የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.14K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቤተክርስቲያን #በአርቴፊሻል #ኢንተለጀንት #ማምለክ #ጀመረች

በጀርመን አንዲት ቤተ ክርስቲያን በአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ የተመራ አምልኮ መርሃ ግብር መደረጉን ተሰምቷል።
ዎርዚ ኒውስ እንዳስነበበው፥ በደቡብ ምስራቃዊ ጀርመን የባቫርያ ግዛት ኑረምበርግ ከተማ የምትገኝ አንዲት የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ናት የአምልኮ መርሃ ግብሩን ሙሉ በሙሉ በአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ የተፈበረከ አምልኮን ያካሄደችው።
አርብ አርብ ለሚካሄደው የአምልኮ መርሃ ግብር ማስታወቂያ ያዩ ሰዎችም በገፍ ወደ አምልኮ አዳራሹ ከ1 ሰዓት በፊት በመምጣት ተሰልፈው ተስተውለዋል ነው የተባለው።

ChatGPT chatbot በሚባለው AI የተመራው የ45 ደቂቃ ፕሮግራም ከ300 በላይ ሰዎች መሳተፋቸውም ተሰምቷል።

ፕሮግራሙ የተለመዱትን የጸሎት፥ መዝሙር፥ ቅዳሴ እና የባርኮት ጊዜ መርቷል።
በሰው ምትክ አቫታር የሚባሉ በሰው ምስል የሚሰራ ሰው መሰል ገጸባህሪ ፕሮግራሙን መርቶታል። አግራሞትን የሚያጭረው ደግሞ አባታችን ሆይ የሚለው የፕሮግራም ማሳረጊያ ጸሎት ጋር ሲደርስ አንድ አንዶች ምቾት እንደነሳቸው መግለጻቸው ነው።

አስተባባሪዎቹ በAI እዚያው መድረክ ላይ የተቀናበረ መዝሙርም መለቀቁን ተናግረዋል።

AI በእለቱ የእምነት መግለጫ ሲመራ፥ ሲባርክም ነበረ። የበረከቱ ወቅት እንደ ሰው እጅ የሚያነሳ አቫተር ቢጠበቅም እንደ ጉርድ ፎቶ ከወገብ በላይ ብቻ ያለው ገጸባህሪ ባርኮት ሲያደርግ ነበረ።
ይሄ ዜና የተሰማው በሺዎች የሚቆጠሩ ተመራማሪዎች AI የሚፈጥረው አደጋ ብዙ ስለሆነ ቢያንስ ለ6 ወራት ገደብ ይጣልበት ሲሉ ፊርማ አሰባስበዋል። የትዊተር ባለቤት እውቁ ኢሎን መስክ ከፈራሚዎቹ መካከል ነው።

እንደኔ ብዙ ጥያቄ ያላቹ ኮሜንት ላይ እየገባቹ አስቀምጡ፥ AI ይመልሰው ይሆናል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/J-5Jkn5axcI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍3
#ቤተክርስቲያን_በአካል_ከመገኘት_ይልቅ_የቤተክርስቲያን_አገልግሎቶችን_በቀጥታ_ስርጭት_መመልከት_ተወዳጅ_እየሆነ_እንደሚገኝ_ አንድ_ጥናት_አመለከተ።
በአሜሪካ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን የሚገለገሉ ምዕመናን ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው በአካል ከመገኘት ይልቅ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፉ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶችን መመልከት በጣም ተወዳጅ አማራጭ እንደሆነ ዘግቧል።
ዘገባው 40% የሚጠጉት ሰዎች ባለፈው ዓመት ውስጥ ከአምስት ጊዜ በላይ በቀጥታ ስርጭት ተመልክተዋል ሲል ሬሌቫንት መጽሔት ዘግቧል።
የሕዝብ አስተያየት መስጫው የተካሄደው በላይፍዌይ ጥናት በፈረንጆቹ ከሴፕቴምበር 19-29/2022 እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን 1,002 ሰዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።
ጥናቱ “ባለፈው ዓመት በአካል ቤተክርስቲያን ከመገኘት ይልቅ በቀጥታ ስርጭት በቪዲዮ ምን ያህል ጊዜ ተመልክተሃል?” የሚል ሲሆን ጥናቱ ከ2019 የኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ ሰዎች በአካል ሄደው ከመሳተፍ ይልቅ የቀጥታ ስርጭትን ምርጫቸው አድርጓል ያለ ሲሆን በዚህም ሴቶችን እና ወንዶችን ጨምሮ እድሜያቸው ከ18-65 ዓመት የሆኑ ሰዎች አሳትፊያለሁ ብሏል።
ዛሬ ዛሬ የምዕራባውያን ቤተክርስቲያን አዳዲስ ነገሮች እየፈጠሩ ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ሕብረት እንዲቀሩ የያደረጉ ይመስለናል።
ይህ የቀጥታ ስርጭት የአገልግሎት አይነት አሁን አሁን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዉስጥ እየተለመደ የመጣ ሲሆን በአካል መገኘት ያልቻሉትን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ይገለጻል።
ነገር ግን በቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚደረገዉ የቅዱሳን ሕብረትና መሰባሰብ በቅዱሳን መካከል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠናክር የደከሙትን ደግሞ እንዲበረቱ የሚያደርግ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የእግዚያብሄር ትዕዛዝ ከመሆኑ አንጻር አሁን እየተለመደ ያለው ይህ አዲስ ልምምድ በቤተክርስቲያን እና በቅዱሳን ሕይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለው ግልጽ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/nxRpY2DOkIQ
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1
#የተመሳሳይ_ፆታ_ጋብቻ እና #ውርጃን_የሚያወግዝ_ሰልፍ_በሐዋሳ_ከተማ_ተካሄደ

በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ 22 የቃለ ህይወት #ቤተክርስቲያን የተወጣጡ ሰልፈኞች ከኃይማኖት እና ከባህል ያፈነገጡ ተግባራትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል።

ግብረሰዶማዊነትን፣ ወርጃን፣ ነብስ ማጥፋትን፣ ምንዝርና እና ሱሰኝነትን እንቃወማለን የሚሉ መፈክሮች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተንፀባርቋል።
ምስል ደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን
ምንጭ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/dSKHuikZTw4
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍83
የሐዋሳ ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታል ከህይወት #ብርሃን #ቤተክርስቲያን #ጋር በመተባበር በኮምፓሽን #ኢንተርናሽናል ድርጅት በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ህጻናት #ሙሉ የጤና ምርመራ ተደረገላቸው።
ለህጻናቱ ሙሉ ምርመራ በነጻ ያደረገው የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው።
የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ቡድን (Family Health Team) ከሆስፒታሉ MCC ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው ለEP 706 ህጻናት ልማት ኘሮጀክት አጠቃላይ የጤና ምርመራ ህክምና ያደረገው።
#ፓስተር ጌቱ አያሌው የሐዋሳ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መጋቢ በከተማችን ካሉ የደሀ ደሀ ህጻናት መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የቀለብና ሌሎችም ድጋፍ የሚደረግላቸው ህጻናት መኖራቸውን ገልጸዋል።
የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራአስኪያጅ አቶ ይርዳቸው አናቶ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን እና ኮምፓሽን ከሚረዱ ህጻናት ውስጥ ዛሬ ለ3 መቶ 26 ህጻናት መሉ የጤና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በሆስፒታሉ ይህንን መሰል ተግባር ቤት ለቤት የጤና ህክምና በሚሰጡ ባለሙያዎች እየተተገበረ ስለመሆኑ ያስረዱት አቶ ይርዳቸው ምርመራው የህጻናቱን እድገት ክትትል የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በዚህም የህጻናቱ እድገት፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ኤችአይቪ፣ የመሳሰሉት ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑንም አክለዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/RHf0HmwYJNM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
3👍2
#በአዲስ #አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት #በኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን #አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተክህነት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ማክሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም “ትብብርና አብሮነትን ማጎልበት ለዘላቂ #ሰላም" በሚል #መሪ #ቃል በተካሄደው ጉብኝት #እና ምክክር ላይ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባላት አባቶች የተሳተፉበት ሲሆን በኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤ/ክ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጉባኤው ቦርድ ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ እና የሀገረ ስብከቱ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች መሪዎችን ተቀብለው አስተናግደዋል። በዚሁ የጉብኝት መርሐ ግብር ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር እና የአ/አ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባል የሆኑት መጋቢ አሸብር ከተማ ተገኝተዋል።
ብጹዕነታቸው የቦርድ አባላቱን በጽ/ቤታቸው በተቀበሉበት ወቅት ወደ ታሪካዊው ሀገረ ስብከት እንኳን በሰላም መጣችሁ በማለት ሀገረ ስብከቱ ከምስረታው #ጀምሮ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎትን እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን #ይህ ጉብኝት አብሮነታችንን የሚያጠናክር በመሆኑ ሊቀጥል ይገባል በማለት እንግዶች በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ #ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው በሃይማኖቶች መካካል መቀራረብ፣ መተዋወቅ፣ መማማር እና መደጋገፍ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጎለብት ሁነኛ መሳሪያ ነው። ያሉ ሲሆን ጉባኤው #ይህንን ጉብኝት ያዘጋጀው በሃይማኖቶች መካካል የሚኖረው መከባበር፣ ትብብር እና አብሮነትን ማጠናከር ለሃገራችንም ሆነ ለከተማችን ዘላቂ ሰላምና ልማት ያለው ፋይዳ #ትልቅ በመሆኑ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት የሊቀ ጳጳሱ ልዩ ጸሐፊ ሊቀ ሕሩያን #ዮሐንስ ቀኖ የሃገረ ስብከቱ መዋቅር ፤ #ከዚህ ቀደም የሰራቸውን ስራዎችን እና ሚሰራቸው ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በሃይማኖቶች መካካል የሚኖረው ትብብር እና አብሮነትን ማጠናከር አላማ ያደረገው የጉብኝት መረሃ ግብር መሰረት በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ቤተመጽሐፍት ወመዘክር እንዲጎበኙ ተደርጓል።
የጉባኤያችን የቦርድ አመራር የሆኑ መሪዎች በጉብኝቱ እና ቤተክርስቲያኒቱ በመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ እየሰራች ያለችውን ስራዎች በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በሃይማኖት ተቋማት መከካል የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶቻቻንን ማጠናከር በመሆኑ በተቋማችን #ስራ አመራር ቦርድ ውሳኔ መሰረት ይህንን የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴት ይበልጥ ለማጎልበት እንዲረዳ የአባል #ቤተ እምነቶቹ ጉብኝት የመጀመሪያ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባ #ከተማ #እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሚከወን ይሆናል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/eIQ2PeyOHN0
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#በአዲስ #አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት #በኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን #አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተክህነት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ።
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ቤተክርስቲያንን ማፍረስ ይቁም #ቤተክርስቲያን ይከበር #
#ሰሚ_ጆሮ_ያለው_ይስማ ህግ ካለተከበረ አሁን ህጋዊ ካርታ አለን ለምንለውም ያሰጋናል፡፡”
ሁላችንም ከህግ በታች እንሁን!!!!!!!!!
ፓስተር ደሳለኝ አበበ የመሰረተ ክርስቶስ መሪ
3👍2
#አስደሳች_ዜና
#የኢትዮጵያ_ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በየትኛዉም_መልክ የተመሳሳይ #ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም።
#የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት #ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከሰሞኑ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የፈቀዱት ቡራኬ ላይ ማብራሪያ ሰጠ።
ከሰሞኑ #የሮማዉ ሊቀ ጳጳስ #ፖፕ_ፍራንሲስ ቤተክርስቲያኗ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ቡራኬ እንዲሰጡ ፈቃድ መስጠታቸዉን የተለያዩ #መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ #ጠቅላይ ጽ/ቤት በጉዳዩ #ላይ #መግለጫ አዉጥቷል። ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጋር የሚጻረር ወይንም ዉዥንብርን ሊፈጥር የሚችል ስርዓተ አምልኮን ያወግዛል ብሏል።
ሆኖም የጳጳሱ መልዕክት በተቃራኒው ተወስዷል የሚል ሃሳብ ያለዉን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጋብቻን #ግን ጳጳሱ ፈቃድ አልሰጡም ብሏል።
አክሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስቀመጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም ፤ አታጸድቅምም ማለቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከመግለጫው ተመልክቷል።
ቤተክርስቲያኒቱ ሀጢያትን አትባርክም ታወግዛለች #እንጂ ያለዉ መግለጫዉ የተመሳሳይ ጾታ #ጋብቻ የኢትዮጵያ ባህል #እና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረዉም በመግለጫው አስታዉቋል።
7👍4👎3🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ቤተክርስቲያን_የሰው_ፍቃድ_የሚፈጸምበት_አይደለም
ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር የሰጠንን ፀጋ በሰፋት ለ ተውልድ የምናደርስበት እንጂ ፤
#አገልጋይ_ገዳ_ረጋሳ
👍13