YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ አበይት የመረጃ ምንጮች የጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መሆናቸውን ጠቅሶ ከሀሰት መረጃ ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል።

በዚህ ፈታኝ ወቅት በሕዝብ ጤናና ደኅንነት ላይ በልዩ ልዩ መንገድ ሽብር የሚነዙ አካላት ላይ የሕግ አስከባሪ አካላት ሕግ የማስከበር ተግባራቸውን በጥብቅ እንዲያከናውኑ የታዘዙ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአሰላ ከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ!

በአሰላ ከተማ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ የታክሲ እና የባጃጅ የትራንስፖርት አገልግሎት መታገዱን የከተማው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።በእገዳው መሠረት ባጃጆች፣ ከገጠር ወደ ከተማዋ የሚመላለሱ ታክሲዎች እና ሞተር ሳይክሎች እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገዋል። ከሌሎች ወረዳዎች እና ዞኖች የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ግን ለጊዜው የሰዎችን አካላዊ ርቀት በጠበቀ መልኩ ለተጓዦች አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ሕዝቡ መንግሥት የሚያወጣውን ሕግጋት እንዲያከብር እና የሐኪሞችን ምክር ተግባራዊ ማድረግ አለበትም ተብሏል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ወደ 80 አገራት ያደርግ የነበረውን በረራ ከዛሬ ጀምሮ ማቋረጡን አስታወቀ።

@YeneTube @FikerAssefa
ትላንት ሲያሸብሩን የነበሩን ዜናዎች የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታል መረጃዎቹ ውሸት መሆናቸውን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታልን የተሰጠው መግለጫ በስክሪንሹት ላይ አያይዘናል።

@Yenetube @Fikerassefa
የመቱ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት የማቋረጥ ውሳኔውን ተቀላቅሏል፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ቀልቤሳ ቶሌራ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ ውሳኔውን አጋርተዋል። ውሳኔው ከነገ ጠዋት የሚጀምር ሲሆን ወደ ከተማው መግባት እንዲሁም መውጣትም ክልከላ ተደርጎበታል ።

Via:- addismaleda
@Yenetube @Fikerassefa
ተጨማሪ 2 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተነገረ። አጠቃላይ ቁጥሩም 21 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 21 ደርሰዋል።
ከመሸ 2 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መኖራቸው ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ታማሚዎቹ :- ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 38 አመት ወንድ እና 35 ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው። የጎዞ ታሪካቸው ሁለቱም በተለያየ ቀናት ዱባይ የተጓዙ መሆናቸው ተነግሯል።

- ሁለት ታማሚዎች ሙሉ ለመሉ አገግመዋል ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ገብተዋል።

@YeneTube @fikerassefa
በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ በናዕዴር አዴት አንድ ወጣት በፖሊስ መገደሉን ለቢቢሲ ትግረኛ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር የማነ ኪዳነማሪያም አረጋግጠዋል።

ወጣቱ የተገደለው ፖሊስ መጠጥ ቤት የነበሩ ሰዎችን በሚበትንበት ወቅት ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ በኮሮና መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 12 መድረሱን የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ገለጸ።ባለፉት 3 ቀናት በተደረገ ምርመራ በረራ ከመከልከሉ በፊት ወደ ኤርትራ የተጓዙ 6 ሰዎች በተሕዋሲው መያዛቸው ተረጋግጧል ብሏል።ከነዚህ ውስጥ4ቱ ሴቶች ናቸው።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና

ከዛሬ ጀምሮ ወደ አማራ ክልል የሚገባ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንደማይኖር የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

ከአገሪቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል የሚገቡ ማንኛውም አይነት የህዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ መጋቢት 20 /2012 ዓ.ም ከለሊቱ 6፡00 ጀምሮ ወደ ክልሉ መግባት የማይችሉ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት የኮረና ወረርሽኝ መካላከል ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

#ከዩኒቪርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸውው እየመጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ግን #በልዩ_ሁኔታ የሚገቡ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የገለጸ ሲሆን ይህ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆንም ለጽጥታ አስከባሪ ሃይል ተዕዛዝ ተሰጥቷል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ታማኝ በየነ ያስጀመረው በጎፈንድ ሚ ገቢ ማሰባሰቢያ 24 ሰዐት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 201ሺ ዶላር አልፏል። ወዳጆቻችን የምትችሉት ገንዘብ ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እርዳታ አድርጉ።
https://www.gofundme.com/f/ethiopiansagainstcoronavirus
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር የበለጠ ለመቆጣጠር ተጨማሪ ወታደሮችን ማሰማራቷን የገዳሪፍ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ተናገሩ።
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ 3 ደረጃዎች ይኖሩታል::

ቅድመ ኮሮና - የመከላከል ጊዜ
ሁነተ ኮሮና - የመጥለቅለቅ ጊዜ
ድህረ ኮሮና - የማገገሚያ ጊዜ!

አሁን ከበረታን ክፉዎቹ ደረጃዎች አይጎዱንም:: አሁንም ስርጭቱን ለመግታት #ጊዜውአልመሸም! #covid19ethiopia በርቱ!

- ዶክተር ምህረት ደበበ
@Yenetube @Fikerassefa
በጀርመኗ ኸስ ክልል የገንዘብ ሚኒስትር የነበረው ቶማስ ሸፈር ኮሮና ቫይረስ ባመጣው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጨንቆ እራሱን ባለፈው ቅዳሜ አጥፍቶ አንደተገኘ አልጀዚራ ዘግቧል።

የባቡር መንገድ ላይ ሞቶ የተገኘው ሸፈር ጀርመን በኮሮና ቫይረስ ካጋጠማት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዴት መውጣት እንዳለባት እያለ ደጋግሞ ይጨነቅ ነበር ሲል ዘገባው ጠቅሷል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
አስፈላጊ ነፃ ቁጥሮች ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት የነፃ ስልክ ቁጥሮችን ይደውሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ ደርሷል!

➡️በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 723,700

➡️ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151,991

➡️በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች 34,005

➡️በቻይና 31 አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል

➡️በኒውዮርክ 1 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።

ምንጭ: አልጃዚራ/ጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከውጭ ገብተው በለይቶ ማቆያ ለሚቆዩ ዜጎች የሚሆኑ የህክምና አልጋዎችን ተረከበ፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከውጭ ገብተው በለይቶ ማቆያ ለ 14 ቀናት ለሚቆዩ ዜጎች የሚሆኑ 282 የህክምና አልጋዎችን በዛሬ ዕለት ተረክቧል፡፡የአልጋ ምርቱ ባሳለፍነው ሳምንት ሮብ የተጀመረ ሲሆን 1.90 በ90 ሣ.ሜ የሆኑና መታጠብ የሚችሉ አልጋዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡የጎፋ ኢንደስትሪያል ፓርክ 303 ሺ ብር ወጪ የተደረገባቸው 100 አልጋዎችን በዛሬው እለት ማስረከቡ ነው የተገለጸው፡፡አልጋዎቹ ከውጭ ሀገር ቢገቡ 10ሺ ብር የሚያወጡ ሲሆን ዛሬ የተረከቡት አልጋዎች አንዱ በ3345 ብር ወጪ የተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡አልጋዎቹ በአጠቃላይ 3.3 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይ ቀናት ምርቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በአጠቃላይ 1000 አልጋዎችን እንደሚረከብ እና እንደሚያከፋፍል ተገልጿል፡፡

Via Addis TV
@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ ባንክ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችለውን የንግድ ሂደት መስተጓጎል ከግምት በማስገባት የሚከተሉትን የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡

1. ከውጪ አገር ምርቶችን የሚያስገቡ ደንበኞቻችን ለኤልሲ ማራዘሚያ ይከፍሉ የነበረው ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ተነስቱዋል፡፡

2. የብድር መመለሻ የመክፈያ ጊዜ ደንበኞቻችን እንዲራዘምላቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ ይከፈል የነበረው ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ተነስቱዋል፡፡

3. ደንበኞቻችን ከኤቲኤም ገንዘብ ሲያወጡ ይከፍሉ የነበረውን የኮሚሽን ክፍያ ተነስቶ ነጻ ሆኗል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ ቤተመንግስት ከበጀቱ ላይ አምስት ሚሊዮን ብር ለኮሮኖ መከላከል ሰጠ፡፡

ክብርት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴም የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት ወስነዋል::

ከድረ ገፃቸው የተገኘ ሙሉ መግለጫ፡-

በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት ለመቋቋም የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል ፡፡ ለዚህም ስኬታማነት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ጽ/ቤትም የበጀት ዓመቱ ለመጠናቀቅ በሚቀሩት ሶስት ወራት ውስጥ ለሚኖሩት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ወጪ በማብቃቃትና በቁጠባ በመጠቀም ከተመደበለት መደበኛ በጀት የሚቀነስ የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ አስታውቋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ክብርት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት ወስነዋል::

የፕሬዝደንት ጽ/ቤት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው እንደ ሀገር የገጠመን ችግር ለመቋቋም የምንችለው ፤ በጋራ እና በጽናት በመቆም እንደሆነ በጽኑ ስለሚገነዘብ ነው ፡፡ በግልም ሆነ በተቋም ደረጃ ሁላችንም ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪ እያቀረበ በቀጣይም የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል::

@Yenetube @Fikerassefa