የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ይህ_ጉዳይ_የቤተክርስቲያን_የህልውና_ጉዳይ_ነው
#እኔም_ከመካነ_ኢየሱስ_ቤተክርስቲያን_ጎን_ነኝ

ልክ ያልሆነውን ልክ አይደለም እንላለን። የፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርክቲያንን ለመዝጋት የተደረገው ነገር ልክ አይደለም ግለሰብ ከቤተክርስቲያን የበለጠ ስልጣን የለውም። ፍትህ ለፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን። ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጎን እቆማለሁ።

#መጋቢ_እና_ዘማሪ_እንዳ ወ/ጊዮርጊስ

ብዙ አቅም የሌላቸው ሴቶችና ህፃናት የሚረዱባት ፣ ብዙዎች አገልጋይ ሆነው የሚነሱባት የፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን እዚህ ግባ በማይባል ምክንያት መዘጋቷ ልባችንን ሰብሮታል። ፍትህ ለፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን።
ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጎን ነኝ

#ነብይት_ዮዲት_ተስፋዬ
#ፍትህ_በፈረንሳይ_አከባቢ_ላለች_የመካነ_ኢየሱስ_ቤተክርስቲያን !

በፈረንሳይ አከባቢ በመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በድምፅ ምክንያት ይዘጋ ተብሎ የተወሰነው ውሳኔ በደንብ ታስቦቦት አይመስለኝም!

ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት አማኝ ነው በሚባልበት ሀገር እያንዳንዱ የሀይማኖት ተቋማት እንዲሁም አማኙ ተከባብረው በሚኖርበት የስርዓተ አምልኮ ድምፅ ረበሸኝ ልጆቼ ማጥናት አልቻሉም በሚል ሰበብ ከ700 በላይ አማኞች ስርዓተ አምልኮ እንዳያካሂዱ ቤተክርስቲያን ይዘጋ ብሎ መወሰን የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በደንብ ካለ መረዳት ወይንም ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል ።ሰለዚህ ጠቅላይ ፍ/ቤት በአስቸኳይ የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በጥልቀት ተመልክቶ እውነተኛ ፍትህ እንድሰጥ እንጠይቃለን።

#መጋቢ_ታምራት_አበጋዝ
#የአዲስ_አበባ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_ጠቅላይ_ጸሐፊ
በዛሬው ጉባኤው #ሐዋርያ_ዮሐንስ_ግርማ የካውስል ምክትል ፕሬዝዳንት፣ በምክትል ጠቅላይ ጸሃፊ መዓረግ የመንፈሳዊና የአለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ #መጋቢ_ይልማ_ዋቄ ፣የአለም አቀፍ ግኑኝነት መምሪያ ዳሬከተር #መጋቢ_አሸብር_ከተማ ሆነው መሰየማቸው ታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/_YQj2_oxohk
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍73
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ዓለም_አቀፍ_የሚሽን_ጉባኤ_በኢንዶኔዥያ_ሀገር_በታላቅ_ድምቀት_በመካሄድ_ላይ_ይገኛል፡፡
በጉባኤው ላይ፤ የመሠረተ ክርሰቶስ ቤ/ክ ፕሬዚዳንት የሆኑት #መጋቢ_ደሣለኝ_አበበ እና የወንጌል ሥርጭት እና ቤ/ክ ተከላ መምሪያ ዳይሬክተር #መጋቢ_አባይነህ_አንጁሎ_በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
መሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የዓለም አቀፍ የሚሽን ጉባኤው መሥራች አባል ስትሆን ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ መሪዎች ጋር ከወንጌል ተልዕኮ አኳያ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
እንዲሁም፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአውሮፓና ከአሜሪካ ከሚመጡ መሪዎች ጋር በተናጥል ውይይት ቤ/ክኗ እያደረገች መሆኑን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/sGrZw8A-344
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1