ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ውበትን መገዘት

ከፊቷ ፀዳል ላይ ጥላ ዐይኑን ጥሎ
እድሜ ጅምር ማድያት ከመልኳ ላይ ስሎ
ዘመኗ በክንዷ ደርሶ እያሸለበ
ጊዜ ደም ግባቷን ገልጦ እያነበበ ::
ውበቷን ልትገዝት ትነሳለች ፎቶ . . .
የሳር መንገድ ወገብ ይቀራል በፎቶ
ተውርጋራጊ ዳሌ ይታተማል ጎልቶ ::

ፎቶ አንሺው ጨነቀው ፣
ያልተኖረ ዘመን የሚል የአኳሏን ቃል
ከምን ላይ ያስቀምጠው ::

©መቅደስ ሞጎስ

https://tttttt.me/GitemSitem

#መቅደስ_ሞገስ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #poetry #poetrylovers #artinaddis
የክፉ ሰው ምላስ*

ምሰሶው ተማግዶ ጎጆኣችን ነደደ
ውበት ትዝታው ላይ ፍም ሳት ወረደ
ጢሱ በአይን ሞላ ነበርን ሸፈነው
አሁን የቆምንበት ጥላሸት አመድ ነው ፡፡
ብለን ተክዘን ሳል
ካመዱ ላይ ቆመን
አንድ እውነት ገረመን
አንድ ሀቅ አመመን
እዚህ እኛ እውነት ላይ
እፍቅራችን ሞት ላይ
ነፋስ ስራው በዛ
ከአመዱ ቆንጥሮ ሰው ፊት እየነዛ ! ! !

©መቅደስ ሞገስ

#መቅደስ_ሞገስ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
አበባ ናት
ለጋ ቀንበጥ
በአረንጓዴ ዘንግነቷ
ከሩቅ የምትታይ
ውሃን ነሷት የምራቃቸውን ጠብታ እንኳ ነፈጓት !
ጠደቀች
አፈር ነሷት የምትደላደለበት
ጠደቀች
በውበቷ አሰማመረቻቸው
በፍቅሯ አቅበጠበጠቻቸው
እስትንፋሷን እፍፍ ብላ ህይወት ዘራች
የመጣችው በምክንያት ነው
ልታኖር
ያላኖሯትን
ልታደላድል
የጎረበጧትን
ፍቅር ሆነችላቸው
ህይወት ሆነችላቸው
ውበት ሆነችላችው
ሲሆንላት ፈክታ ፍንድቅድቅ ብላ
ደሞ እየጠወለገች እየሞተችም
ጠደቀች
እየረገፈች ጠደቀች
ሞቷም ውበት ነው::
ትገርመኛለች !!!
እውነቷን ያሠረችበት ዘመኗ ግን ብዙም አይደል
አጃኢብ እላለሁ ሁሌም ሳስባት !

©መቅደስ ሞገስ

#Mekdes_Moges #መቅደስ_ሞገስ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers