YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ ዜጎቿን መልሳ ለማቋቋም እየሰራች ነው ሲሉ አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ!

መንግስት በስደት ሱዳን የሚገኙ ዜጎችን በትግራይ ክልል መልሶ የማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ።አቶ ዛዲግ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከጀርመን ድምጽ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ህወሃት በትግራይ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማቶችን በማውደም የትግራይ ህዝብን ከተቀረው አለም ጋር እንዳይገናኝ ስለማድረጉ አብራርተዋል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌ መግባቱን ተከትሎ ባለሙያዎች #የስልክ_መስመሮችን ለማስተካከልና ግንኙነቱን ለማስጀመር እየተሰሩ መሆኑንም አብራርተዋል።የህወሃት ቡድን በክልሉ ኤርፖርትን ጨምሮ መንገዶችንና ድልድዮችን ማፈራረሱን ገልጸዋል።

አሁን መንግስት እነዚህን መሰረተ ልማቶች መልሶ እየገነባ ነው ሲሉ ገልጸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ነገሮች በግልጽ የሚያደርግና ምንም የሚደበቅ ነገር እንደሌለው ነው ያስረዱት።አለምአቀፍ ስደተኞችን በማስተናገድ ኢትዮጵያ ከአለም ሶስተኛዋ ሃገር በመሆኗ ሰብአዊ እርዳታዎችን እንዴት ማሰራጨት እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች ብለዋል።የተበላሹ መሰረተ ልማቶችን በማስተካከል ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ ቀንና ሌሊት እየተሰራ ነው ብለዋል።ህወሃት በመረጠው ወታደራዊ አማራጭ የተሸነፈ በመሆኑ ድርድር ማድረግ የሚባለው የማይሆን እንደሆነ ነው ያስረዱት።አቶ ዛዲግ አብርሃ የትግራይ ህዝብ በህወሃት አስተዳደር የተማረረ በመሆኑ በድርድር ሰበብ ህወሃት ተመልሶ እንዲረግጠው አይፈልግም ብለዋል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa