YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጋምቤላ ክልል በእርሻ ዘርፍ መሬት ወስደው ያላለሙ የ285 ባለሃብቶችን የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰረዙ ተገቢ ያልሆነና ጊዜውንም ያላማከለ ነው ሲሉ በክልሉ በእርሻ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ ባለሀብቶች ቅሬታቸውን ገለፁ።

የባለሀብቶቹ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰረዙን ተከትሎ በጋምቤላ ኢንቨስተሮች ማኅበር ሊቀ መንበር ጊዜውን የጠበቀ ውሳኔ አይደለም ሲሉ #ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጥቃት የፈጸሙ አምስት አጥቂዎች #ሲገደሉ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ በተፈጸመ ጥቃት የ13 ዜጎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ አምስት ሽፍታዎች መገደላቸውን ቢሮው #ለአዲስ_ማለዳ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa