የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
https://youtu.be/_YQj2_oxohk
#ቪዲዮውን_ለመመልከት_ከላይ_ሊንኩን_ይጫኑ
#መግለጫ
የኢትዯጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት በመካከላቸው የተፈጠረውን ልዩነት በእርቅ ፈቱ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/_YQj2_oxohk
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏21
https://youtu.be/8f0kbYG0EJM
ቪዲዮውን ለመመልከት ከላይ ሊንኩን ይጫኑ
#መግለጫ
የእምነት ተቋማት ሊከበሩ ይገባል ፡፡ መንግስት ህዝብ የሰጠውን አደራ እንዲጠብቅ እናሳስባለን፡፡

የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል #ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/8f0kbYG0EJM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2
ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ወጣቶች የተሰጠ #መግለጫ
የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል ወጣቶች ኮሚሽን ከመቼውም ጊዜ በላይ በወንጌል አማኞች ቤተ እምነቶች ውስጥ ያሉ ወጣቶችን በማስተባበር እና በመቀናጀት ለማገልገል እንዲሁም ጉብዝናችንን ለእግዚአብሔር ክብር ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ለማድረግ ተደራጅተን እየሰራን እንገኛለን ።ወንጌላውያን
ወጣቶች ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን የሰጣትን መለኮታዊ ትዕዛዝ ከግብ ለማድረስም እስትራቴጂ በመቀየስ ዘርፈ ብዙ ሁለንተናዊ ስራዎችን ለመስራት እየተዘጋጀን እንገኛለን ።
ዛሬም በካውንስሉ አባል ቤተ እምነቶች ውስጥ ያላችሁ ወጣቶች የተደረገላችሁን ጥሪ አክብራችሁ ስለተገኛችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን ይህ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ እጅግ ተቀራርበንና ተደራጅተን ለቤተ እምነቶቻችን ድምጽ መሆን እንደሚገባን እያሳሰብን በዚህ ወቅት በታችኛው የመንግስት መዋቅር ላይ የተቀመጡ የመንግስት ስልጣን በሚጠቀሙ አካላት
1.በቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ላይ
2.በቃለ ሕይወት ኩሪፍቱ ማዕከል
3.በሐላባ ጋለቶ ቃለ ሕይወትና ርሆቦት መካነ ኢየሱስ
4.በኦሎምፒያ መሰረተ ክርስቶስ
5.በመካነ ኢየሱስ ጉድ ሸፐርድ
6.በቄራ ብርሀነ ክርስቶስ
7.በእምነት መጥምቃውያን
8.በአዲስ ከተማ ገነት ቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረሱ ያሉትን ሕገ መንግስቱን የሚጣረስ አሰራር እና ጫና እንዲቆም እኛ የወንጌል አማኝ ወጣቶች እየጠየቅን የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ጣልቃ በመግባት የታችኛው የመንግስት መዋቅር በ ቤተ እምነቶቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና እንዲያስቆሙ እየጠየቅን እኛ ወጣቶች መሪዎቻችን በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሰረት ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እስከሚገኝ ድረስ ድምጻችንን ማሰማት የምንቀጥል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ።

ህዳር 30/2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዪጲያ
ዩዝ ኮሚሽን
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/xOph9o-zDfo
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍71
#አስደሳች_ዜና
#የኢትዮጵያ_ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በየትኛዉም_መልክ የተመሳሳይ #ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም።
#የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት #ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከሰሞኑ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የፈቀዱት ቡራኬ ላይ ማብራሪያ ሰጠ።
ከሰሞኑ #የሮማዉ ሊቀ ጳጳስ #ፖፕ_ፍራንሲስ ቤተክርስቲያኗ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ቡራኬ እንዲሰጡ ፈቃድ መስጠታቸዉን የተለያዩ #መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ #ጠቅላይ ጽ/ቤት በጉዳዩ #ላይ #መግለጫ አዉጥቷል። ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጋር የሚጻረር ወይንም ዉዥንብርን ሊፈጥር የሚችል ስርዓተ አምልኮን ያወግዛል ብሏል።
ሆኖም የጳጳሱ መልዕክት በተቃራኒው ተወስዷል የሚል ሃሳብ ያለዉን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጋብቻን #ግን ጳጳሱ ፈቃድ አልሰጡም ብሏል።
አክሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስቀመጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም ፤ አታጸድቅምም ማለቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከመግለጫው ተመልክቷል።
ቤተክርስቲያኒቱ ሀጢያትን አትባርክም ታወግዛለች #እንጂ ያለዉ መግለጫዉ የተመሳሳይ ጾታ #ጋብቻ የኢትዮጵያ ባህል #እና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረዉም በመግለጫው አስታዉቋል።
7👍4👎3🔥1