ወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ለ2012 ዓም ተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ!
የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ #MoSHE ከዛሬ ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ዩንቨርስቲዎች ጥሪ እንዲያደርጉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ህዳር 24 እና 25/2013 ዓም የምዝገባ ጊዜ መሆኑን አስታውቋል። ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ህዳር 28 መሆኑን ጨምሮ አሳውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa

በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!
በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ (radio therapy) ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ::በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀደም ሲል የካንሰር የጨረር ህክምና ይሰጥ የነበረ ቢሆንም አሮጌ በመሆኑ የካንሰር ህመምተኞች መስተጓጐል እንደነበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሎጅ ዲን ዶክተር ዳዊት ወንድማገኘው ተናግረዋል፡፡የጨረር ህክምና ለማግኘት ወረፋ በመጠበቅ ላይ እያሉም ህይወታቸው የሚያልፉ የካንስር ህመምተኞች ብዙ መሆናቸውን የጠቆሙት ዶክተር ዳዊት አሁን የተመረቀው የካንሰር የጨረር ህክምና መሳሪያ ቀደም ሲል ይከሰቱ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሆስፒታሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት አድርገው መስራት አለባቸው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡የካንሰር ህክምናን ማእከላት ለማስፋፋት መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የጠቆሙን የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ የተመረቀውን የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጨምሮ በቀጣይ በጅማ፣ ጎንደር፣ ሀዋሳ እና ሀረሪ ሆስፒታሎች አገልግሎቱን ለመጀመር መታሰቡን ተናግረዋል፡፡ከካንሰር ህክምና ማእከል በተጨማሪ ህክምናውን የሚሰጡ ባለሙያዎች እየጨመረ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ የሙያ እርከኖች ባለሙያዎች የማስተማር ስራ ጤና ሚኒስቴር ይሰራል ብለዋል፡፡
[ኤፍ ቢ ሲ]

ከሰሞኑ በኮንሶ ዞን፣ አማሮ፣ ዴራሼ፣ አሌና ቡርጂ ወረዳዎች ባሉ ግጭቶች የተጠረጠሩ 137 ሰዎች ተያዙ።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ እንዳሉት ህዝቡ እርስ ችግር ባይኖርበትም ነባር ጥያቄዎችን ሰበብ በማድረግ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች አማካኝነት በ17 ቀበሌዎች በተነሳ ግጭት የ66 ሰዎች ህይወት አልፏል።እንዲሁም በዚህ ግጭት ሳቢያም 39 ሰዎች የአካል ጎዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ130 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለዋል ብለዋል።በአካባቢው የህወሃትና ኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት የተፈጸመውን ጥቃት በመፍራትም ከ130ሺ በላይ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አስረድተዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ለእነዚህ ወገኖች አሰቸኳይ የእለት እርዳታ እየቀረበላቸው መሆኑንም ሀላፊው ይናገራሉ፡፡ህግን የማስከበር ስራ 4 የምርመራ ቡድኖች ተቋቋመው መረጃዎች እየተሰባሰቡ መሆኑንም ተናግረዋል። የክልሉ እና የወረዳዎቹ ነዋሪዎች ባደረጎት ከፍተኛ ጥረትም ግጭቱ እንዲነሳ ተሳትፎ ያደረጉ 137 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ቀሪዎቹን የጥፋት ቡድን አባላት ህግ ፊት የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
[Ethio FM]

ኢትዮጵያ ዜጎቿን መልሳ ለማቋቋም እየሰራች ነው ሲሉ አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ!
መንግስት በስደት ሱዳን የሚገኙ ዜጎችን በትግራይ ክልል መልሶ የማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ።አቶ ዛዲግ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከጀርመን ድምጽ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ህወሃት በትግራይ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማቶችን በማውደም የትግራይ ህዝብን ከተቀረው አለም ጋር እንዳይገናኝ ስለማድረጉ አብራርተዋል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌ መግባቱን ተከትሎ ባለሙያዎች #የስልክ_መስመሮችን ለማስተካከልና ግንኙነቱን ለማስጀመር እየተሰሩ መሆኑንም አብራርተዋል።የህወሃት ቡድን በክልሉ ኤርፖርትን ጨምሮ መንገዶችንና ድልድዮችን ማፈራረሱን ገልጸዋል።
አሁን መንግስት እነዚህን መሰረተ ልማቶች መልሶ እየገነባ ነው ሲሉ ገልጸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ነገሮች በግልጽ የሚያደርግና ምንም የሚደበቅ ነገር እንደሌለው ነው ያስረዱት።አለምአቀፍ ስደተኞችን በማስተናገድ ኢትዮጵያ ከአለም ሶስተኛዋ ሃገር በመሆኗ ሰብአዊ እርዳታዎችን እንዴት ማሰራጨት እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች ብለዋል።የተበላሹ መሰረተ ልማቶችን በማስተካከል ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ ቀንና ሌሊት እየተሰራ ነው ብለዋል።ህወሃት በመረጠው ወታደራዊ አማራጭ የተሸነፈ በመሆኑ ድርድር ማድረግ የሚባለው የማይሆን እንደሆነ ነው ያስረዱት።አቶ ዛዲግ አብርሃ የትግራይ ህዝብ በህወሃት አስተዳደር የተማረረ በመሆኑ በድርድር ሰበብ ህወሃት ተመልሶ እንዲረግጠው አይፈልግም ብለዋል።
[ኢዜአ]

በትግራይ ክልል የባንክ እና ቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ።
ኮሚሽኑ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን አለባቸውም ብሏል።ቀደም ሲል በኢሰመኮ የቀረቡ፣ በተለይም በሲቪል ሰዎች ላይ ማንኛውም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲደረግ አጽንዖት የሚሰጡት ምክረ ሃሳቦችንና ጥሪዎችን በማስታወስ፣ በቀጣይ የሚደረጉ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ተግባራት በፌዴራል መንግሥቱ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የመጠበቅ ግዴታ የሚመራ እንዲሆን አሳስቧል።የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙና ተገቢው ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን የተቋረጡ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃና ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ አካላት አገልግሎት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ማሳሰቡን ኮሚሽኑ በላከው መግለጫ ገልጿል።
እንዲሁም በግጭቱ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ሰዎች ወደ መደበኛ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እና የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙ የሚያስችል አስፈላጊ የሆነው የሎጂስቲክስና የሰብአዊ እርዳታ መሰረተ ልማት እንዲደራጅም ጠይቋል።ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ያስከተለውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛና ግልጽ የሆነ አሰራር ከወዲሁ እንዲተገበር፣ ተዓማኒና አካታች የሆኑ የእርቅና የፍትሕ ሂደቶች በጊዜ ሊደራጁ ይገባልም ብሏል።በተጨማሪም ኢሰመኮ በትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ መድሎዎና መገለል ስለመድረሱ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰበውና እየተከታተለው መሆኑን ገልጿል።
[ኢትዮ ኤፍ ኤም]

አክሱም ተያዘና አውሮፕላን ተመታ መባሉን መንግሥት ሐሰት ነው አለ!
የህወሓት ኃይሎች ትላንት [እሁድ] ምሽት አክሱም ከተማ መልሰው እንደያዙና የፌዴራል መንግሥት ንብረት የሆነ ተዋጊ ጄት መትተው መጣላቸውን ገልጸው ነበር።ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በህወሓት በኩል ተባሉት ነገሮችን "ነጭ ውሸት" ሲሉ አጣጥለውታል።ሚኒስትር ዛዲግ ጨምረውም "የህወሓት የመጨረሻ ይዞታ የነበረችው መቀሌ ናት፤ ይህንን ሊያደርጉ አይችሉም" ሲሉ ተናግረዋል።ከሦስት ሳምንት በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ዋና ከተማዋን መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መከላከያ "ሕግ የማስከበሩ ዘመቻ" መጠናቀቁን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከመቀለ መያዝ በኋላ ለሮይተርስ ዜና ወኪል በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደገለጹት በውጊያው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።በተጨማሪም የቡድኑ ኃይል መቀለ ከተማ አቅራቢያ ውጊያ እያካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ይህንን በተመለከተ ህወሓት የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ዛዲግ አብረሃ ሲመልሱ "የህወሓት አመራሮች በአሁኑ ጊዜ ሕይወታቸውን ለማዳንና በሕግ ከመጠየቅ ለማምለጥ እየሸሹ ነው እንጂ ውጊያ ላይ አይደሉም" ሲሉ መልሰዋል።ትናንት ምሽት ከየት ቦታ እንደሆነ ካልታወቀ ስፍራ ከህወሓት በኩል ወጣ በተባለ መግለጫ ላይ የቡድኑ ተዋጊዎች ከሳምንት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች የተያዘችውን የአክሱም ከተማን መልሰው እንደተቆጣጠሩና አንድ ተዋጊ አውሮፕላን መትተው መጣላቸውን ገልጸዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ግን ተመትቶ የወደቀ የጦር አውሮፕላን እንደሌለና የአክሱም ከተማ "መያዝም በፍፁም ከእውነት የራቀ ነው" ብለው፤ "ህወሓት በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት ወታደራዊ አቅም የለውም፤ ሚሊሻውም ሆነ ልዩ ኃይሉ እጅ እየሰጠ ነው" ሲሉ ከቢቢሲ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።ሚኒስትሩ አክለው በክልሉ ያለውን ሁኔታ ለጋዜጠኞች ክፍት ለማድረግ በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች በርካታ መሠረተ ልማቶች በህወሓት ኃይል በመውደማቸው እነሱ ከተጠገኑ በኋላ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው ሄደው ሁኔታውን ማጣራት ይችላሉ ሲሉ የመገናኛ መስመሮች አለመኖራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
[BBC]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ወቅት ከዓመታት በፊት አባይ የተባለ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያለው የመገናኛ ብዙሀን ተቋም መኖሩን ጠቅሰዋል።የተጠቀሰው ተቋም በዩቲዩብ ሥራውን በመከወን ላይ ከሚገኘው እና በቅርቡ የቴሌቪዥን ስርጭት ከሚጀምረው #አባይ_ሚዲያ ጋር አንድነት እንደሌለውና ሁለቱ ተቋማት የተለያዩ እና ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ጀምሮ ያበቃል!
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከነገ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።
የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ መግለጹ ይታወሳል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

በምስረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን አጠናቀቀ፡፡
የአማራ ባንድ አክሲዮን ማህበር በምስረታ ሂደት ላይ በቆየበት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ160 ሺህ በላይ አክሲዮኖችን በመሸጥ ከሰባት ቢሊዮን በላይ ብር መሸጡን አስታውቋል፡፡እንዲሁም ከአምሰት ቢሊየን በላይ ብር ደግሞ በካፒታል መሰብሰቡንም ገልጿል።በዚሁ ወር መጨረሻ ደግሞ ከባለአክሲዮኖች ጋር ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።
[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ባንድ አክሲዮን ማህበር በምስረታ ሂደት ላይ በቆየበት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ160 ሺህ በላይ አክሲዮኖችን በመሸጥ ከሰባት ቢሊዮን በላይ ብር መሸጡን አስታውቋል፡፡እንዲሁም ከአምሰት ቢሊየን በላይ ብር ደግሞ በካፒታል መሰብሰቡንም ገልጿል።በዚሁ ወር መጨረሻ ደግሞ ከባለአክሲዮኖች ጋር ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።
[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
#REMINDER!!
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ዛሬ ያበቃል!
በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት ከዛሬ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም በህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከዛሬ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም። የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ መግለጹ ይታወሳል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

በአልጀርስ ከዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ጋር ውይይት ተካሄደ!
በአልጀርስ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት /IOM/ ኃላፊ ፓውሎ ካፑቶና የኘሮጀክት ኃላፊ ከሆኑት ፍላቪያ ጂኦርዳኒ ጋር ዜጐቻችን IOM ድጋፍ ማግኘት በሚችሉበትና በወቅታዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ ማስከበር ዙሪያ የተወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ ኀዳር 21 ቀን 2013 በኢፌዲሪ ኤምባሲ ጽ/ቤት ውይይት ተካሄዷል። አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አልጄሪያ በተለያየ ምክንያት በስደተኝነት የመጡ ኢትዮጵያውያን ክብራቸው ተጠብቆና ተገቢው ድጋፍ ተደርጐላቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በዓለም ዓቀፉ ስደተኞች ድርጅት አልጄሪያ ቢሮ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ሚስተር ፓውሎ ካፑቶ በበኩላቸው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአዲስ አበባው ዓለምዓቀፍ በስደተኞች ጽ/ቤት በኃላፊነት መስራታቸውን በማስታወስ ተቋማቸው በስደትና ስደት ተመላሾች ጉዳይ ዙሪያ ምንግዜም ቢሆን ዜጐች ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሁም ህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውርን ለማስቀረትም የተለያዩ ሥራዎችን እንደሚሠሩ ገልፀዋል። አምባሳደር ነብያትም በውይይቱ የፌደራል መንግስት ሕግንና ሥርዓትን በማስከበር እንቅስቃሴው አጥፊው ቡድንና ሕወሃት የተቆጣጠረውን የትግራይ ክልል ዜጐች ለጉዳት ሳይጋለጡ በኃላፊነትና በጥንቃቄ በአጭር ጊዜ ነፃ ለማውጣት መቻሉንና በግጭቱም ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት እንዲመለሱ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
[በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ]

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያልተገባ 1.5 ሚሊዮን ብር ለስልክ ከፈለ!
የመሥሪያ ቤቱ ላልሆኑ ስልኮች 271 ሽሕ ብር መክፈሉ በኦዲት ተረጋግጧል።የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ተገቢ ያልሆነ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ለስልክ ክፍያ መፈጸሙን በኦዲት ግኝት መረጋገጡ ታውቋል፡፡
[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የመሥሪያ ቤቱ ላልሆኑ ስልኮች 271 ሽሕ ብር መክፈሉ በኦዲት ተረጋግጧል።የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ተገቢ ያልሆነ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ለስልክ ክፍያ መፈጸሙን በኦዲት ግኝት መረጋገጡ ታውቋል፡፡
[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መርሃ-ግብር:
ረቡዕ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ፣
• በሻሌ ሆቴል፣ በወሰን ግሮሰሪ፣ በቆሼ፣ በወለቴ እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ፣
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤ/ክ፣ በሳሪስ አቦ ቤ/ክ፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንደሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው፣
ሐሙስ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 6:30 ድረስ፣
• በአደይ አበባ፣ በሳሪስ አዲስ ሰፈር፣ በአዋሽ ቆዳ ፋብሪካ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፣
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ፣
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ፣ በለገሃር፣ በቴሌ እና አካባቢዎቻቸው፣
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]

ፌስቡክ በአዲሱ ዓመት ታላቋ ብሪታኒያ ውስጥ ለሚገኙ ዜና ሰሪ አውታሮች ክፍያ መክፈል ሊጀምር ነው።
ለዚህም የፌስቡክ መተግበሪያው ላይ ራሱን የቻለ የዜና መጠቆምያ ነቁጥ ይበጅለታል ተብሏል።ይህ አገልግሎቱን በአሜሪካ ከወዲሁ ሥራ ጀምሯል ተብሏል። በታላቋ ብሪታኒያ ደግሞ ከአንድ ወር በኋላ በአዲሱ ዓመት ይጀምራል።ፌስቡክ ክፍያ የምፈጽምላቸው የዜና አገልግሎቶች ዜናውን በራሳቸው ገጽ ያላተሙ ከሆነ ብቻ ነው ብሏል።ይህም ማለት የዜና አገልግሎቶቹ በፌስቡክ እንዲከፈላቸው ከፈለጉ ዜናውን ለፌስቡክ ብቻ የሚጽፉት ይሆናል።በራሳቸው ድረገጽም ሆነ በጋዜጦቻቸው ላይ ሊያትሙትም አይችሉም።ፌስቡክ ላይ እንጂ የትም ላልታተሙና የይዘት ደረጃቸው ከፍ ያሉ ናቸው ለሚባሉ የዜና ዘገባዎች ብቻ ክፍያ እፈጽማለሁ የሚለው ድርጅቱ የዜና ዘገባዎችንና ስርጭትን ያለምንም ክፍያ ለደንበኞቹ ሲያጋራና ሲጠቀምበት ነበር፥ በዝባዥ ሆኖ ቆይቷል በሚል ሲተች ነበር።

በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለ2ኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ።
በከተማዋ ህግን የማስከበር ግዳጅ እየተወጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ህገወጥ ድርጊቶችን ለማስወገድ እና የህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ እየሠሩ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮማንደር ሙላት ማሞ ገልፀዋል።ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ በአንድ ሰው ስም የተመዘገቡ 11 የቤት ካርታዎች እና በዚሁ ግለሠብ ስም ከፍተኛ ገንዘብ የተዘዋወረበት ቼክ ተገኝቷል።ተጨማሪ ገጀራዎች፣ መጥረቢያዎች እና የወንድ ማንኮላሻም መገኘቱን ተናግረዋል።
[አብመድ]

ያለመከሰስ መብታቸውን ካጡ የህወሓት አባላት መካከል አንዷ በትናንቱ የምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ ተገኝተዋል!
ያለመከሰስ መብታቸውን ካጡ የምክር ቤት እና የህወሃት አባላት መካከል አንዷ ትናንት በነበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው ተገለጸ፡፡በስብሰባው የተገኙት ወ/ሮ ናፈቅኩሽ ደሴ በ2007 ዓ.ም በተደረገው ሃገር አቀፍ ምርጫ ነበር ከወልቃይት ተወክለው በህወሓት አባልነት ምክር ቤት የገቡት፡፡ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳባቸው አባላት መካከልም አንዷ ናቸው ወ/ሮ ናፈቅኩሽ፡፡ምክር ቤቱ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ38 የሕወሓት የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ወ/ሮ ናፈቅኩሽ ያለመከስስ መብታቸው እንዲመለስ ማመልከቻ አስገብተው ነበረ፡፡ይህ ጉዳይ በምክር ቤቱ አንድ ጊዜ ውሳኔ ስለተወሰነ፣ በተጠቀሰው ወንጀል ሕግ የማይፈልጋቸው ከሆነ፣ ያለመከሰስ መብታቸው ሊመለስ እንደሚችል የምክር ቤቱ ምንጮች ለአል ዐይን አማርኛ አረጋግጠዋል፡፡

የሀይሌ ዝዋይ ሪዞርት ዛሬ ስራ ጀመረ።
በኦሮሚያ ክልል ባቱ ወይም ዝዋይ ከተማ ላይ የተገነባው የሀይሌ ዝዋይ ሪዞርት እደሳው ተጠናቆ ዛሬ ዳግም ስራ ጀምሯል፡፡የአርቲስት አጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ሁከት ዝዋይ ከተማ በሚገኘው የሀይሌ ዝዋይ ሪዞርት ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል፡፡በሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞቶች የኦፕሬሽን ዘርፍ ዳሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ እንደገለፁት ሪዞርቱ 80 በመቶ ውድመት ስለደረሰበት ስራ አቁሞ ነበር።አሁን ላይ ግን ሀይሌ ዝዋይ ሪዞርት የደረሰበት ውድመት እንደገና በማደስ ዛሬ ስራ ጀምሯል ብለዋል፡፡ሪዞርቱ በተሰነዘረበት ጥቃት ሳቢያ ስራ ከማቆሙ በፊት 60 የሚደርሱ የመኝታ አልጋዎች የነበሩት ሲሆን በየቀኑ በአማካኝ 80 በመቶ የሚሆኑት አልጋዎች እንደሚያዙ አስታውሰዋል፡፡
ሪዞርቱ አሁን ላይ 52 የተለያዩ አይነት የመኝታ ክፍሎች ፤ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፤ 2 ሬስቶራንት ፤ መዋኛ ገንዳ እንዲሁም የጤና ክለብም ሙሉ እደሳ ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ቀደም ሲል የነበረንን ገበያ መመለስ በሚያስችል መልኩ እደሳው ተጠናቆ ዛሬ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡አቶ ጋዲሳ ግርማ ሪዞርቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ እና የሆቴል ረገድ እድሳት የተደረገ ሲሆን በሁለቱ ዘርፍ ለእደሳ የወጣው ገንዘብ አሁን ላይ ሪፖርቱ አልደረሰም ብለዋል፡፡ለእደሳው መንግስት በቃል ደረጃ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ከመስጠት ባለፈ ለእደሳው ምንም አይነት ካሳ እንዳልከፈለ ከሆቴሉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 44 ተሽከርካሪዎች ተሰርቀዋል!
በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው 2013 ዓመት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 44 ተሽከርካሪዎች መሰረቃቸው ተገለጸ።የተሽከርካሪ ስርቆት በተለይም በየካ ፣ቦሌ፣ ኮልፌ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የስርቆት ድግግሞሽ ከተገመዘገበባቸው መካከል መሆናቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዘርፍ ኋላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
አብዛኛው የስርቆት ወንጀል የሚፈፀመው ተሽከርካሪዎችን ጠባቂ በሌለባቸው አካባቢዎች ማቆም፣የተሽከርካሪ ቁልፍን ውስጥ ጥለው በመሄድ እና የተሸከርካሪ መስታወትን ክፍት በማድረግ እንደሆነም ተነግረዋል፡፡ፖሊስ የመኪና ስርቆት በመፈፀም ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መሀል ለፍርድ በማቅረብ እንዲቀጡ ያደረገ ሲሆን በቀሪዎቹ ላይ ደግሞ ምርመራ የማጣራት ስራን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በ2012 ዓ.ም በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ 85 ተሽከርካሪዎች መሰረቃቸው የሚታወስ ሲሆን ይህም ከተያዘው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ መቀንሱን ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ጨምረው ተናግረዋል።
[Bisrat Radio/Addis Maleda]

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደገለፁት ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ዘመኑ ሳይጠናቅ ትምህርት መዘጋቱን አስታውሰዋል፡፡በዘንድሮው ዓመት ደግሞ በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ህዳር ወር ሊሰጥ የነበረው ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ከዚህ ባለፈም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሰሜን ወሎ ዞን ዋግኸምራ፣ ሰሜን ጎንደር ፣ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ውስን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተው እንደነበርም ገልፀዋል፡፡አሁን በክልሉ ሰላም በመፈጠሩ የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ከትናንት ጀምሮ ተከፍተዋልም ነው ያሉት፡፡
[FBC]

የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡
የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው፡፡በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል፡፡