YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኢትዮጵያ_በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 ደረሱ

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ_19) በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መገኘታቸውን ለማሳወቅ የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡

የመጀመሪያዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስትሆን መጋቢት 8፣ 2012 ከብራሰልስ ቤልጅየም እንዲሁም መጋቢት 10፣2012 ዓ.ም ወደ ካሜሮን የጉዞ ታሪክ የነበራት ሲሆን ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ አድርጋለች፡፡ ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በመጋቢት 19፣2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል፡፡

ሁለተኛ እና ሶስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ከዚህ በፊት በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር፡፡

ግለሰቦቹ በመጋቢት 19፣2020 ዓ.ም በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

Via:- Ministry of Health
@Yenetube @Fikerassefa