YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ነገ⬆️ዳልዲሞች በጋምቤላ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅተዋል፡፡

ነገርግን መንግስት እውቅና አልሰጠውም እናም #የኔቲዩብ አባላቶች መንግስት እውቅና ካልሰጠው ማንኛውም አይነት ሰላማዊ ሰልፈ እንዳትወጡ እናሳስባለን።

ከተማችሁን በአይነቁራኛ እንድትከታተሉ እናሳስባለ። የጋንቤላ ህብረተሰብም ጥንቃቄ እንድታደርጉ ከወዲሁ እናሳስባለን።
@YeneTube @Fikerassefa
ትብብር ትብብር ‼️

አሁን ከጎናችሁ ላሉ #ለዶርም_ሜታችሁ #ለጓደኛችሁ#ለወንድማችሁ#ለእህታችሁ እንዲሁም #ለቤተሰቦቻችሁ በአጠቃላይ Telegram ተጠቃሚ ለሆነ ሰው #የናንተ የሆነሁ ቻናል #የኔቲዩብ t.me/yenetube ይላኩለት ቤተሰባችን ይሁን።

በቀላሉ ይችን ⬇️
T.me/YeneTube አሁን ይላኩለት።

እናመሰግናለን🙌🙌
ጋምቤላ !!
ኢትዮ ቴሌኮም ጋምቤላ ዲስትሪክት የሰራተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ምሳ ግብዣ አዘጋጅቷል።

በተመሳሳይ አዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የሰራተኞች ቀን እየተከበረ ይገኛል።

#Belayneh #የኔቲዩብ
@Yenetube @Fikerassefa
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የዲጅታል ላይብራሪ አገልግሎት በየዶርሙ ሊሰጥ ነው። #የኔቲዩብ

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለተማሪዎቹ የላይብራሪ አገልግሎት እስከ መኝታ ክፍል ማድረስ ጀመረ። በአሁኑ ሰዓት በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ተማሪዎች ለ15 ቀናት ያህል ግቢ ውስጥና መኝታ ክፍላቸው ውስጥ ብቻ በመሆን እንድያጠኑ ተደርጓል።

ተማሪ ከላይብራሪ ርቆ አስቸጋሪ ስለሆነ አዲስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከ72 ሺህ በላይ መጽሐፍትና የተወሰኑ ቪዲዮዎች እንዲሁም የአንደኛ ዓመት የ2ኛ ሴሚስተር ኮርሶችን መኝታ ክፍላቸው ድረስ እናደርሳለን። በላፕቶፕ ወይም በስማርት ስልክ መጽሐፍ አውርደው ማንበብና ቪዲዮ ማየት ይችላሉ። በ1.5 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ጥላ ስር ወይም ሜዳ ላይ ዘና ብለው ቴክኖሎጂውን መጠቀም ይችላሉ። SRE የራሱ Wi-fi ስላለው ኢንተርኔትም ሆነ ከቢል አይፈልግም።

የቴክኖሎጂው ልዩ ብቃት መምህራን በራሳቸው አካውንት ፎልደር በመክፈት ለተማሪዎች ሞጁሎችና በቪዲዮ የተቀረፁ ሌክቸሮችን ማሽኑ ላይ በመጫን ተማሪዎች በቀላሉ በስልክና በላፕቶፕ አውርደው እንዲጠቀሙ ማስቻሉ ነው። አጠቃቀሙ wi-fi መጫን፣ SRE Digital Library የሚለውን መምረጥ፣ ከ1-8 የሚሰጥ ቁጥር ማስገባት፣ ጉግል ክሮም (Google Chrome) ኦፐራ (Opera) ወይም ዩሲ ብራውዘር (UC browser) በመጠቀም 20.20.8.8 በማለት መፈለግ (Search ማድረግ) ነው።

ሁሉም ስማርት ስልክና ላፕቶፕ ስለለለው በተማሪዎች መሃል የአጠቃቀም ልዩነት አለ። ላይብራሪ ውስጥ የጋራ ኮምፒውተሮች ቢኖሩንም ከላይብራሪ ውጭ ሲሆን ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ የለላቸው አገልግሎቱን አይጠቀሙም። ከእነዚህ ተማሪዎች ውስጥ ጥቂቱን እንኳ መደገፍ የሚትፈልጉ ወገኖች ካላችሁ ከታላቅ ምስጋናና አክብሮት ጋር እናመቻቻለን።

መረጃውን ያደረሰን - የላይብራሪና ዶክመንቴሽን አገልግሎት ዳይረክቶሬት
@YeneTube @Fikerassefa
👍1
በቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት በለይቶ ማቆያ ያሉ ዜጎች ወደ አገር ውስጥ ከገባን 21 ቀን ቢሞላንም እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አልተደረገልንም አሉ፡፡

ከውጭ መተው 21 ቀን የሞላቸው በማቆያ ቦታ የሚገኙ ዜጎች እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የኮሮና ምርመራ እንዳልተደረገላቸው ነው የተናገሩት፡፡

ዜጎቹ እንደሚሉት ከሆነ ከገባን ጀምሮ ምንም ትኩረት አልተሰጠንም እንደ ዜጋም እየተቆጠርን አይደለም ብለዋል፡፡

15ቀን ሲሞላችሁ የኮሮና ምርመራ ተደርጎላችሁ ወደ ቤታችሁ ትሄዳላችሁ ብንባልም ከመጣን 21 ቀን አስቆጥረናል ግፍ እየተሰራብን ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጥያቄ ይዞ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጠይቋል፡፡

#በኢንስቲትዩቱ የኮቪድ 19 ምክትል አስተባባሪ አቶ ዘውዱ አሰፋ እንደሚሉት ሰዎቹ እስካሁን ለምን መመርመር እንዳልተቻለ እናጣራለን ቅሬታቸውንም በአፋጣኝ እንፈታለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

Via:- Ethio FM
Photo :- የኮሮና ምልክት አለማሳየታቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት #የኔቲዩብ

@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ የሙዚቃ አልበም ጥቆማ⬇️
የልጅ ሚካኤል ሁለተኛ አልበም አትገባም አሉኝ ነገ ገበያ ላይ ይውላል ኦርጅናል ሲዲ በመግዛት የበኩላችንን እንወጣ።

#የኔቲዩብ
ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

በበርካታ የአገራችን ፊልሞች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ወጣቱ ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ/ባባ/ በድንገተኛ ህመም ዛሬ ታሕሳስ 2 ቀን 2015 ማለዳ ላይ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ታውቋል።

ላውንደሪ ቦይ፣ 300 ሺ፣ ሹገር ማሚ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ፣ ኢንጂነሮቹ፣ ህይወቴ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ከቃል በላይ፣ ህይወት እና ሳቅ፣ ሀገርሽ ሀገሬ፣ እዮሪካ፣ ከባድ ሚዛን፣ ወፌ ቆመች፣ ይመችሽ ያአራዳ ልጅ 2፣ በቁም ካፈቀርሽኝ፣ እንደ ቀልድ፣ እርቅ ይሁን፣ አስነኪኝ፣ ሞኙ ያአራዳ ልጅ 4፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ ወጣት በ97 እና ባሌ ማነቅያ፤ ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ) ከተወነባቸው ፊልሞች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።

በተጨማሪም ተዋናይ ታሪኩ የጉዳዬ ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር ሲሆን፤ በ2ተኛው ለዛ አዋርድ፣ በ7ተኛው አዲሲ ሙዮዚክ አዋርድ እንዲሁም በ12 ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ በምርጥ ተዋናይነት አሸናፊ ነበር።

በሰላሳዎቹ የእድሜ አጋማሽ ላይ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው አዲስ አበባ ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን፤ የአንድ ልጅ አባትም ነበረ። አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ/ባባ/ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ታሕሳስ 2/2015 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

#የኔቲዩብ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1