YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የህግ ባለሙያዋ ብርቱካን ሚደቅሳ አዲስ አበባ #ገቡ፡፡

ዛሬ ጧት አዲስ አበባ የገቡት ወ/ሪት #ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሰባት ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ነው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡

ከዚህ በፊት በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገው ነበር፡፡
አሁንም ለፍትህ መስፈን የበኩላቸውን እንደሚወጡ #ገልፀዋል ፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ፣ ከዩናይትድ ስቴትሱ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል ።

ወ/ሪት #ብርቱካን በፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣በሕግ ባለሞያና ጠበቃ፣ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መስራች የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል ።
ከ97 ምርጫ በኋላ ሁለት ጊዜ የፖለቲካ እስረኛ ሆነዋል ።

ለዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ላደረጉት አስተዋጽኦም ዓለም አቀፍ ሽልማት ማግኘታቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው ።
ምንጭ ፦ኢቢሲ
@yenetube @mycase27