YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እንግሊዝ የኮሮና ተጠቂዎችን ከሞት የሚታደግ መድሃኒት ማግኘቷን አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ የጤናዉ ዘርፍ ተመራማሪዎች እንዳሉት፣ህክምናዉ ብዙ ወጭን የማይጠይቅ በመሆኑ ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡መድሃኒቱ የሰዎችን የበሽታ መከላከል አቅም በማሳደግ ቫይረሱን በቀላሉ እንዲቋቋሙ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡መድሃኒቱ ቀደም ብሎ መገኘት ቢችል በሃገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ከሞቱ ሰዎች ዉስጥ ቢያንስ 5 ሽህ ያህሉን ማትረፍ ይቻል እንደነበር ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡የመድሃኒቱ ወጭ ዝቅተኛ በመሆኑም በተለይም ለድሃ ሀገራትም ጭምር በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ይቻላል ነዉ የተባለዉ፡፡ዴክሳ ሜታሶን የተሰኘዉ ይህ መድሃኒት የተገኘዉ በአለማቀፋ የመድሃኒት ጥናት አማካኝነት ሲሆን ለፈዋሽነቱ ማረጋገጫ እንደተሰጠዉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በቀብርና በሐዘን ሥነ ሥርዓት ላይ ከታደሙ ሰዎች 4ቱ ቫይረሱ ተገኘባቸው!

ባለፈው ሳምንት ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሆኖ በደረሰባቸው አደጋ በህክምና ላይ ሳሉ ህይወታቸው አልፎ ወደ ትውልድ መንደራቸው በተወሰዱ ግለሰብ ሐዘንና ቀብር ላይ ከተሳተፉ ሰዎች መካከል በአራቱ ላይ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘ ተነገረ።ባለፈው ሳምንት የምርመራ ውጤታቸው ሳይታወቅ አስከሬናቸው ከአዲስ አአበባ ወደ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በተወሰደው ግለሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙና ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተው ምርመራ መካሄዱን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ጸዳለ ሰሙንጉሥ ለቢቢሲ ገልጸዋል።"በሰዎቹ ላይ በተለያዩ ቀናት ምርመራ ተደርጎ በመጨረሻ ላይ ትላንት የወጣው ውጤት የ4 ናሙና ውጤት ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል" በማለት ግለሰቦቹ ወደ ህክምና ማዕክል እንዲገቡ ተደርጎ ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት (2658) ደርሷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አንድ (81) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት (2658) ደርሷል፡፡በአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በአስክሬን ምርመራ አንድ (1) ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ ማገገማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 40

👉ቦሌ 8

👉ጉለሌ 3

👉ልደታ 1

👉ኮልፌ ቀራንዮ 11

👉ቂርቆስ 0

👉አራዳ 4

👉የካ 2

👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 3

👉አቃቂ ቃሊቲ 0

👉አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ 9

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ከዚህ በኋላ ለድርድር የምትቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ አለመኖሩን ኢትዮጵያ አሳወቀች፡፡

ኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ሰሞኑን እየተካሄደ ያለውን የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በመግለጫቸው እንዳመላከቱት ግብጽ ከዚህ በፊት በድርድሩ ስታሳየው የነበረውን ሙሉ የዓባይ ውኃ ይገባኛል አካሄድ አሁንም እየተከተለች ነው፡፡ በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመናት የተከተሉት ይህ አካሄድ ለአሁኑ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን በምንም መልኩ የማያስኬድና የማንቀበለው ነው ብለዋል አቶ ገዱ በመግለጫቸው፡፡

ግብጽ አሁንም ፍላጎቷ ድርድሩ እንዲቋረጥ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት በ2015 (እ.አ.አ) ከነበረው የመርህ ስምምነት ውጭ ሌላ መተሳሰሪያ የሌለን በመሆኑ ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ከዚህ በኋላ ለድርድር የምንቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም ሲሉም አስጠንቅቀዋል።እየተደራደርን ያለነው ሁሌም እኔ ብቻ ልጠቀም ከምትለው፣ እድሜ ልኳን የኢትዮጵያን ጥቅም ከምትጻረረው፣ ሀገራችን ዘላቂ ጥንካሬ እንዳይኖራት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከምትሠራው ግብጽ ጋር ነው ሲሉም አቶ ገዱ የግብጽን አቋም አስረድተዋል፡፡የግብጽ ሕዝብ መንግሥታቸው ምክንያታዊና ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ተመስርቶ እንዲደራደር ጫና እንዲያሳድሩም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሐይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች የፌድራሉን መንግሥት ከትግራይ መስተዳድር ለማስታረቅ የጀመሩትን ጥረት ውድቅ ማድረጋቸውን ፓርቲያቸው ህወሓት አስታወቀ።

አስታራቂው ቡድን መቐለ የደረሰው ዛሬ ነበር።“ሁሉም ፖለቲካዊ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የሚወክሉ ፌደራሊስት ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ትግራይ መንግስት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም" ብለዋል።


ውይይቱ በመጨረሻ ሰአት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው ያለው ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማነኛውም የአገሪቱ ችግር ለመፍታት የሚቀሳቀስ አካል ካለ ችግሩ ወይም ውጥረቱ የተፈጠረው ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማፍረስ በአገሪቱ አምበገናናዊ ስርአት ለመገንባት እየተሯሯጠ በሚገኘው ብልፅግና የተሰኘው ቡድንና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እንጂ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ብቻ የተፈጠረ አለመግባባት አድርጎ መመልከት የለበትም ብለዋል፡፡

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በሚያደርጉት ድርድር ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስን ሚና በተመለከተ በግላቸው ለሀገሪቱ የግምጃ ቤት ኃላፊ ደብዳቤ ፃፉ።

የአሜሪካ የገምጃ ቤት ሀላፊ ስቴቨን መኑሸን በዋሽንግተን ሲደረግ ነበረው የሶስቱ ሀገራት ድርድር ላይ አሜሪካን ወክለው ሲሳተፉ ነበር።ፕሮፌሰር ዓለማየሁ በደብዳቤያቸው አሜሪካ በድርድሩ ውስጥ ከአሜሪካ ህግ እና ከፍትሃዊነት መርህዎች አንፃር ሊኖራት ስለሚገባው ሚና የግላቸውን ምክረ ሀሳብ በደብዳቤያቸው አስፍርዋል።በዚህ ደብዳቤያቸውም ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብፅ ጋር ከዚህ በፊት ስታደርጋቸው የነበረቻቸውን ንግግሮችም ሆኑ ድርድሮች ላይ ሁልጊዜ ሰላምን ስትመርጥ እንደነበር እና በሁለትዮሽ ግንኝነቷም ሁልጊዜ መሻቷ ሰላም እንደነበረ፥ በተቃራኒው ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ብቸኛ የበላይ የሆነ ተጠቃሚነትን ለማስጠበቅ በታሪኳ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነትን ስታውጅ እንደኖረች እና አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ ለግብፅ ፍላጎቶች የማትገዛ ከሆነ ጦርነት አማራጭ መሆኑን እያስፈራራች መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ ልታውቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።ሚኒስትሩ የሚመሩት የአሜሪካ የገንዘብ መስሪያ ቤት በግድቡ ድርድር ላይ ያለው ተሳትፎንም በተመለከተ የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትን ሚና የቀማ መሆኑንም በደብዳቤያቸው አመልክተዋል።ፕሮፌሰር ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሲሆኑ፥ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ናቸው።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ገዥው ፓርቲ ደቡብ ክልልን በ5 ክልሎች ለማዋቀር የያዘው ጥረት የድሮውን ስህተት የሚደግም ነው- ሲል ኢዜማ ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ወቅሷል፡፡ ሕዝቡ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ወኪሎቹን ሳይመርጥ፣ ገዥው ፓርቲ ዘላቂ ውጤት ባለው ራስን በራስ ለማስተዳደር የተቀመረ የአደረጃጀት ለውጥ የማድረግ መብት የለውም፡፡ የታሰበው ለውጥም የሕዝቡን ሃቀኛ ጥያቄዎች አይፈታም፡፡ ገዥው ፓርቲ ራሱን የሕዝብ መብት ሰጭ እና ነሺ አድርጎ በሂደቱ ከገፋበት፣ በሕይወት እና ንብረት ላይ ለሚደርሰው ጥፋት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አዲስ ለሚመሰረተው የሲዳማ ክልል ስልጣን ለማስተላለፍ በቀጣይ ሀሙስ ድንገተኛ ጉባኤ መጥራቱን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
EmpowerMed የተሰኘ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ዘርፍ በእጅጉ የመደገፍ ብሎም የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረሠናይ ድርጅት ነው። መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው ይህ ግብረሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ ይገኛል። በቅርቡ በተቀሰቀሰው COVID-19 ወረርሽኝን ምክንያት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ለመርዳት ፕሮግራም በመቅረፅ ማገዝ ይፈልጋል። በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ያላችሁ የህክምና ተማሪዎች ማለትም Medical, Nursing, Midwifery ወዘተ እና የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በሙሉ ከድርጅታችን ጋር ህብረት መፍጠር የምትፈልጉ በሙሉ በተገለፀው ዌብሣይት እና የ ፌስቡክ ገፃችን ላይ በመግባት መመዝገብ እና ህብረት መፍጠር ትችላላችሁ ።
የድርጅቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ facebook.com/empowermed.ngo ነው።


የድርጅቱ ዌ ብ ሳ ይ ት
http://EmpowerMed.ngo

ነው።
Forwarded from Nat Computers®️ (Natnael Endrias)
🔵💻HP_Core_i3 (8th Generation)

Model :Notebook (2019 Model)

Condition: Brand New

🖥 Screen :15.6”

📼 Hard disk : 1tera (1000gb)

Ram : 4gb

2.2 Ghz Speed

⭕️Color : Silver

🔋:>5hrs - 6hrs

💵Price 17,800br 👈

+251911522626
+251953120011

📩 : @natyendex


🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ in front of angla burger
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች በዋስትና

A01 2019 /16 GB/ 5,500 ብር
A10S 2019 /32 GB/ 7,200 ብር
A20S 2019 /32 GB/ 8,500ብር
A30S 2019 /64 GB/ 11,300 ብር
A30S 2019 /128 GB/ 11,900 ብር

A50S 2019 /128 GB/ 4GB 14,000
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 14,500
A31 2020 /128 GB/ 4GB 13,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 14,999 ብር

A60 2019 /64 GB/ 6GB 13,500 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 16,500 ብር
A71 2020 /128 GB/ 6GB 21,500 ብር
A71 2020 /128 GB/ 6GB 22,000 ብር

M30S 2019 /64 GB/ 4GB 11,500
M30S 2019 /128 GB/ 4GB 13,500
📌M31 2020 /128 GB/ 6GB 15,400

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii

@HEYOnlinemarket
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጦር ኃይሎች አካባቢ የነበረው ፍትሐብሔር ምድብ ችሎት ከሐሙስ ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ዳርማር ፊትለፊት፤ ልደታ ኮንዶሚኒየም አካባቢ ወደ እሚገኝ ሕንጻ አዛውሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

ይህን የገለጹት የምድብ ችሎቱ አስተባባሪ ዳኛ የሱፍ መሐመድ ሲሆኑ አዲስ በመደራጀት ላይ የሚገኘው “የከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ፍትሐብሔር ምድብ ችሎት” ከዳርማር ፊት ለፊት በተስፋ ኮከብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና በኑር ህንጻ መካከል ካለ ሕንጻ ጀርባ የሚገኝ ሲሆን የምድብ ችሎቱ አደረጃጀት እስካሁን ጦር ኃይሎች አካባቢ አገልግሎት ሲስጥበት ከነበረው ሕንጻ አንጻር የተሻለና ለፍርድ ቤቱ ሠራተኞችም ሆነ ለተገልጋዮች ምቹ እንደሚሆን የታመነበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አንጋፋው የሳይኮሎጂ መምህር ዶ/ር አብርሃም ሁሴን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ዶ/ር አብርሃም በሳይኮሎጂ የትምህርት ፍልስፍና ከፍተኛው ማዕረግ ላይ የደረሱ በበርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎቻቸው የሚታወቁ የስነ ትምህርት ሙያተኛ ናቸው። የባህርዳር መምህራን ማሰልጠኛን ከመሩ ቀደምት ሙያተኞች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አብርሃም በስርአተ ትምህርት፣ በትምህርት አስተዳደር፣ በትምህርታዊ ሳይኮሎጂ ዘርፎች አሉ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ሙያተኞች ውስጥ ይመደባሉ፡፡የባህርዳር የስነ ትምህርት ኮሌጅ ዲን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ እንዱሁም የሴኔት አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባዔዎች በአብዛኛዎቹ ላይ ተካፋይና ቡድኑ መሪም ነበሩ።

እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ ባገለገሉበት ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍልን ከማቋቋም እስከ ሃላፊነት አገልግለዋል፡፡ ከ14 በላይ የምርምር ስራዎችንም አበርክተዋል።ዶ/ ር አብርሃም ሁሴን በቀድሞው የከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ተቋም የስኮላርሺፕ ሃላፊም በመሆን ማገልገላቸው ማህደራቸው ያስረዳል፡፡ ዕውቁ የሳይኮሎጂ መምህር ዶ/ር አብርሀም ስርአተ ቀብራቸው በሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ይፈፀማል ሲሉ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ብርሃኑ ሲሳይ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የደንበኞች የኦንላይ አገልግሎትን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ!

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና የደንበኞችን ጊዜና ወጪ ለመቆጠብ የጉምሩክ አገልግሎት በኦንላይ ለመስጠት የጉምሩክ ኮሚሽን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ይህ የተገለፀው የጉምሩክ አገልግሎትን ለማዘመን ከኮሚሽኑ ጋር እየሰራ የሚገኘው እና ሶፍትዌር በማልማት ስራ የተሰማራ “ዌብፎንቴይን” የተሰኘ ድርጅት ለኮሮና መካከል እንዲያግዝ ያደረገው ድጋፍ ርክክብ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ አንስቶ የተከናወኑ ሥራዎች ሲመዘኑ በ2012 ዓ.ም የላቀ ሥራ መሰራቱን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ።

የግድቡ ግንባታ በሁሉም መስክ የተሳካ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አመለከቱ ።ሥራ አስኪያጁ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣ ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅም በሁሉም አቅጣጫ በሶስት ሽፍት እየተሰራ ነው።የግድቡ የሲቪል ኢንጅነሪንግ ሥራው 87 በመቶ ፣የብረታ ብረት ሥራዎቹ ደግሞ ከ 31 በመቶ በላይ ፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል የተርባይንና የጀነሬተር ሥራዎች አፈጻጸምም 45 በመቶ ፤ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም ደግሞ 74 በመቶ ደርሷል።ከዚህ ቀደም ችግር የነበረባቸው የቅድመ ሀይል ማመንጫ የብረታ ብረት ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ተነስተው በአዲስ መተካታቸውን ያመለከቱት ሥራ አስኪያጁ፤ የግድቡ የግርጌ የውሃ ማስተንፈሻ (የቦተም አውትሌት) እንዲሁም ከቅድመ ሀይል ማመንጨት ጋር የተገናኙ የሁለት ጀነሬተር ተርባይን ሥራዎች ተጠናቅቆ በኮንክሪት እየተሞሉ መሆኑን አብራርተዋል።

የ 11 ቀሪ ዩኒቶች የብረታ ብረት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተው ፣ ሌሎች ለሲቪል ኮንትራክተሮች የተሰጡ ሥራዎች ደግሞ በቅርቡ እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል። ለሁለቱ ቅድመ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የሚሆን የብረታ ብረት ሥራዎች ተከናውነው ኮንክሪት እየተሞሉ መሆኑን ጠቁመዋል። በቀጣይም የጀነሬተር ተርባይን ተከላ እንደሚጀመር ጠቁመዋል።በግድቡ በተለይም የመካከለኛው ውሃ ይፈስበት የነበረው ቦታ ርዝመቱ 525 ሜትር የነበረ ሲሆን፤ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ 560 ሜትር ለማድረስ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ጎንና ጎኖቹም በኮንክሪት እየተሞሉ መሆኑን አስታውቀዋል።

#EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ስርጭት ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በ73 በመቶ መጨመሩን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ።

ክረምት መግባቱን ተከትሎ በክልሉ በአንዳንድ ወረዳዎች በወረርሽኝ መልክ የተከሰተውን የወባ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ ከተከሰተባቸው ወረዳዎች መካከል ደራ፣ ጎንደር ዙሪያ፣ አንዳቤት፣ ፎገራ፣ ባሕርዳር ዙሪያ፣ ምስራቅ ደንቢያ፣ ፋርጣ፣ ሊቦከምከም፣ እብናት እና ባሶሊበን እንደሚጠቀሱ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡ በባሕርዳር ከተማም ችግሩ መኖሩ ታውቋል።በበጀት ዓመቱ በሽታውን ለመከልከልና ለመቆጣጠርም ለ93 ወረዳዎች 4 ሚሊዮን የአልጋ አጎበር፣ ከፍተኛ የወባ ስርጭት ላለባቸው 26 ወረዳዎች ደግሞ 26 ሺህ 245 ኪሎ ግራም የፀረ-ትንኝ ኬሚካል ርጭት እንደተካሄደ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

በቆላማ እርሻ ቦታዎች ጊዜያዊ የወባ ህክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ማቋቋም፣ የወባ ቅኝትን ማጠናከር፣ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች እና ሌሎችም ስርጭቱን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውንም ነው ኢንስቲትዩቱ ያስታወቀው።አሁንም በክልሉ ከፍተኛ የወባ ስርጭት ባለባቸው 53 ወረዳዎች 264 ሺህ 209 ኪሎ ግራም የቤት ውስጥ የፀረ-ትንኝ ኬሚካል ርጭት ለማድረግ፣ በዘጠኝ ታላላቅ የልማት ቀጣና ባለባቸው ወረዳዎች ጊዜያዊ የወባ ህክምና ጣቢያ ለማቋቋም፣ የግንዛቤ ፈጠራ ለመሥራት፣ የበሽታው ስርጭት በጨመረባቸው ወረዳዎች ቤት ለቤት ምርመራና ህክምና አገልግሎት ለማጠናከር እና የአልጋ አጎበር ለማሰራጨት ታቅዶ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።

በአማራ ክልል ከ2005 እስከ 2011 ዓ.ም ያለው የወባ ህሙማን ቁጥር በ75 በመቶ፣ የሞት መጠኑም በ89 በመቶ መቀነሱን የገለጸው የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ የ2012 በጀት ዓመት የወረርሽኙ ስርጭት ግን ከ2011 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 73 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡የአየር ንብረት መዛባት፣ ወረርሽኙን የመከላከያ ግብዓት አቅርቦት መቆራረጥ፣ በፀረ-ትንኝ ኬሚካል ርጭት ይሸፈኑ የነበሩ ወረዳዎች ባለፈው ዓመት እና በዚህ ዓመትም ሳይረጩ መዘግየቱ፣ ወባ በመቀነሱ ምክንያት ኅብረተሰቡ መዘናጋቱ፤ የአልጋ አጎበር በአግባቡ አለመጠቀም፣ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የወባ ምርመራና ህክምና አገልግሎት መቆራረጥ እና ለወባ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆን ለስርጭቱ መጨመር ምክንያቶች መሆናቸውን ኢንስቲትዩቱ አስረድቷል፡፡በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ከ350 በላይ አዲስ ኢንዱስትሪዎች በኃይል እጥረት ምክንያት ሥራ መጀመር አልቻሉም!

የኢትዮጵያን የዘይት ዕጥረት ይቀርፋሉ የተባሉ ፋብሪካዎችም ይገኙበታል። በአማራ ክልል ከ350 በላይ የሚሆኑ አዲስ ኢንዱስትሪዎች በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት የግንባታ ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ ቢያጠናቅቁም ወደ ሥራ መግባት አለመቻላቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው የኃይል አቅርቦት ሳይሟላላቸው ወደ ሥራ የገቡ ኢንዱስትሪዎችም በዚሁ ችግር በሙሉ አቅማቸው እያመረቱ አለመሆኑ ተጠቁሟል።በተለይ በኢትዮጵያ ያለውን የምግብ ዘይት እጥረት እንደሚፈቱና የኢትዮጵያን ፍላጎት አጥግበው ለውጭ ገብያ ይተርፋሉ ተብለው የታሰቡ በክልሉ የተገነቡ ኹለት ግዙፍ የምግብ ዘይት ፋብሪካዎች፣ የዚሁ ችግር ሰለባ መሆናቸውን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ይሄነው አለሙ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በመሆኑም ከፋብሪካዎቹ ከፊታቸው የኃይል አቅርቦት ችግሩ እንደተጋረጠባቸውና ትኩረት እንደሚሹ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

Via @addismaleda
@YeneTube @FikerAssefa
"የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎ ከአፍንጫዎ እስከ አገጭዎ ካልሸፈንዎት ከኮሮና ቫይረስ በሽታን አይከላከልም።"-የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

@YeneTube @FikerAssefa
#Dexamethasone
የኮሮናቫይረስ ጽኑ ህሙማንን ህይወት ይታደጋል የተባለውን መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት ተቀበለው!

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ዴክሳሜታሶን በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል።የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት "ይህ ኦክስጂንና የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው መድኃኒት ነው" ብለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የቀብሪ-ደሐር ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች ተከፋፈሉ!

በሶማሊ ክልል ቀብሪ ደሐር ከተማ በቅርቡ የተገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅመ ደካሞችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለነዋሪዎች መከፋፈላቸውን ተገለፀ፡፡የጋራ መኖርያ ቤቶቹ እጣ ላይ አቅመ ደካማ ሰዎች ቅድሚያ እንዲያገኙ ሲደረግ በተጨማሪም በከተማው ያሉ በስራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ታታሪ የሆኑ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡አቅመ ደካሞች፣ ታታሪ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎቹ በጥንቃቄ እና በመስፈርት ከተመረጡ በሗላ እጣ የወጣላቸው ነዋሪዎች የቤቶቹን ቁልፍ ተረክበዋል፡፡ወደ እጣው እንዲገቡ ከተደረጉ መምህራን በብቃታቸው የተመሰከረላቸው እና ተማሪዎቻቸውን ለማብቃት ባደረጓቸው ጥረቶች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች ባላቸው የአገልግሎት ብቃት ተመዝነው ወደ እጣው ከገቡት ውስጥ የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

አዲስ ተገንብተው ለነዋሪዎች የተላለፉት የጋራ መኖርያ ቤቶች በቁጥር 56 ሲሆኑ እጣ ለወጣላቸው 56 አቅመ ደካሞች፣ ታታሪ መምህራን እና የጤና ባለ ሙያዎች ተከፋፍለዋል፡፡ከቤቶቹ 50 በመቶ አቅመ ደካማ ከሆኑት ነዋሪዎች ውስጥ እጣ አውጥተው እንዲወስዷቸው ሲደረግ ቀሪዎቹ ደግሞ በአገልግሎታቸው የተመሰገኑ እና በወጣው እጣ እድለኛ ለሆኑ መምህራን እና የጤና ባለ ሙያዎች የተላለፉ ናቸው፡፡የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና ክፍፍል በቀጣይ በሌሎች የክልሉ ከተሞች እና ወረዳዎች የሚከናወን እና የሚዳረስ መሆኑን የሶማሊ ክልል የቤቶች ልማትና የ መንግስት ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ አስታውቋል፡፡

ምንጭ: የሶማሊ ክልል መ/ኮ/ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa