ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከዚህ በፊት በታዩ ጥቃቶች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ በመሉ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ከሁሉም በላይ ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲቻል የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ ያስፈልጋል ተብሎአል።
#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭ ላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ባዘጋጀው ምጥን የፖሊሲ ሃሳብ ላይ ውይይት እንዳዘጋጀ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ በመጭው ቅዳሜ በሚካሄደው ውይይት፣ አንጋፋዎቹ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በፍቃዱ ደግፌ (/ዶ/ር) እና ዐለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ጥናታዊ ወረቀቶችን ያቀርባሉ፡፡ ፓርቲው በዚሁ ጉዳይ ላይ ያዘጋጀውን ምጥን የፖሊሲ ሃሳብ ቀደም ብሎ ይፋ ያደርጋል፡፡
#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 22.3 በመቶ አሻቅቧል።
የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው የምግብ ዋጋ ግሽበት 24.9 በመቶ ሲደርስ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 18.9 በመቶ ደርሷል።የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሐምሌ ወር "አብዛኛዎቹ የእህል ዓይነቶች እና አትክልት ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን ለምግብ ዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛ አሰተዋጽዖ አላቸው" ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ሊያሳድር የሚችለውን ማሕበራዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ጫና በተነተነበት እና ባለፈው ግንቦት ይፋ ባደረገው ጥናት ግን በተለይ የምግብ ዋጋ ግሽበት በሚቀጥሉት አምስት ወራት ሊጨምር እንደሚችል ጥቆማ ሰጥቷል።የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮ ትንታኔ ኮሮና በአገሪቱ ሊስፋፋ የሚችልበትን ፍጥነት፤ ወረርሽኙን ለመቋቋም ገቢራዊ የሚደረጉ ክልከላዎችን ክብደት፤ የበረሐ አንበጣ መንጋ እና የውጭ ምንዛሪ ተመን የሚደርስበትን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት በሶስት ሁኔታዎች የተከፋፈለ ነው።
በትናንታኔው መሠረት ኮሮና በኢትዮጵያ እጅግ ከከፋ እና ወረርሽኙን ለመከላከል ተግባራዊ የሚደረጉ እርምጃዎች ከጠነከሩ የምግብ ዋጋ ግሽበት እስከ 40 በመቶ ሊያሻቅብ ይችላል።ይኼ ሶስተኛው እና አስከፊው ኹኔታ ሊከሰት የሚችለው በወር በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺሕ በላይ ካሻቀበ እና በመላ አገሪቱ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ሥራ ላይ ከዋሉ ነው።የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው አቶ አብዱልመናን መሐመድ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የባሰ ገጥሟት ቢያውቅም የዋጋ ግሽበቱ የተባበሩት መንግሥታት ሰነድ ባለው መጠን ከጨመረ ፈታኝ መሆኑ አይቀርም።

⬆️“ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው”
#ድምጻዊ_ኢቲቃ_ተፈሪ
በኦሮምኛ የፖለቲካ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ ሳምንታት መቆጠሩን ለቢቢሲ ተናግሯል።
ድምጻዊው "በሽታው እንዲህ አይነት ቦታ ያዘኝ ብዬ መናገር አልችልም" ካለ በኋላ የሚጠረጥረው ስፍራ እንዳለ ግን ገልጿል።
ድምጻዊው ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ በተገደለበት እለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ ከጓደኞቹ ጋር በሆስፒታል ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ እንደነበር ያስታውሳል።
አምቦ በነበረው የቀብር ስነስርዓት ላይም አብዛኛው ሰው በሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልተጠቀመም ነበር።
ትልቁ ጥርጣሬዬ ይህ እንደሆነ የሚናገረው ድምጻዊ ሂቲቃ፣ ከአምቦ ከተመለሰ በኋላ የሕመም ስሜት ተሰምቶት ወደ ግል ጤና ጣብያ ቢሄድም ሌላ በሽታ ነው ተብሎ መርፌና ኪኒን ታዘዘለት።
ይሁን እንጂ በራሱ ላይ የተመለከታቸው የሕመም ስሜቶች የኮሮናቫይረስ ነበሩ ይላል ድምጻዊ ሂቲቃ።
" ሰውነቴ በጣም ይደክማል፤ ደረቅ ሳል ሳያቋርጥ ለሶስት ሰዓት ያስለኝ ነበር" በማለት ከዚያ በኋላ ለጤና ቢሮ በመደወል ምርመራ እንደተደረገለት እና በኮሮናቫይረስ መያዙ ሲረጋገጥም ወደ ሚሌኒየም አዳራሽ ተወስዶ ሕክምና እና እንክብካቤ ሲደረግለት መቆየቱን ይናገራል።
"የምኖረው ከእህቴ ጋር ነው፣ እርሷም ተይዛ ነበር፤ እርሷ ህመም እንደኔ ስላልጠናባት ቤት ውስጥ በተደረገላት እንክብካቤ ነው የተሻላት፤ እኔ ግን ለሁለት ሳምንታት ሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ ሕክምና ድጋፍ ተደርጎልኛል።" ይላል
በሚሊኒየም አዳራሽ ያሳለፋቸው ሁለት ሳምንታት ፈታኝ እንደነበረ የሚናገረው ኢቲቃ ሆኖም በጤና ባለሙያዎቹ ለታማሚዎች የሚደረገው ህክምናና እንክብካቤ ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን ይጠቅሳል።
በከባድ ህመም ያሳለፈባቸው ሳምንታት በመጥቀስ ማህበረሰቡ በሽታውን አቅልሎ ማየት እንደሌለበትም ይመክራል።
" ሳሉ በጣም ከባድ ነበር፤ ሁለት ለሊት ጭንቅላቴን ይዤ ነበር ሳስል ያሳለፍኩት፤ ከሚነገረው በላይ በጣም በጣም ከባድ ጊዜ ነበር፤ ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው፤ ስለዚህ ለራስ ጥንቃቄ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው።" በማለት መልእክቱን አስተላልፏል።
ድምጻዊ ሂቲቃ፣ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ የዳነ ባይሆንም ከአምስት ቀናት በፊት ከሚሌኒየም የማቆያና ህክምና ማእከል በመውጣት ወደ ቤቱ ተመልሷል።
"ቤት እየተመላለስን እንከታተልሃለን ተብዬ ነው የወጣሁት" በማለት የጤና ባለሙያዎቹ ቃል በገቡት መሰረት ከማቆያው ከተመለሰ በኋላ ቤቱ ድረስ እየመጡ ክትትል እንዳደረጉለት ገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት ሞልቶ ባይሻለውም ከነበረበት ሁኔታ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
"በህመሜ ሰዓት በሁሉም መንገድ ይጠይቁኝና ሲያበራቱኝ የነበሩ አድናቂዎቼና ማህበረሰቡን ላመሰግን እወዳለሁ፤ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ፤ ከሚያሰጋኝ ነገር ውስጥ ወጥቻለሁ ማለት እችላለሁ።"
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጥቃት የፈጸሙ አምስት አጥቂዎች #ሲገደሉ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ በተፈጸመ ጥቃት የ13 ዜጎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አምስት ሽፍታዎች መገደላቸውን ቢሮው #ለአዲስ_ማለዳ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ በተፈጸመ ጥቃት የ13 ዜጎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አምስት ሽፍታዎች መገደላቸውን ቢሮው #ለአዲስ_ማለዳ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ፌስቡክና ትዊተር፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የቅስቀሳ ቡድናቸው ተገቢ ያልሆነ መረጃ አስተላልፈዋል በሚል እርምጃ ወስደውባቸዋል።
ፌስቡክ የፕሬዝደንቱ መልዕክቱ ጎጂ የኮቪድ-19 መረጃ ይዟል በሚል ከመድረኩ ላይ እንዲወገድ አድርጓል። ትዊተር ደግሞ የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን የለጠፈውን መልዕክት እስኪያወርድ ድረስ አግዶታል።
ትራምፕ ፎክስ ኒውስ ከተሰኘው ጣብያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ላይ 'ሕፃናት ኮሮናቫይረስ አይዛቸውም' ያሉበትን ምስል በማጋራታቸው ነው እርምጃ የተወሰደባቸው።
የአሜሪካ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ሕፃናት ለኮሮናቫይረስ ይጋለጣሉ ይላል።
የፌስቡክ ቃል-አቀባይ 'ምስሉ ስለ ኮቪድ-19 ሃሰተኛ የሆነ መረጃ ይዟል፤ ይህ ደግሞ ስለ ኮቪድ-19 ያለንን ፖሊሲ የሚጥስ ነው' ብለዋል።
via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa

በኮቪድ 19 ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮ ጅቡቲ ድንበር እንዲከፈት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ።
ወሳኔው የጅቡቲ ዜጎች በሚቀመጡ የጤና ቅድመ ሁኔታ መሰረት ወደ አገር መግባት ይችላሉ።
የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ሙጂብ ጀማል እንደገለፁት በዚህ ወቅት የጅቡቲ አየር በጣም የሚሞቅ በመሆኑ የአገሪቱ ዜጎች ወቅቱን በኢትዮጵያ ለማሳለፍ ፍላጎት በመኖሩ የተወሰነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
Via:- Capital News

የኢትዮጵያ የባህር እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት በበጀት አመቱ 25.7 ቢሊየን ብር ገቢ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ በ2011 በጀት አመት አጠቃላይ ገቢው 18.7 ቢሊየን ብር የነበር ሲሆን ዘንድሮ በ37 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡የኢትዮጲያ የባህር እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት አጠቃላይ ጭነቱ 16.7 ሚሊየን ቶን መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ከዚህ በፊት አገልግሎቱን ሰጥቶባቸው በማያውቃቸው የስንዴና የአፈር ማዳበሪያም የጭነት አገልግሉት መስጡን አስታውሰዋል፡፡አቶ ሮባ እንዳሉት በስንዴ 2.45 ሚሊየን ኮንታል በላይ እንዲሆም በአፈር ማዳበሪያ 6.7 ሚሊየን ቶን የጭነት አገልግሉት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡
በበጀት አመቱ በድርጅቱ መርከቦች ብቻ 1 ሚሊየን ቶን የሚጠጋ የጭነት አገልግሉት ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡በዛሬው እለትም የድርጅቱ ሰራተኞችና የማኒጅመንት አባላት በሞጆ ሎሚ ወረዳ 17 ሄክታር መሬት ላይ የችግኝ ተከላ እያከናወነ ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭነት ለመከላከል የሚያስችል 3 ሚሊየን የሚጠጋ የመከላከያ ቁሳቁስ አቅርቢያለሁ ብሏል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከድርጅቱ ሰራተኞች በማወጣት 2.3 ሚሊየን ብር ድጋር አድርጓል፡፡
Via Ethio FM

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 564 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን 429 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 9068 የላቦራቶሪ ምርመራ 564 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 900 ደርሷል።በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 429 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9027 ሆኗል።በዛሬው ዕለት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 365 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት 170 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ይገኛሉ፤ 11 ሺህ 506 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል

ስራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከኃላፊነታቸው ለቀቁ!
የስራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ለኹለት ዓመታት ገደማ ሲያገለግሉ ነበሩት ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ።ዶክተር ኤፍሬም በግል ምክንያታቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ያስታወቁ ሲሆን በአጭር ጊዜያት ውስጥ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ሲለቁ ከቀድሞው ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ አበባየሁ ቀጥሎ ዶክተር ኤፍሬም ኹለተኛው መሆናቸው የሚታወቅ ነው።
Via Addis Maleda

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድና እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ።
አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው እለት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋርን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ የከፈተ ሲሆን፥ በዚህ መዝገብ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ ጋዜጠኛም ተካቷል። አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 215585 የቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል።
በተጨማሪም የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 15 ምስክሮች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን፤ እንዲሁም 5 ምስክሮች ደግሞ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ አቅርቧል።በተጨማሪም በዝግ ችሎት ምስክሮቹ ቃላቸውን እንዲሰጡም ጠይቋል።የሁሉም ተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው አቃቤ ህግ ያቀረበው አቤቱታ ላይ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል።በዚህም በዝግ ችሎት ተብሎ ለቀረበው አቤቱታ በግልፅ ችሎች ምስክሮቹ እንዲሰሙ እንደሚፈልጉ እና አቃቤ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ጭብጥ ለመከላከል እንደሚያመች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
እንዲሁም ምስክሮቹ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃል መስጠት እንደሌለባቸው እና ስም ዝርዝራቸውም ተለይቶ ተሰጥቷቸው አውቀዋቸው የምስክርነት ቃላቸውን ሊሰጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።ክሱ ስልጣን ባለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ የምስክር ቃልም ለክሱ መከላከል እንዲያስችላቸው አስቀድመው ሊያውቁት እንደሚገባም በመቃወሚያዎችን አንስተዋል።ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ፥ “የማስመዘግበው አቤቱታ አለኝ፤ ሀሳቤን ፍርድ ቤቱ ይቀበለኝ” ያሉ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ “በጠበቆቻችሁ በኩል በቂ ሀሳብ ተነስቷል” ሲል አልተቀበላቸውም።የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ብይን ሰጥቷል።
በተለይም በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት የቀረበው የቅድመ ምርመራ የአቃቤ ህግ ምስክሮች በዝግ ችሎት ቃላቸው እንደሚሰማ እና ይህም ክስ ከመመስረቱ በፊት የሚደረግ የቅድመ ምርመራ በዝግ ችሎት እንደሚሆን አብራርቷል። የምስክሮችን ዝርዝር እና ጭብጥ ጉዳይ ይሰጠን ተብሎ በቀረበ መቃወሚያ ላይም ለደህንነታቸው ታሳቢ ተደርጎ እንደማይሰጥና አምስቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮችም ከመጋረጃ በስተጀርባ ቃላቸውን እንዲሰጡ ብይን ሰጥቷል።የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቅድመ ምርመራ መዝገቡ ላይ የምስክሮች ቃል እንዲሰማ ለነሃሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
#FBC

የትግራይ ክልል ምክርቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ሕገ-መንግስት ማሻሻያ አደረገ፡፡ ምክርቤቱ የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 48 ቁጥር ሁለት የቀየረ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት የምርጫ ስርዓቱ ከአብላጫ ድምፅ ወደ ቅይጥ (mixed) ቀይሯል፡፡
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa1
ፌደራል ፖሊስ ትናንት ሦስት ጋዜጠኞቹን እንዳሰረበት አሥራት ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡ ታሳሪዎቹ ጋዜጠኞች በላይ ማናየ፣ ሙሉጌታ አንበርብር እና ምስጋናው ከፈለኝ ናቸው፡፡ ከጣቢያው ቀደም ሲል የለቀቀው የካሜራ ባለሙያ ዮናታን ሙሉጌታም እንደታሠረ ዘገባው ጠቅሷል፡፡
#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
የሰሞኑ ከባድ ቅዝቃዜ ለተከታታይ ቀናት ሊዘልቅ እንደሚችል ብሄራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ የቅዝቃዜው ምክንያትም የሆነው ከደቡብ ህንድ እና ከደቡብ አትላንቲክ ውቅያኖሶች የሚገባው እርጥበት አዘል ከባድ ነፋስ ነው ተብሏል፡፡
#Sheger
@YeneTube @FikerAssefa1
#Sheger
@YeneTube @FikerAssefa1
ከትናንት በስትያ ምሽት መዲና ቤይሩትን ባናወጠዉ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ እስካሁን 10 ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉ መታወቁ ተነገረ።
በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ኢትዮጵያዊትዋ ትዕግስት ለዶቼ ቬለ በስልክ እንዳረጋገጠችዉ የአገሪቱ መንግሥት እስካሁን አስር ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉን አረጋግጦአል።በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ይህች ኢትዮጵያዊት መዲና ቤይሩት አሁንም በፍርስራሽ ስር የተቀበሩ አስክሪንን እያወጣች መሆኑን ተናግራለች። በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ተመስገን ዑመር ትናንት ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት በሊባኖስ ከ 250 እስከ 300 ሺህ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ፤ አብዛኞቹ ደግሞ ደግሞ የሚገኙት ቤይሩት ከተማ ዉስጥ ነዉ።

በኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል ተባለ!
በሃገሪቱ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትሉ የሚችሉ የዝናብ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትርዎሎጂ ኤጄንሲ አስጠነቀቀ። ኤጄንሲው እንዳለው በሃገሪቱ በተከታታይ እየጣለ የክረምቱ ዝናብ ድንገተኛ ጎርፍ አስከትሎ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ብርቱ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲል አሳስቧል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአዋሽ ወንዝ ከተፈጥሮ ፍሰቱ ሰብሮ በመውጣት በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በሰብል እና የግጦሽ መሬቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው።

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን ተሸገረ፡፡
በአፍሪካ በኮቪድ -19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊየን መሻገሩን የተናገረው መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የጆንስ ሆፒከንስ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ከዚህ ከተያዙት ግማሽ ያህሉን የያዘችው ደግሞ ደቡብ አፍሪ ናት ብሏል ቢቢሲ ዩኒቨርስቲውን ጠቅሶ፡፡በርካታ የአፍሪካ ሀገራት አሁን እየመረመሩት ያለው ናሙና አነስተኛ በመሆኑ ነው እንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችልም ተገምቷል፡፡በአህጉሪቱ ባሉ ትልልቅ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑም ተነግሯል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በአለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18.6 ሚሊዮን ነው፡፡ ከ702 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።በአፍሪካ ደግሞ 21ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲሞቱ ከ670 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።
የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀዋሳ መካሄድ ጀመሯል።ምክር ቤቱ በ3 ቀናት ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።ጉባኤውን በንግግር ያስጀመሩት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ የዘመናት የህዝቦች ጥያቄና ቁጭት የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ወደ ውጤት መቃረብና የመጀመሪያ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
የሀገራችንን ለውጥ ለመቀልበስ የፓለቲካና የግጭት መንገድን በመቀላቀል የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ሁሉም ዜጋ ሊታገላቸው ይገባል ያሉት አፈ ጉባኤዋ መንግስትም ሆነ የምክር ቤት አባላት የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ በንቃት ሊንቀሳቀሱ እንደሚባም ተናግረዋል።ተስፋ ሰጪ የሆነውን የሀገራችን የዴሞክራሲ ሂደት እንዳይቀለበስ ሁላችንም የተለየ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል ሲሉም አክለዋል።ለዚህ ደግሞ ከእኔ ሀሳብ ውጭ የሚል አመለካከትን መዋጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
መንግስት በተቋማት ግንባታ ላይ በመረባረብ ዘላቂና አስተማማኝ የህዝብ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጥ እንደሚገባም ወ/ሮ ጥሪ አቅርበዋል።የክልሉ መንግሥት የህዝቡን የአደረጃጀት ጥያቄዎች ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ያነሱት አፈ ጉባኤዋ በዚህ ሂደት ውስጥ የሚታዩ አፍራሽ መልዕክቶችን መመከት ይገባል ብለዋል።ህብረተሰቡ የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራን በማጠናከርና የባህሪ ለውጥ በማውጣት የሚደርሰውን ሰብኣዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሊደግፍ ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በአሁኑ ወቅትም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የስራ አፈጻጸም እያቀረቡ ነው።
ምንጭ: የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽን

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገብተው በደቡብ አፍሪካ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ 218 ዜጎች ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1