YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሲዳማ ዞን እና በሀዋሳ ከተማ የሚደረገው ሪፈረንደም ድምፅ ለመስጠት ሀዋሳ ከተማ ጨምሮ ሲዳማ ዞን ላይ ትላልቅ ስልፎች ተስተውለዋል። ድምፅ መስጠት ምንም እንኳን ከ12 ሰዐት ጀምሮ የመስጠት የጀመረ ቢሆንም ከትላንት ለሊት ጀምሮ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ተገኘተዋል።

ነዋሪዎች አሁን ላይ ድምፅ እየሰጡ ይገኛሉ !!
@YeneTube @Fikerassefa
"የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ዘመናት ይህን ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ብዙ ዋጋም ከፍሏል፡፡

የሀገሪቱ ህገ መንግስት ያጎናጸፈውን መብት ባለፉት ጊዜያት የሲዳማ ህዝብ ተነፍጎ ነው የቆየው፡፡ የራሱን እድል በራሱ ለመወሰን ድምጽ የመስጠት እድል ሳያገኝ ነው የቆየው፡፡ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አሁን በደረስንበት የለውጥ ምዕራፍ እንደ አንድ የለውጡ ስኬት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ያጎናጸፈው መብት ተተግብሮ ዜጎች የፈለጉትን በነጻነት የሚመርጡበት እድል መፈጠሩ ለእኔ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ እንደ መንግስታችንም ይህ ለመንግስታችን ትልቅ ስኬት ነው፡፡"

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በታቦር ክፍለ ከተማ በሂጣታ ቀበሌ የህይወት ብርሃን ምርጫ ጣቢያ ላይ ድምጽ በሰጡበት ወቅት የተናገሩት።
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማ የሀገር ውስጥ አሰሪ እና ሰራተኛን የሚያገኛኙ ኤጀንሲዎች እና ደላሎች ህግን ተከትለው እንደማይሰሩ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ አለምጸሀይ ጳውሎስ በሀገር ውስጥ አሰሪ እና ሰራተኛን በማገናኘት አገልግሎት የሚሰጡ ኤጀንሲዎች እና ደላሎች እንቅስቃሴን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ መራጮችን ሲያጭበረብርና ሲያታልል የነበረ አንድ ግለሰብ መያዙን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ቦርዱ ከህዝብ በደረሰ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቆማ እንደደረሰው እንዲሁም የቦርዱ ሰራተኞች እንዳጣሩት መሰረት ተስፋዬ ዳንጊሶ የተባሉ ግለሰብ፣ የምርጫ ጣቢያው ውስጥ ሰልፍ የማስተባበር ስራ በመስራት ሽፋን፣ መራጮችን ወደሚስጥር ክፍል ተከትሎ በመግባት በማስፈራራት፣ የሚመርጡትን ምልክት በማየት፣ ምልክቱን እንዲቀይሩ በመንገር ከዚያም ስማቸው ተጣርቶ አቤቱታ ሲቀርብ ስማቸውን በመደበቅ የምርጫ ሂደቱን ሲያስተጓሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብሏል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌደራል ፓሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና ማጣራት እንዲደረግባቸው ማድረጉን ቦርዱ አስታውቋል፡፡
ከዚህ ውጪ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የታይም መጽሔት የአመቱ ሰው የመጨረሻ እጩዎች ዝርዝር ለመለየት ከአንባቢያን አስተያየት እየተቀበለ ነው፡፡
በአሜሪካን ሀገር የሚታተመው ታይም መጽሔት አርታኢያን በፈረንጆቹ 2019 የአመቱ ሰው የመጨረሻ እጩዎችን ለመለየት ከአንባቢያን አስተያየት እየሰበሰበ ነው፡፡ እ.ኤ.አ 1927 ጀምሮ በየአመቱ በጎም ሆነ መጥፎ ተጽእኖ በመፍጠር ብዙ የዜና ሽፋን ያገኙትን ሰዎችን በመለየት በመጽሔቱ ልዩ ዕትም ሽፋን ሲያወጣ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ መጽሔቱ በምርጫ ሂደቱ የህዝብ አስተያየት ቢሰበስብም የመጨረሻ ወሳኞቹ የራሱ አርታኢያን ናቸው፡፡

በዚህ አመት የታይም መጽሔት አንባቢያን ድምጽ እንዲሰጥባቸው ከለያቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአሜሪካ፣ ህንድ፣ ቱርክ፣ ቻይና፣ ብሪታኒያ፣ ራሺያ፣ ብራዚል፣ ዪክሬን፣ ሰሜን ኮርያ፣ ፈረንሳይ እና የጀርመን መሪዎች ሲካተቱ፣ በተጨማሪ ጸሐፊዋ ማርጋሬት አትውድ፣ የጀኔራል ሞተርስ ኃላፊ ሜሪ ብራ፣ የፌስቡክ ፈጣሪ ማርክ ዙከርበርግ፣ ግብጻዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ፣ የፊልም ተዋናዩ ኬኑ ሬቪስ እና የልዕልት ዲያናን ልጅ ልዑል ሔነሪን በማግባት የእንግሊዝን ንጉሣዊ ቤተሰብ የተቀላቀለችው ሜግሃን ማርክሌ ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እ.ኤአ. በ1936 የአመቱ ሰው ተብለው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

Via :- Addiszeybe
@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
GBC Business Leadership Training

📌Basic Managerial Skills
📌Change Management
📌Records Management
📌Kaizen Philosophy

Business Communication

📌Business English
📌Marketing Strategy
📌Digital Marketing
📌Presentation Skill

For Detail information See the above photo⬆️

Call for further information
💥 +21521309530

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥 ጫማ ይሸምቱ

PUMA (GV SPECIAL)

📎ORIGINAL

Size 40-41-42-43
📌 Made in Vietnam
📌 Price 2200 birr
📌 With delivery
📌 በ 5 አይነት ከለር

📞 0912732493
@Hkaeg
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መሰብሰቡን የትግራይ ክልል ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው በኢሕአዴግ ውህደት ውሳኔ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡ ሕወሃት በግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ውህደቱን ከተቃወመ ወዲህ ኮሚቴው ሲሰበሰብ የመጀመሪያው ነው፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንትና ምሽት በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ “ምግብ ተመርዟል ተብሎ የተነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ” መሆኑን ደግሞ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ባለው ባዬ የተባለው ነገር ሀሰት እንደሆነና “ተመረዝን” ያሉ ተማሪዎች በጤና ባለሙያዎች ተመርምረው ጤነኛ መሆናቸው ገልጸዋል። ጉዳዩ “ሆን ተብሎ የተሰራ ሴራ ነው” ብለዋል፡፡ ተመረዝን ብለው ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች ጉዳያቸው በፖሊስ እየተመረመረ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የየኢትዮዽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን ሂደት ሊያውክ የሞከረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን አስታወቀ። ተስፋዬ ዳንጊሶ የተባሉ ግለሰብ፣ የምርጫ ጣቢያው ውስጥ ሰልፍ የማስተባበር ስራ በመስራት ሽፋን፣ መራጮችን ወደሚስጥር ክፍል ተከትሎ በመግባት በማስፈራራት፣ የሚመርጡትን ምልክት በማየት፣ ምልክቱን እንዲቀይሩ በመንገር ከዚያም ስማቸው ተጣርቶ አቤቱታ ሲቀርብ ስማቸውን በመደበቅ የምርጫ ሂደቱን ሲያስተጓሉ እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ነገ አዲስ አበባ ይገባል!

በአገራችንና በሱዳን ህዝቦች መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በተለይም አገራችን በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ላበረከተችው አስተዋጽኦ ምስጋና የማቅርብ ዓላማን ያነገበ ከ50 በላይ አባላትን ያካተተ የሱዳን የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልኡክ ከነገ ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያካሂዳል፡፡

ምንጭ: ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ቋሚ ጥበቃ የሚያደርግ የፖሊስ ሀይል እንዲመደብ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጠየቀ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ሌሎችም ኢንቨስትመንቶች የደህንነት ስጋት አለባቸው ብሏል፡፡ኮሚሽነሩ አቶ አበበ አበባየው ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አለመረጋጋት አንፃር፣ መዋዕለ ነዋያቸውን በተለያየ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆኑ በኋላ ወደ ኋላ የሚሸሹ እየበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ባለፉት 3 ወራትም ወደ ስራ ይገባሉ ተብለው ሲጠበቁ ከነበሩ 66 ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ የገቡት 39 ያህሉ ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሚሽኑን የ3 ወር የስራ ክንውን በተመለከተ ከሥራ ሀላፊዎቹ ጋር ሲነጋገሩ ነው፡፡ቋሚ ኮሚቴው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ ለኢንዱስትሪ ፓርኮችና ለሌሎችም የኢንቨስትመንት ዘርፎች መንግስት ቋሚና ዘላቂነት ያለው ጥበቃ እንዲያደርግ ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል፡፡በሰላም እጦቱ ምክንያት ባለፉት 3 ወራት ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርክና ከሌሎችም የኢንቨስትመንት ዘርፎች የወጪ ንግድ ማግኘት ትችል የነበረውን 300 ሚሊዮን ዶላር እንዳጣች መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ተፈጥሯል!

የአካባቢው ማህበረሰብ የሃገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶችና ወጣቶች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ሰላም የመፍጠር ጥረት ሁሉም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ላይ ሰላም ተፈጥሯል::የአካባቢው ማህበረሰብ ፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ወጣቶች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ፣ ከሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ከደባርቅ ወረዳ እና ከደባርቅ ከተማ አስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር ባደረጉት ሰላም የመፍጠር ርብርብ ሁሉም ተማሪዎች ተቃቅፈው ወደ ዶርማቸው ገብተዋል። ተቃቅፈው ወደ ዶርማቸው ገብተዋል።

ምንጭ: ደባርቅ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የቆየው የመማር ማስተማር ስራ ወደነበረበት እየተመለሰ ነው!

ከሰሞኑ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የቆየው የመማር ማስተማር ስራ ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተፈጠሩ ችግሮች ውስጥ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ከ100 በላይ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደና ተገቢ እርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡ እነዚህም በጅማ፣ ድሬዳዋ፣ መቱ፣ ወልድያ፣ ደብረብርሃን፣ ወሎ፣ መደወላቡ፣ ሀሮማያ፣ ደምቢዶሎ እና ጎንደር ዩኒቨርስቲዎች ሲሆኑ በሌሎችም ተጠርጣሪዎችን የመለየቱና ወደ ተጠያቂነት የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ህውኃት በነገው ስብሰባ ላይ አይገኝም!!

ህወሓት የኢህአዴግ ምክር ቤት በውህደቱ አጀንዳ ተወያይቶ ለመወሰን ነገ ማለትም ህዳር 11 2012 በጠራው ስብሰባ ላይ እንደማይገኝ በደብዳቤ (መግለጫ) አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልሽ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ዛሬ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ በመላው ሲዳማ ሲካሄድ የነበረው የድምጽ አሰጣጥ ያለ እንከን መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
በጥቂት ጣቢያዎች የድምጽ ሰጪዎች ቁጥር በመብዛቱ እስከ ከምሽቱ 12 ሰዓት መጠናቀቅ የነበረበት የድምጽ አሰጣጥ ተጨማሪ ደቂቃዎችን መውሰዱን ተናግረዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልሽ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ዛሬ ከጠዋቱ 12 ጀምሮ በመላው ሲዳማ ሲካሄድ የነበረው የድምጽ አሰጣጥ ያለ እንከን መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ በጥቂት ጣቢያዎች የድምጽ ሰጪዎች ቁጥር በመብዛቱ እስከ ከምሽቱ 12 ሰዓት መጠናቀቅ የነበረበት የድምጽ…
የሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔ ውጤት ከ24 እስከ 48 ሰዓታት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን የምርጫ ቦርድ የኮምዩንኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በሐዋሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። እንደ ሶሊያና ከሆነ በዛሬው ዕለት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት አንድ ሚሊዮን ገደማ የዞኑ ነዋሪዎች ድምፅ ሰጥተዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
GBC Business Leadership Training

📌Basic Managerial Skills
📌Change Management
📌Records Management
📌Kaizen Philosophy

Business Communication

📌Business English
📌Marketing Strategy
📌Digital Marketing
📌Presentation Skill

For Detail information See the above photo⬆️

Call for further information
💥 +21521309530

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የኢህአዴግ ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባውን ያካሂዳል!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ ያጸደቀው የግንባሩ የውህደት ጉዳይ ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል።በዚህም በውህድ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ ዝርዝር ውይይት እና ክርክር በማካሄድ ረቂቁ ለኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲቀርብ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡ በተመሳሳይ ስራ አስፈፃሚው በተዋሐደው ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለምክር ቤቱ እንዲመራ ወስኗል።በመሆኑም ምክር ቤቱ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ እና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ: ዋልታ ቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa