YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዋልታ ይህንን ዘገባ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ማስፈሩን ተከትሎ እኛም ይህንኑ መረጃ አድርሰንላችሁ ነበር፣ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ዜናውን ማጥፋቱን አስተውለን እኛም ከገፃችን ላይ አስወግደነዋል!

@YeneTube @FikerAssefa
የዋልታ ዘገባ #ትክክል_እንዳልሆነ SMN የሚሰሩ ባልደረባዎቻችን ነግረውናል፣ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሰጠው ሙሉ መግለጫ ከደቂቃዎች ብኃላ በSMN እንደሚተላለፈ ነግረውናል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Misinformation_Alert

ዋልታ ኢንፎርሜሽን ዛሬ ጠዋት በሰራው ዘገባ የሃዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ የከተማው ነዋሪ 90 በመቶ ሻፌታን መምረጡ ተረጋገጠ በሚል የሰራው ዘገባ የተሳሳተ መረጃ ሲሆን ምክትል ከንቲባው የመራጮችን ተሳትፎንና ጸጥታን እንጂ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት የሚመለከት ምንም አይነት መግለጫ አልሰጡም፡፡የምርጫ ውጤትን ማሳወቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሃላፊነት ብቻ መሆኑ እየታወቀ የሚዲያ አካላት የምርጫን አይነት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ዜናዎች ሲሰሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ትኩረት እንዲያደርጉ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

-ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
ዋልታ ይቅርታ ጠይቋል!


ይቅርታ ስለመጠየቅ
በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ የሀዋሳ ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምጽ ውጤት ከ90 በመቶ በላይ መራጭ ሻፌታን መምረጡን ማረጋገጣቸውን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አስታወቁ በሚል የተዘገበው መረጃ ስህተት መሆኑን እየገለጽን፤ ለዚህም ዋልታ ይቅርታ ይጠይቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Jimma ማስታወቂያ

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ቅደመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተከሰተዉ ችግር ጋር ተያይዞ በተፈጠረዉ አለመረጋጋት በዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመማር ማስተማር ሂደት ለተወሰኑ ቀናት መቋረጡ ይታወሳል፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን አመራር፣ አካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች በተለያዩ ደረጃዎች ከተለያዩ አካላት ጋር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታ እንዲፈጠር ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

የዩኒቨርሲቲያችን ሴኔት ዛሬ በ11/03/2012 ባደረገዉ ሁለተኛዉ አስቸኳይ ስብሰባ አሁናዊ ሁኔታዉን በመገምገም ትምህርት ለማስጀመር አስቻይ ሁኔታዎች በመፈጠራቸዉ ሰኞ 15/03/2012 ዓ.ም. ትምህርት እንዲጀመር ወስኗል፡፡

በመሆኑም፣ ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ከዓርብ ህዳር 12 እስከ 14/ 2012 ዓ.ም. በየካምፓሶቻችሁ ዳግም-ምዝገባ (Re-registration) በማካሄድ ሰኞ 15/03/2012 ዓ.ም. ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን፡፡

Via:- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@Yenetube @Fikerassefa
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ የመንግሥት ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ!

በምዕራብ ወለጋ ዞን አንድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣን መንገድ ላይ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ተገደሉ።ትናንት [ረቡዕ] በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ውስጥ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቶላ ገዳ ለሥራ ጉዳይ ወደ ምዕራብ ወለጋ ቄለም ወለጋ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት፣ ላሎ አሳቢ ተብሎ በሚታወቀው ወረዳ ውስጥ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋግብለው ብሏል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤሊያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህ ግድያ የተፈጸመው ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ጋራ ቶሬ በሚባል ቦታ ላይ ረቡዕ ዕለት ጠዋት አምስት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል። አስተዳዳሪው ጨምረው እንደተናገሩት አቶ ቶላን የገደሉት ታጣቂዎች እየተጓዙበት በነበረው መኪና ላይ ከግራና ከቀኝ ሆነው በከፈቱት ተኩስ በመኪናው ውስጥ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞችን ኢላማ አድርገው እንደሆነ አመልክተዋል።በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት አቶ ቶላ ገዳ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ እንደሆኑ አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልጸዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሲዳማ ህዝበ ወሳኔ የድምፅ አሰጣጥ በሀዋሳ ከተማ የነበረው ሂደት በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን አምና በተከሰከሰበት ስፍራ የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆም ነው ተባለ፡፡

የመታሰቢያ ሐውልቱ በሚቆምበት ሁኔታ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቦይንግ ኩባንያ መነጋገራቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ተናግረዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የተናገሩት ሰሞኑን በፈረንሳይ በተካሄደው ፎር ፈን ግሎባል ፎረም ላይ ተገኝተው ነው፡፡

ባለፈው አመት መጋቢት አንድ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በቢሾፍቱ አቅራቢያ ቱሉ ፈራ ተከስክሶ 157 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ይታወሳል፡፡

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ የመታሰቢያ ሐውልት ለማቆም ከመታሰቡ በተጨማሪ ለአካባቢው ነዋሪዎች አንደ ሆስፒታል የመሰሉ የጤና ተቋማትና መንገድ ለመገንባት መወጠኑንም ሰምተናል፡፡

Via:- sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ውጤቱ #የሲዳማ ዞንን ወደ ክልልነት የሚመራ ከሆነ ከዚህ በኋላ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ #ደኢሕዴን ጋር ግንኙነት አይኖረንም ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
አሁን የተለያዩ መልእክቶች ከስድስት ኪሎ ተማሪዎች ደርሰውኛል። በግቢው መጠነኛ አለመረጋጋት ነበር።

#አሁን_ተራጋግቷል

ተኩስ ነበር ተብሎ አንድ በተማሪ የቀረብልኝ ሪፓርት ውሸት ነው ብለውኛል።

Via:- Tesfay getnet
@Yenetube @Fikerassefa
አዋሽ ባንክ ዛሬ ኅዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ቤተል አካባቢ በመክፈት ያስመርቃል፡፡

በአሁኑ ወቅት 11 ባንኮች ከወለድ ነፃ ባንክ የባንክ አገልግሎቶችን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡የወለድ አልባ የባንክ አገልግሎትን ለማስፋፋትና እስካሁን በእምነቱ ምክንያት ወደ ባንክ ከመምጣት የተቆጠቡ የኅብረተሰቡን ክፍል ለማዳረስ፣ ከመስኮትና ከቅርንጫፍ ባሻገር ራሱን የቻለ ባንክም ወደ ማቋቋም ተገብቷል፡፡ራሱን የቻለ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆኑ ሲነገርላቸው ከነበሩት ውስጥ ዘምዘምና ሒጅራ ባንኮች ወደ ሥራ የሚያስገባቸውን ካፒታል በማሟላት ወደ ሥራ ለመግባት እየተዘጋጁ መሆኑ ይታወቃል፡፡ዘምዘምና ሒጅራ ባንኮች በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እስካሁን ባለው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች አሥራ አንዱ ባንኮች ከ45 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ መስብሰባቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ
@YeneTube @FikerAssefa
#Update አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቅድም የተዘጉት በሮች አሁን ሁሉም ተከፍተዋል ተማሪ መውጣት መግባት ጀምሯል የተጎዳ ሰው የለም ሁሉም ፌደራሎች ከግቢ ወጥተዋል ግቢ ውስጥ ተማሪ ብቻ ነው ያለው ሙሉ ለመሉ ወደ ነበረበት ተመልሷል ማለት ይቻላል።

ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች አትጨነቁ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ሰላም ነው።

#አማን_AAU
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ካርል አደባባይ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ13 ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ።አደጋው የደረሰው ዛሬ ረፋድ 5 ሰዓት ገደማ ከፒያሳ አትክልት ተራ 13 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ በልደታ አዲሱ አስፓልት ወደ ካርል አደባባይ መሄጃ ፍርድቤቱን ወረድ እንዳለ ፍሬን በጥሶ ከቆመ አይሱዙ ጋር በመጋጨቱ ነው።በአደጋውም ሹፌሩን ጨምሮ ሁሉም ተሳፋሪዎች ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል።

(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡጁምቡራ በአሸባሪነት በተጠረጠረ ግለሰብ ችግር ገጠመው!

ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቡጁምቡራ ውስጥ ካረፈ በኋላ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቡሩንዲ ባለስልጣናት አረጋገጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን አንድ ተሳፋሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ አውሮፕላኑ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም መደረጉም ተነግሯል።አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩ የተከሰተው ተብሏል። ቢቢሲ ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ለማረጋገጥ እንደቻለው የተባለው ችግር እንዳጋጠመና ምንም ጉዳት ሳይደርስ ቡጁምቡራ አርፏል።

ቢቢሲ ክስተቱን በተመለከተ ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል ደውሎ ጥያቄ ቢያቀርብም የተሰጠው ምላሽ ስለጉዳዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ እንደሚሰጥ ብቻ ነው።ነገር ግን መረጃ የተጠየቁት የአየር ባልደረባ ስለክስተቱ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበው ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ለመስጠት አልፈቀዱም።ክስተቱን በተመለከተ ለቢቢሲ ያረጋገጡት የአየር መንገዱ ባልደረባ እንደሚሉት ከሆነ "አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ወታደራዊ ክፍል ውስጥ እንዲያርፍ ተደርጎ ችግሩን የፈጠረው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል።"

ነገር ግን በአውሮፕላኑ ውስጥ ያጋጠመውን ችግር የፈጠረው ግለሰብ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።ግለሰቡ ፈንጂ መያዙን በመግለጽ አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው ባስፈራራበት ወቅት ከፍተኛ ፍርሃት በተሳፋሪዎቹ ዘንድ መፈጠሩን ቢቢሲ ያነጋገራቸው መንገደኞች ገልጸዋል።የቡሩንዲ የደህንት ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ ላይ ክስተቱን አረጋግጦ "በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ተሳፍሮ የነበረ ተጠርጣሪ ሽብርተኛ ቡጁምቡራ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል" ብሏል።

ክስተቱን በተመለከተ ቢቢሲ ያገኘውና እስካሁን በሁለተኛ ወገን ያልተረጋገጠው መረጃ እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በአውሮፕላኑ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው በመግለጽ በማስፈራራቱ ችግሩ መከሰቱ አመልክቷል።ከዚህ አንጻር ለቢቢሲ የተናገሩት የአየር መንገዱ ባልደረባ ክስተቱ በሰላም መጠናቀቁንና በተሳፋሪዎችም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል። በእርግጥ ግለሰቡ እንዳለው የሚፈነዳ ነገር ይዞ እንደነበረ የሚያመለክት ነገር ያልተገኘ ሲሆን፤ ለፈጸመው ድርጊትም ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን ምንም የታወቀ ነገር የለም።

አውሮፕላኑ ምን ያህል ተጓዦችን አሳፍሮ እንደነበረና ችግሩ የተከሰተው ለማረፍ በተቃረበበት ይሁን ወይም በጉዞ ላይ እንዳለ አልታወቀም።ክስተቱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የወታደራዊ አውሮፕላኖች ማቆሚያ ክፍል እንዲቆይ እንደተደረገ ምንጮች ከቡጁምቡራ አመልክተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥 ጫማ ይሸምቱ

PUMA (GV SPECIAL)

📎ORIGINAL

Size 40-41-42-43
📌 Made in Vietnam
📌 Price 2200 birr
📌 With delivery
📌 በ 5 አይነት ከለር

📞 0912732493
@Hkaeg
Forwarded from YeneTube
🤜🏾መኪናዎትን ከሌባ ለመጠበቅ የሚረዳ 🚔🚔🚔 ኣዲስ ምርት ኣስመጥተናል🚔🚔🚔
🤜🏾•ሰሞኑን እየተበራከተ የመጣው የመኪናዎች ስርቆት ሀሳብ ሆኖቦታል እንግዲያውስ ሀሳብ አይግባዎ አስተማማኝ መሪ መቆለፊያ አምጥተንሎታል
🤜🏾የመኪናዎን መሪ ጥርቅም ኣርጎ በመቆለፍ ቁልፍ የያዝን ሌባ ጨምሮ መሪውን እንዳያዞረው በማድርግ መኪናውን ክስርቆት ይጠብቀዋል::
+251912894364

• Made of hardened iron material to resist cutting and durable in using.
• Comes with anti-theft security lock and 2 keys.
• Can be adjustable to fit for most steering wheels.
• Highly visible deterrent, can frighten the thieves to avoid being stolen.
• Weight 2kg
ለበለጠ መረጃ እና ለተለያዩ አዳዲስ እቃዎች ቻናላቸንን ጆይን ያድርጉ
@ZenachBrands
የኢህአዴግ ምክር ቤት የፓርቲዎቹን ውህደት አፀደቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመራለትን የፓርቲውን ውህድ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ፡፡

Via :- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ መማር ማስተማር ለማይጀምሩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀጣዩን ርምጃየን አሳውቃለሁ- ብሏል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር፡፡ እስካሁን ከ100 በላይ በሁከት የተጠረጠሩ ተማሪዎች ተይዘዋል፡፡ ብዙ የባንክ ደብተርና የስልክ ሲሞችም ተገኝተውባቸዋል፡፡ ባንዳንድ ተቋማት ተማሪዎችን በስቃይ ያገቱ፣ ግቢ እንዳያድሩ፣ በማንነታቸው እንዲሸማቀቁ ያደረጉና የሐሰት ወሬ ያሰራጩ አሉ፡፡ ምርመራው በ2 ቀናት እንደሚገለጽ ኢቢሲን ጠቅሶ ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢሕአዴግ ምክር ቤት ዛሬ የፖርቲውን ውሕደት አጽድቋል። በሥራ አስፈጻሚው የጸደቀው የፓርቲው ፕሮግራምና በምክር ቤቱ የጸደቀው የፓርቲው ውሕደት፣ ኃይልን አሰባስቦ በመንቀሳቀስ የጋራ ራእይን ለማሳካት ወሳኝ ርምጃ ነው። በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ አማካኝነት ሁሉም የታላቋ ኢትዮጵያ ዜጎች የሚሳተፉበት ጠንካራ፣ አካታችና እውነተኛ የፌደራል ሥርዓት ለመፍጠር ቆርጠን ተነሥተናል። ጸንተንም እንታገላለን።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ
@YeneTube @FikerAssefa
ለወንዶች!!!!
የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን
RJ FASHION
ለውድ ደንበኞቹ ጥራት ያላቸውን የወንዶች ብራንድ እና አዲስ Style
➡️ሹራቦች
➡️ጃኬቶች
➡️ቱታዎች
➡️ጫማዎችን
በቅናሽ ዋጋ አቅርበናል:
ሾው ሩም አድራሻ:
ገርጂ መብራት ሀይል (ዊዝደም ህንፃ ፊት ለፊት)
ስልክ:-+251900628132
:-011-6296465
የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለውን ሊነክ በመጫን ያገኙናል
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA