ኢትዮጵያችን ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በድል ያጠናቀቀውንና ከሃዲውን ቡድን ከማይጠቅመው ሃሳቡ ጋር እንዲቀበር በማድረግ ለህዝቦችን ሳቅ የመለሰው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በአሁኑ ሰዓት ቀድሞውኑ ከተደበቁበት የውድቀት ዋሻ መውጣት ያቃታቸውን ሰው በላ ጭራቆች ከተደበቀበት ፈልፍሎ ለማውጣትና ለመላው ህዝባችን እንካችሁ ሊል በመማሰን ላይ ይገኛል ።
ለሁሉም አሁን ላይ ሰራዊታችን ከህዝባዊ ተልዕኳችን እና ከጣፋጭ ድላችን መልስ ይሄን ይመስላል ።
አበበ ሰማኝ (ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም)
ፎቶ በብርሃኑ ወርቁ
@YeneTube @Fikerassefa

ከሆስፒታል ህጻን የሠረቀችው ግለሠብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።
በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል በ18/03/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በሚሆንበት ግዜ ከስናን ወረዳ ሆስፒታል አንድ ልጅ ወልዳ አንደኛውን ለመውለድ ባለመቻሏ በሪፈር ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል መጥተው እናትየዋ በመታከም ላይ እያለች የተወለደውን ህጻን አባትየው ታቅፎ እንደቆመ አዛኝ መስላ በመጠጋት ላግዝህ ብላ ተቀብላ እቃ እንዲያመጣላት በማዘዝ እቃውን ሊያመጣላት ሲሄድ ህጻኑን ይዛ በመሠወሯን የሚገልፅ መረጃ ለደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ደርሷል።
የከተማው የወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር መሀሪ አለማየሁ እንደገለጹት ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሠረት አድርጎ ተጨማሪ መረጃዎችን ከደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል በመሰብሰብ እና በመተንተን ጉዳዩ ወደ አንድ ተጠርጣሪ ላይ ያርፋል።
ተጠርጣሪዋ 13/03/2013 ዓ,ም ለመውለድ ከደጀን ወረዳ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ገብታ በሠላም ተገላግላ ወደ ሀገሯ የተመለሰች ቢሆንም በ18/03/2013 ዓ,ም ልጁን አሞት ለማሳከም ተመልሳ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የመጣች ቢሆንም መዳን ባለመቻሉ የልጇ ህይወት አልፏል።
ህይወቱ ያለፈውን ልጇንም ሽንት ቤት በመክተት ወደ ማዋለጃ ክፍል በመሄድ አጋጣሚውን ተጠቅማ አቶ ስማቸው የኔአለም ታቅፎት የነበረውን ህጻን ይዛ በመጥፋቷን ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስም ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 10 ከወንድሟ ቤት ልጁን እንደያዘች ተገኝታለች።በተጠርጣሪዋ ላይም ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የምርመራ ክፍል ሀላፊው ጨምረው ገልጸዋል።የህፃኑ አባትም ልጁ እንዲገኝ ከፍተኛ ጥረት ላደረገው ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።
መረጃው የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የምርጫ ቦርድን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ አደረገ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው አመራር አባላት አቤቱታ ላይ ለመወሰን ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ ማድረጉን አስታወቋል።
[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው አመራር አባላት አቤቱታ ላይ ለመወሰን ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ ማድረጉን አስታወቋል።
[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ቤት በተደረገ ኦፕሬሽንና ብርበራ በግለሰቦች እጅ መያዝ የሌለባቸዉ የጦርመሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ከሀዲ ጁንታዉ የህዉሃት ቡድን እንደ ሀገር ብጥብጥና ቀውስ ለማድረስ አልሞ ረጅም አመታት በመዘጋጀት ጥቃት ማድረስ ከጀመረበት እለት አንስቶ በተደረጉ ፍተሻዎችና ብርበራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የተለያዩ የጦርመሳሪያዎች መያዛቸዉ ይታወቃል፡፡ በዚህም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከሀገር መከላከያ ሚንቴር ጋር በመተባበር በሀገር ክህደትወንጀል የተጠረጠሩ የጦር መኮንኖች ቤት በተደረገ ፍተሻ ከፋተኛ ጉዳትና ኪሳራ ማድረስ የሚችሉ የጦር መሳሪያዎች የጦር ሜዳ መነፀሮች፣ ጅፒኤስ፣ በሳተላይት የሚሰሩ ስልኮች፣ ቦንቦች፣ክላሽንኮቭ፣ብሬን፣ለእኩይ ተግባር ማስፈፀሚያ የሚውሉ የተቀየረው የሰራዊቱ የደንብ ልብስ እና ሌሎች በግለሰብ እጅ መያዝ የሌለባቸዉ መሳሪያዎች በፍተሻ ሊያዝ መቻሉ ተገልጿል፡፡
ፍተሻው አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችና የሀገሪቱ ቦታዎች የተካሄደ ሲሆን የተያዙ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎቹ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ሽብር ለመፍጠርና ሀገርን ለማበጣበጥ ጁንታዉ የህወሓት የጥፋት ቡድንና ተላላኪዉ የኦነግ ሸነ ሊጠቀሙባቸዉ እንደነበር ተደርሶባቸዋል፡፡
በመከላከያ ሚንስቴር ከፍተኛ አመራሮች በነበሩ ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ ከተቋሙ ወደ ግለሰቦች እጅ እንዲገቡ የተደረጉ መሳሪያዎች ባይያዙ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ቀውስ ያስከትሉ እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡በተደረገዉ ኦፕሬሽንና በህብረተሰቡ ጥቆማ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ መረጃ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

የምክር ቤቱ አባላት የህወሓት ቡድን በማይካድራ ዘርን መሰረት አድርጎ በፈጸመው ዘግናኝ ግድያ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጠየቁ!
የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የህወሓት ቡድን በማይካድራ ዘርን መሰረት አድርጎ በፈጸመው ዘግናኝ የንጹሃን ዜጎች ግድያ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጠየቁ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ጥያቄ እና አስተያየት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
የምክር ቤቱ ቤቱ አባላትም ጁንታው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አውግዘው፤ መከላከያ ሰራዊቱ ሀገርን ከጥፋት ለማዳን ለሰራው አኩሪ ስራ አድንቀዋል።
መንግስት ተገዶ የገባበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በቆራጥነት በመምራት የወሰደውን እርምጃም አስደናቂ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በሑመራ እና ሌሎች የወልቃይት አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት ዳግም ተመልሷል-ነዋሪዎች
ከህወሓት ቡድን ነጻ በወጡ የወልቃይት እና ሑመራ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት ዳግም መጀመሩን የአካባቢውን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ አረጋገጡ፡፡
ነዋሪዎቹ በሑመራ በባዕከር በቃፍታ እና በአካባቢው የአገልግሎቱን መጀመር አረጋግጠዋል፡፡
የአገልግሎቱን ዳግም መመለስ ለአል ዐይን አማርኛ ከተናገሩት መካከል አንዱ የሑመራ ነዋሪ የሆኑት አቶ አደም ጅብሪል አንዱ ናቸው፡፡
በአገልግሎቱ መቋረጥ ምክንያት በዙሪያችን በውስጥም በውጭም ካሉ ቤተሰቦቻችን ጋር መገናኘት ስላለሁ ሁኔታ መጠያየቅ እንኳ ሳንችል ቀርተን ነበር የሚሉት አቶ አደም አሁን ስላለንበት ሁኔታ መጠያየቅ መገናኘትም ችለናል ብለዋል፡፡
ሌላኛዋ የአካባቢው ነዋሪ ወ/ሮ አሚና መሃመድም ይህንኑ ነው ለአል ዐይን አማርኛ ያረጋገጡት፡፡
ተጠፋፍተን ስለ ገጠመን ችግር እንኳን ለመጠያየቅ ሳንችል ቀርተን ብዙ ተጨንቀን ተቸግረን ከርመናል ብለዋል አሁን ችግሩ እንደቀለላቸው በመጠቆም፡፡
የአካባቢው የስልክ እና ተያያዥ የቴሌኮም አገልግሎት በህወሓት እና በፌዴራል መንግስት መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ያለፉትን 30 ያህል ቀናት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በግጭቱ ምክንያት በማይካድራ እጅግ አሰቃቂ በሚል የተገለጹ ዘር ተኮር ሰብዓዊ ጥቃቶች መፈጸማቸው እና በርካቶች ቀያቸውን ለቀው ወደ አዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች መሰደዳቸውም አይዘነጋም፡፡
Via:- Al Ain
@Yenetube @FikerAssefa

‹‹ብሔራዊ ደህንነት ከሕግ እና ከአዋጅ ውጪ በግሉ ልዩ ትጥቅ ያላቸው ወታደሮች ነበሩት›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ወደ ስልጣን በመጡበት የመጀመሪያ ወራት አካባቢ አይደለም የአገርን ደህንነት ማስጠብቅ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ደህንነት እንኳን መጠበቅ የማይችሉብት ደረጃ ላይ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በዚህም የብሔራዊ ደህንነትም ከሕግና ከአዋጅ ውጭ በግሉ ልዩ ትጥቅ ያላቸው ወታደሮች እንደነበሩትም ለምክርቤቱ አባላት አስረድተዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ኅዳር 21/2013 እያካሄደ ባለው 6ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ተኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ እየሰጡ ይገኛል።

YeneTube
‹‹ብሔራዊ ደህንነት ከሕግ እና ከአዋጅ ውጪ በግሉ ልዩ ትጥቅ ያላቸው ወታደሮች ነበሩት›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ወደ ስልጣን በመጡበት የመጀመሪያ ወራት አካባቢ አይደለም የአገርን ደህንነት ማስጠብቅ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ደህንነት እንኳን መጠበቅ የማይችሉብት ደረጃ ላይ እንደነበሩ አስታውሰዋል። በዚህም የብሔራዊ ደህንነትም ከሕግና ከአዋጅ ውጭ በግሉ ልዩ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለውጡ እንደመጣ የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ላይ የነበሩ ሁኔታዎችን አስመልክተው ለፓርላማ ከሰጡት አስተያየቶች የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች-
👉 ቀድሞ ለምን ወደ እርምጃ አልተገባም የሚለው የኃይል አሰላለፍ ትንተና ስለሚጠይቅ ነበር፡፡
👉 አንድን ነገረ ከማድረግ በፊት በጥንቃቄ የኃይል አሰላለፍ ትንተና ማድረግ ስለሚፈልግ ነው፤
👉 መንግስት ለመሆን ጠላትን ማወቅ፣ የራስን አቅም ማወቅ፣ የጠላትን የማድረግ አቅምና የራስን አቅም ማወቅ ያስፈልጋል፤ ፓርቲ ነን እና ለምን በሶስት ወር ውስጥ መንግስት አንሆንም የሚባለው የኃይል አሰላለፍ ትንተና ካለመስራት የሚመነጭ ነው፣
👉 በህወሃት ጁንታ ላይ ለምን እርምጃ ቀድሞ አልተወሰደም የሚለው ከዚህ አንፃር ተገቢ አይደለም፡፡
👉 ጠቅላይ ሚኒስትር የሆንኩኝ ሰሞን ቢሮዬን ከፍተው የሚያስገቡኝ፣ ቆልፈው የሚያወጡኝ እነሱ ነበሩ፡፡
👉 የቤቴ ዋናው ቁልፍ እነዚህ ኃይሎች እጅ ነው የነበረው፣ ማታ አስገብተው የሚቆልፉብኝ እነሱ ነበሩ፣ ጠዋት ከፍተው የሚያስወጡኝ እነሱ ነበሩ፡፡
👉 እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን በእስር ቤት ውስጥ እንዳለ ግን ሚዲያ ላይ መቅረብ እንደሚችል ሰው ነው የነበርኩበት ሁኔታ፤
👉 የመጀመሪያ ጉዞ ወደ ሱማሌ ክልል የወሰድነው ከ30 ሺ በላይ ልዩ ኃይል ተደራጅቶ ኢትዮጵያ የመፈራረስ ስራ በዚያ በኩል ነበር የሚሰራው፤
👉 ሱማሌ ክልል ለመሄድ እኔ ሲነሳ አልሸባብ ሊገድልህ ስለሚችል መሄድ አትችልም አለኝ የደህንነት ሹሙ፡፡
👉 ትግራይ ሲሄድ ወጣቱ ለውጥ ፈላጊ ስለነበረ ሁሉም ተባባሪ ነበር፡፡
👉 አምቦ ለመሄድ ሲሞክር አትሂድ ኦነግ ይገድለሃል ተብያለሁ፣
👉 የሚገድልኝ ኦነግና አልሸባብ ሳይሆኑ ሊገድለኝ ያሰበው በጉያዬ ያለው ኃይል መሆኑ ስለገበኝ ተጨማሪ ጥበቃ አድርገን አምቦ ሄድን፡፡

ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ያዘች!
ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር በምትገኘው ከሰላ ግዛት አከባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ መያዟን አስታውቃለች።በሱዳን በግዛቷ ያተያዙት በርካታ የተለያዩ የጦር መሰሪያዎች ጠብመንጃ እና የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ጥይቶች ናቸው ተብሏል።የሀገሪቱ በፀጥታ ኃይሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዝ የቻሉት ከኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በኩል ወደ ሱዳን በሚያገናኘው ድንበር አከባቢ ሰሞኑን በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን የሱዳኑ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል።ከሰላ ግዛት የሚገኘው የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች አከባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ህገወጥ የጦር መሳሪያዎቸ ለመቆጣጠር ሁሌም በተጠንቀቅ እንደሚገኝ የግዛቷ የፖሊስ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ካሊድ አዋድ ቦሱፍ ተናግረዋል።
[ኢቢሲ]

‹‹ባለፉት ኹለት ዓመታት ውስጥ 113 ግጭቶች ነበሩ›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
ባለፉት ኹለት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ 113 ግጭቶች እንደ ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐበይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ከነበሩ ግጭቶች መካከል ፤በኦሮሚያ ክልል 37 ግጭቶች የነበሩ ሲሆን በግጭቱ ከአማራ እና ከሌሎች ብሔሮችም ውጭ የኦሮሞ ተወላጆች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና የኦሮሞ እናት ባሏን እንዲሁም ልጇን አጥታለችም ሲሉ ተናግረዋል።
ከኦሮሚያ ክልል ውጭ በአማራ ክልልም 23 ግጭቶች ፣በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 15 በአዲስ አበባ 14 ግጭቶች፣ በጋምቤላ በስደተኛ ካምፕ ወስጥ ጭምር 7 ግጭቶች እንደነበሩም ለምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል።
ከነዚህ ክልሎች በተጨማሪም በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ፣በሲዳማ ፣በጅግጅጋ እና በአፋር ጭምር ግጭቶች እንደነበርም ተናግረዋል።
ክልል ከክልሎች ጋር ጭምር ተጋጭተው እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚሁ ሁሉ ግጭቶች ውስጥ ግን በትግራይ ክልል አንድም ግጭት አልበረም ብለዋል።
✍Addis Maleda

በደጋሀቡር የመኪና አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላትን ህይወት ቀጠፈ!
በሱማሌ ክልላዊ መንግስት ደጋሀቡር ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለቱ ደግሞ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።አደጋዉ ቅዳሜ ከምሽቱ 12፡30 ላይ የደረሰ ሲሆን የጭነት መኪና ከቶዮታ መኪና ጋር በመጋጨታቸዉ መሆኑን የጃራር ዞን አደጋ መኮንን ሳጅን አህመድ ሀሰን ተናግረዋል።ተሽከርካሪው በጃረር ዞን ዮአሌ ወረዳ ወደ አውል መንደር በሚጓዝበት ወቅት ነበር አደጋውን ያደረሰው፡፡
Via @addiszeybe

የመከላከያ ሠራዊት በአብዛኛው ከአንድ አካባቢ በመጡ ሰዎች የተሞላ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ በመከላከያ ሠራዊት ሁሉም አዛዦች የትግራይ ተወላጆች እንደነበሩም አስታውቀዋል፡፡መከላከያና ደህንነት የነበሩ ሰዎች ለሥራ አመች ሜዳ የማይፈቅዱ እንደነበሩ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በመንግሥት ውስጥ ያሉ መንግሥታት ማንሳት አስፈላጊ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙንና የደህንነት ሹሙን በአንድ ጊዜ ማንሳታቸውን ነው ያስታወሱት፡፡ የደህንነት ሹሙ ከስልጣን ሲነሱ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ሰርቀው ወደ መቀሌ መሄዳቸውንም ነው የተናሩት፡፡
የተሰረቀው መሳሪያ የታወቀውም ከሰኔ 16 የግድያ ሙከራ በኃላ በተደረገ የተቋሙ ፍተሻ እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢያንስ መሳሪያውን ይመለስ በሚል ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር መወያዬታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ ፈታኝ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመከላከያ ተቋሙን፣ የደህንነት ተቋማት፣ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት ተቋም፣ የፖሊስ፣ የገንዝብ ደኅንነት ተቋማትን መለወጥ እንዳስፈለገም አስታውሰዋል፡፡
በመከላከያ ተቋም ባለ አራት ኮከብ ጄኔራሎች ከትግራይ ክልል 60 በመቶ፣ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ 40 በመቶ ብቻ ነበሩ ነው ያሉት፡፡ ሌትናል ጄኔራል ደግሞ 50 በመቶ ከትግራይ ክልል የነበሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሜጄር ጄኔራል 45 በመቶ፣ ብርጋዴል ጄነራል 40 በመቶ፣ ኮሎኔል 58 በመቶ፣ ሌትናል ኮሎኔል 66 በመቶ፣ ሺሕ አለቃ 53 በመቶ ከአንድ አካባቢ የመጡ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ በዚህ አካሄድ መከላከያውን ሚዛናዊ የሆነ ተቋም ለመፍጠር አስቸጋሪ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡
መከላከያውን አመራር የሚሰጠው ኃይል 80 በመቶው የሚሆነው ከትግራይ ክልል የመጣ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ በሀገሪቱ የነበሩ እዞች ዋና አዛዥና ምክትል አዛዥ ሙሉ በሙሉ ከትግራይ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ከሰሜን እዝ ውጭ በሌሎቹ እዞች ሎጂስቲክና የሰው ኃይል ከሌሎች ክልሎች የተውጣጡ ነበሩበት፡፡ በሰሜን እዝ ግን አዛዥ፣ ምክትል አዛዥ፣ ሎጂስቲክስና ሰው ኃይል አስተዳደር አራቱም ከትግራይ የመጡ መሆናቸውን ነው ያስታወሱት፡፡
የኢትዮጵያ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር መቶ በመቶ ከትግራይ ክልል የሆኑ እግረኛ ክፍለ ጦር ደግሞ 80 በመቶ ከትግራይ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ ሜካናይዝድ ብርጌዶች 85 በመቶና እግረኛ ብርጌድ 80 በመቶ ከትግራይ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡የመካለከያ ተቋም ስልጠና ተቋማት 85 በመቶ በትግራይ ተወላጆች ሲመራ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ ይህን የተዛባ አካሄድ የትግራይ ህዝብ ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ እንዳለበትና መደገም እንደሌለበትም ነው ያስገነዘቡት፡፡
የሙያ ብቃት እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም በሚገባው መውሰድ እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት፡፡ ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ መገንባት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ካሁን ቀደም የተገነባበት ስርዓትም የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል ለመወሰን የሚያስቸግር እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የደህንነት እና የመከላከያ ተቋም ስሪት ለበርካታ ግጭቶች መነሻ እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተከሰቱት ግጭቶች መነሻው ትግራይ ክልል ውስጥ የመሸጉት ቡድኖች እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ እነዚህ የቡድን ስብስቦች የሀገር ውስጥ ብጥብጥ ከመፍጠር ባለፈ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለማጋጬት ብዙ ሙከራ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ከለዉጡ በኃላ የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ማሻሻያ እንደተደረገበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ወታደሩ የህዝብ እንጂ የብልጽግና እንዳይሆን መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡
✍AMMA

በአማራ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ በሆኑት በመተከል እና በአዊ ዞን በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ በመምከር አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት ጥምር ኮሚቴው ውይይት እያካሄደ ነው።
ውይይቱ የአዊ ዞን አዋሳኝ በሆነው የመተከል ዞን በተደጋጋሚ ለሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እልባት ለመስጠት ያለመ መሆኑም ተገልጿል።እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት መውደም ለመታደግና መፍትሄ በማስቀመጥ የጋራ ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።በውይይቱ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት እና ቀጠናውን በኮማንድ ፖስት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አዛዦች መገኘታቸውን የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።

የሮኬት ክምችት ላይ ጥቃት ባለማድረስ ህዝብን ከጥፋት መታደግ ተችሏል። -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
በመቀሌና አድዋ ከተሞች የሚገኘውን የሮኬት ክምችት ባለ ማጥቃት ህዝብን ከጥፋት መታደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።በመቀሌና አድዋ ከተሞች በጠላት እጅ ወድቆ በነበረው ከፍተኛ የሮኬት ክምች ላይ ጥቃት ቢደረግ ከሚያስከትለው ጥፋት አንጻር መንግስት ሮኬቶቹን ከማውደም መቆጠቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።በዚህም ሊከሰት የሚችለውን ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋት መታደግ መቻሉን ነው የገለጹት።የጥፋት ቡድኑ ከዚህ ቀደም ላሰበው የጥፋት ተልዕኮው እንዲሆን አብዛኛውን የመከላከያ የጦር መሳሪያ በሰሜን እዝ ብቻ እንዲሆን ማድረጉንም አስታውሰዋል።

ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ስደተኞችን በሳምንት ውስጥ እንደሚቋቋሙ ተገለጸ!
በለውጥ ሂደት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆሩ ሰዎች ተፈናቅለው መልሰናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በሱማሌ እና በሌሎች ክልሎችም ስደተኞችን የመመለስ በቂ ልምድም አለን ሲሉ ተናግረዋል።ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥራቸው ወደ 30 ሺህ ገደማ ሰዎች እንደተሰደዱ ሪፖርቶች ያመላክታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ ስደተኞችን በሳምንት ውስጥ እናቋሙማለን ብለዋል።
ከተባበሩት መንግስታት አና ከሱዳን መንግስት ጋር ስደተኞችን ለማስመለስም በራችን ክፍት ነው ሲሉም ገልጸዋል።ግን አንድ ችግር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ፤ ከስደተኞቹ ውስጥ ሴቶች የሉም ሕጻናት የሉም ወጣት ብቻ ነው ስደተኛ የተባለው ይህ ወጣት ማነው የሚለው ጉዳይ ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል ብለዋል።አክለውም ‹‹ማይካድራ ላይ አርዶ ሄዶ ከሆነና ማስረጃ እና መረጃ ከተገኘበት በሕግ ይጠየቃል›› ያሉ ሲሆን ንጹሃን ዜጋ ለመመለስ ፍላጎት ላለው በራችን ክፍት ነው ሲሉም ተናግረዋል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ኅዳር 21/2013 6ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ተኛ ልዩ ስብሰባ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተው መርሃግብሩም ተጠናቋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል መባሉን አስተባበሉ!
የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል «ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል» ተብሎ የተነገረዉ ዘገባ «ሐሰት ነው» በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ደብረጽዮን «አሁንም በመቀሌ ከተማ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተዋጋን ነው።»ብለዋል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ባለፈው ቅዳሜ የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል።በወቅቱ ደብረጽዮን የመቀሌ ከተማን ለቀው መውጣታቸውን ለሮይተርስ በላኩት አጭር የጽሁፍ መልዕክት አረጋግጠዋል።የሕወሓቱ መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ወደ ደቡብ ሱዳን ሸሽተዋል የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ በሰጡት መልስ« ከትግራይ ክልል አልወጣሁም» ሲሉ ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል አቃባይ ቢለኔ ስዩም በበኩላቸው «የፌዴራል መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በማረጋጋት ስራ ላይ ተጠምዷል፤ ተበታትኖ ላለ ወንጀለኛ ንግግር መልስ መስጠት ጉዳያችን አይደለም» ሲሉ ደብረጽዮን «በመቀሌ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውግያ ቀጥለናል» ብለው መናገራቸውን ያጣጣሉበትን ሃሳብ ለሮይተርስ ነግረዋል።
[Reuters/DW]

ከ3 ሺህ በላይ በ'ጁንታ'ው ቡድን ታፍነው የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አልዋጋም ብለው ያመለጡ የጁንታው ልዩ ሀይል አባላት በደባርቅ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው!
በበየዳና ጠለምት መስመሮች የመጡ 3 ሺህ በላይ በ'ጁንታ'ው ታፍነው የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አልዋጋም ብለው ያመለጡ ጁንታው ያደራጃቸው ልዩ ኃይል በደባርቅ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው።የሠሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያየአለም ፈንታሁን እንደተናገሩት ከበየዳና ጠለምት ወረዳ ከተሞች ጀምሮ ሕብረተሠቡ አቀባበል በማድረግ የደከሙትን በማዘልና በመመገብ ደባርቅ እንዲደረሱ አድርገዋል ተብሏል።
[EBC]