚ ውቢት!
በምሸሸው እቅፍ እወድቃለሁ
መኖሬ ስለሞት እንሆነ አውቃለሁ

የማይቀር ሽሽቴ ሲወስደኝ
ከተራራው አናት ላይ በአበቦች እቅፍ ቅበሪኝ

ደህና ሁኚ ውቢት!
ተረኞች በዚያ የሚልፉ
ወደሚሸሹት ሚጣደፉ

ወጪ ወራጁ ሁሉ አበባውን እያስተዋሉ
መውደቄን ውብ ነው ይላሉ

እዪልኝ ይህንን ክቤን ፈርሶ ሌላ ክብ ሲሰራ
የምሸሸውን ሞት ሞቼ የምሸሸው ሕይወት ሲዘ'ራ።

Bella Ciao!

Cheers! ስለመሸሽ!
👍42