YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው ኃይል ተቋረጠ!

በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው በተፈፀመ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ስርቆት በኢንደስትሪ መንደሩና በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል።132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በዘራፊዎች ተፈቶና ተቆርጦ በመውደቁ በሌላ ምሰሶ ላይ ተጨማሪ ጉዳት በማድረስ ነው ኃይል የተቋረጠው።በዚህም የኢንደስትሪ መንደሩን ጨምሮ በሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ በቦሌ አራብሳ፣ በአየር መንገድ ማህበር፣ በጎሮ፣ በአይሲቲ ፓርክ፣ በገርጂ ወረገኑና በገርጂ ካሳንቺስ አካባቢዎች ኃይል ተቋርጣል።

ችግሩ እንደተከሰተ የተቋማችን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የጥገና ባለሙያዎች ችግሩን ለመቅረፍ እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምሰሶውን መልሶ በማቆም መስመሩን ማገናኘት አልተቻለም።

የተሰረቁትን የምሰሶ አካላት በሌላ ተክቶ መልሶ ለማቆም መለዋወጫና በርካታ ቀናት የሚፈልግ ቢሆንም ሌላ ተለዋጭ የእንጨት ምሰሶ በመትከል መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ተጀምሯል።በመሆኑም በኢንደስትሪ መንደሩም ሆነ ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል መልሰን እስከምናገናኝ ድረስ ህብረሰተቡ በትዕግስት እንዲጠብቀንና ሌሎች የኃይል አማራጮችን እንዲጠቀም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያሳስባል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቦሌ ለሚ መስመር ጋር የተገናኘው የቃሊቲ አካባቢ መስመር ተጠግኖ ኃይል መስጠት ጀምሯል።

#EEPCO
@YeneTube @FikerAssefa
ሸገር ዳቦ : 2 ሚሊዮን ዳቦ በአንድ ቀን

2 ሚሊዮን ዳቦ በአንድ ቀን የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ማምረቻ ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ ይመረቃል
ዛሬ - ኢንጂነር ታከለ ኡማና ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ልዩ ልዩ ባለስልጣናት በተገኙበት ይመረቃል።
@YeneTube @Fikerassefa
መልካም ቀን ይሁንሎት
#ግድቡየኔነው
#itsmydam
በኢትዮጵያ የ'114 ዓመት' የእድሜ ባለጸጋ ከኮሮናቫይረስ አገገሙ!

በኮሮናቫይረስ ተይዘው በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የ114 የእድሜ ባለጸጋ ከበሽታው አገግመው መውጣታቸውን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ያሬድ አግደው በፌስቡክ ገጻቸው አስታወቁ፡፡አዛውንቱ ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል እንደሚገኙም ሥራ አስኪያጁ አክለዋል፡፡አዛውንቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ለዚህ ስኬት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ የጤና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
“የአፍሪካ ሎጀስቲክስ” ባወጣው ሪፖርት መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚያጓጉዛቸው መንገደኞች ብዛት፣ በሚበርባቸው መዳረሻዎች ብዛት ፣ ባለው የአሮፕላን ቁጥር ብዛት እንዲሁም በሚያገኘው ገቢ ከአፍሪካ የአንደኛነት ስፍራ አግኝቷል። በአለም አቀፍ ደረጃም በሚበርባቸው መዳረሻዎች ብዛት 4ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ በቅቷል።

Via Ethiopian Airlines
@YeneTube @FikerAssefa
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በ2013 በጀት ዓመት የበጀት ዝግጅት ላይ ተወያይቷል።

በውይይቱም የበጀት ዝግጅቱን አስመልክቶ በገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ማብራሪያ ተሰጥቷል።ዶክተር እዮብ በዘህ ወቅት እንደገለጹት የ2013 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሲዘጋጅ የ2012 ዓ.ም የበጀት አፈጻጸም ግምገማ ከመካሄዱም ባለፈ የኮረና ወረርሽኝ ተጽዕኖ ታሳቢ ተደርጎ በቅርብ ጊዜያት በአገራችን በኢኮኖሚው ዘርፍ የተገኙ ድሎችን ለማስጠበቅ ታስቦ የታቀደ በጀት ስለመሆኑ አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ ለካፒታል እና ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ድጋፍ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ግቦች ማጠናከሪያ በጥቅሉ 476 ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልጸው÷ ከዚህ ውስጥ 350 ቢሊየን ብሩ ከሀገር ውስጥ የገቢ ምንጮችና ከዕርዳታ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት።አያይዘውም ለ2013 በጀት ዓመት የቀረበው በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር መጠነኛ ጭማሪ እንዳለው ጠቁመው÷ በጀቱ በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ለምለም ሐድጉ÷ በቀጣይ በረቂቅ በጀቱ ላይ ተጨማሪ ውይይት መኖሩን መጠቆማቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለሲሚንቶ ግብዓት የሚያገለግለውን የድንጋይ ከሰል 60 በመቶ በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉ ተገለፀ!

ለሲሚንቶ ግብዓት የሚያገለግለው የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተደረገው ጥረት 60 በመቶ የሚሆነውን በአገር ውስጥ ምርት መተካቱ መቻሉ ተገለፀ።የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ ስመኝ ደጉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ሲሚንቶን ለማምረት አስፈላጊ ከሆነው አጠቃላይ ግብዓት 60 በመቶውን በአገር ውስጥ መተካት መቻሉ ዘርፉን ውጤታማ ማድረጉን አመልክተዋል።ቀሪው 40 በመቶ ለሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሚሆነው አሁንም ከውጭ እንደሚገባ አመልክተው ፣ሁሉም የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ከሚጠቀሙት መጠን እና ከላብራቶሪ ውጤታቸው በመነሳት በቀጣይ በዘርፉ የሚታዩትን ችግሮች ለመቅረፍና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የድንጋይ ከሰል በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ማለትም በአማራ፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መኖሩ በጥናት መረጋገጡን አመልክተው ፣ ይሁንና የተፈጥሮ ሀብት መጠኑ፣ ዘላቂነቱና ጥራቱ ምን ያህል ነው የሚለውን ለመመለስ ምርምር እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል ። ይህም በምርምር ኮሚቴው እየተጠና መሆኑን አመልክተዋል።በሲሚንቶ ገበያ የንግድ ሰንሰለት ውስጥ ደላሎች የሚፈጥሩትን ጤናማ ያልሆነ የንግድ ቅብብሎሽ ጤናማ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አመልክተው ፣ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ ምርቱን እንዲትረፈረፍ በማድረግ ገበያውን መቆጣጠር ይቻላል ብለዋል።በተለይም የሀገር ውስጥ ግብዓቶች ላይ በመስራት ከውጭ የሚገባውን ምርት በመቀነስ የውጭ ምንዛሪን ማዳንና ዘርፉን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ምንጭ፡- ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ማኪ ሳል ራሳቸውን ለሁለት ሳምንት አግለዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ይህንን ያደረጉት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር መገናኘታቸው ከታወቀ በኃላ ነው።ፕሬዝዳንቱ ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ ቢሆኑም ለማንኛውም በሚል ነው ለሁለት ሳምንት ያህል ራሳቸውን አግለው ለማቆየት የወሰኑት ብሏል ጽ/ቤታቸው፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ!

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውና በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ። በፋብሪካው ምርቃ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ካርቱም ገቡ።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ሱዳን ካርቱም ያቀኑት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ጋር በሁለቱ አገራት እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር እንደሆኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ አስታውቋል።ፕሬዘዳንቱ ወደ ካርቱም ያቀኑት በሱዳኑ አቻቸው ጀነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን ግብዣ እንደሆነም ተገልጿል። ፕሬዘዳንቱ ወደ ካርቱም ያቀኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ኦስማን ሳሌህ እና አማካሪያቸውን የማነ ገብረአብን አስከትለው ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር የምስረታ ጉባኤና ጋዜጣዊ መግለጫ አራት ኪሎ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ግቢ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Photo: Samuel Getachew(on Twitter)
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር የምስረታ ጉባኤና ጋዜጣዊ መግለጫ አራት ኪሎ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ግቢ በመካሄድ ላይ ይገኛል። Photo: Samuel Getachew(on Twitter) @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ!

በኢትዮጵያዊያን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተነሳሽነት የተጀመረው እና በርካታ አባላትን የያዘው ማህበር ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ ተመሰረተ።በአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የመገናኛ በዙሀን ድርጅቶች ባልደረቦች አባልነት የተቋቋመው ማህበሩ ዛሬ ሰኔ 18/2012 ምስረታውን በሚመለከት መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው በመገናኛ ብዙሃን ሙያና ሙያተኞች ላይ የተለያዩ አካላት በተለያየ መልኩ የሚደረገውን ተፅዕኖ እና ጫና ለማስቀረት ፣ ለባለሙያው መብት እና ጥቅም የሚቆም፣ ሙያዊ ብቃቱን የሚያሳድግለት እና የኔ የሚለው የሙያ ማህበራት ጥቂት በመሆናቸው እንዲሁም በአመርቂ ሁኔታ ለሙያተኛው ጥቅም እየሰሩ ባለመሆኑ ይህ የመገናኛ ባለሙያዎች ማህበር በመገናኛ ብዙሃን እና በሙያተኞች መካከል ትብብር እና አብሮ የመስራትን መንፈስን ለመፍጠር ታቅዶ መመስረቱ ተገልጿል።

ማህበሩ ከሲቪክ ማህበራት ማደራጃ ኤጀንሲ ህጋዊ እውቅናን አግኝቶ የተመሰረተ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተከናወነው የመስራቾች ጉባኤ ላይ የማህበሩን መመስረት አስፈላጊነት፣ ስያሜውን እንዲሁም አላማዎቹ ላይ በመወያየት የማህበሩን አደረጃጀት በማፅደቅና ዘጠኝ የስራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ እና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በማርቀቅ ወደስራ መግባቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በመግለጫው ላይ አስታውቋል።በዚህም መሰረት ማህበሩ መስራች፣ መደበኛ እንዲሁም የክብር አባላትን በማህበሩ ዌብሳይት እና የአባላት ምልመላ ክፍል አማካኝነት የሚመዘግብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በቁርጠኝነት ለመስራት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተገልፆል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ከ3500 በላይ ሰዎች በእብድ ዉሻ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በመገባደድ ላይ ባለው ዓመት ከ3 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ የተጠቁ ሲሆን 15 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለይም በክረምት ወቅት፣የህብረተሰቡን ጤና በእጅጉ ከሚፈትኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የእብድ ዉሻ በሽታ መሆኑ ይነገራል፡፡በአማራ ክልል ከ 3 ሽህ 500 በላይ ሰዎች በእብድ ዉሻ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጡረታ ለተሰናበቱ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች የተፈቀደው ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ተወሰነ!

ከሁለት ዓመት በፊት በተላለፈ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጨማሪ ውሳኔ በጡረታ ለተሰናበቱ ከፍተኛ የአገርና የመንግሥት አመራሮች ሲሰጥ የነበረ ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ተወሰነ።የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም.  ባካሄደው ስብሰባ በጡረታ ለተሰናበቱ  የአገርና የመንግሥት አመራሮች ከአዋጅ  ውጪ በልዩ ውሳኔ የተፈቀደላቸው ልዩ  ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ወስኗል።

እነዚህም በጡረታ የተሰናበቱ የአገርና የመንግሥት አመራሮች በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት በተሰጣቸው ቤት መኖር እንዲቀጥሉ፣ አንድ አውቶሞቢልና አንድ  የመስክ ተሽከርካሪ እንዲሰጣቸው  እንዲሁም በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት  ያገኙ የነበረው የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንዲቀጥሉ የሚፈቅዱ ናቸው።

ከሳምንት በፊት የተላለፈው አዲሱ  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ከላይ  የተገለጹት ሦስት ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች እንዲሻሩና በአዋጁ መሠረት ብቻ  እንዲስተናገዱ የሚል ነው:: በዚህ ውሳኔ መሠረት ቤት የተሰጣቸው በጡረታ የተሰናበቱ አመራሮች እንዲኖሩበት የተሰጣቸውን ቤትና የመስክ ተሽከርካሪ እንዲመልሱ የተባለ ሲሆን፣ የገንዘብ ሚኒስቴርም ይህንን  ውሳኔ እንዲፈጽም ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም.ትእዛዝ ደርሶታል።

#Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት እና ኢዲዩ ከኢትዮጵያ የፌዴራሊስ ኃይሎች ጥምረት አባልነት ታገዱ!

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓት እና ኢዲዩን ከጥምረቱ አባልነት አገደ፡፡ጥምረቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ በነበረው ጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባወጣው የአቋም መግለጫ እንዳመለከተው፤ ጥምረቱ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦች አካትቶ በማቀፍ የተሻለ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ለመገንባት እና ለብሔር ብሔረሰቦች ተጠቃሚነት ሲል በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እየሰራ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ህወሓትና ኢዲዩ የጥምረቱን ጉዞ ለማደናቀፍ ብሎም ጥምረቱን ተጠቅመው አገር ለማተራመስ እየሰሩ ይገኛል ይላል መግለጫው፡፡ይህ ደግሞ በጥምረቱ ዓላማ፣ አሰራርና ደንብ መሰረት ተቀባይነት ያለው ባለመሆኑ ሁለቱ ድርጅቶች ከጥምረቱ እንዲታገዱ ሆኗል ተብሏል፡፡በተለይ ህወሓት ጥምረቱ የራሱ ጥገኛ አድርጎ ሊጠቀምበት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የተናገሩት የጥምረቱ ሰብሳቢ አቶ ደረጀ በቀለ፤ ህወሓትና ኢዲዩ የጥምረቱ ማዕከል መቀሌ እንዲሆን በመሻት በአዲስ አበባ ያካሄደው ሶስተኛ እና አራተኛ የጥምረቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ተናግረዋል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው መርምሮ ያፀደቃቸው ረቂቅ አዋጆች፦

👉የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ፤

👉የገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤

👉የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኳታር መንግሥት የማዕድን ሥራዎች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ናቸው።

ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀደቃቸው ስምምነቶች፦

👉በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለበረሃ አንበጣ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገው የብድር ስምምነት፤

👉ኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንዲያግዝ ለሁለተኛው የኢትዮጵያ የዕድገትና ተወዳዳሪነት የልማት ፖሊሲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት፤

👉በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት፤ በሁለቱ አገሮች መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት፤

👉በኢትዮጵያ እና በሩዋንዳ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት እና በሁለቱ አገራት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት የሚያስችለው ስምምነት ናቸው።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
አነስተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጫናን የሚያቃልል ጥናት አስጠንቶ ለመንግሥት ሊያቀርብ መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ችግሩን ይፈታል የተባለ ጥናት ኮሚሽኑ ከኮንስትራክሽንና ቤቶች ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጥናት ማስጠናቱንና ጥናቱም በቅርቡ ለመንግሥት እንደሚቀርብ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ገልጸዋል።”ጥናቱ በዋነኛነት ለረጅም ዓመታት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሲሰሩ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ደሞዝ የሚኖሩ ሰዎች አሁን ላይ ከተፈጠረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መናርና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚበሉበትን እስከማጣት የሚደርሱ መሆናቸውን ጥናቶቻችን አሳይተውናል” በማለት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ/ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ የሲዳማ ክልል በመጪው ሳምንት ለሚካሄደው የክልላዊ መንግስት መስረታ አስፈላጊውን መሰናዶ ማጠናቀቁን የሲዳማ የክልል ምስረታ ዝግጅት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለማ አንዳስታወቁት የፊታችን ሰኔ 27/2012 ዓም የሲዳማ ክልል መንግስትን በይፋ ለመመስረት የሚያስችሉ የረቂቅ ህገ መንግስት ዝግጅት ፣ የስንደቅ ዓላማ መረጣና ሌሎች ተያያዥ የቅደመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል።ምክትል ዳይሬክተሩ በማያያዝም «በአሁኑወቅት ብሄራዊ ክልሉን ለመመስረት ለሚደራጀው ምክር ቤት ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች 300 ያህል ሰዎች ተወክለዋል።የሚቋቋመው ምክር ቤትም በገዢው የብልፅግና ፓርቲ አማካኝነት የክልሉን ርእሰ መስተዳድርና የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ ክልሉ በቀጣይ የሚኖረውን የተዋረድ አስተዳደር መዋቀሮች ላይ በመወያየት ውሳኔ የሚያሳልፍ ይሆናል።» ብለዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa
መነሻ ምክንያቱ በመጣራት ላይ ባለ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሸን ገለጸ፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሸን ህዝብ ግንኙነት እና ለውጥ ስራዎች ዳሬክቶሬት ኃላፊ የሆኑት ኮ/ር ገመቹ ካቻ እንዳሉት ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፈዱ 3 ፡30 ሰዓት ገደማ በቀበሌ 05 በተለምዶ ገንደ ጉራጌ ተብሎ በሚጠራው አካበቢ በተፈጠረ ግጭት አንድ የ35 ዓመት ጎልማሳ ህይወቱ ማለፉን የገለፀ ሲሆን አንድ ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱን እንዲሁም ንብረት ላይም ጉዳት መድረሱንም አብራተዋል፡፡ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ፖሊስ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡

ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮምሽን
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,675 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ አንድ (141) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

ተጨማሪ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 81 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 3 ሰዎች ሁኔታ

1.በህክምና ላይ የነበሩ የ52 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)

2.በጤና ተቋም የነበሩ የ72 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ(ወንድ)

3.በጤና ተቋም የነበሩ የ62 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ሴት)


@YeneTube @FikerAssefa