YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የሲዳማ ብሔር #የሀገር ሽማግሌዎች በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው #ግጭት ሕይወታቸውን ያጡ #የወላይታ ብሔር ተወላጆች ቤተሰብ ላይ ለቅሶ በመድረስ አጽናንተዋል፡፡

ረጅም ዘመናትን የዘለቀው የሁለቱ ህዝቦች ትስስር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሟች ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡
የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሐዋሳና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት ልጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በሞት ለተለዩ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በደረሱበት ወቅት ከሟች ቤተሰቦች አንዳንዶቹ እንደተገለጹት ሁለቱ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳስረው፣ ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡
በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚቀሰቅሱ አካላት ሊገስጹ ይገባል ብለዋል፡፡

በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት በመጥፋቱ እጅግ ማዘናቸውን የሟች ቤተሰቦች ገልፀው እርቀ ሰላም እንዲወርድ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፣ አስታራቂ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደተናገሩት የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው አብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡
የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትስስር በአንድ መድረክ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተከሰተው ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ከመጥፋቱም በላይ በሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ በርካታ ንብረት የወደመበት እና በርካታ ሰው የተፈናቀለበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ጥፋት ሁለቱንም ህዝቦች የማይወክል ጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ሆን ብለው ግጭቱ የብሔር ይዘት እንዲኖረውና የህዝቦቹ ትስስር እንዲሻክር ያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት በወላይታ ሶዶ በመገኘት ወገኖቻቸውን በሞት ላሰጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ ለመድረስና ለማጽናናት የመጡበት ዋናው ዓላማ የሁለቱ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸውንና አብሮነታቸውን ለማደስ ነው፡፡

የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ረጅም ዘመን የቆየው አንድነትና አብሮነት ቀጣይነት አንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የሀገር ሽማግሌዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱ ህዝቦች አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የሟች ቤተሰቦችን የማጽናናት ሥራ በባህላዊ የዕርቅ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በነገው ዕለት ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም የወላይታ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሐዋሳ በማቅናት በሲዳማ ብሔር በኩል በግጭቱ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በመድረስ እንደሚያጽናኑ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ:- የወላይታ ዞን መንግስት ኮምንኬሽን
@YeneTube @Fikerassefa
#የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የደኢህዴን አመራሮች #በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የፓርቲው ስብሰባ ረግጠው ስለመውጣታቸው በሲዳማ ብሔር ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ድረ ገጾች ዘግበዋል።

አመራሮቹ ስብሰባውን አቋርጠው የወጡት ደኢህዴን ለመወያያነት ያዘጋጀው ሰነድ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ የሚጻረር ሆኖ ስላገኙት እንደሆነ ተገልጿል።
@YeneTube @FikerAssefa
የሲዳማ ህዝብ ከዓመታት በፊት ያቀረበዉ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዘግይቶም ቢሆን ምላሽ ማግኘት በመጀመሩ መላው #የሲዳማ ብሔር #እንዲረጋጋ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ #ሲአን ጠየቀ። የንቅናቄው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደስላኝ ሜሳ፣ «ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ተቀብሎ ህዝበ ውሳኔ
ለማድረግ መዘጋጀቱን አረጋግጧል።» ብለዋል።

በዚሕም ምክንያት የሲዳማ ሕዝብ የህዝበ ውሳኔውን ሂደት እንዲጠባበቅ ንቅናቄው ጥሪ ማስተላለፉን አቶ ደሳላኝ ለሐዋሳዉ ዘጋቢያችን ለሸዋንግዛዉ ወጋየሁ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አመልከተዋል። ይሁንና አቶ ደሳለኝ እንደሚሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ዉሳኔዉ ሊደረግ ከሚገባዉን ቀን #አዘግይቷል ብሎ ንቅንቄያቸዉ እንደሚያምን ጠቅሰዉ ለዚሕም ቦርዱ፣ ሕዝቡን #ይቅርታ_መጠየቅ_ይገባዋል_ብለዋል

በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ( ሲአን ) ፣ የሲዳማ ሀድቾ ዴሞክራሲያዊ ደርጅት ( ሲሀዴድ ) እና የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ሲብዴፓ )፣ የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የሚያስችለው የህዝበ ውሳኔ የሚደረግበትን ቀን መንግሥት በአምስት ቀናት ዉስጥ ይፋ እንዲያድርግ ባለፈዉ ሳምንት መጀመሪያ ጠይቀዉ ነበር። የተቀሩት ሁለቱ ፓርቲዎች አስከ አሁን ሥለ ጉዳዩ በይፋ ያሉት ነገር የለም።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመሩት የሲአን አንጃ እንደሚለዉ ባለፈዉ ኃምሌ 11 በተከሰተዉ ግጭት ሰበብ በርካታ ሰዎች ተይዘዉ ታስረዋል።

አንጃዉ እንደሚለዉ አፈሳና እስራቱ አሁንም በተለያዩ ወረዳዎች እንደቀጠለ ነዉ። #የሲዳማ_አርነት_ንቅናቄ (ሲአን) አንደኛዉ አንጃ የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች በጅምላ ታፍሰዉ እየታሰሩ ነዉ በማለት እርምጃዉን አቀወገዘ።አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመሩት የሲአን አንጃ እንደሚለዉ ባለፈዉ ኃምሌ 11 በተከሰተዉ ግጭት ሰበብ በርካታ ሰዎች ተይዘዉ ታስረዋል።አንጃዉ እንደሚለዉ አፈሳና እስራቱ አሁንም በተለያዩ ወረዳዎች እንደቀጠለ ነዉ።አንጃዉ በጅምላ ታሰሩ ያላቸዉን ሰዎች ቁጥር፣ የታሰሩበትን ትክክለኛ ቀንና ሥፍራና ግን አልገለፀም።ዶይቼ ወሌ ሥለዉግዘቱ፣ የሲዳማ ዞንና የደቡብ ክልል ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካለትም።

ምንጭ: ዶይቸ ወሌ
@YeneTube @FikerAssefa
#የሲዳማ የክልልነት ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ቀን ወደ ህዳር 10 ተዘዋወረ


ከዚህ ቀደም ቦርዱ የህዝበ ውሳኔው የድምፅ አሰጣጥ ህዳር 03 2012 ዓ.ም ይካሄዳል ብሎ የነበረ ሲሆን፥ በዛሬው እለት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ግን ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ቀን ሽግሽግ መደረጉን አስታውቋል።

ተጨማሪ ⬇️
https://telegra.ph/Yenetube-10-16
የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ውጤቱ #የሲዳማ ዞንን ወደ ክልልነት የሚመራ ከሆነ ከዚህ በኋላ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ #ደኢሕዴን ጋር ግንኙነት አይኖረንም ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa