#update ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ፈረንሳይ #ገቡ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር #ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፓ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉበኝት በዛሬው እለት ጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ የጀመሩ ሲሆን፥ በዛሬው እለትም ፈረንሳይ ገብተዋል።
በፈረንሳይ በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በቆይታቸውም በአጠቃላይ የሁለትዮሽና የጋራ አጀንዳ በሆኑ አካባቢያዊና አለምዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ምንጭ ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@yenetube @mycase27

#የህግ ባለሙያዋ ብርቱካን ሚደቅሳ አዲስ አበባ #ገቡ፡፡
ዛሬ ጧት አዲስ አበባ የገቡት ወ/ሪት #ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሰባት ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ነው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡
ከዚህ በፊት በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገው ነበር፡፡
አሁንም ለፍትህ መስፈን የበኩላቸውን እንደሚወጡ #ገልፀዋል ፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ፣ ከዩናይትድ ስቴትሱ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል ።
ወ/ሪት #ብርቱካን በፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣በሕግ ባለሞያና ጠበቃ፣ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መስራች የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል ።
ከ97 ምርጫ በኋላ ሁለት ጊዜ የፖለቲካ እስረኛ ሆነዋል ።
ለዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ላደረጉት አስተዋጽኦም ዓለም አቀፍ ሽልማት ማግኘታቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው ።
ምንጭ ፦ኢቢሲ

#update በቁጥጥር ስር የዋሉት የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው አዲስ አበባ #ገቡ
በዛሬው እለት በቁጥጠር ስር የዋሉት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው አዲስ አበባ ገብተዋል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው ተጠርጣሪው በሁመራ በኩል ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።
©FBC