YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለመጣው ለውጥ ዋጋ ለከፈሉ እና አስተዋፅኦ ላደረጉ የቤት እና የገንዘብ ሽልማት ሊሰጥ ነው፡፡

••>የሪፍት ቫሊ ዩንቨርስቲ ፣ ሶደሬ ሪዞርት ፣ የሪፍት ቫሊ ሆስፒታል፣ የቀርሽ ማይክሮ ፋይናንስና የናፍያድ ትምህርትቤቶች ባለቤት የሆኑት ባለሃብቱ ድንቁ ደያሳ በጥሬ ገንዘብ እና ቤት ሰርተው ሊሰጡ ነው፡፡

••>ድጋፉ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና ፍትህ ሲታገሉ ለነበሩ የተመረጡ እና በእስር ላይ የቆዩ እንዲሁም በአስር ቆይታቸው ግፍ የተፈጠመባቸው እና የተለያየ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ለህዝቡ ነፃነት ሲታገሉ የነበሩና በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የኦሮሞ አርቲስቶች መሆኑ ታውቋል፡፡

••>ባለሃብቱ ከዚህ ቀደም ከኢትዮ ሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ12 ሚሊየን ብር በላይ እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዉ በተግባር ከ28 ሚሊየን ብር በላይ የሰጡ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ትምህርት የሚሰጥበትን ሙሉ የከፍተኛ የትምህርት ማእከል ከአብራኩ ከወጣሁት ህዝብ አይበልጥብኝም በማለት ለተፈናቃይ ወገኖች ሙሉ በሙሉ በመልቀቅ እስከ አሁኑ ተፈናቃይ ወገኖች በዚሁ ኮሌጅ እየኖሩ ከመንግስት የሚደረግላቸዉን የመጨረሻ እርዳታ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም ታወቋል፡፡

••>ባለሀብቱ በ2008ዓ.ም መጨረሻ በሶደሬ ሪዞርት ሆቴል በተደረገዉ የኦሮሞ አባገዳ ምክር ቤት ላይ አባዱላ በመሆን የተመረጡ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡

#ሸገር_ታይምስ
@Yenetube @Fikerassefa
የአውቶቢሱ ታርጋ ታውቋል...

እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ጀርባ በሚገኝው ድልድይ ውስጥ የወደቀው አደጋ የገጠመው የከተማ አውቶብሱ ምክንያት ለጊዜው የሰሌዳ ቁጥር የማንነግራችሁ ኮድ 3 አ. አ መኪና #ለመሸሽ_ሲል እንደሆነ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች የኮምንኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለሽገር አስረድተዋል።

አውቶብሱ የተለመደ የመስመር ቁጥር ያልተሰጠው አዲስ ስምሪት እንደሆነም አውቀናል።

አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 3- አ/አ 68377 እንደሆነ ታውቋል።

በዚሁ አደጋም 31 ሰዎች ብርቱ ጉዳት እንደገጠማቸው ሰምተናል፤ካሰቡበት ለመድረስ በአውቶብሱ ተሳፍረው አደጋው ያገኛቸው ኢትዮጵያውያንም ወደ ጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል መወሰዳቸውን ባለሙያው ነግረውናል።

በደረሰው አደጋ እስካሁን የሁለት ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል። #የሟቾች_ቁጥርም_ሊጨምር ይችላል ያሉት የኮምንኬሽን ባለሙያው ናቸው።

#ሸገር
@YeneTube @Fikerassefa
ጁነዲን ሳዶ ሸገር የተሰኘ አዲስ ባንክ ሊመርቱ ነው!

የቀድሞው የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጁነዲን ሳዶ #ሸገር የተሰኘ አዲስ ባንክ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።

የባንኩ መስራች ቦርድ የሆኑት ጁነዲን እንደተናገሩት ድርሻ የመሸጥ ፍቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝተው ከየካቲት 7 ጀምሮ በይፋ አክሲሆን መሸጥ ይጀምራል ብሏል ።

Via:- አዲስ ማለዳ ጋዜጣ 🖊 YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
የኦዴሳ ጦርነት

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ የሶቪየት መፈራረስና የሩሲያ ልዕልና ማነስ ሲያንገበግባቸው ማደጋቸውን የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ፡፡ በተለይ የዩክሬይን አገር መሆን ውስጥ ውስጡን ይበላቸዋል፡፡ የፑቲንን ስነልቦና እናውቃለን የሚሉ በርካቶች የአሁኑ ጦርነት የሩሲያን ክብር ለመመለስ የሚደረግ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ዋነኛዋ ቁልፍ የጥቁር ባህር ፈርጥ የሆነችውን ኦዴሳን መቆጣጠር ግዴታ ነው፡፡ ዩክሬኖቹ ኦዴሳን አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል፡፡ በፑቲን ህልምና በዩክሬይኖች መካከል ስለሚደረገው የኦዴሳ ጦርነት ይህን አስደናቂ ቪዲዮ ይከታተሉ!!!

https://youtu.be/sW0rM_nr8Uo

ለመሆኑ ቅጥረኛ ወታደሮች በወር ምን ያህል ይከፈላቸዋል???
============
ከሰሞኑ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዩክሬይኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ለመዋጋት ተሰልፈው ታይቷል። ወዶ መዝመት ከጥንት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የወጣቱን ልብ ያሸፈተው የርዕዮተ ዓለም ፍቅር አይደለም። አማላይ ክፍያው እንጂ። ለመሆኑ ቅጥረኛ ወታደሮች ምን ያህል ይከፈላቸዋል??? የሚሰጣቸው ስልጠና እና ዋነኛ ስራቸው ምንድነው? ይህን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ። ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!

https://youtu.be/Q0Uj40oaOho
ኦዴሳ

ፑቲን ኦዴሳ ከተማን ሳይቆጣጠር የዩክሬይን ዘመቻው ስኬታማ ሊሆንለት አይችልም። ኦዴሳን ከተቆጣጠረ ግን በአውሮፓ ትልልቅ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦች ይጠበቃሉ። ለምን? ኦዴሳ ይህን ያህል ጥቅሟ ምንድነው?? ይህን አጭር ቪዲዮ ተከታተሉ