በኤች አይ ቪ ሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ20,000 ጨመረ!
በኢትዮጵያ በ2012 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከባለፈው 2011 ጋር ሲነፃፀር የኤች አይ ቪ ስርጭት በ20 ሺህ በ2011 ከነበረው 649 ሺህ አመታዊ ስርጭት በ2012 ወደ 669 ሺህ ከፍ ማለቱን የፌዴራል ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ።የስርጭቱ መጨመር ምክንያት በህብረተሰቡ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለኤች አይ ቪ የሚሰጠው ትኩረት እየቀነሰ መምጣቱ ነው።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ኮቪድ 19 በመከሰቱ የቫይረሱ ምርመራ አየተቀዛቀዘ መምጣቱን የፌዴራል ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የኮምኒኬሽንና ህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር ዳንኤል በትረ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከሶስቱ ክልሎች ማለትም ከሶማሌ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ውጭ በሚገኙ በሁሉም ክልልና ከተማ መስተዳድሮች በወረርሽኝ ደረጃ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ ጋዜጣ፣ ነሀሴ 2 እትም
@YeneTube @FikerAssefa1

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ነሃሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም አምስተኛ ዙር ነፃ የስራ ዘመቻ ያካሂዳል!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዋናው መስሪያቤትና በስሩ በሚገኙ በሁሉም የክልልና የመስተዳድር ተጠሪ ቢሮዎች ዛሬ ነሃሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም አምስተኛ ዙር ነፃ የስራ ዘመቻ ያካሂዳል፡፡የዋናው መስሪያቤት፣ የሪጅኖች፣ የዲስትሪክቶች፣ የሁሉም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ሠራተኞች በተሟላ መልኩ በቢሮና በመስክ ደረጃ እንደ መደበኛ የስራ ቀን ለደንበኞች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡እንዲሁም የተቋሙ የቴክኒክ ሰራተኞች በተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ብልሽት ያጋጠማቸው የኤሌክትሪክ መስመሮችን ይጠግናሉ፡፡አገልግሎት ፈላጊ ደንበኞች ይህንን አውቃችሁ፣ ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን መስሪያ ቤቱ አሳውቋል፡፡
ምንጭ:የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በጉባ በተፈጸመው ጥቃት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 121 ደረሰ።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጉባ ወረዳ ሐምሌ 20/2012 ዓ.ም ምሽት 2፡30 አካባቢ በጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ የ13 ንጹኃን ዜጎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል::የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው የብሔር ግጭትና አለመረጋጋት ለመፍጠር ዓልሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ቡድን አካል ናቸው ተባሉ 121 ተጠርጣሪዎችና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል፡፡የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ ሀምደኒል ወጣቶችን በመመልመል፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር መከላከያ እና ከመንግስት የጸጥታ ሥራ የተቀነሱ ግለሰቦችን በመያዝ በሱዳን ድንበር አካባቢ አቡልታ በተባለ ቦታ በአማርኛ፣ በጉሙዝኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች የጥፋት ስልጠና ሲሰጥ እንደነበር በኦፕሬሽኑ ወቅት መረጋገጡንና አስረጂ መረጃዎች መገኘታቸውንም አብራርተዋል፡፡የአካባቢውን ሠላም ለማረጋገጥ የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከሀገር መከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት እያደረጉት ያለውን መስዋዕትነት የታከለበት ትግል አጠናክረው እንደሚቀጥሉና እየተወሰደ ያለውን የሕግ የበላይነት ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ህብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ ማቅረባቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

በህንድ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ በጥቂቱ 18 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡ ንብረትነቱ የህንድ የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን በደቡባዊቷ ኬራላ ግዛት ካሊከት አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ነው የተከሰከሰው፡፡
አውሮፕላኑ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ህንዳውያንን ከዱባይ ወደ ሃገራቸው ይዞ ከተመለሰ በኋላ በሚያርፍበት ወቅት መጋጨቱም ነው የተሰማው፡፡
Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa

የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ባጋጠመው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ግምገማ እያካሄደ ነው፡፡
ግምገማው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡በግምገማው ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከልና በልዩ ትኩረት በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል ማህበረሰብ ንቅናቄ እና ምርመራ (ማንም) ዘመቻ፡ 'ምክንያት አልሆንም' በሚል መሪ ቃል ይፋ አድርገዋል፡፡
የ “ምክንያት አልሆንም!” ዋነኛ አላማ ማንኛውም ሰው ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት ላለመሆን ራሱን የሚከላከልበት፣ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡንና አካባቢውን የሚጠብቅበት እንዲሁም በተሰማራበት ሙያ ሁሉ ሃላፊነት በመውሰድ በእኔነት ስሜት ለራሱ ቃል የሚገባበት ነው፡፡
#EPHI
@YeneTube @FikerAssefa1
የ “ምክንያት አልሆንም!” ዋነኛ አላማ ማንኛውም ሰው ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት ላለመሆን ራሱን የሚከላከልበት፣ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡንና አካባቢውን የሚጠብቅበት እንዲሁም በተሰማራበት ሙያ ሁሉ ሃላፊነት በመውሰድ በእኔነት ስሜት ለራሱ ቃል የሚገባበት ነው፡፡
#EPHI
@YeneTube @FikerAssefa1
በአፊኒ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚቀርበው አፊኒ መፅሄት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ ይመረቃል።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች ይገኛሉ። እንዲሁም ጋቦ የተሰኘው የሲዳማ ባህል ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ይመረቃል።
ምስል :- አፊኒ መፅሄት የፊት ገፅ
@Yenetube @Fikerassefa
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች ይገኛሉ። እንዲሁም ጋቦ የተሰኘው የሲዳማ ባህል ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ይመረቃል።
ምስል :- አፊኒ መፅሄት የፊት ገፅ
@Yenetube @Fikerassefa
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል!
የወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በበይነ መረብ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት እያስመረቀ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው የፌስ ቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።በዕለቱ የተመረቁት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች 359 ወንድ እና 70 ሴት በድምሩ 429 መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን ገልጸዋል።

ከኢህአፓ መስራቾች አንዱ የነበረው የብርሃነመስቀል ረዳ የትግል ታሪክ በባለቤቱ ታደለች ኃይለሚካኤል ተጽፎ ለንባብ በቃ። “ዳኛ ማነው ?” የተሰኘው መጽሐፍ የኢህአፓ ታጋይ የነበሩት የመጽሐፉ ደራሲ ታሪክንም በጥምር ያካተተ ነው።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች በድኅረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 72 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። የድህረምረቃ ተማረዎችን ያስመረቀው ለ3ኛ ዙር መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው ገልጸዋል።
#MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa1
#MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት አመት 14 ቢሊዮን ብር አተረፈ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት አመት የ14 ቢሊዮን ብር ወይም (424 ሚሊዮን $) ትርፍ አስመዝግቧል። ይህ ትርፍ ግን ይህ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ10.2 % ያነሰ፣ ለማሳካት ከተያዘው እቅድ ደግሞ 64% ብቻ እንዳሳካ ሪፖርተር ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት አመት የ14 ቢሊዮን ብር ወይም (424 ሚሊዮን $) ትርፍ አስመዝግቧል። ይህ ትርፍ ግን ይህ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ10.2 % ያነሰ፣ ለማሳካት ከተያዘው እቅድ ደግሞ 64% ብቻ እንዳሳካ ሪፖርተር ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
የደቡብ ክልል ምክር ቤት 38 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የክልሉ መንግስት በጀትን አጽድቋል።
የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው ውሎውም የ2013 የየደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት በጀትን ተመልክቷል።ምክር ቤቱ ለ2013 በጀት ዓመት 38 ቢሊየን 21 ሚሊየን 970 ሺህ 828 ብር ሆኖ የቀረበለት የክልሉ መንግስት በጀት ላይም ተወያይቷል።በጀቱ ከፌደራል መንግስት ድጎማ፣ ከውስጥ ገቢና ከሌሎች የገቢ አማራጮች የሚገኝ እንደሆነ በጉባኤው ላይ መነሳቱን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህም ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 28 ቢሊየን ከፌደራል መንግስት የሚገኝ ድጎማ ሲሆን፥ 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚሆነው ደግሞ ከክልሉ ልዩ ልዩ ገቢዎች የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።
የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት ዓምናው ማለትም ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃር የ12 ነጥብ 24 በመቶ ብልጫ ያመው መሆኑም ተጠቁሟል።የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በበጀቱ ላይ በሰጡት ማብራሪያም፥ በ2013 በጀት በሁሉም ዘርፎች የበጀት አቅምን ባገናዘበ መልኩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ እንደሚሰራ ገልፀዋል።የበጀት ክፍተት ከተገኘ ደግሞ አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች በጥናት ላይ በመመርኮዝ እንደሚሰራም ነው አቶ ርስቱ ያብራሩት።የክልሉ ምክር ቤትም በቀረበለት የ2013 የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምጽና በአንድ ድምፀ ታቅቦ አጽድቆታል።
#FBC

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 801 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ10 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 10 ሺህ 919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ 253 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።ከዚህ ባለፈ የ10 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 390 መድረሱንም አመላክተዋል።በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 292 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 707 መድረሱም ተገልጿል።

በህፃናት ዙሪያ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች በሚሰሩ ተቋማት የስቱዲዮ ጉበኝትና ዉይይት ተካሄደ፡፡
በህፃናት ዙሪያ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች በሚሰሩ የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥንና ኢትዮጲስ ስቱዲዮ በመገኘት ጉብኝት ያደረጉት ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር፤ ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ ፕሮግራሞች እንዴት ደረጃውን በጠበቀና ወጥነት ባለዉ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ይቻላል በሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ ዉይይት በጋራ ማካሄድ ነው፡፡ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን የቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ ትዉልድን የሚቀርፅና የሚያንፅ ስራዎችን በፕሮግራሞቻቸው ላይ አፅንዖት ሰጥተው እየሰሩ በመሆናቸዉ አመስግነው በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጎናችሁ ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ዶ/ር ጌታቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እንደተናገሩት በህፃናት ላይ የሚሰሩ የሬድዮ እና የቴሌቭዥን ጣቢያ ፕሮግራሞች ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጠን እና በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሚመራ በዘርፉ ልምድ ያላቸው የግልና የመንግስት የብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ያካተተ ግብረ ሀይል (Task Force) የተቋቋመ ሲሆን ግብረ ሀይሉ የሚመራበት የድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል፡፡ጉብኝት የተካሄደባቸው የዝግጅት ክፍል የበላይ አመራሮች በስራዎቻቸው ላይ እየገጠማቸው ያሉ ችግሮችና ተግዳሮቶችን በመግለጽ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እና ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ: የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚ/ር

ፈረንሳይና ተመድ በቤይሩቱ ፍንዳታ ለደረሰው ውድመት ለመታደግ እርዳታ ሊያሰባስቡ ነው!
በሊባኖስ መዲና ቤይሩት በተከሰተው ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ የደረሰውን ከፍተኛ ውድመት ለመታደግ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመሆን የእርዳታ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማዘጋጀታቸውን ፈረንሳይ አስታወቀች። መርሃ ግብሩ ነገ እሁድ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በቪዲዮ በሚደረግ የቃል መግባት ስነስረዓት እንደሚካሄድ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ዛሬ አስታውቋል።የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው በመርሃ ግብሩ ላይ እንደምትሳተፍ ከወዲሁ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የመርሃ ግብሩ መ,ዘጋጀቱን እንደሰሙ በሰጡት መግለጫቸው ከፕሬዚዳንት ማክሮን ፣ ከሊባኖስ መሪዎች እና ከተቀረው የዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ ጋር ሊባኖስ መረዳት በምትችልበት አግባብ እንመክራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን» ብለዋል። «ሊባኖስ የደረሰባትን ድንገተኛ አደጋ ሁሉም ማገዝ ይፈልጋል» ሲሉ ትራምፕ አክለዋል።ባለፈው ማክሰኞ በቤይሩት ወደብ ያለጥንቃቄ ለአመታት ተከማችቶ የነበረ አሞንየም ናይትሬት የተባለ የኬሚካል ፈንድቶ ከ150 በላይ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቶ ከ6,000 ሺ በላይ ሰዎችን ለአካል ጉዳት ዳርጎ ከፊሉን የከተማዋን ክፍል እንዳልነበር አድርጓል።
#DW

በጥቁር አንበሳ ኮሌጅ የህክምና ተማሪ ለነበረችውና በግፍ ለተገደለችው ሀይማኖት በዳዳ ሐውልት እንዲቆም ወላጅ አባቷ ጠየቁ ።
ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ም በኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ላይ በሚገኘው የላቦራቶሪ ቤተ ሙከራ ክፍል ለምርምር በገባችበት ሁኔታ በግድያ ህይወቷ ያለፈው ሀይማኖት በዳዳ ወላጅ አባት የሆኑት አቶ በዳዳ ፈይሳ ትናንት ነሀሴ 1,2012 ዓ.ም አመሻሽ 11 ሰአት ላይ በጥቁር አንበሳ ት/ቤት የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባዘጋጀው ሟች ሐይማኖት በዳደን ለማሰብ በተዘጋጀ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ልጃቸው ላይ ለተፈፀ ግድያ ፍትህ አንዲሰጥ እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ተመሳሳይ ነገር አንዳይፈፅማባቸው በስሟ ፍውንዴሽን አንዲሁም በገተደለች ግቢ ውስጥ ሀውልት ሊቆምላት ይገባል ብለዋል ።
" ልጄ እምቅ ሀይልና እውቀት እያላት በነፍሰ በሎች ሒወቷ ተነጥቋል ።ለቤተሰብ መሪር ሀዘን ለሀገር ኪሳራ ነው ።ፍትህ ፣ፍትህ እፈልጋለው " በማለት በሀዘን ስሜት ንግግር አድረግዋል።
የጥቁር አንበሳ ሳይንስ ኮሌጅ ሀላፊ ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ የተፈፀመው ወንጀል አሳፋሪ አና አሳዛኝ መሆኑን ገልፀው ሀውልት የማቆሙን ጉዳይ የኮሌጁ ሀላፊዎች ተማክረው በቀጣዩ ሳምንት ለሟች ቤተሰቦች አንደሚያሳውቁ ቃል ገብተዋል።
የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ተዋካይ ኮሌጁ የዚህ አይነት ተግባር አንዳፈፀም ለተማሪዎች ጠበቀ ያለ ጥበቃ ማድረግ አንደሚገባው ገልፀው የሐይማኖት ጉዳይ በጥልቀት መርምሮ ትክክለኛውን ፍርድ ሊሰጥ አንዲመገባ አሳስበዋል። ለዚህም ማህበሩ የተቻለውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
Via Fidelpost

👍1
ፎቶ:ጃፓን፣ ቶክዮ አንድ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ ከመስተዋት የተሰራ የህዝብ መፀዳጃ ቤት(Public Toilet)
ውስጡ ሰው ቆልፎ እየተጠቀመበት ከሆነ መስተዋቱ (Opaque) ወይም ብርሃን የማያስገባ(ውስጡን ማየት የማይቻል) ይሆናል፣ ከ30 ደቂቃ በኋላ ደግሞ ተመልሶ ብርሃን የሚያስገባ፣ ውስጡም በግልጽ የሚታይ ይሆናል።
እድሉን አግኝተው ቶኪዮን ቢጎበኙዋት ይህን መፀዳጃ ቤት ደፍረው ይጠቀሙታል?😊 መልሱን ለራሳችሁ!

በቼክ ሪፐብሊክ በአንድ ሕንፃ ላይ በተነሳ እሳት 11 ሰዎች ሞቱ !
በቼክ ሪፐብሊክ በአንድ ሕንፃ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ሦስት ህፃናትን ጨምሮ 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።ከሟቾቹ መካከል ስድስቱ በእሳቱ የሞቱ ሲሆን አምስቱ ከአደጋው ለማምለጥ ከ11ኛ ፎቅ ከዘለሉ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የእሳት አደጋ ሰራተኞችንና አንድ ፖሊስን ጨምሮ አስር ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።በሰሜን ምስራቅ ከተማ ቦሁሚን ቅዳሜ ዕለት በአንድ ሕንፃ ላይ ከነበረ ክፍል የተነሳው ይህ የእሳት አደጋ በአገሪቷ ታሪክ የተከሰተ አስከፊ አደጋ ነው ተብሏል።
#BBC

በሀረሪ ክልል 35 ህገወጥ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው÷በክልሉ ሶፊ ወረዳ የፀጥታ ሀይሉ ባደረገው ቅንጅታዊ ስራ 35 ሽጉጦችና 2 ክላሾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ይዘው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ያህያ አብዱሰላም አስታውቀዋል።ሀላፊው አያይዘውም በክልሉ በተለያዩ ግዚያት ሲነሱ የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲባል በተያዘለት እቅድ መሰረት የመከላከያ ሰራዊት ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የፌደራልና የሀረሪ ፖሊስ በጋራ በመቀናጀት በሶፊ ወረዳ ባደረጉት የኦፕሬሽን ስራ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹና 1 ኮምፒዩተር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።