በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህሲ መድሃኒቶች ርጭት(Fumigation) እየተከናወነ ነው።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ በተለይም ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ትናንት በሰጡት መግለጫ መሰረት በከተማዋ ከሚገኙ መንገዶች ውስጥ ዋና ዋና ተብለው በተለዩ 13 መንገዶች ላይ ዛሬ ማለዳ ጀምሮ የፀረ ተዋህሲ መድሃኒቶች ርጭት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡41 ኪሎ ሜትር በሚሸፍኑት መንገዶች ላይ እየተከናወነ ባለው የፀረ ተዋህሲያን መድሃኒቶች ርጭት ምክንያትም እስከ ረፋዱ አምስት ሰዓት መንገዶቹ ዝግ ሆነው ይቆያሉ።የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ዑማ በማለዳ ገብተው ይህንን ስራ እያከናወኑ ላሉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Via Addis TV
@YeneTube @FikerAssefa

ጎመጁ ኦይል በ700 ሚሊዮን ብር የሞተር ዘይትና ቅባት ማቀናበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው!
አገር በቀል የነዳጅ ኩባንያ የሆነው ጎመጁ ኦይል ኢትዮጵያ፣ በ700 ሚሊዮን ብር ወጪ የሞተር ዘይትና ቅባት ማቀናበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ በዝግጅት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ለተለያዩ ተሽከርካሪዎችና የግብርናና የግንባታ ማሽነሪዎች ማለስለሻነት የሚውሉ የሞተር ዘይትና ቅባት ማቀናበሪያ ፋብሪካው የሚገነባው፣ አዲስ አበባ ውስጥ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ኩባንያው 40,000 ካሬ ሜትር ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረከቡን ገልጿል፡፡ድርጅቱ የገነባውን ሆቴል ለኮሮና ለይቶ ማቆያነት ማበርከቱም ይታወሳል።
ምንጭ: ሪፖርተር

የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ተራዘሙ!
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ3 ሃገራት የሚካሄዱ የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች መራዘማቸው ይፋ ሆኗል፡፡የተራዘሙት ውድድሮች በስዊድን ስቶኮልም፣ በጣሊያን ሮም እና በሞሮካ ራባት በሚቀጥለው ግንቦት ሊካሄዱ ቀደም ተብሎ መርሃ ግብር የወጣላቸው ነበሩ፡፡
በቀጣይ የዳይመንድ ሊጉን መርሃ ግብር ከዓለም አትሌቲክስ መርሃ ግብር ጋር በማጣጣም ይፋ እንደሚደረግ ድርጅቱ ገልጿል፡፡በቻይና እና በኳታር ሊካሄዱ የነበሩ የ2020 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችም በወረርሽኙ ምክንያት ሳይካሄዱ መቅረታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡- ዳይመንድ ሊግ/ETV

መንግሥት ከ7,000 በላይ የንግድ መደብሮች መታሸጋቸውንና ነጋዴዎች መታሰራቸውን አስታወቀ!
በኮሮና ቫይረስ ሰበብ ምርት በመደበቅ፣ በሕገወጥ መንገድ በማዘዋወርና ዋጋ በማናር የተሳተፉ ብሎም በወንጀል የተጠረጠሩ ነጋዴዎችን እንዳሰረና ከ7,300 ያላነሱ መደብሮችን እንዳሸገ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታዎቹ አቶ እሸቴ አስፋውና አቶ ተካ ገብረየሱስ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች ጭምር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የምግብ ሸቀጦችን ሆነ ብለው በመደበቅና ከሚገባው በላይ ዋጋ በማናር ሲያግበሰብሱ የተደረሰባቸው ነጋዴዎች፣ ከዚህ ተግባር አልፈው ባዕዳን ነገሮችን በመቀየጥ፣ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ውህዶችን እንደ ሳኒታይዘርና ሌሎችም መከላከያዎች እያስመሰሉ ሲሸጡ የተያዙ ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
የጥራትና ሬጉላቶሪ ዘርፍን የሚመሩት አቶ እሸቴ እንዳብራሩት፣ በአዲስ አበባ ከ1,400 በላይ ነጋዴዎች ዋጋ በማናርና ሸቀጦችን ሲደብቁ ተደርሶባቸው መደብሮቻቸው ታሽገውባቸዋል፡፡ከእነዚህ ውስጥ ከ1,150 ያላነሱት ለሕግ መቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በአማራ ክልል 1,800 መደብሮች ሲታሸጉ፣ 34 ነጋዴዎች ታስረዋል፡፡
በኦሮሚያም ከ1,792 ያላነሱ መደብሮች ሲታሸጉ፣ 30 ነጋዴዎች መታሠራቸው ተጠቅሷል፡፡ በደቡብ ክልል ከ1,000 በላይ መደብሮች ታሽገው ንግድ ፈቃዶቻቸው እንደተሰረዙባቸው ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡በትግራይ 111፣ በአፋር 610፣ በቤንሻንጉል 213፣ በጋምቤላ 34፣ በድሬዳዋ 209፣ በሶማሌ 29፣ በሐረሪ 9 መደብሮች ሲታሸጉ፣ በአፋር 78 እና በሶማሌ 23 ነጋዴዎች መታሰራቸው ታውቋል፡፡
Via Reporter

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለሕዝባቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጻፉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ ከመሻሻሉ በፊት የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ብሪታኒያ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች በላኩት ደብዳቤ ላይ አስጠነቀቁ።በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ እራሳቸውን ለይተው የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አስፈላጊ ከሆነ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም ገልጸዋል። የአገሪቱ ዜጎች ከቤታቸው ውጪ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦችና የጤና መረጃዎችን ያየዙ በራሪ ወረቀቶች እንዲሰጧቸው ተነግሯል።
ይህም የሚደረገው መንግሥት ዜጎች ማድረግ ስለሚገቧቸው ነገሮች ግልጽ የሆነ መምሪያ አልሰጠም በሚል ከተተቸ በኋላ ነው።ለ30 ሚሊዮን ቤተሰቦች እየተሰራጨ ያለውና 5.8 ሚሊዮን ፓዉንድ ወጪ ወጥቶበታል በተባለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላይ
"ከመጀመሪያው ትክክለኛውን እርምጃ በትክክለኛው ሰዓት ለመውሰድ ሞክረናል።
"ከሳይንስና ከህክምናው ዘርፍ የሚሰጡ ምክሮች ከዚህም በላይ የምንወሰድው እርምጃ እንዳለ ካመለከቱ ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን በደብዳቤያቸው ላይ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም "ግልጽ ላደርግላችሁ የምፈልገው ነገር፤ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ ከመሻሻሉ በፊት የከፉ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ እናውቃለን" ብለዋል በደብዳቤያቸው።
"ነገር ግን ዝግጅቶችን እያደረግን ሲሆን፤ ሁላችንም የተሰጠንን መመሪያ መከተል ከቻልን በበሽታው የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ጥቂት ይሆናል። በቅርቡም ህይወት ወደ መደበኛ መስመሯ ትመለሳለች።"
ባለሙያዎች እንደሚሰጉት ከሆነ አሁን እየተወሰዱ ያሉት የእንቅስቃሴ እገዳ እርምጃዎችና አካላዊ እርቀትን የመጠበቅ ምክሮች ተግባራዊ ሆነው ውጤታቸው እስኪታይ ድረስ በሚኖሩት ሁለትና ሦስት ሳምንታት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም። በታላቋ ብሪታኒያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1,019 የደረሰ ሲሆን ትናንት ብቻ 260 ሰዎች ሞተዋል።በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ 17,089 በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ይገኛሉ።
Via BBC

ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ሴት አለች?
ትናንት ቅዳሜ ማታ በማህበራዊ ሚዲያ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ሴት ተገኘች የሚለውን ወሬ ለማጣራት የሆስፒታሉ አስተዳደር ከፍል ጋር fidelpost.com ደውዬ አገኘሁት ያለው መልስ ይሄን ይመስላል ;
” ሴትዮ የኤች አይ ቬ እና የአኔሚያ በሸታ እንዳለባትና የኮሮና ምልክት ስለታየባት ደሟ ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ ሆስፒታሉ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ነው ።ለጥንቃቄም ሲባል ከበሽተኛዋ ጋር ንክኪ የነበራቸውወደ 22 የሚጠጉ ነርሶች ፣ዶክተሮች እና አስታማሚዎች መለያ ክፍል ውስጥ ገብተዋል።”
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለፊደል ፖስት እንዲህ አይነት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚነገር ነገር በጤና ሚኒስቴር እና በኢንስቲትዩት ብቻ እንደሚገለፅ ገልፆ ህብረተሰቡ በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይወናበድ ተናግሯል።
Via fidelpost.com

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በህንድ ቼናይ አንድ ፖሊስ የኮሮና ቫይረስ ቅርፅ ያለውን ሄልሜት በማድረግ በጎዳና ላይ የውጡትን አሽከርካሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ እየነገራቸው ይገኛል። ግለሰቡ ይህን ያረገበትን ምክንያት ሲናገር ግንዛቤ ለማስጨበጥና በሀገሪቱ የታወጀውን የመንግስትን ከቤታችሁ አትውጡ ጥሪ የሚተላለፉትን ለማስፈራራት እንደሆነ ተናግሯል።
ምንጭ: አጃንስ ፍራንስ ፕረስ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: አጃንስ ፍራንስ ፕረስ
@YeneTube @FikerAssefa
አርማ ወርሃንሰን ኮሮና ቫይረስ መመርመር ሊጀምር ነው ።
በአዲስ አበባ የሚገኘው አርማ ወርሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በነገው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ሊጀምር ነው፡፡
አሁን ላይ በሃገሪቱ በብቸኝነት ምርመራ ከሚያደርገው ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተጨማሪ አርማ ወርሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ እንደሚጀምር የኢንስቲትዩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደጅይጥኑ ሙላው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ለምርመራው የሚሆኑ የላብራቶሪ ቁሳቁሶች እና የሰው ሃይል መሟላታቸውንም ተናግረዋል፡፡
ምርመራውም እንደ ሃገር ያለውን የመመርመሪያ ቦታ ለማስፋት ያለመ እንደሆነ ደጅ ይጥኑ ሙላው ተናግረዋል፡፡
Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa

#ኢትዮጵያ_በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 ደረሱ
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መገኘታቸውን ለማሳወቅ የተሰጠ መግለጫ
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
የመጀመሪያዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች፡፡ ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በመጋቢት 19፣2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡
ሁለተኛ እና ሶስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡
ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
Via:- Ministry of Health

አዳማ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር የዛሬዎቹን ሁለት ጨምሮ በአጠቃላይ ሶስት ደርሷል።
ከሁለት ቀን በፊት አንድ የ61 አመት የአዳማ ከተማ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኗ ይታወሳል።
ዛሬ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡ ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AdamaLockdown አዳማ ከቤት መውጣት ተከለከለ !!
በአዳማ ከተማ ባሉ ጎዳናዎች "ከአሁን ሰዐት ጀምሮ በከተማው ውስጥ አንገብጋቢ ካልሆነ በስተቀር #እንቅስቃሴ ማድረግ ተከልክሏል" የሚሉ ማስታወቂያዎች በአማርኛ እና በኦሮምኛ በትልልቅ ድምፅ ማጉያዎች እየተነገሩ መሆናቸው ከአዲስ ማለዳ ድረገፅ ላይ ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa
በአዳማ ከተማ ባሉ ጎዳናዎች "ከአሁን ሰዐት ጀምሮ በከተማው ውስጥ አንገብጋቢ ካልሆነ በስተቀር #እንቅስቃሴ ማድረግ ተከልክሏል" የሚሉ ማስታወቂያዎች በአማርኛ እና በኦሮምኛ በትልልቅ ድምፅ ማጉያዎች እየተነገሩ መሆናቸው ከአዲስ ማለዳ ድረገፅ ላይ ተመልክተናል።
@Yenetube @Fikerassefa
#ድሬዳዋ_ዩንቨርስቲ
ከጅቡቲ ወደ ኢትዮዽያ የገቡ 1,500 ሰዎች በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ከ10,000 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ቦታዎችን ማዘጋጀቱንም አስታውቋል።

የመጨረሻው የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሪፖርት ከተደረገ 40 ቀናት ያለፉ ሲሆን በሽተኛው ድኖ ከሆስፒታል ከወጣ 25 ቀን ሆኖታል። ይህንንም ተከትሎ በሚቀጥሉት 15 ቀናት አዲስ ተጠቂ ሪፖርት ካልተደረገ የበሽታው "Outbreak" እንዳበቃ ሊታወጅ እንደሚችል የWHO ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ በሽታ(ኮቪድ-19) አስመልክቶ ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት በእነዚህ የነፃ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ።
#MoHE
#EPHI
@YeneTube @FikerAssefa
#MoHE
#EPHI
@YeneTube @FikerAssefa
ቤት እንሁን ህይወት እናድን!!
STAYHOMESAVELIVES
ጊዜው አሁን ነው የጤና ባለሙያዎች እንስማቸው #ቤት_እንሁን_ህይወት_እናድን። ለኮሮና ቫይረስ ትክክለኛው መድኃኒት ከቤት አለመውጣት ነው።
ይህንን ፕሮፋይል ፒክቸራችሁ በማድረግ ዘመቻውን መቀላቀል ትችላላችሁ።
#እኛ_ቤት_ነን_እናንተስ?
ቤት እንሁን ህይወት እናድን!!
STAYHOMESAVELIVES!!
Graphics :- ስዩመ እግዚአብሔር