YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የ10ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 1.3 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል 912 ሺ 292 ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፍ ችለዋል።

በአጠቃላይ ወደ ቀጣይ ክፍል ከተዘዋወሩት ተማሪዎች መካከል 750 ሺ 174 ወንዶች ናቸው፡፡162 ሺ 118 ተማሪዎች ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ሰምተናል፡፡በአጠቃላይ ወደ 11ኛ ክፍል ከተዘዋወሩ ተማሪዎች መካከል የሴቶች ድርሻ 17.77 በመቶ መሆኑን ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲን ጠቅሶ የዘገበው ሸገር ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ እስጢፋኖስ አከባቢ......

ከአራት ኪሎ ወደ ስቴዲየም እየተጓዘ የነበረ አንበሳ አውቶብስ እስጢፋኖስ አከባቢ የሚገኘው ውንዝ ውስጥ መንገድ ስቶ መግባቱ ከስፍራው የኔቲዩብ ቤተሰቦች ነግረውናል።

የሞቱ እና የተጎዱ ተሳፋሪዎች እንዳሉ አክለሁ ነግረውናል እንዲሁም አሁን ላይ የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አገልግሎት በስፍራሁ ደርሷል ክሬኖች አሉ ቦታው ላይ.....

እንዲሁም የተጎዱ ሰዎችን ወደ ዘውዲቱ ሆስፓታል ተወስደዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለ2012 ዓ.ም በአዲሲ አበባ ዩኒበርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህጻናት የህክምና ትምህርት ክፍል (Pediatrics and Child Health) ለሪዝደንሲ የተመደባችሁ ሐኪሞች ትምህርት መስከረም 15 የሚጀምር መሆኑን አዉቃችሁ ከዕለቱ ቀደም ብላችሁ መስከረም 13 እና 14 እንድትገኙ ዲፓርትመንቱ አስታዉቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ባለ ወንዝ መውደቁ ተሰማ።

አደጋው 12:30 ግድም እንደደረሰ ሰምተናል። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ ከየትኛው አቅጣጫ እንደመጣም ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል።እስካሁንም ምን ያህል ሰው ህይወት እንዳለፈ አልታወቀም ተብሏል።ይህንኑ አደጋ በተመለከተም 12 አምቡላንስ መመደቡን ሰምተናል።

የሰው ህይወትም ለማትረፍ ክሬን እና ሌሎች ከባ ድ ማሽነሪዎች ወደ ቦታው ተስዷል ተብሏል። አደጋው ያገኛቸው ተሳፋሪዎችም ወደ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል።

ሸገር ራዲዮ ወሬውን ከእሳት እና ድንገተኛ ኮምንኬሽን ሰምቻለው ሲል ነው የዘገበው። አንበሳ አውቶብሱ ሙሉ ሰው እንዳጫነ ነው ተብሏል።

ስንት ቁጥር አውቶብስ እንደሆነም ለጊዜው አልታወቀም መባሉን ሰምተናል።

ቅዱስ እስጢፋኖስ አካባቢ በደረሰው የመኪና መገልበጥ አደጋ 41 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል


@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአዲስ አበባ አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ባለ ወንዝ መውደቁ ተሰማ። አደጋው 12:30 ግድም እንደደረሰ ሰምተናል። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ ከየትኛው አቅጣጫ እንደመጣም ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል።እስካሁንም ምን ያህል ሰው ህይወት እንዳለፈ አልታወቀም ተብሏል።ይህንኑ አደጋ በተመለከተም 12 አምቡላንስ መመደቡን ሰምተናል። የሰው ህይወትም ለማትረፍ ክሬን እና…
#አንድ_ወንድ እና #አንድ_ሴት አርፈዋል፤ በርካታ ተሳፋሪዎች ጉዳት ላይ ናቸው።

የአንበሳ ከተማ አውቶብስ አገልገሎት ላይ የነበረ ፤ #ከፈረንሣይ_ለጋሲዮን_የተነሳችው 55 ቁጥር ተሳፋሪዎችን እንደያዘ እስጢፋኖስ ድልድይ ሥር ወድቋል፡፡

የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ ሠራተኞች - በክሬይን በመታገዝ የተገለበጠውን አውቶብስ ለማንሳት እየጣሩ ነው፡፡ ከተገለበጠው አውቶብስ ስር ሰዎች ይኖራሉ ተብሎ ተጠርጥሯል፡፡
ፖሊስ ‹‹ሾፌሩ ከአደጋው ተርፏል፤ የአደጋ መንስኤን በማጣራት ላይ ነኝ ››- ብሏል፡፡
ከመስቀል አደባባይ ወደ 4 ኪሎ የሚወስደው መንገድ ለጊዜው #ተዘግቷል

Via :- ጌጡ ተመስገን
@YeneTube @FikerAssefa
Year founded.

Dolce and Gabbana: 1985
Versace: 1978
Giorgio Armani: 1975
Yves Saint Laurent: 1961
Chloe: 1952
Givenchy: 1952
Christian Dior: 1946
Coach: 1941
Fendi: 1925
Gucci: 1921
Prada: 1913
Chanel: 1910
Nordstrom: 1901
Burberry: 1856
Louis Vuitton: 1854
Hermes: 1837
@Yenetube @Fikerassefa
Number of Bitcoin ATMs

US: 2,606
Canada: 700
Austria: 271
UK: 215
Spain: 85
Russia: 54
Australia: 54
Switzerland: 48
Italy: 38
Colombia: 30
Malaysia: 10
Japan: 9
South Africa: 5
Brazil: 2
France: 2
Saudi Arabia: 2

(CoinATMRadar)
@YeneTube @Fikerassefa
#Update በትግራይና በአማራ ክልሎች ምዕራባዊ ድንበር ግጭው በተባለ አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አንድ የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል አባል ሲገደል አራት ቆሰሉ።

የልዩ ሀይሉ አባልት በተሽከርካሪ ቅኝት (patrol) በሚያደርጉበት ወቅት ነበር ጥቃት የተከፈተባቸው።

Via:- Elu
@YeneTube @Fikerassefa
💥💥💥10ኛው አዲስ ሚውዚክ ሽልማት💥💥💥

⚡️⚡️ የአመቱ ምርጥ #የሙዚቃ_ቪዲዮ⚡️⚡️

💥አብርሀም በላይነህ (እቴ አባይ)💥

⚡️⚡️የአመቱ #ምርጥ_ተዋናይት⚡️⚡️

💥እድለወርቅ ጣሰው (ወደፊት)💥


⚡️⚡️የአመቱ #የክብር_ተሸላሚ ⚡️⚡️

💥አቀናባሪ ኤልያስ መልካ💥


⚡️⚡️የአመቱ #ምርጥ_የነጠላ_ዜማ⚡️⚡️

💥ራሄል ጌቱ (ጥሎብኝ)💥


⚡️⚡️የአመቱ #ምርጥ_ተዋናይ⚡️⚡️

💥💥ግሩም ኤርሚያስ (ተፈጣሪ)💥💥


💥💥የአመቱ #ምርጥ_ፊልም💥💥
⚡️⚡️⚡️ወጣት በ97⚡️⚡️⚡️


💥💥የአመቱ #ምረጥ_አልበም 💥💥
⚡️⚡️ጎሳዬ ተስፋዬ (ሲያምሽ ያመኛል )⚡️⚡️


💥የአመቱ ምርጥ #አዲስ_የአልበም_ድምጻዊ💥
⚡️⚡️ጃኪ ጎሲ (ባላምባራስ)⚡️⚡️


💥💥የአመቱ ምርጥ #የሙዚቃ_አቀናባሪ 💥💥
⚡️⚡️ጊልዶ ካሳ (በነጠላ ዜማዎች)⚡️⚡️

ምንጭ:- ዳሰሳ አዲስ
@YeneTube @Fikerassefa
የአውቶቢሱ ታርጋ ታውቋል...

እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ጀርባ በሚገኝው ድልድይ ውስጥ የወደቀው አደጋ የገጠመው የከተማ አውቶብሱ ምክንያት ለጊዜው የሰሌዳ ቁጥር የማንነግራችሁ ኮድ 3 አ. አ መኪና #ለመሸሽ_ሲል እንደሆነ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች የኮምንኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለሽገር አስረድተዋል።

አውቶብሱ የተለመደ የመስመር ቁጥር ያልተሰጠው አዲስ ስምሪት እንደሆነም አውቀናል።

አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 3- አ/አ 68377 እንደሆነ ታውቋል።

በዚሁ አደጋም 31 ሰዎች ብርቱ ጉዳት እንደገጠማቸው ሰምተናል፤ካሰቡበት ለመድረስ በአውቶብሱ ተሳፍረው አደጋው ያገኛቸው ኢትዮጵያውያንም ወደ ጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል መወሰዳቸውን ባለሙያው ነግረውናል።

በደረሰው አደጋ እስካሁን የሁለት ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል። #የሟቾች_ቁጥርም_ሊጨምር ይችላል ያሉት የኮምንኬሽን ባለሙያው ናቸው።

#ሸገር
@YeneTube @Fikerassefa
ድሬደዋ❗️

በድሬዳዋ በሦስት ቀበሌዎች የሚኖሩና በጣም ዝቅተኛ በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ከ15ሺ በላይ ነዋሪዎች ከያዝነው ወር ጀምሮ የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ መሆን ይጀምራሉ።

ይህም በድሬዳዋ በሁሉም ቀበሌዎች የከተማ ምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎችን ቁጥር ወደ 44ሺ ገደማ ያሳድገዋል።

የከተማ ምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎች በከተማ ፅዳት፣ የተፋሰስ ልማት እና መሰል ሥራዎች እየተሰማሩ ክፍያ የሚፈፀምላቸው ሲሆኑ ምንም መስራት የማይችሉ ደግሞ ቀጥታ ወርኃዊ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበት መርኃ ግብር ነው።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerasssefa
በነቀምት የታሳሪ ቤተሰቦች አቤቱታ

ላለፉት ሦስት ወራት በነቀምቴ ኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንግሥት ታስረው የሚገኙ ግለሰቦች እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እንዳሳሰባቸው ከቤተሰቦቻቸው መካከል አንዳንዶቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል::

ከታሳሪዎቹ መካከልም "ምግብና ውሃ ባለማግኘታችን ለእንግልትና ለበሽታ እየተጋለጥን ነው" ብለዋል።

ትናንት ጥቂት ታሳሪዎች የተለቀቁ ሲሆን አስተያየታቸውን ግን መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። የከተማው ባለሥልጣናት ተጠይቀው መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል::
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ከፍያለው ተፈራ ግለሰቦቹ “በምዕራብ ኦሮምያ ይንቀሳቀሳል” ካሉትና “ሽፍታ” ሲሉ ከጠሩት ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ጥርጣሬ መያዛቸውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
ኢህአዴግ "የኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ" በሚል ስያሜ ውህድ ፓርቲ ሊሆን ነው!

በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሲመራ የቆየው ኢህአዴግ የጋምቤላ ፣ አፋር፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የሶማሌና ሀረሪ ክልል ገዢ ፓርቲዎችን በመያዝ ሊዋኸድ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከመስከረም 8 ጀምሮ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በጉባኤው አብዮታዊ ዴሞክራሲን በመተካት የአዲሱ ፓርቲ የፖለቲካ ፍልስፍና ይሆናል በተባለው "መስመር" ፍልስፍና ዙሪያ ውይይት በባህርዳር፣ አዳማና ሀዋሳ ከተሞች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ወጣቶችና ምሁራን በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ንግድ ባንክ የሰራተኞቹን ደመውዝ በእጥፍ አሳደገ!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሐምሌ 2011 ባካሄደው ስብሰባ የባንኩ ሰራተኞች ለሁለት አመታት ሲያቀርቡ የነበሩትን የደመውዝ ጭማሪ ጥያቄ ተቀብሎ ከያዝነው የበጀት አመት ጀምሮ የሚታሰብ የ100% ጭማሪ እንዲደረግ አፅድቋል። የጭማሪው መጠን ሰሞኑን በውስጥ ማስታወሻ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የግብፁ ፕሬዝደንት ሲሲ ስልጣን እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው!

በርካታ ግብፃውያን ካይሮ የሚገኘው የታህሪር አደባባይ እና በሌሎች ከተሞች በሚገኙ የመሰብሰብያ ስፍራዎች በመገኘት ፕሬዝደንቱ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ምክንያቱ ደግሞ በፕሬዝደንቱ አስተዳደር ላይ እየተነሳ ያለው የሙስና ውንጀላ ነው።

ሰሞኑን "እኛ በ2011 ትርምስ ውስጥ ገብተን ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን አትገነባም ነበር" ሲሉ ተደምጠው የነበሩት የግብፁ ፕሬዝደንት አብደልፈታ አልሲሲ አሁን ራሳቸው ላይ ትልቅ ተቃውሞ ተቀስቅሶባቸዋል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
አትሌት ታምሩ ደምሴ ወደ ሀገሩ ተመለሰ!

በፓራኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክሎ በሪዮ 2016 ኦሎምፒክ ተሳትፎ የነበረው አትሌት ታምሩ ደምሴ ትናንት ምሽት ወደ ሀገሩ ተመለሰ።ከአትሌት ታምሩ ደምሴ ጋርም ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት መገርሳ ታሲሳ ትናንት ምሽት ወደ ሀገሩ ተመልሷል።አትሌቶቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ጨምሮ ሌሎች የስፖርቱ ቤተሰቦች እና የአትሌቶቹ ቤተሰቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አትሌት ታምሩ ደምሴ እና አትሌት መገርሳ ታሲሳ በአውሮፓውያኑ 2016 በብራዚል በተካሄደው የሪዮ ፓራኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው ተሳትፈዋል።አትሌት ታምሩ ደምሴ በሪዮ ኦሎምፖክ ከፊል ማየት በተሳናቸው የ1500 ሜትር ውድድር ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅም ለሀገሩ የብር ሜዳሊያን አስገኝቶ እንደበረ ይታወሳል።ከውድድሩ በኋላም አትሌቶቹ ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ በሄደበት ሪዪ ዴጄኔሮ ጥገኝነትን የጠየቀው እዛው መቆየታቸውም ይታወሳል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ 3,200 (የዶላር) ሚሊየነሮች አሉ!

ከምስራቅ አፍሪካ ኬንያ 8,600 ሚሊየነሮችን በመያዝ አንደኛ ስትሆን ታንዛንያ በ2,400 ሚሊየነሮች ሶስተኛ ነች።

Via:- AfrAsia Bank ( ኤልያስ እንደተረጎመሁ)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግስት፣ በነደፈው የምጣኔ ሐብት ማሻሻያ ፕሮግራሙ “አትራፊ ናቸው” የሚባሉ የመንግስትን ድርጅቶች ጨምሮ ወደ ግል ድርሻ ለማካፈል እቅድ ነድፏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዎች፣ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ድርጅትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ድርሻውን መንግስት ይዞ ቀሪው ለውጭና ለሃገር ውስጥ ባለሀብቶች እንዲተላለፉ ከተወሰነባቸው ድርጀቶች መካከል ናቸው፡፡

መንግስት ውሳኔው፣ የድርጅቶቹን ውጤታማት ይጨምራል የገንዘብ አቅማቸውን ያሳድጋል፣ በሚያስገኙት ገቢም የዕዳ ጫናን ማቃለል ይቻላል ይላል፡፡ አንድ ምሁር ግን ይኽን አስተያየት ክፉኛ ይቃወሙታል፡፡

በተለይ እንደ አየር መንገድ ያለ አትራፊ ድርጅት በአክሲዮን መሸጡ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል እያሉ ይሞግታሉ፡፡

Via:- ሸገር FM
@YeneTube @Fikerassefa
በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ቆፍቱ ቀበሌ የተገነባው የሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በትናንትናው ዕለት መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
ጋምቤላ !!
ኢትዮ ቴሌኮም ጋምቤላ ዲስትሪክት የሰራተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ምሳ ግብዣ አዘጋጅቷል።

በተመሳሳይ አዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የሰራተኞች ቀን እየተከበረ ይገኛል።

#Belayneh #የኔቲዩብ
@Yenetube @Fikerassefa