ግብፅ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንዳይዘግቡ እገዳ ጣለች!
የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ በሀገሪቱ ስላለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ከሊቢያ ጋር አገሪቱ እያረገች ስላለው ጦርነት በተመለከተ ምንም ዓይነት ዘገባ እንዳይሰሩ የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኋን ካውንስል ማገዱን አስታውቋል። ካውንስሉ ባስተላለፈው እገዳ መሰረት የግብፅ መገናኛ ብዙኃን እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምንም ዓይነት ዘገባም ሆነ ውይይት አንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም።በሀገሪቱ የህትመት ሚድያዎች ላይ የሚሰሩ መገናኛ ብዙኋን ይዘቶችን ከማሳተማቸው በፊት ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማስገምገም እና በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበው ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸውም ተገልጿል።ሀገሪቱ እርምጃውን የወሰደችው ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚል ሽፋን መሆኑንም የሚድል ኢስት አይ ኔት ዘገባ ያመለክታል።
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa

እንሥራ" የሸክላ ስራ ማእከል የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተመረቀ።
የማእከሉ ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ እንደሆነም ተገልጿል።በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ እና ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር እንደሚያገኙም ተገልጿል።የሸክላ ስራ የሙያውን ያህል ያልተከበረ የድካሙን ያህልም ጥቅም ያልተገኘበት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ይሄን ዘርፍ ባለሙያዎችን በሚያሳድግ ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።የሸክላ ምርቶቹ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ገበያ እንዲያገኝ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ዘርፉን የሚደግፉ የህግ ማሻሻያዎችም እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጸሀይ ግርዶሽን በላልይበላ ከተማ መመልከት ለሚፈልጉ ዜጎች አውሮፕላን ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
አየር መንገዱ እንዳስታወቀው ነገ ረፋድ ለሚከናወነው የጸሀይ ግርዶሽን በማስመልከት የበረራ አውሮፕላኖችን ማዘጋጀቱን ገልጿል።በረራው ጠዋት አንድ ሰአት ላይ ተጀምሮ 1:45 ላልይበላ ከተማ የሚያርፍ ሲሆን ከሰዓት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ ተገልጿል። በመሆኑም ይሄንን ታሪካዊ ሁነት ክስተቱ በዋናነት እና በግልጽ በሚካሄድበት ስፍራ ለመመልከት ዛሬውኑ ትኬት ቁረጡ ተብላችኋል።የደርሶ መልስ ትኬት ለአዋቂ 5 ሺህ ብር ለህጻናት ደግሞ 4 ሺህ ብር መሆኑም ተገልጿል።መንገደኞች ማስክ እና የጸሀይ ግርዶሽ መመልከቻ መነጽር ይዛችሁ ኑ ተብላችኋል።
Via Ethio FM

የቤተሰብ ግብዣ ወደ ሀዋሳ መጣ!
አንድ የኬራውድ ስፔሻል ፒዛ + አራት ማልታ ጊነስ
በ 240 ብር ብቻ።
የቤተሰብ ግብዣ ለማዘዝ 0952626262 ላይ ይደውሉ።
ይደውሉ :- 0952626262
0952626262
ቤቶ ድረስ ዴሊቨሪ ሀዋሳ ያደርሳል!
Join @Deliveryhawassa
አንድ የኬራውድ ስፔሻል ፒዛ + አራት ማልታ ጊነስ
በ 240 ብር ብቻ።
የቤተሰብ ግብዣ ለማዘዝ 0952626262 ላይ ይደውሉ።
ይደውሉ :- 0952626262
0952626262
ቤቶ ድረስ ዴሊቨሪ ሀዋሳ ያደርሳል!
Join @Deliveryhawassa
በትግራይ ክልል ደ/ዞን ራያ ዓዘቦ ወረዳ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጠረ ጸብ ምክንያት የ2 ወጣቶች ህይወት ማለፉን ፓሊስ ገለፀ። የወጣቶቹ ህይወት ሊያልፍ የቻለው የተፈጠረውን ጸብ ለመገላገል የገባ የአካባቢው ሚሊሻ በተኮሰው ጥይት በመመታታቸው ነው።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በባህር ዳር ከተማ ከገጠር መንገድ ፊት ለፊት የሚገኘውና በከተማው ማህበረሰብ ዘንድ የሀውልቱ የትርጉም የባህርዳርን ገጽታ የማይመጥን ነው በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ሲያቀርቡበት የነበረው የአደባባይ ሀውልት ዛሬ ፈረሰ፡፡
ለወደፊትም ከተማዋን ሊመጥን የሚችል አደባባይ ህብረተሰቡ ከሚመለከታቸው የዲዛይን ባለሙያዎች ጋር ተወያይቶ ሊሰራ እንደሚችል የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
ምንጭ: የከተማው ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
ለወደፊትም ከተማዋን ሊመጥን የሚችል አደባባይ ህብረተሰቡ ከሚመለከታቸው የዲዛይን ባለሙያዎች ጋር ተወያይቶ ሊሰራ እንደሚችል የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
ምንጭ: የከተማው ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
ግንባታው ከተጀመረ 12 ዓመት ያስቆጠረው የወላይታ ዩንቨርስቲ የዋናው ግቢ (ገንደባ ካምፓስ) መግቢያ በር ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። -ዩንቨርስቲው
12 አመት🙄
@YeneTube @FikerAssefa
12 አመት🙄
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንንና ጓዶቻቸው የተሰዉበት አንደኛ ዓመት በደም ባንክ አገልግሎት ቅጥር ግቢ ውስጥ ደም በመለገስ ታሰበ።
መርሃ ግብሩ "ደም እንለግሳለን እንጂ ደም አናፈስም፤ ደም ያፈሰሱትን በሕግ እንጠይቃለን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተከናወነው።በዚህም ከመቶ በላይ የሚሆኑ የቀድሞ የሥራ ባልደረቦች፣ ቤተሰቦችና ሌሎች ወዳጆቻቸው የመታሰቢያ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ደም ለግሰዋል።
#ETV
@YeneTube @FikerAssefa
መርሃ ግብሩ "ደም እንለግሳለን እንጂ ደም አናፈስም፤ ደም ያፈሰሱትን በሕግ እንጠይቃለን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተከናወነው።በዚህም ከመቶ በላይ የሚሆኑ የቀድሞ የሥራ ባልደረቦች፣ ቤተሰቦችና ሌሎች ወዳጆቻቸው የመታሰቢያ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ደም ለግሰዋል።
#ETV
@YeneTube @FikerAssefa
"ከ49ኙ የጤና ባለሞያዎች 40 ድነው ወጡ"
ዶ/ር ሀብታሙ መንጌ እባላለሁ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 10 የኮቪድ 19 ህክምና መስጫ ማዕክል አስተባባሪ ነኝ። ወደ ቦታው ተመድቤ ስሄድ 41በኮቪድ መያዛቸውን ያረጋገጡ የህክምና ባለሞያዎች ማለትም ኢንተርን ሀኪም ፣ ሬዚደንት ፣ ጠቅላላ ሀኪም ፣ ነርስ ፣ ፋርማሲስት ፣ ጤና መኮንን...ሌሎችም ነበሩ።
የመጀመርያ ቀናቶች ለኔም ሆነ ለታካሜዎች እጅግ ከባድ ነበሩ ፤ ምክንያት ደግሞ የውሀ ፣ መብራት ፣ አስተዳደሪዎ ችግሮች ስለነበሩ፡፡ ከዛም በኋላም ቢሆን የተደረጉ ለውጦች ቢኖሩም አሁንም ክትትል የሚያስፍልጋችው ስራዎች አሉብን።
በነዚህ ችግሮች ውስጥ ሆናቹህም ቢሆን ከበሽታው አገግማቹህ በመውጣታቹህ እና ላሳያችሁት ትግስተና ፣ ትብብር እኔም ሆንኩ የስራ ባልደረቦች እጅግ ደስ እንዳለን መግለፅ እወዳለሁ።
ዶ/ር ሀብታሙ መንጌ
የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 10 ኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል አስተባባሪ
Via Hakim

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ፅህፈት ቤት በኮቪድ 19 ምርመራ ላይ የተሰማራ ከእኛ የእውቅና ምስክርነት የወሰደ አንድም ላብራቶሪ የለም አለ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ ለሸገር ሲናገሩ ፅህፈት ቤታቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የኮቪድ 19 ምርመራ የማድረግ ብቃትን ለመመዘንና እውቅና ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት ቢያደርግም፣ ብቃቴን መስክሩልኝ ብሎ የመጣ መንግስታዊም ሆነ የግል ላቦራቶሪ የለም ብለዋል፡፡
Via Sheger FM

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 18 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 683 ናሙናዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 18 ሰዎች (14 ወንዶች እና 4 ሴቶች) ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡እድሜያቸውም ከ13 እስከ 49 ዓመት ናቸው።ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸውም 14 ከምዕራብ ጎንደር ዞን ለይቶ ማቆያ፣ ሁለት ከደቡብ ወሎ ዞን ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ፣ አንድ ከደብረ ማርቆስ እና አንድ ከደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ ናቸው፡፡በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 13/2012 ዓ.ም ድረስ ለ9 ሺህ 160 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ 271 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡በክልሉ ባለፉት 24 ሰዓታት ከበሽታው ያገገመ የለም፤ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰውም የለም፡፡በጽኑ ሕሙማን የሕክምና ክፍል ውስጥ የገባ ታማሚ አለመኖሩንና ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙ ሁሉም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ቢሮው አስታውቋል፡፡
Via AMMA

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 95 ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 399 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት ከአንዱ ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(195) ሴት(204) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ4-85 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 95 ሰዎች(82 ከአዲስ አበባ፣ 1 ከኦሮሚያ፣ 8 ከአማራ፣ 1 ከትግራይ ፣ 1 ከጋምቤላ እና 2 ከሶማሊ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።
➡️የተገኙት ከሲቪል ሰርቪስ ለይቶ ማቆያ(135)፣ ከደዋሌና ጋሊሌ ለይቶ ማቆያ(132)፣ አዲስ አበባ(86)፣ ከኦሮሚያ ክልል(9)፣ከአማራ ክልል(18) ፣ ከትግራይ ክልል(2)፣ከሶማሊ ክልል(1)፣ ከድሬዳዋ(14)፣ ከደቡብ ክልል(1) እና ከጋምቤላ ክልል(1) በድምር 399 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 30 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ ምንም ሞት ያልተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 72 ነው።

ዴክሳሜታዞን መድሃኒትን ያለ ሃኪም ትእዛዝ መውሰድ ለጤና ጉዳት እንደሚዳርግ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ!
ዴክሳሜታዞን ለፅኑ የኮሮና ህሙማን የሚሰጥ መድኃኒት እንጂ ለኮሮናቫይረስ መከላከያ እንዳልሆነ እና መድሃኒቱን ያለ ሃኪም ትእዛዝ መውሰድ ለጤና ጉዳት እንደሚዳርግ የጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።በቅርቡ የዴክሳሜታዞን መድሃኒት ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ በሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን ዘንድ ሊከሰት የሚችለውን የሞት አደጋ መቀነስ እንዳስቻለ መገለፁ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን እንደ ድንገተኛ ህክምና ጥቅም ላይ እንዲውል ወስኗል።
ነገር ግን ዴክሳሜታዞን የኮቪድ-19 መድሃኒት ያልሆነና ለመከላከል የማይጠቅም ሲሆን የራሱ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለው ግንዛቤ እንዲወሰድ እና ያልታመሙ ሰዎች ያለ ህክምና ባለሙያ ትእዛዝ ከወሰዱት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ህብረተሰቡ ያለ ሃኪም ትእዛዝ መድሃኒቱን እንዳይወስድ እንዲሁም የፋርማሲ እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎችም የዴክሳሜታዞን መድሃኒትን ያለ ሃኪም ትእዛዝ ለደንበኞቻቸው መሸጥ እንደሌለባቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአፅንኦት አሳስቧል።
Via ETV

ለ30 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የጣና በለስ አየር ማረፊያ በአዲስ መልክ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ኢትዮጵያዊው ባለሃብት አቶ ወርቁ አይተነው አስታወቁ።
የደብሊው ኤ ዘይት ማምረቻና ማከፋፈያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት የሆኑት አቶ ወርቁ አይተነው የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግና ቀጠናው የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች መገኛ በመሆኑ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ለማልማት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን አየር መንገድ የእድሳት ሙሉ ወጭውን በመሸፈን እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።በተደረገው እድሳት መሰረትም ነገ የሙከራ በረራ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።በፓዊ ወረዳ የሚገኘውን የጣና በለስ የአየር መንገድ ዕድሳት ዋና ዓላማ በዞኑ ውስጥ የእርሻ ኢንቨስትመንት ስራዎችን ከማገዝ በተጨማሪ የተለያዩ ባለሃብቶች ወደ ቀጠናው እንደመጡ ያግዛል ብለዋል ባለሃብቱ።
ምንጭ: የመተከል ዞን ኮ/መምሪያ

አትሌት እታፈራው ተመስገን ከማንኛውም የአትሌቲክስ ውድድር ለ12 አመት ታገደች!
የብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (NADO) ዛሬ ሰኔ 13/2012 ዓ. ም ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በላከው መረጃ መሠረት አትሌት እታፈራሁ ተመስገን ወዳጆ እ.ኤ.አ october 20,2019 ዓ. ም. በካናዳ በተካሄደው የወተር ፍሮንት ማራቶን በግሏ በተካፈለችበት ወቅት በተወሰደው የደምና ሽንት ናሙና የተከለከሉ 2 ንጥረ ነገሮችን (ኢፒኦ እና ቴስቴስትሮን - EPO and Testestrone) መጠቀሟ በመረጋገጡ እና በተጨማሪም ይሄንን ጥፋት ለመሸፋፈን ሃሰተኛ የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ለፈፀመችው 3 ተደራራቢ ጥፋቶች እ.ኤ.አ ከNovember 20,2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ November 20, 2031 ዓ. ም. ድረስ ለ12 አመት የሚቆይ ከማንኛውም የአትሌቲክስ ውድድሮች እገዳ አስተላልፎባታል።
#EAF

ባህርዳርና ፋሲል ከነማ የ6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገላቸው!
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ባህርዳርና ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለቦች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለማገዝ የስድስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር በባህር ዳር ከተማ ማምሻውን ገንዘቡን ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት ድጋፉ ክለቦቹ በኮሮና መከሰት ምክንያት የገጠማቸውን የፋይናንስ እጥረት ለማገዝ ታስቦ የተደረገ ነው።“ክለቦቹ በእግር ኳሱ ዘርፍ ጠንክረው በመስራት ሀገራቸውንና የክልላቸውን ስም እንዲያስጠሩ የፋይናንስ ችግራቸው እስኪፈታም የክልሉ መንግስትና ፓርቲው ድጋፍ ያደረጋል”ብለዋል።
ምንጭ: ኢዜአ

👆👆 ነገ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል የሚከሰተውን የፀሐይ ግርዶሽ ለመታዘብ፣ የግርዶሹን ሰዐት እና መጠን ይመልከቱ።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa