ኢትዮ ቴሌኮም የCDMA አገልግሎትን ከገበያ ሊያስወጣ ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም በሲ.ዲ.ኤም.ኤ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ላይ ምንም ዓይነት ማስፋፊያ የማያደርግ መሆኑን ተከትሎ በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሲ.ዲ.ኤም.ኤ ተጠቃሚዎች ከአገልግሎት ጥራት ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥማቸው በማሰብ ነው በሂደት አገልግቱን ለማቆም የወሰነው።
ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa

መንግስት በአዲስ አበባ ለሚገኙ ሁሉም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ እንደሚያቀርብ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እናንተ ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት ላኩ እንጂ ቁርስና ምሳቸውን በኔ ጣሉት ብሏል፡፡የከተማ አሥተዳደድሩ ትምህርት ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፀው በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ማለትም ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በሙሉ ለመመገብ መርሃ ግብር ተይዟል።
የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ አበበ ቸርነት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የምገባ መርሃ ግብሩ ታቅዶ እየተሰራበት ነው፤ ተማሪዎች የ 2012 ዘመን ትምህርታቸውን ሲጀምሩ ይጀመራል ብለውናል፡፡እንደ አቶ አበበ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ማንም ተማሪ ሆዱ ባዶ ሀኖ ትምህርት ገበታ ላይ መቀመጥ የለበትም የሚለውን ታሳቢ ያደረገ መርሃ ግብር ነው ብለዋል፡፡
አቶ አበበ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ተማሪን መመገብ አይከብድም ወይ ብላን ለተነሳላቸው ጥያቄም ከዚህ ቀደም እንዲህ በስፋት ባይሆንም የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ይመግቡ እንደነበር ያነሱ ሲሆን ልምዱ ስላለ አስቸጋሪ አይሆንም ሲሉ ነግረውናል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ምገባ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ለሚገኙ አጠቃላይ ተማሪዎች የደንብ ልብሳቸውንና የትምህርት ቁሳቁሳቸውንም እንደሚችል አሳውቋል፡፡
የትምህርት አከባቢውን ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ለማድረግና አዲስ መንፈስ ለመፍጠርም 488 ትምህርት ቤቶች መታደሳቸውንም አቶ አበበ ለEthio FM ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ አካላት ከ7 ሚሊዩን በላይ ደብተር እንደተሰበሰበ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡በ2011 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በአጠቃላይ 918 ሺህ 207 ተማሪዎች ነበሩ፡፡
ሌሎች አጋሮች ይሳተፉበታል የተባለው ተማሪዎችን ከማንኛውም ወጪ ነፃ አድርጎ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ያቀደው መርሃ ግብር ወጪው በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን አቶ አበበ ነግረውናል፡፡ምን ያህል በጀት እንደተያዘና ሌሎች ከወጪ ጋር የተገናኙ ዝርዝር ጉዳዮችን ግን በቅርቡ እናሳውቃለን ብለዋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube FikerAssefa

ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሉአላዊነትን የሚጋፋ ማንኛውንም አይነት ሃሳብ እንደማትቀበል አስታወቀች::
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአገሪቱ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ነው።በግድብ ዙሪያ ላይ ግብጽ ያመጣችው ሃሳብ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማይኖረውና የህዳሴው ግድብ አሁንም ግንባታው እንደማይቋረጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ አሁንም የአባይን ግድብ መገንባቷን ትቀጥላለች ኢትዮጵያ ግብጽንም ሆነ ሱዳንን የመጉዳት ፍላጎት የላትም ይልቁንም ግብጽ የተለየ እና ኢትዮጵያን የማይጎዳ ሃሳብ ይዛ ከመጣች ለቀጣይ ድርድር በሯ ክፍት ነው ብለዋል።ነገር ግን ከዛ ውጪ የሚነሱ ኢ ፍትሃዊ ሃሳቦች ወደፊትም ተቀባይነት አይኖራቸውም ሲሉ አቶ ነብያት በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።
ምንጭ:Ethio FM

👍1
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፡
Galmee barattoota Idilee Yuunivarsiitii Amboo:
1. Buleeyyiif-Onkoloolessa3-4 bara 2012
Adabbiidhaan Onko.5/2012
ለነባር ተማሪዎች ጥቅምት 3-4/2012
በቅጣት ጥቅምት 5/2012
2. Haaraaf-Onkoloolessa 17-18/2012
*Adabbiidhaan Onkoloolessa 19/2012
*ለአዲስ ተማሪዎች ጥቅምት 17-18/2012
በቅጣት ጥቅምት 19/2012
Bara barumsaa gaarii isiniif haa ta'u!
መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንላችሁ!

11ኛ ክፍል መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።
በ2011ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት (10ኛ ክፍል) ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
📌 የመደበኛ፣የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2.00 እና በላይ ለሴት 1.86 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይቀጥላሉ።
📌 ለአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ለወንድ 1.86 እና በላይ ለሴት 1.71 እና በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ለወንድ 1.71 ለሴት 1.61 እንዲሆን ተወስኗል።
📌 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች፣አርብቶ አደር አካባቢዎች እና የፀጥታ ችግር የታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 1.86 ለሴት 1.71 እንዲሆን መወሰኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ
📌 ሁሉም ወደ 11ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የሚመርጡት የትምህርት መስክ በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታው በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በምርጫ ተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ይሆናል፡፡
📌 ከዚህ በፊት የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 2.00 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያመጡ በማታው ፕሮግራም የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን መቀጠል የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃ መሸጥ አይቻልም አለ፡፡
ባለስልጣኑ ከቅርብ ጊዜያው ወዲህ ቦቴ መኪናዎችን በመጠቀም የሚከናወኑ የውሃ ሽያጮች ራስ ምታት እንደሆኑበት ተናግሯል፡፡የውሃ ሽያጩ ምሽትን ተገን አድርጎ የሚከናወን በመሆኑ ለቁጥጥርም አዳጋች ሆኖብኛል ብሏል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ አርጋው ድርጊቱ ከተማዋ ለውሃ ብክነት ከሚያጋልጡ ነገሮች አንዱ ነው ብለዋል፡፡
ድርጊቱንም ለመቆጣጠር አዲስ ስልት አውጥተው እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበራቸው ጠይቀዋል፡፡የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከመንገዶች ባለስልጣንና ሌሎች ተቋማት ጋር ባለመቀናጀቴ ባለፉት 40 አመታት በተገቢው መንገድ ሳልሰጥ የቆየሁትን ፍሳሽ ቆሻሻን የማስወገድ ስራ ከዚህ አመት ጀምሮ ቀልጠፍ ብዬ መስጠት እጀምራለሁም ብሏል፡፡
Via Sheger

በአዲስ አበባ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህርን ምዝገባ ተጠናቀቀ።
በከተማዋ የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በብቃታቸው በተሻሉ መምህራን በአዳሪ ትምህርት ቤቶች መርሃ ግብር ለማስተማር ማቀዱ ይታወሳል።ለነዚህ ትምህርት ቤቶች የታማሪዎችና የመምህራን ምዝገባና ምልመላ ከጥቂት ቀናት በፊት ተጠናቋል ተብሏል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገሩ ሲሆን ውጤቱን በቅርብ ቀናት ውስጥ አናሳውቃለን ብለዋል፡፡
በውጤታቸው የላቁ በአቃቂ 500 ወንዶችን በእቴጌ መነን ደግሞ 500 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ በልዩ ክትትል በአዳሪ ትምህርት ቤት መርሃ ግብር ለማስተማር ከተማ አስተዳደሩ ማቀዱን ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡እንደ አቶ አበበ ቁጥሩ ከምልመላው በኋላ ከተያዘው ዕቅድ ከፍም ሊል እንደሚችልም ነግረውናል፡፡
via Ethio FM

ከዚህ በፊት የ10ኛ ክፍል ውጤት 2.00 እና ከዛ በላይ አምጥተው ነገር ግን ያኔ በነበረው መቁረጫ ያላለፉ ተማሪዎች አሁን የማታ 11ኛ ክፍል መግባት ይችላሉ ።
-የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ-
@YeneTube @Fikerassefa
-የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ-
@YeneTube @Fikerassefa
ጋህአዴን በ2012 በጀት ዓመት የህግ የበላይነትን በማረጋገጥና ህገ- ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን መግታት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቀ!!
የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ በጋምቤላ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ የቀጣይ ስራዎችን አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቀቀ።
የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ በሰጡት መግለጫ ኮሚቴው ባለፈው ዓመትና በቀጣይ እቅዶች ዙሪያ በስፋት በመምከር ውሳኔዎችን አሳልፏል።
ወይዘሮ ባንቻየሁ ድርጀቱ በ2011 በጀት ዓመት አልፎ አልፎ ከነበሩት የጸጥታ ችግሮች ጋር ተያይዞ በተሻገሩ የልማትና የፖለቲካ ስራዎች ላይ በስፋት መወያየቱን ተናግረዋል።
በተለይም በትምህርት፣ መንገድ፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የታቀዱት የልማት ስራዎች በተፈለገው ደረጃ አለመከወናቸውን ኮሚቴው ገምግሟል።
በ2012 በጀት ዓመት ካለፈው ዘመን በተሻገሩ የልማትና የፖለቲካ ስራዎች ላይ በትኩረት እንዲሰራ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧልም ብለዋል።
ኮሚቴው በ2012 በጀት ዓመት በተለይም የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ ህገ- ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመግታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን በማጠናከር ረገድ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ውሳኔ ማሳለፉን ኢዜአ ዘግቧል።

“ግማሽ ጨረቃ” ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ከመስከረም 23 ቀን ጀምሮ በዋልታ ቴሌቭዥን ብቻ ይቀርባል።የቴሌቭዥን ድራማውን የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ትላንት ምሽት በኔክሰስ ሆቴል ተከናውኗል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
በረከት ሞገስ #ከታል_ጋርመንትስ ማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ እና ዋና ቢሮ ጋር በመተባበር #በባደዋቾ_ሀዲያ_ሾኔ ከተማ ለ130 ህፃናት አጠቃላይ የትምህርት ቁሳቁስ #ድጋፍ አድርጓል።
በተጨማሪም በሐዋሳ ከተማ ከሜሪ ጆይ ጋር በመተባበር በኒው ብራንድ ትምህርት ቤት 12 ወላጅ አልባ ህፃናትን የነፃ የትምህርት እድል ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል። በተጨማሪም ከ12 ህፃናት ውስጥ 5ቱ የምሳ ድጋፍ ትምህርት ቤት ውስጥ ይደረግላቸዋል።
እናመሰግናለን በረከተ ሞገስ
@YeneTube @Fikerassefa
በተጨማሪም በሐዋሳ ከተማ ከሜሪ ጆይ ጋር በመተባበር በኒው ብራንድ ትምህርት ቤት 12 ወላጅ አልባ ህፃናትን የነፃ የትምህርት እድል ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል። በተጨማሪም ከ12 ህፃናት ውስጥ 5ቱ የምሳ ድጋፍ ትምህርት ቤት ውስጥ ይደረግላቸዋል።
እናመሰግናለን በረከተ ሞገስ
@YeneTube @Fikerassefa
ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ክርስቲያን ታደለ እንደገና 28 ቀናት ተጠይቆባቸዋል፡፡ ችሎቱም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሏል፡፡ ተጨማሪ ጊዜ የተሰጠው፣ ፖሊስ ምርመራየን አላጠናቀቅሁም በማለቱ እንደሆነ አሥራት ሜዲያ ሀውስ ዘግቧል፡፡ በጳጉሜ 1ዱ ቀጠሮ ችሎቱ ምርመራው ተጠናቆ እንዲቀርብለት አዞ ነበር፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከሚገነባቸው 16 ተርባይኖች 2ቱን ለመቀነስ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡ ግድቡ 14 ተርባይኖች ብቻ እንዲገጠሙለት እና የዕቀድ ክለሳም እንዲደረግ የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት አዘዋል፡፡ 16ቱ ተርባይኖች 6 ሺህ 450 ሜጋ ዋት እንዲያመነጩ ታስቦ ነበር፡፡ ሆኖም በቂ ውሃ ካለ፣ የተርባይኖች መቀነስ መጠኑን ላይጎዳው እንደሚችል ባለሙያዎች ገልጠዋል፡፡ ለ2ቱ ተርባይኖቸ ማስቀመጫ ግንባታ የወጣው ወጭ ግን ኪሳራ ይሆናል፡፡
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በሕገ ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ 52 አይሱዙ ሙሉ እህልና ጥራጥሬ ዛሬ ዓርብ መስከረም 9/2012 በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ልዩ ስሙ ኳስ ሜዳ በተባለ ቦታ በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚንስትሩ ወደ ሀዲያ ሊያቀኑ ነው!
መስከረም 13 ያሆዴ (የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ )ለማክበር እና በተጨማሪም ከህዝቡ ጋር ውይይት ለማድረግ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሀዲያዋ ከተማ ሆሳና ያቀናሉ ተብሏል።
ምንጭ: Maleda Media
@YeneTube @FikerAssefa
መስከረም 13 ያሆዴ (የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ )ለማክበር እና በተጨማሪም ከህዝቡ ጋር ውይይት ለማድረግ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሀዲያዋ ከተማ ሆሳና ያቀናሉ ተብሏል።
ምንጭ: Maleda Media
@YeneTube @FikerAssefa
በባህር ዳር ከተማ በ20 ሚሊየን ብር ወጪ የዓሳ ጫጩት ማስፈልፈያ እየተገነባ ነው።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በባህር ዳር ከተማ የዓሳ ጫጩት ማስፈልፈያ እየተገነባ ነው፡፡በባሕር ዳር ዓሳና ሌሎች የውኃ ውስጥ ሕይወት የምርምር ማዕከል ውስጥ እየተገነባ ያለው የጫጩት ማስፈልፈያ ሥራ ሲጀምር በዓመት ከ750 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን የሚደርሱ የዓሣ ጫጩቶችን ማስፈልፈል ያስችላል ተብሏል፡፡ ይህም የዓሳ ፍላጎት እና አቅርቦትን ያመጣጥናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ምንጭ: ፋና