አሁን እንሞላለን ፤ በሙሌቱ ግን እንስማማ የሚል ነባር እና አዲስ ያልሆነ ሀሳብ እንጂ ምንም አይነት አዲስ ሀሳብ ኢትዮጵያ አላቀረበችም ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል። ይህን ያህል ውሀ ገድቡ ወይም ይህን ያህል ውሀ ልቀቁ የሚል ድርድር ውስጥ ግን አንገባም ሲሉም አክለው አስታውቀዋል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1
አፋን ኦሮሞ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በጨፌ ኦሮሚያ የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ወ/ሮ አለምነሽ አስፋው አስታወቁ፡፡
መንግስት አፋን ኦሮሞ አንዲስፋፋ ካከናወናቸው ስራዎች መካከል አንዱ በዚህ አመት የኦሮሚያ ት/ት ቢሮ መፅሀፍቶችን በማሳተም ለዘጠኝ ክልሎች በማበርከት ሁሉም ክልሎች ቋንቋውን እንዲያስተምሩ መደረጉን ወ/ሮ አለምነሽ ለኦቢኤን ገልፀዋል፡፡ጨፌ ኦሮሚያ አፋን ኦሮሞ ይበልጥ እንዲስፋፋ ከ1ኛ ክፍል አስከ PHD ድረስ በቋንቋው ትምህርት እንዲሰጥ ሲሰራ ቆይቷል ነው ያሉት ሊቀመንበሯ፡፡በዚህ አመት በአምቦ ዩንቨርስቲ በተደረገ ፎረም ላይ ሌሎች ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን ቋንቋውን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ በሚቻልበት ሂደት ጥናታዊ ፅሁፍ ቀረቧል፡፡ጨፌው ጥናቶቹን እንደግብአት በመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ አለምነሽ ተናግረዋል፡፡በህግ መንግስቱ ላይ የተቀመጠውን የፌደራል የሥራ ቋንቋ አማርኛ ብቻ የሚለውን ለማሻሻል የሁሉም ክልሎች ተወካዮች ቢያንስ 2/3ኛው ጉዳዩን አምኖበት ሊወስን ይገባል ብለዋል፡፡
#OBN

በባሕር ዳር ከተማ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ለተሠው 'ሠማእታት' መታሠቢያ ዝግጅት ተካሄደ!
ለአማራ ሕዝብ ነፃነት፣ ፍትሕ፣ እኩልነት እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ሲታገሉ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ለተሠው 'ሠማእታት' የመታሠቢያ ዝግጅት ተካሂዷል።ለእነዚህ 'ሠማእታት' ከሐምሌ 28 ጀምሮ መታሠቢያ ዝግጅት እየተከናወነ ሲሆን፣ በዚህም የችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ እና የፅዳት ዘመቻ መርሐ-ግብሮች ተካሂደዋል። ዛሬ በተካሄደው የማጠቃለያ ፕሮግራም ለሠማእታቱ መንገድ የመሠየም እና የመታሠቢያ ሐውልት የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
ሠማእታቱን ለመዘከር በባሕር ዳር ከተማ ከቤዛዊት ቤተ መንግሥት መገንጠያ መንገድ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን መንገድ ድረስ ያለው 1.5 ኪሎ ሜትር "የነሐሴ ሠማእታት ጎዳና" በሚል ተሰይሟል። ወደ ባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደው እና ገጠር መንገድ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ባለው አደባባይ ላይም የመታሰቢያ ሐውልት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦላቸዋል። በመታሠቢያ ዝግጅቱ ላይ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የባሕር ዳር ከተማ ም/ከንቲባ አቶ አማረ ዓለሙ፣ የክልሉ እና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የከተማው ወጣቶች ታድመዋል።
#ETV

ከ700 ሺ በላይ የፓስፖረት ደብተር በክምችት እንደያዘ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ!
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል በቂ ፓስፖት መግባቱን ገልፀው በፓስፖርት ማግኘት ሂደት ውስጥ የሚኖረውን የተንዛዛ ስራ ለመቅረፍ በተለያየ መልኩ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የፓስፖረት እድሳት በተቋሙ መምጣት ሳያስፈልግ በአማራጭነት ኦንላይን ሂደቱን ማከናወን የሚያስችል ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ተደራሽነትን ማስፋት ሌላው አካሄድ ነው፡፡ ሆሳእና፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ቅርንጫፍ የመክፈት ሂደቱ እየተጠናቀቀ ነው ያሉት አቶ ሙጂብ በአዲስ አበባም 2 ቅርንጫፍ ከመክፈት የቢሮ ኪራይ ጨረታ አውጥተናል ብለዋል፡፡እጥረት ሲፈጠር ብልሹ አሰራር ይታያል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በህገወጥ ተዋናዮች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ጠቅሰዋል፡፡የፓስፖርት እጥረት ባለፉት ሁለት አመታት ግድም በመታየቱ የፓስፖርት መስጫ ግዜ ወደ 75 ቀን ግድም ሆኖ ነበር፡፡ ሆኖም እጥረቱ በመቀረፉ የመስጫ ግዜ ወደ 30 ቀን ወርዷል ብለዋል፡፡ይህም የተለመደ አሰራር ነው ለምሳሌ በፓስፖርት ምርት ታዋቂ የሆነችው ጀርመን ፓስፖረት ለመስጠት ከ4 እስከ 6 ሳምንት ያስፈልጋል፣ በማለት አብራርተዋል።አጣዳፊ ጉዳይ ኖሮት ማስረጃ የሚያቀርብ ባለጉዳይ በተጨማሪ ክፍያ በቀናት ፓስፖርቱን ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡
#Capital

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 13 ሰዎች ሲሞቱ በ8 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
በጭነት ተሽከርካሪ ላይ ሰዎችን በመጫን በሚከናወነው አገልግሎት የሚደርሰው ጥፋት ከፍተኛ እንዲሆን ምክንያት ነው ተብሏል።የዞኑ ፖሊስ መመሪያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ተጠባባቂ ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለዶቼ ቬለ በስልክ በሰጡት መረጃ አደጋው የደረሰው ከወረዳው በሬዳ ገጠር ቀበሌ ወደ ሐረዋጫ ከተማ 21 ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-09576 አ/አ አይሱዙ የጭነት መኪና ሙሉኢሳ ገጠር ቀበሌ ላይ በመገልበጡ መሆኑን አመልክተዋል።ትናንት ምሽት ደረሰ በተባለው በዚህ አደጋ 13 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ስምንት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል። እሳቸው እንደገለጹት ጉዳት ከደረሰባቸው አብዛኞቹ ለንግድ ሥራ ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሱ ናቸው።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደደር ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን እና የሟቾች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው እየወሰዱ እንደሚገኙም አስረድተዋል።የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የነበረው ዝናብና ጉም ተሽከርካሪው ወደኋላ እንዲሸራተት በማድረጉ መሆኑን የጠቆሙት ኢንስፔክተር ቶሎሳ ትክክለኛውን መንስኤ ለማወቅ ለጊዜው የተሰወረውን አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ በክትትል ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በአካባቢው ለሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ በጭነት መኪና እንደሚጠቀም ጠቅሰው ይህም በየጊዜው በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከፍተኛ እያደረገው መሆኑንም አመልክተዋል።
#DW

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ ጥይት ተኩሶ በመግደል ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ወንጀሉን መፈፀሙን አመነ!
በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ ጥይት ተኩሶ በመግደል ወንጀል የተጠረጠረው አቶ ጥላሁን ያሚ የተባለው ግለሰብ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ ለፖሊስ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል አረጋገጠ። ተጠርጣሪው “ይህንን ተልእኮ የሰጡኝ ሰዎች ድርጊቱን መፈፀምህን በሚስጥር የማትይዝ ከሆነ በቤተሰቦችህ ላይ ጉዳት እናደርሳለን” በማለት እንዳስጠነቀቁት ለፈደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የአራዳ ምድብ፣ አንደኛ ወንጀል ችሎት ተናግሯል።በዚህም “ለቤተሰቦቼ በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸው እና የኔም ጉዳይ በፍጥነት እልባት እንዲያገኝ” በማለት ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል።“የፀሀይ ብርሀን አግኝቼ አላውቅም፣ ካቴና ከእጄ አልወለቀም፣ ክስ እስከሚመሰረትብኝ እንኳን ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር እንድቀላቀል ይደረግልኝ” በማለት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርቧል።
ተጠርጣሪው ባለፈው የጊዜ ቀጠሮ በዚሁ ችሎት ቀርቦ “እራሴን እንዳጠፋ ይፈቀድልኝ” ማለቱን ችሎቱ አስታውሷል።በዚያው ቀጠሮው መርማሪ ፖሊስ ካቴናው ከእጁ የማይወልቀው ተጠርጣሪው እራሱን እንዳያጠፋ ለመከላከል መሆኑንም ችሎቱ ገልጿል።መርማሪ ፖሊስ በዛሬው ቀጠሮው ተጠርጣሪው የካቴናውን ጉዳይ ዳግም በማንሳቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሚመለከተው የስራ ሀላፊ በቀጣይ ቀጠሮው ስለሁኔታው ያስረዳ ብሏል ችሎቱ።ፖሊስ ባለፈው የተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ያከናወነውን የምርመራ ስራ ያደመጠው ፍርድ ቤቱ በቀጣይ በተለይም በቁጥጥር ስር ከሚገኙ ተጠርጣሪዎች ጀርባ ድርጊቱን ያቀነባበሩ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን ለማደራጀት ከጠየቀው 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱ 11 ቀን ፈቅዷል።ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
Via ETV

የትምህርት ሚኒስቴር ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ውጭ ላሉ ተማሪዎች የነፃ ዝውውር መደረጉ ትምህርት ጥራት ላይ የሚፈጥረው ችግር የለም አለ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከ8ኛ እና 12 ኛ ክፍል ውጭ ያሉ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ካለፈተና እንዲዛወሩ መወሰኑን ተከትሎ የትምህርት ጥራት ላይ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢ/ር) የነፃ ዝውውር መደረጉ ተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ጫና መንግስት እንዲሸከም በማድረግ ከትምህርት ውጭ የቆዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ታስቦ ነው ብለዋል።አሁን በምንከተለው ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ አንችልም ያሉት ሚኒስትሩ 2014 ላይ ወደ ተግባር የሚገባ ስረዓተ ትምህርት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።የትምህርት ጥራት ችግርን በዘላቂነት የሚፈታው ይህ ስርዓተ ትምህርት እንጂ ፈተና በመፈተንና ባለመፈተን የሚረጋገት የትምህርት ጥራት አይኖርም ነው ያሉት።የትምህርት ሚኒስቴር የነፃ ዝውውር ውሳኔን ሲወስን የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ በመውሰድና በተለያየ ምክንያት የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን ተከትሎ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ስለቆዩ በዚያው እንዳይቀሩ ለማድረግ ታስቦም ጭምር ነው ተብሏል።
ምንጭ: የትምህርት ሚኒስቴር

የጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
የኦንላይን አገልግሎቱ ደንበኞች በኦንላይን የሚጠበቅባቸውን ሰነዶች በማስገባት ወደ ጉምሩክ ጣቢያ መሄድ ሳይጠበቅባቸው አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ፡፡በኮሚሽኑ በከፊል የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ አገልግሎቱ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ታውቋል፡፡ለዚህም የሚያግዝ በመላ አገሪቱ ላሉ የኮሚሽኑ አመራሮች በቪዲዮ ኮንፈረንስ በመታገዝ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የኦንላይን አገልግሎቱ ተገልጋዮች ወደ ጉምሩክ ጣቢያዎች መምጣት ሳይጠበቅባቸዉ ካሉበት ሆነዉ አስፈላጊዉን ቅድመ ሁኔታ ብቻ በማሟላት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸዉ መሆኑ ጊዜ፣ ወጪ እና ጉልበት በመቀነስ ምቹ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የአሰራር ስርአት መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገልፀዋል፡፡
ከአንድ ወር በኋላ ስራ ላይ ይዉላል ተብሎ የሚጠበቀዉ እና በዝጅት ላይ ያለዉ የኦንላንይን አገልግሎትም ከዚህ በፊት ስራ ላይ ከዋለዉና የጉምሩክ አገልግሎቱ ምልልስ አልባ እና ወረቀት አልባ በማድረግ ትግበራ ላይ ያለዉን የአንድ መስኮት አገልግሎት ጋር እንዲናበብ በማድረግ አገልግሎቱ ከትራዚት እስከ ክሊራንስ እና ቁጥጥር እንዲሁም የታክስ ክፍያን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ለመስጠት ኮሚሽኑ በዝግጅት ላይ መሆኑን ነዉ ምክትል ኮሚሽነሩ የገለፁት፡፡የኦንላይን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደ ተግበራ ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የመስራት፣ ለአመራሮች ስልጠና የመስጠት እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር

ቤይሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ቆንሱል ጄኔራል አቶ ተመስገን ኡመር የቤይሩት ወደብ ፍንዳታ ባስከተለው አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን በአሽረፍየ ሽርክት ካራባ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን ጎብኝተዋል፡፡ዜጎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የህክምና እርዳታ ማግኘታቸውንም ማረጋገጥ ተችሏል፡፡በተጨማሪም ዜጎቻችን የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ቆንስላ ጽ/ቤቱ በሊባኖስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበርና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር የተለያዩ ድጋፎች ተደርጎላቸዋል፡፡
ምንጭ: በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ
@YeneTube @FikerAssefa1
ምንጭ: በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ
@YeneTube @FikerAssefa1
ከሃይማኖት በዳዳ ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት አቀረበ!
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ ከነበረችው ሃይማኖት በዳዳ ግድያ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ዛሬ ፍርድ ቤት አቀረበ።በዋና ወንጀል አድራጊነት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ከዋለው ደግነት ወርቁ ከተባለ ግለሰብ ባሻጋር ፖሊስ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስምንት ግለሰቦችን በቁጥጥር አውሎ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቧል። ከስምንቱ ግለሰቦች አብዛኛዎቹ በሆስፒታሉ በጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የሃይማኖት በዳዳ የትምህርት አማካሪ (አድቫይዘር) የነበሩ ሰው መሆኑም ታውቋል።
ዛሬ ችሎቱ ፊት የቀረቡት የሆስፒታሉ ጥበቃዎች የሃይማኖት በዳዳ ግድያ በተፈፀመት ወቅት ሟቿ የነበረችበት ሕንፃ አጥር ያልነበረው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸውም ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።ፖሊስ ግን ከሟች ጋር የተደረጉ የስልክ ልውውጦችን ለመመርመር እንዲሁም የጥበቃ ሠራተኞች ዋናው ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠረው ግለሰብ ድምፅ አልባ የጦር መሣሪያ ይዞ ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ ያደረጉት ቁጥጥር እንዴት እንደነበር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ምርመራ ለማካሄድ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።ፍርድ ቤቱ በቀጣይ ቀጠሮ የእያንዳንዱ ተጠርጣሪ በወንጀሉ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ ለይቶ እንዲያቀርብ ለፖሊስ የ7 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።ባለፈው ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ሕይወቷ ካለፈው ሃይማኖት በዳዳ ግድያ ጋር በተያያዘ ደግነት ወርቁ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።

ጠ/ሚ ዐቢይ ከመደመር መፅሐፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ እንዲውል አበረከቱ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመደመር መፅሐፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ ይሆን ዘንድ ለቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አስረክበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መፅሐፍን ገቢ በመላው አገሪቱ ለትምህርት ቤቶች ማሰሪያ እንደሚውል ቃል በገቡት መሰረት ነው እስካሁን ከመፅሀፉ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ዛሬ ያስረከቡት።በየክልሎቹ መደመር መፅሐፍ ተሸጦ የተሰበሰበው ገንዘብም ተመልሶ ለየክልሎቹ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።
#FBC

የአስራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ!
ሁከት እና ግጭት በማስነሳት ወንጀል የተጠረጠሩ የአስራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡መርማሪ ፖሊስ በአስራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ላይ ከህገ መንግስት እና ከሙያ ስነ ምግባር ውጭ ያፈነገጠ የሃይማኖትና የብሄር ግጭት የሚያስነሳ ፕሮግራም ሰርተዋል ሲል ይህንን አስመልክቶ የሰራውን ስራ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡በፕሮግራሙ ላይም የሰነድ ማስረጃ ማሰባሰቡን ገልፆ እጃቸው ላይ ያገኘውን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) እንዲመረምር እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡መርማሪ ፖሊስም ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቃ በበኩሉ 4 ኪሎ የሚገኘው የአስራት ቴሌቪዥን በቂ ምርመራ ተደርጎበታል ተጨማሪ ምርመራ አደርጋለሁ መባሉም አግባብ አይደለም ሲል ተከራክሯል፡፡አየር ላይ የዋሉ ፕሮግራሞች ከዩ ቲ ዩብ እና ሌሎች ድረ ገፆች ላይ ማግኘት ይችላሉ፤ የተጠርጣሪዎች የተናጠል ድርሻ ሊቀርብ ይገባል ያለ ሲሆን የዋስትና መብታቸው ሊከበር እንደሚገባም ጠይቋል፡፡ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዳልተደረገላቸው ገልፀው ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ሶስተኛ ተጠርጣሪ የጤና ሁኔታውን ገልፆ አያያዛቸው እንዲስተካከል የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ሁሉም ተጠርጣሪዎች ጤንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን አዟል፡፡ከቤተሰብ ጋርም በጥንቃቄ እንዲገናኙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ለተጨማሪ ምርመራ 12 ቀን ፈቅዷል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1ሺህ 7መቶ 71 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 86 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ21 ሺህ ደርሷል
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,203 የላብራቶሪ ምርመራ 552 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 388 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 21,452 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 380 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,415 ናቸው።
@yenetube @Fikerassefa

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ጉባዔውን እንደጀመረ የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ክልሉ በምን አጀንዳዎች ላይ እንደሚነጋገር እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል በጎርፍ የተከበቡ ሰዎችን የማውጣት ስራ መጀመሩ ተገለፀ!
በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ባስከተለው ጎርፍ የተከበቡ 1ሺህ 126 ሰዎችን በሁለት ሔሊኮፕተሮች የማስወጣት ስራ መጀመሩን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ገለፀ።በጽህፈት ቤቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን በክልሉ በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ የሚገኙ 7 ወረዳዎች የጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል።በክረምቱ የሚጥለው ዝናብ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ እስከ አሁን ድረስ 49 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።
በተለይ ደግሞ በአይሳኢታ ወረዳ ኮሌዶራና ገልአሊ ወረዳዎች 1ሺህ 126 ሰዎች ላለፉት አምስት ቀናት በጎርፍ ተከበው ቆይተዋል።የክልሉ መንግስት ከሰላም ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ጋር በመተባበር ከትናንት ጀምሮ በጎርፍ የተከበቡ ሰዎችን በሁለት ሔሊኮፕተሮች የማስወጣት ስራ መጀመሩን አቶ አይዳሂስ ተናግረዋል።በታችኛው የአዋሽ ተፋሰስ የሚገኙ የአይሳኢታ፣ ዱብቲና አፋምቦ ወረዳዎች የበለጠ ለጎርፉ ተጋላጮች በመሆናቸው የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር የእለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት የቢሮ ሃላፊው በዘላቂነትም ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ከወዲሁ እንቅስቃሴ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።

የሕዳሴዉ ግድብ ድርድር ሰኞ ይቀጥላል ተባለ!
በአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ቢሮ አማካኝነት ነሐሴ ሦስት ቀን ተጀምሮ የነበረውና የተቋረጠው የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ የቴክኒክና የሕግ ቡድኖች ድርድር ዳግም የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ከሰሞኑ በቤይሩት በተከሰተው ፍንዳታ እስካሁን እንድ ኢትዮጵያዊ ሲሞት ዘጠኝ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በኮሮና ተኅዋሲ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኙ የየብስ እና የአየር መሥመሮችም ተከፍተዋል ተብሏል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ማሻሻያዉን ተቃወመ!
የትግራይ ክልል ምክርቤት ያደረገው የምርጫ ስርዓት ለውጥ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቃውሞና ድጋፍ አስተያየት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መግለጫ የሰጠው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በምክርቤቱ የተደረገው ማሻሻያ ተቃውሟል፡፡
#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የትግራይ ክልል ምክርቤት ያደረገው የምርጫ ስርዓት ለውጥ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቃውሞና ድጋፍ አስተያየት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መግለጫ የሰጠው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በምክርቤቱ የተደረገው ማሻሻያ ተቃውሟል፡፡
#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
👍1
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኢፒዲምዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት ተለዩ፡፡
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኢፒዲምዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ ተስፋሚካኤል (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ሕብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ታመው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በሃላ በቀን 01/12/2012 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት ተለይተዋል፡፡

"ከኦፌኮ ጋር መድረክ ውስጥ መቀጠል እንቸገራለን" -በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አባል ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣ ሌላኛው የድርጅቱ አባል ከሆነው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጋር በተፈጠረ የአቋም ልዩነት በመድረክ ውስጥ መቀጠል እንደሚቸገር አስታወቀ። ኢሶዴፓ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው ነመድረክ ግንባር ውስጥ ወደፊት ላለመቀጠል ምክንያት ነው ያለው ኦፌኮ ከመድረክ ውጭ ኢሶዴፓ ባልተስማማበት ጉዳይ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የትብብር ፊርማ መፈራረሙ መሆኑን የኢሶዴፓ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ተናግረዋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ ጋዜጣ፣ ነሀሴ 2 እትም