YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኦሮሚያ ክልል 8 ዞኖች ላይ የአንበጣ መንጋ እየታየ ነው ተባለ።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዳለው የአንበጣ መንጋው በደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ወደ አካባቢዎቹ እየገባ ነው።እንደ ባሌ እና ቦረና ባሉ ዞኖች መንጋው ከዚህ ቀደምም ሶስት እና አራት ጊዜ ተከስቶ እንደነበር ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ገረመው ኦሊቃ ለሸገር እንዳሉት የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የአንበጣ መንጋውን በባህላዊ መንገድ ለመከላከል ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል።ሁኔታው እየከፋ የሚሄድ ከሆነ ግን በግብርና ሚኒስቴር አማካይነት በአውሮፕላን የመድሃኒት ርጭት ይካሄዳል ብለዋል።

ከአንበጣ መንጋው በተጨማሪ በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የክልሉ አካባቢዎች ጎርፍ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ከምክትል ኮሚሽነሩ ሸገር ሰምቻለው ብሏል።ጎርፉ ከተከሠተ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ለኮሮና ቫይረስ ሳይጋለጡ ወደ የት ማሸሽ ይቻላል? የሚለው ከወዲሁ እየተጤነ ነው ብለዋል።ሊደረግላቸው ስለሚገባ ድጋፍም እንዲሁ አስበንበታል ብለዋል።ክልሉ በአሁኑ ወቅት በመደበኛነት ድጋፍ የሚያደርግላቸው 2.4 ሚሊየን ዜጎች እንዳሉ ሠምተናል።በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ደግሞ እስከ 2.2 ሚሊየን ተጨማሪ ሠዎች ድጋፍ ለመጠበቅ ይገደዱ ይሆናል የሚል የመጀመሪያ ዙር ጥናት እንዳለ አቶ ገረመው ተናግረዋል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀምሯል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ የሺጌታ ገላው (ዶክተር) ለአብመድ እንዳሉት ጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀን 96 ናሙናዎችን መርመር የሚያስችል ላቦራቶሪ ሥራ ጀምሯል፡፡በሆስፒታሉ አንድ የመመርመሪያ ማሽን እንዳለና ወደፊት ተጨማሪ ለማምጣት እንቅስቃሴ እንደተጀመረም አስታውቀዋል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ተጨማሪ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4809 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አስራ ስድስት (116) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4070 ደርሷል።ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 37 (24 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከጤና ተቋም እና አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።በተጨማሪ አምስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ሁለት (72) ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ7 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 72 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 7 ሰዎች ሁኔታ

1.በህክምና ላይ የነበሩ የ70 አመት የሶማሊ ክልል ነዋሪ (ወንድ)

2.በህክምና ላይ የነበሩ የ70 አመት የድሬዳዋ ነዋሪ (ሴት)

3.በህክምና ላይ የነበሩ የ68 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)

4.በጤና ተቋም የነበሩ የ85 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)

5.በህክምና ላይ የነበረ የ4 ወር ህፃን የሀረሪ ክልል ነዋሪ

6.በህክምና ላይ የነበረ የ45 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

7.በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 116 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(76) ሴት(40) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ3-78 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 93 ሰዎች(88 ከአዲስ አበባ፣ 1 ከኦሮሚያ፣ 2 ከአማራ እና 2 ከሶማሊ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1027 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(101)፣ ከኦሮሚያ ክልል(6)፣ከአማራ ክልል(1) ፣ ከትግራይ ክልል(1)፣ከጋምቤላ ክልል(1)፣ ከድሬዳዋ(1)፣ ከደቡብ ክልል(4) እና ከአፋር ክልል(1) በድምር 116 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4070 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 32 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 7 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 72 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ አወሉ አብዲ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ለየኔቲውብ ምንጮች ተናግረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ሆነው እየሰሩ የነበሩት አወሉ አብዲ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል ተብሏል። ከዚህ ቀደም አቶ ዮሐንስ ቧያለው በዚህ ቦታ ሹመት ተሰጥቷቸው አልቀበልም ማለታቸው ይታወሳል።በአቶ አወሉ አብዲ ምትክ በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት ሃላፊ የሆነው እየሰሩ የሚገኙት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ሊተኩ እንደሚችሉም ምንጫችን ጨምረው ገልጸውልናል።

@YeneTube @FikerAssefa
 የኮሮናቫይረስ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባሉ አንዳንድ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን ገልጸዋል።በማሻሻያው መሠረት በተለያዩ ምክንያቶች ለሞት የሚዳረጉ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በማኅበረሰቡ የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸም ተፈቅዷል።ይህም ከዚህ ቀደም የአስክሬን የላብራቶሪ ውጤት ከመምጣቱ በፊት የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸም አይቻልም የሚለውን መመሪያ መሻሻሉን ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ በቀብር ሥፍራ ላይ ከዚህ ቀደም የተቀመጠው 50 ሰዎች ብቻ ተገኝተው ሥርዓቱን ማከሄድ አለባቸው የሚለው መመሪያው አልተሻሻለም ብለዋል።ግለሰቦች በኮሮናቫይረስ ቢያዙ የሚያገለግሏቸው የቤተሰብ አባላትና የራሳቸው ፍላጎት ከግምት በማስገባት ተፈጻሚ የሚሆን መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የግለሰቦችን የአኗኗር ሁኔታ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት አግባብ ከሆነ በቤታቸው እንዲቆዩ እንደሚደረጉም ተገልጿል።ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ወደ አገር ከገቡ በኋላ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት አገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸወ 14 ቀናት እንዲቆዩ ይደረጋልም ተብሏል። ኢዜአ እንደዘገበው ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርት ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ናሙናቸው ተወስዶ ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ እንደሚደረግ ዶክተር ሊያ ተናግረዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ለ14 ቀናት የነበረውን አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ወደ ለ7 ቀናት ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት ተጀመረ!

የትራንስፖርት ሚኒስቴር በዘርፉ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመከላከል እና ለመቀነስ ልዩ ልዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለትም በመናህሪያዎች አካላዊ እርቀትን ለማስጠበቅ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል ተጠቃሚዎች ትኬት ለመቁረጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚፈጠር አካላዊ ጥግግት ለመቀነስ የሚረዳ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት በይፋ ተጀምሯል፡፡የትራንስፖርት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አግልገሎቱ በይፋ መጀመሩን ሲያበስሩ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ ስርዓት ወረርሽኙን ከመከላለከል ጎን ለጎን ዘርፍን በቴክኖሎጂ አስደግፎ በመምራት እና የተጠቃሚውን የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እነደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ የአገልግሎት ስረዓት አሰጣጡ ተጓዞች ወደ መናህሪያ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ባሉበት ሆነው ትኬት መቁረጥ የሚያስችል ነው።

Via MoTE
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 101 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2988 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በከተማዋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 88 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-

👉አዲስ ከተማ 17

👉ቦሌ 3

👉ጉለሌ 21

👉ልደታ 28

👉ኮልፌ ቀራንዮ 7

👉ቂርቆስ 6

👉አራዳ 0

👉የካ 2

👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 14

👉አቃቂ ቃሊቲ 1

👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 2

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የእንግሊዙ ቮዳፎን ግሩፕ ለ2ቱ የኢትዮጵያ የግል ቴሌኮም አገልግሎት ፍቃዶች የሚጫረተው፣ ከእህት ኩባንያዎቹ ከደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም እና ከኬንያው ሳፋሪኮም በጋራ በመጣመር መሆኑን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ በአፍሪካ ትልቁ ኩባንያ ኤምቲኤን እና የፈረንሳዩ ኦሬንጅ ኩባንያዎችም መጫረት ይፈልጋሉ፡፡ 

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለጸ!

የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ356 ሰዎች በላይ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ ከ1,200 ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጿል፡፡በመረጃ መሠረት ከአደጋዎቹ መንስኤዎች መካከል የከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲም ለመንገድ ደህንነት፣ ለትራፊክ አደጋ እና ለትራንስፖርት ፍሰቱ ማነቆ የሆኑትን ችግሮችን በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በከተማዋ የትራፊክ አደጋን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል የተባለው የተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡በአዲስ አበባ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የአንበሳ ከተማ አውቶብስ እና የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት እንዲሁም የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያው ገጥመው ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ሌሎች መንግስታዊ ተቋማትም በማስገጠም ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡በቀጣይም የአሰራር ሥርዓት መመሪያን በማዘጋጀትና የአፈጻጸም ሲስተሞችን በመዘርጋት የንግድ ትራንስፖርት እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ማሞ የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። ጠ/ሚ አብይ አህመድ አማካሪያቸውን በምክትል ኮሚሽነርነት የሾሙት ከሰኔ 1 ጀምሮ ነው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል ያለው የኮሮና ምርመራ ማዕከል አንድ ብቻ ነው። የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክት ኃላፊ ዶክተር ሙክታር ይሱፍ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው ይኸው የምርመራ ማዕከል በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ በትግራይ ክልል የተመሰረተው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ የተባለው የፖለቲካ ድርጅት የመጀመሪያ ጠቅላይ ጉባኤው አካሂዶ ፕሮግራሙ በማፅደቅ አመራሮቹ መርጧል፡፡ ፓርቲው ትግራይ ክልልን በሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ ለመነጠልና ሉዓላዊት ሀገር ለማድረግ እንደሚታገል አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀሰው ይህ ፓርቲ በትግራይ ይካሄዳል በተባለው ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ እንዳለም ገልፅዋል፡፡ "ኢትዮጵያ የትግራይ ብሔራዊ ህልውናና የተጋሩ ብሔራዊ ማንነት የምትቀበል አይደለችም" የሚለው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤው አመራሮቹን መርጧል። የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ደጀን መዝገበ "የትግራይ ብሔራዊ ህልውናና ብሔራዊ ማንነት በተሟላ መልኩ እውን መሆን የሚችለው ትግራይ አገር ሲሆን ነው" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ አደገኛ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው አለ።

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ “ወደ አዲስና አደገኛ” ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ሲል አስጠነቀቀ። ድርጅቱ ይህንን ያለው ሐሙስ ዕለት በዓለም ዙሪያ ከዚህ ቀደም ከታየው በበለጠ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በበሽታው መያዙን በተመለከተ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት በአንድ ቀን 150 ሺህ አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በማቋረጥ በድጋሚ ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት መውሰዷን አስታወቀች።

ያለ ሶስቱ ሃገራት ስምምነት ኢትዮጵያ በተናጥላዊ ውሳኔ ግድቡን ውሃ መሙላት ሳትጀምር የፀጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሳሜህ ሽኩሪ በኩል መጠየቋን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ግብፅ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩን ለመውሰዷ ምክንያት ያደረገችው እየተካሄደ የሚገኘው የውሀ ሚንስትሮች የሶስትዮሽ ውይይት አዎንታዊ ውጤት ስለማያመጣ መሆኑን ሚንስትሩ ገልጸዋል።በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በተናጥል ውሀ መያዝ እንዳትችል የፀጥታው ምክር ቤት እንዲያስቆምላት መጠየቋ ተገልጿል።

ግብጽ ከአንድ ወር በፊት ተመሳሳይ ደብዳቤ ለጽጥታው ምክር ቤት ማስገባቷ ይታወሳል።ኢትዮጵያም ለግብጽ መልስ በላከችው ደብዳቤ ለጸጥታው ምክር ቤት በራሴ ተፈጥሯዊ ወንዝ የማንንም ፈቃድ አልጠይቅም ውሀውን መጠቀሜንም እቀጥላለሁ ማለቷም አይዘነጋም።በዚህም ምክንያት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽ ጉዳዩን በሶስትዮሽ ድርድር እንድትፈታ ጫና ማሳደሩን ተከትሎ ወደ ድርድሩ ተመልሳ ነበር።ይሁንና የተጀመረው የሶስቱ አገራት የውሀ ሚንስትሮች ውይይት ሳይጠናቀቅ ግብጽ በድጋሚ ድርድሩን ማቋረጧን አስታውቃለች።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikeAssefa
ለአዋሽ - ወልዲያ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦት የሚያገለግል የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ስራ ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

Via MoTE
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ለዜጎች ብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ለማዘጋጀት ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከተባለ የህንድ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ።

ሥምምነቱን በማስመልከት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ዛሬ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የሙከራ ትግበራ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል።በሥምምነቱ መሠረት ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ዘመናዊ የአሰራር ሲስተም ይዘረጋል።የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ለማድረግ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በርካታ ክንውኖች ሲካሄዱ እንደቆዩም ሚኒስትሯ ግልጸዋል።የብሔራዊ መታወቂያ አገልገሎት የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ አገልግሎት ለማግኘት ይረዳል ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ወንጀል ከመከላከልና የፋይናንስ ዘርፉን ከማዘመን አኳያም ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።በሙከራ ትግበራው 30 ሺህ ዜጎች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በአጠቃላይ የመግባቢያ ሥምምነቱ ቴክኖሎጂውን በራሳችን አቅምና ነባራዊ ሁኔታ ደህንነቱ የተጠበቀ ብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።እንደ ኢዜአ ዘገባ የሙከራ ትግበራው ከስምንት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

#EPA
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱ በኮሮና ወቅት የ12 ሀገራት አውሮፕላኖች መጠገኑን አሳወቀ!

ኮሮና በዓለም ከተስፋፋ ጀምሮ በጥቂት ወራት ውስጥ ከእራሱ አውሮፕላኖች በተጨማሪ 40 የሚጠጉ የ12 ሀገራት አውሮፕላኖችን መጠገኑን የኢትዮጵያን አየር መንገድ አስታወቀ።በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጣሰው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፤ኮሮና በሽታ በተከሰተበት ወቅት በርካታ ሀገራት አውሮፕላኖቻቸውን ለማስጠገን ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ አምጥተው ለማስጠገን ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ከቀረቡለት ጥያቄዎች ውስጥም 12 ለሚሆኑ ሀገራት 40 አውሮፕላኖቻቸውን ለመጠገን ችሏል።የጥገና አገልግሎቱ ከተሰጣቸው አየር መንገዶች መካከል የሳኡድ አረቢያ፤ የደቡብ አፍሪካ እና የሌሎች ሀገራት አየር መንገዶች እንደሚገኙበት የገለጹት፤ አቶ መስፍን፤ ለአብነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥገና ማዕከል ስር የሳኡዲ አየር መንገድ ዘጠኝ አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸዋል።

አሁንም ጥገና እየተሰራላቸው የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አውሮፕላኖች መኖራቸውን አስታውሰው፤ በቀጣይ ጊዜያትም ከሞተር ጀምሮ የተለያየ የኢንጂነሪንግ ባለሙያዎችን ተሳትፎ የሚጠይቁ ከባድ እና ቀላል የጥገና አገልግሎቶችን ለማግኘት የተለያዩ ሀገራት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።እንደ አቶ መስፍን ገለጻ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመናዊ የሚባሉትን እንደ ኤር ባስ ኤ 350 እና የተለያዩ የቦይንግ አውሮፕላኖችን የመጠገን አቅም ገንብቷል። የድሪምላይነር ቦይንግ አውሮፕላኖች ሞተርን ጨምሮ የተለያዩ የአውሮፕላን ሞተር /ኢንጂኖችን/ ሀገር ውስጥ ለመጠገን የሚያስችል ብቃት ፈጥሯል።

አየርመንገዱባቋቋመው ማዕከል ውስጥ የተለያዩ የአውሮፕላን ክፍሎችን የመጠገን ብቃት በመፍጠሩ የውጭ ምንዛሪን በማዳን ረገድ ሰፊ ሥራ እያከናወነ ይገኛል። ለዚህም ሥራ አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን እና ከአሜሪካን አቪዬሽን ተቋም ጭምር ፈቃድ አግኝቷል። በቀጣይም በርካታ አውሮፕላኖችን ለመጠገን የሚያስችለውን ብቃት ለማሻሻል በየዓመቱ አዳዲስ 300 አይነት የመለዋወጫ እቃዎችን ለመጠገን የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እቅድ ተይዟል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa