የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ150 ዳኞች ሹመት ሰጠ።
ምክር ቤቱ ሁለት አዋጆችንም መርምሮ አጽድቋል።11ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት በመጨረሻ ቀን ውሎው 150 ለሚሆኑ ዳኞች ሹመት ሰጥቷል።የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አጎ በምልመላ ወቅት እጩ ዳኞቹ እድሜያቸው ከ25 አመት በላይ የሆነ፣የተሻለ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውና በጥሩ ስነ ምግባር ረገድ በህብረተሰቡ ዘንድ የተመሰከረላቸው እንዲሆኑ ጥረት መደረጉን አብራርተዋል።
በዚህም 24 ለከፍተኛ ፍርድ ቤት እና 126 ለወረዳ ፍርድ ቤት ዳኝነት በድምሩ 150 ዳኞች በእጩነት ቀርበው ምክር ቤቱ ሹመታቸውን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
ምንጭ: የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa1

ሥልጣን የሚለቁ የፓርቲ አባል ያልሆኑ ተሿሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው!
(በሪፖርተር የቀረበ)
የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር የመንግሥት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በርካታ የፓርቲ አባል ያልሆኑ ኃላፊዎች ቢሾሙም፣ በየጊዜው ከኃላፈነታቸው በመልቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር የነበሩት አቶ አበበ አበባየሁ፣ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ አስታውቀው ነበር፡፡ ይሁንና ከሰሞኑ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽንን ከጥንስሱ ጀምረው በመሥራች ኃላፊነት የመሩትና በሕክምና ሙያ የሠለጠኑት ኤፍሬም ተክሌ (ዶ/ር) ኃላፊነታቸውን ከለቀቁ ጎራ ተቀላቅለዋል፡፡ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ ኮሚሽኑን ሲመሩ የቆዩት ኤፍሬም (ዶ/ር)፣ በግል ጉዳይ ምክንያት ለመልቀቅ መገደዳቸውን ይፋ ያደረጉት ሐሙስ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ደብዳቤ ነበር፡፡
‹‹ውድ የሥራ አጋሮቼና ወዳጆቼ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነርነቴን በመተው መልቀቂያ የማስገባቴን ዜና የማካፍላችሁ በተደባለቀ ስሜት ነው፡፡የምለቀውም ሙሉ በሙሉ በግሌ ምክንያት ነው፤›› በማለት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኃላፊነታቸው ወቅትና ከዚያም በፊት በነበረው የመንግሥት አገልግሎት በጠቅላላው ከአሥር ዓመታት ያላነሰ ጊዜ ማሳለፋቸውን ያስታወሱት ኤፍሬም (ዶ/ር)፣ በዚህ ወቅት ቤተሰባቸው ላይ ጫና ማሳደሩን፣ በሥራ ምክንያት ለረዥም ጊዜ ከቤተሰብ ጋር የሚያሳልፉበት ወቅት እምብዛም መሆኑን ጠቃቅሰዋል።ከእሳቸው በፊት የኃላፊነት ቦታቸውን የለቀቁትም ተመሳሳይ ምክንያቶችን አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር የነበሩት አቶ አበበም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሐሳብ ማካፈላቸው ይታወሳል፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርብ በሆነ ኃላፊነት ቦታ ይሠሩ የነበሩት አቶ አበበ፣ ወደ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዲመጡ የተደረገው የቀድሞው ባልደረባቸው የነበሩት በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር) በተመሳሳይ ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ማስታወቀቸው ተከትሎ ነበር፡፡በአሁኑ ወቅት ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ማስገባታቸው ከሚነገርላቸው መካከል፣ የስትራቴጂ ጉዳዮች ኢንስቲዩት ኃላፊ አቶ ሃሌሉያ ሉሌ እንደሚገኙበት የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡እንደ ምንጮች ማብራሪያ ከሆነ አቶ ሃሌሉያ መልቀቂያ ካስገቡ ሁለት ወራት አስቆጥረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጥያቄያቸው እንደ ሌሎቹ ወዲያውኑ ተቀባይነት እንዳላገኘ ይነገራል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሥራ የማያመቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ እንደመጡ፣ አንዳንዶችም መስቀል አደባባይ አካባቢ የሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው ብዙ ዕድሳት ተካሂዶበት ለሥራ በሚያመች መንገድ ታድሶ በተዘጋጀበት ወቅት ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት ለሚዘረጋው ፕሮጀክት በጽሕፈት ቤትነት የተወሰደበትን አጋጣሚ በማጣቀስ፣ ለመልቀቃቸው አንዱ ምክንያት ያደርጉታል፡፡
እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን በማንሳት ለአቶ ሃሌሉያም ሆነ ለኤፍሬም (ዶ/ር) ጥያቄ ለማቅረብና ምላሾቻቸውን ለማካተት የተረደገው ጥረት አልተሳካም፡፡ሁለቱም ኃላፊዎች በስልክም በአጭር ጽሑፍ መልዕክትም ተጠይቀው ምላሽ አልሰጡም፡፡ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየተመናመነ የመጡትና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ያልሆኑ የመንግሥት ሹማምንት የስንብት ጉዳይ ጥያቄ እያስነሳ ነው፡፡አንዳንዶቹ ኃላፊዎች የፓርቲ አባል ባለመሆናቸው ምክንያት፣ የፓርቲ አባል በሆኑት ዘንድ የሚነሳባቸው ጥያቄ አለ፡፡ ቢሮክራሲውን ለታማኝ የፖለቲካ ሹማምንት ከማስጠበቅ ባሻገር ከጥቅማ ጥቅምና ከክፍያ ጋር በተያያዘ በፓርቲ አባላት ዘንድ ቅሬታና ስሞታ እንደሚቀርብ የሚገልጹ ወገኖች፣ እየለቀቁ ለሚገኙ ሹመኞች መነሳት አንዱ መንስዔ እንደሆነ ያቀርባሉ፡፡
በሌላ በኩል ከፓርቲና ከፖለቲካ ውጪ የተሾሙ ኃላፊዎች የመንግሥትን መዋቅር ለማጎልበትና ቢሮክራሲውን ለማጠናከር ሲባል በተመድና በሌሎችም ተቋማት የሚፈከላቸው ደመወዝና ሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞች ለረዥም ጊዜ በቦታቸው የማያቆያቸው እንደሆነ፣ ለአጭር ጊዜ በተመደቡበት ቦታ ሠርተው የሚፈልገለውን ውጤት አስገኝተው እንዲሄዱ ስለሚፈለግ መልቀቃቸው ብዙ እንደማያስገርም የሚያነሱም አልታጡም፡፡በዚህም ተባለ በዚያ እየለቀቁ ያሉት ኃላፊዎች ለመንግሥት የቢሮክራሲ መዋቅር አመኔታን ለማትረፍና ግልጽነትን ለማስፈን ብዙ አስተዋጽኦ ሊያደርጉበት የሚችሉበት ዕድል እንደነበር፣ መንግሥት የሥራ ኃላፊነቶችን የሚሰጠው ለፖለቲካ ታማኞች ብቻ ሳይሆን በዕውቀት፣ በክህሎትና በትምህርታቸው ብሎም በሚመደቡበት ቦታ ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚችሉ ለሚታመንባቸው በተለይም ደግሞ ወጣቶች ለሆኑት መሆኑ ትልቅ ትርጉም እንደነበረው የሚጠቁሙ አስተያየት ሰጪዎች፣ ይህ አሠራር እየደበዘዘ እንዳይመጣ ሥጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ቢሮክራሲው በፖለቲከኞችና በፓርቲ አባልነታቸው ብቻ በሚሾሙ ኃላፊዎች ከተሞላ ነባሩ አዙሪት ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ያሳስባሉ፡፡

በአማራ ክልል ተጨማሪ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 2 ሺህ 293 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።በአጠቃላይ እስከ ዛሬ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 703 መድረሱንም ጤና ቢሮው ገልጿል።በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ በክልሉ ሰባት ሰዎች ማገገማቸውን ጤና ቢሮው አስታውቋል። በአጠቃላይ ያገገሙትም 489 ደርሰዋል።
#AMMA

100 ሺህ የኮቪድ 19 የምርመራ ኪት በድጋፍ መገኘቱን ጠቅላይ ሚ/ሩ አስታወቁ።
ጠ/ሚር አብይ በማህበራዊ ገፃቸው "የኮቪድ 19 ምርመራን በስፋት በምናካሂድበት በዚህ ወቅት፣ የአጋሮቻችን ድጋፍ ስላልተለየን እናመሰግናቸዋለን። ዛሬ በልገሳ የቀረቡ 100,000 መመርመሪያ ኪቶችን ተረክበናል" ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠ/ሚር አብይ በማህበራዊ ገፃቸው "የኮቪድ 19 ምርመራን በስፋት በምናካሂድበት በዚህ ወቅት፣ የአጋሮቻችን ድጋፍ ስላልተለየን እናመሰግናቸዋለን። ዛሬ በልገሳ የቀረቡ 100,000 መመርመሪያ ኪቶችን ተረክበናል" ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa1
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለአንድ መቶ 85 ሰዎች በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 44 ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ ተገለጸ፡፡ከክልሉ ላራብራቶሪ ምርመራ ማዕከል የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ በአጠቃላይ በክልሉ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥርም 9,282 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ዛሬ
በበሽታው የተያዙ ሰዎች :- 565
ህይወታቸው ያለፈ :- 17
ከበሽታው ያገገሙ :- 499
በጽኑ የታመሙ :- 163
ዛሬ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገው :- 9035
@YeneTube @FikerAssefa
በበሽታው የተያዙ ሰዎች :- 565
ህይወታቸው ያለፈ :- 17
ከበሽታው ያገገሙ :- 499
በጽኑ የታመሙ :- 163
ዛሬ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገው :- 9035
@YeneTube @FikerAssefa
የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት መያዛቸው ተሰማ።
ተጨማሪ መረጃዎች ሲደርሱን የምናቀርብ ይሆናል።
@Yenetube @Fikerassefa

ሰበር ዜና!
የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ!
የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገለፀ።ፓርቲዉ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ዛሬ ምሽት ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ዉሳኔዉች ላይ በመድረስ ነዉ።የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ጉባዔዉን ሲያጠናቅቅ በሰጠዉ መግለጫ አቶ ለማ መገርሳን፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ማገዱን አስታዉቋል። የኦሮምያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ስብሰባዉ እንደተጠናቀቀ ለክልሉ የመንግሥት ቴሌቭዥን «OBN» ዛሬ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በፓርቲ ዉስጥ ካላቸዉ ኃላፊነት ተነስተዋል፤ እገዳዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል። እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ አንደሚችሉ ፓርቲዉ መወሰኑን አቶ ፈቃዱ በመግለጫቸዉ ተናግረዋል።አቶ ለማ መገርሳና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ አባለት የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።
#DW

በወላይታ የዞኑን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ 26 ግለሰቦች ታሰሩ!
(በኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ቁጥራቸው 26 የሚሆኑ ግለሰቦች ትናንትና እሁድ ነሐሴ 3፤ 2012 በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ ክልል አስታወቀ። የግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ የዞኑ አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ሶዶ ከተማ ወጣቶች ተቃውማቸውን ሲያሰሙ ማምሸታቸውን እና የጥይት ተኩስም ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።የደቡብ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን እና ጸጥታ ቢሮን ጠቅሶ ምሽቱን ባቀረበው የዜና እወጃ፤ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ 26 ግለሰቦች ዛሬ ከሰዓት መያዛቸንው ዘግቧል። ጣቢያው የአመራሮቹን ማንነት ግን በዝርዝር አላሳወቀም።
በወላይታ በተቃዋሚ ፓርቲነት የሚንቀሳቀሰው የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ እና የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች መታሰራቸውን ምሽቱን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። ዛሬ ከታሰሩት ውስጥ የሌላኛው ተቃዋሚ ፓርቲ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ምክትል ሊቀመንበር፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተወካዮች፣ የተለያዩ አክቲቪስቶች እና ሌሎች ግለሰቦች እንደሚገኙበትም ይፋ አድርጓል።ዎብን፤ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በሶዶ ከተማ ካለው ጉተራ አዳራሽ በስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት እንደሆነ በመግለጫው ጠቁሟል። ከአመራሮቹ ጋር ተሰብስበው የነበሩት ከተለያየ አደረጃጀት የተወጣጡ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ አስተባባሪ ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት እንደነበሩም አመልክቷል።
ግለሰቦቹ ከጉተራ አዳራሽ ተይዘው ሲወሰዱ የተመለከቱ አንድ የአይን እማኝ የአዳራሹ ቅጥር ግቢ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል ቀይ ኮፍያ ባጠለቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲጠበቅ እንደነበር መመልከታቸውን አስረድተዋል። ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ ከአዳራሹ ግቢ የተወሰኑ ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታጅበው ወደ ውጭ ከወጡ በኋላ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ በሚጠቀሙበት የላንድክሩዘር መኪና እና የፌደራል ፖሊስ አባል በጫነ ሌላ ተሽከርካሪ እንዲገቡ ተደርጎ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን አብራርተዋል።ሁለቱ ተሽከርካሪዎች ከፊታቸው እና ከኋላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በጫኑ ፒክ አፕ መኪናዎች ታጅበው እንደነበር እማኙ ተናግረዋል።የተወሰዱትን ሰዎች ማስክ አጥልቀው ስለነበር ማንነታቸውን ከርቀት ለመለየት እንዳልቻሉም አክለዋል። ሆኖም በጉተራ አዳራሽ የነበሩ ሰራተኞች ከተወሰዱት ሰዎች መካከል “የዞኑ አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤ እና አክቲቪስት አሸናፊ ከበደ እንደሚገኙበት ነግረውኛል” ብለዋል።
ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ የነበረውን ይህን ክስተት፤ የተለመደ የባለስልጣን እንግዳ አጀብ እንደሆነ በማሰብ የአካባቢው ሰዎች ለሁኔታው እምብዛም ትኩረት አለመስጠታቸውን እማኙ ጠቁመዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ግን በርካታ ወጣቶች ወደ አዳራሹ በመምጣት ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸውን አመልክተዋል።ወጣቶቹ ወደ አዳራሹ የሚወስደውን ጨምሮ በከተማይቱ ያሉ ሌሎች መንገዶችን ድንጋይ በመደርደርና ጎማ በማቃጠል መዝጋታቸውን የሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የተዘጉ መንገዶች ለማስከፈት እና ተቃዋሚ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት በተደጋጋሚ ይተኮስ እንደነበርም ገልጸዋል። በጸጥታ ኃይሎች እና በወጣቶች መካከል የነበረው ፍጥጫ በተለይ በርትቶ የተስተዋለው “አንደኛ መስመር” ተብሎ በሚታወቀው የአስፋልት መንገድ እንደነበርም አስታውቀዋል።
የጥይት ተኩሱ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎች ከዚያ በኋላ በከተማው ያለው ሁኔታ ረገብ ማለቱን አመልክተዋል። በከተማይቱ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡም ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው ለመሄድ ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል።ተቃዋሚው የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፤ የወላይታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄውን ሲያቀርብ የነበረው በሰላማዊ መንገድ እንደነበር አስታውሶ ሆኖም የፌዴራል እና የደቡብ ክልል መንግስታት ሰላማዊ ጥያቄን “ወደ ሁከት ለመቀየር” ሞክረዋል ሲል ከስሷል። ሁለቱም አካላት የጀመሩትን “ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲያቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለን” ሲል አሳስቧል።
“ፍትሐዊ፣ ሕገ-መንግሥታዊና ፍፁም ሠላማዊ የሆነ መንገድ በመጠቀም የዎላይታ ሕዝብ ለሚጠይቀው ጥያቄ በሠላም ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አመራሮችንና ታጋዮችን የማሠር እርምጃ ፈፅሞ ሕገ-ወጥና የመብት ጥሰት ተግባር ነው” ሲል ፓርቲው የዛሬውን እስር ኮንኗል።ዎብን የታሠሩ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና የዎላይታ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው በመግለጫው ላይ ጥያቄውን አቅርቧል።

በቤሩት የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ ሁለት የሀገሪቱ ሚንስትሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
በቤሩት ወደብ ወደብ አቅራቢያ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ሳቢያ በጥቂቱ ከ158 በላይ ዜጎች ሲሞቱ 6 ሺህ የሚሆኑት ቀላልና ከባድ ጉዳት አስተናግደዋል፡፡በዚህም ሳቢያ በከተማዋ ሀይል የቀላቀለ የተቃውሞ ሰልፍ በሁለተኛ ቀኑም ቀጥሎ ተስተውሏል፡፡ከፍንዳታው በኋላ በፈረንሳይና በአሜሪካ የሚመራው አለም አቀፍ ድጋፍ ጥሪ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡በዚህም 300 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የሚሆን ገንዘብ ለሊባኖስ ህዝብ በቀጥታ እንደሚሰጥ ቃል ተገብቷል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ የነበሩ ሁለት የሀገሪቱ ሚንስትሮች በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣን መነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡ሚንስትሮቹ ስልጣን የለቀቁት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ለሁለተኛ ጊዜ በጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ጠንካራ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው፡፡የሊባኖስ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ማናል አብደል ሳማድ ስልጣን መልቀቃቸውን ባሳወቁ በሰዓታት ልዩነት የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትሩ ዳሚያኖስ ካታር ስልጣን መልቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡ሚንስትሮቹ ስልጣን መልቀቃቸውን ባሳወቁት ወቅት የሀሰን ዲያብ መንግስት የህዝብን ፍልጎት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡
(Ethio FM)

የሶማሌ ክልል መንግሥት በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላትን ተከትሎ በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ መላኩን አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
ዶናልድ ትራምፕ በራሽሞር ተራራ የራሳቸውን ምስል ሊያስቀርፁ ነው የሚለውን ዜና አስተባበሉ!
ኒውዮርክ ታይምስና ሲ ኤን ኤን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የራሳቸውን ምስል በደቡባዊ ዳኮታ ግዛት ራሽሞር ተራራ ላይ ምስላቸው ከሚገኘውና በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ከሚባሉት 4 ሰዎች ማለትም ጆርጅ ዋሽንግተን ፣ ቶማስ ጀፈርሰን፣ አብርሃም ሊንከንና ቴዎዶር ሮዝቬልት ጎን ለማስቀመጥ የግዛቲቱን ገዢ እያናገሩ ነው ሲሉ ዘግበው ነበር። ይህ ዜና ወትሮውንም የሀሰት ዜና ያቀርባሉ በሚል ከሚተቿቸው አውታሮች የመጣባቸው ትራምፕ ዜናውን ፍፁም ሀሰት ነው ብለዋል። ነገር ግን ባለፉት 3 አመት ተኩል ለሀገሪቱ በሰራሁት ስራ የተባለው ነገር ቢደረግልኝ ሚበዛብኝ አይደለምም ብለዋል።

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በባሕር ዳር እየመከሩ ነው።መድረኩ በለውጥ ሂደቱ የተመዘገቡ ውጤቶችና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በመለዬት የመፍትሄ እርምጃዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።መድረኩ እስከ ነገ ነሐሴ 5/2012 እንደሚቀጥልም ታውቋል።
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
የአቶ ለማ መገርሳና ሌሎች 2 አመራሮች ለጊዜው መታገድን በተመለከተ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ኮንፌረንስ መጠናቀቅን ተከትሎ የተሰጠው መግለጫ በዝርዝር👇👇
(በዶይቸ ቨለ)
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የኮንፌረንስ መጠናቀቅን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ኮንፌረንሱ ፓርቲውንና ፓርቲው የሚያስተዳድረውን ክልል አጋጥሞታል በሚል እንደ ክፍተት ከገመገማቸው ጉዳዮች አንደኛው የአመራሮች በኃላፊነታቸው ልክ አለመስራት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም “በየደረጃው ያሉት አመራሮች ተጨባጭ ውጤት ከማስመዝገብ ይልቅ አውርተው የመኖር አዝማሚያ መስተዋሉ ተገምግሟል” የሚሉት የጽህፈት ቤት ኃላፊው በቅርቡ በክልሉ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ክፍተት አሳይተዋል የተባሉ ከ800 በላይ የወረዳ፣ እንዲሁም 117 የዞንና ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ለማጥራት መታሰቡን አስረዱ፡፡መሰል ውሳኔ በታችኛው የአመራር እርከን ብቻ መቆም የለበትም የሚል ሃሳብ ከአባላቱ ተነስቷል ያሉት አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተደረገው ግምገማ ለጊዜው ሶስት የድርጅቱ የበላይ አመራሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል፡፡
ከነዚህ መሃከል አንደኛው የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ ናቸው፡፡የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ተሰማ አቶ ለማ መገርሳ ከማዕከላዊ ኮሚቴው የታገዱበትን ምክኒያት ሲያስረዱም፤ “ጓድ ለማ በአንድ ወቅት ሃሳባቸውን በሚዲያ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ያንን ተከትሎ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ እሳቸውም ተሳስቻለሁ ብለው ይቅርታ ጠይቀው ነበር፡፡ከዚያም በአመራርነታቸው እንዲቀጥሉ ተደረገ፡፡ ይሁንና በብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነቱን ሰጥቶአቸው የነበረውን አካል ወክለው ድምጽ እንዲያሰሙ ቢጠየቁም ያን አላከበሩም፡፡ ይህ ደግሞ በፓርቲው መተዳደሪያ አሰራር ክልክል በመሆኑ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ጉዳዩን ካዩት በኋላ እኚህ ሰው ምንም እንኳ አገራዊ ለውጥ በማምጣት ሂደት ውስጥ ትልቅ ክብር የሚገባቸው ቢሆኑም፤ ማንም ከፓርቲውና ከኦሮሞ ህዝብ በላይ ባለመሆኑ፣ በዚህ ኮንፌረንስ ላይም እንዲሳተፉ በተደጋጋሚ ተጠይቀው መሳተፍ ባለመቻላቸው፣ ሃሳባቸውንም ዴሞክራሳዊ በሆነ መንግድ ወደ መድረክ ለማቅረብ ፈቃደንነትን ባለማሳየታቸው፣ ለጊዜው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል” ብለዋል፡፡
አቶ ለማ መገርሳ እንደ ክፍተት የተነሳባቸውን ነጥቦች ለማስተካከል ፈቃደኛ ሲሆኑ ወደ የፓርቲው አመራርነት መመለስ እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው፡፡ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች ዶ/ር ሚልኬሳ ሚዴጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ናቸው፡፡አቶ ፍቃዱ ለእነዚህ አመራሮች መታገድም ምክኒያቱን ሲያስረዱ፤ “ዶክትር ሚልኬሳ ሚዴጋ የፓርቲውን አሰራር ጠብቀው እዲሳተፉ ብጠየቁም መፈጸም ስላልቻሉ፣ ያላቸውን የሃሳብ ልዩነትም በፓርቲው ውስጥ ማንጸባረቅ ሲችሉ ወደ ውጪ በመውሰዳቸው በፓርቲው ደምብ መሰረት በአመራርነት ሊያስቀጥላቸው ባለመቻሉ ነው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት፡፡በርግጥ ይህ ጉዳይ በቀጣይነት በብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚረጋገጥ ነው የሚሆነው፡፡ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንም በተለያዩ መንገዶች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ብቆዩም ከአባላቱ በተነሳው ሃሳብ መሰረት በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ላይ በእጅ አዙር ተሳትፈዋል የሚል ጥርጣሬ ስለተፈጠረ ጉዳያቸው እስኪጣራ እሳቸውም ታግደዋል” ነው ያሉት፡፡
ኮንፌረንሱ የፓርቲው ውስጣዊ ችግር ነው ብሎ የገመገመው ሌላው ጉዳይ የአመራሮቹ የተለያዩ ቦታዎችን መርገጥ ነው ተብሏል፡፡ችግሩ በየአመራር እርከኑ በሰፊው የተስተዋለ ቢሆንም በርካቶቹ ህሳቸውን አውርደው በቀጠይነትም እንደሚሰራበት ነው የተጠቆመው፡፡ሌላው በየደረጃው ያሉ አመራሮች ይታሙበታል የተባለው የሌብነት ጉዳይ እንዲለዩና ማስተካከያ እንዲደረግበትም አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡ውሳኔዎቹ የተላለፉትም በመገፋፋት ስሜት ሳይሆን የፓርቲው አሰራርና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በማሰብ ነው ሲሉም አስረድተዋል አቶ ፍቃዱ ተሰማ፡፡

👍1
በነሀሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል!
የነሃሴ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል። የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በነሃሴ ወር በሊትር በ26 ብር 50 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑ ገልጿል። በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደርግ እንደሚችል ከንግድና ኢንዱስትሪ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ የጣራ ገዳም ናዳ በራሱ ጊዜ ተደርምሶ ከጠዋት ጀምሮ ከጎንደር ባህርዳር የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ አርፍዷል፡፡የወረዳውና የዞኑ የፀጥታ ሃይል በቦታ ተገኝተው ናዳውን ለማንሳትና መንገዱን ለመክፈት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው ከረፋዱ 5፡30 ላይ መንገዱ ለትራንስፖርት ክፍት መሆኑን በቦታው ተገኝተው መረጃ ያደረሱት የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ክንዱ ሲሆን በናዳው የደረሰ ምንም አይነት አደጋ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
(የደቡብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)
@YeneTube @FikerAssefa1
(የደቡብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች ሹም ሽር እና የመዋቅር ለውጥ አደረገ!
(በካፒታል)
ግዙፉ የፋይናንስ ተቋም ምንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ኢንባ) ደካማ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ተከትሎ የመዋቅር እና ሃላፊዎች ለውጥ አድርጓል፡፡ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገው የምደባ መዋቅር ማሻሻያ 9 የቺፍ ኦፍሰርነት ቦታዎች በሙሉ እንዳይኖሩ ተደርጓል፡፡በምትኩ በምክትል ፕሬዝደንትነት ደረጃ ብቻ የመዋቅር ለውጥ የተደረገ ሲሆን፡፡የምክትል ፕሬዝደንቶች ብዛትም ከቀድሞው 24 ወደ 18 እንዲወርድ ተደርጓል፡፡ባንኩ የሚጠበቀውን ውጤት ባለማስመዝገቡ መንግስት የቀድሞው ፕሬዝደንት አቶ ባጫ ጊናን በመጋቢት ወር በማሰናበተ የቀድሞውን መሪ አቶ አቤ ሳኖን መመለሱ ይታወሳል፡፡
በአቶ ባጫ አስተዳደር የአመራር መዋቅር መብዛት እና ወደ ጎን ያለቅጥ መለጠጥ ለአስታዳደር አመቺ ያልነበረ ነው የሚሉት የካፒታ ምኝጮች የአሁኑ ለውጥ ተቋሙን በአግባቡ ለመቆጣጠር የሚረዳ ነው በማለት ደግፈውታል፡፡በመዋቅር ለውጡም አንዳንድ ሃላፊዎች መነሳታቸው ታውቋል፡፡ በቀድሞው መዋቅር መሰረት ምክትል ፕሬዝደንቶች ለቺፍ ኦፊሰሮች ተጠሪ የነበሩ ሲሆን ቺፍ ኦፊሰሮች ለፕሬዝደንቱ ተጠሪ ነበሩ፡፡በአዲሱ ለውጥ ምክትል ፕሬዝደንቶቹን በቀጥታ ፕሬዝደንቱ ይከታተላቸዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በውስጥ ኢሜል አቶ አቤ ‘ምን ይሆን ምክንያቱ? መድኃኒቱስ?’ በሚል ርእስ በ2012 የፋይናንስ አመት ስለነበረው ደካማ አፈፃፀም ለሰራተኞች በደብዳቤ ሁኔታውን አሳይተዋል፡፡የስራ አፈፃፀሙን ካወቅን ቆይተናል ያሉት አቶ አቤ ውጤቱን የምገልፅበት ቃላት ፈልጌ በማጣቴ ውጤቱን ከመግለፅ ስለዘገየሁ ይቅርታ ይደረግልኝ ብለዋል ለሰራተኞቻቸው በፃፉት የውስጥ ደብዳቤ፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ👇👇👇
https://telegra.ph/-08-10-361

ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በሀገር ውስጥ የልብ ህክምና ማእከል ህክምና እንዲያገኙ እንዲያደርግ ለፖሊስ ትዕዛዝ ቢሰጥም ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ!
ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው በህክምና ምክንያት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ፥ መርማሪ ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዷል።በምስራቅ ሸዋ ዞን የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ በቀረቡት አቶ ለደቱ አያሌው ላይ መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ተጨማሪ 14 ቀናት ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን የምርመራ ስራዎች ገልጿል።አቶ ልደቱ እጅ ላይ የተገኙ ሁለት ሽጉጦች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የተላላኳቸውን የስልክ መልዕክቶች በፎረንሲክ እያስመረመረ መሆኑን ተናግሯል።
በእጃቸው ላይ የኢትዮጵያ ህዳሴ እርቅና አንድነት የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሚልና ሌሎች የፖለቲካ ሰነዶችን ማግኘቱን የገለፀው መርማሪ ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ መንግስት ለመገልበጥ እቅድ ይዘው ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በቢሾፍቱ ሁከትና አመፅ እንዲፈጠር ሲቀሰቅሱ ነበሩ ብሎ እንደጠረጠራቸውና ለዚህም የምስክሮችን ቃል መቀበሉን ገልጿል።ለጀመርኩት ምርመራ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት ለማምጣትና ተጨማሪ ሰነዶቸን ለማሰባሰብ 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
አቶ ልደቱ ዛሬም በጠበቃ ያልተወከሉ ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ ለምን በጠበቃ እንዳልተወከሉ ለጠየቃቸው ጥያቄ ሁለት ጠበቆች ፍቃደኛ አለመሆናቸውን፤ አንድ ፍቃደኛ ቢያገኙም በዚሁ ሰዓት በሰበር ችሎት ቀጠሮ ስላለው እኔው ለዛሬ ልከራከር ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ፈቅዶላቸዋል።በዚሁ መሰረት ፖሊስ ባቀረበው ምርመራ ላይ መቃወሚያ አሰምተዋል።ሽጉጡን በተመለከተ 1998 ዓመተ ምህረት ላይ መንግስት ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንደሰጣቸው አንደኛው ሽጉጥ ደግሞ ከአባታቸው በውርስ ያገኙት እና ፍቃድ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
በ1998 ዓመተ ምህረት ማስፈራሪያዎች ይደርስባቸው ስለነበር በወቅቱ የነበረው መንግስት ችግሩ ሲያልፍ ትመልሳለህ ብሎ እንደሰጣቸው ነው ያስታወቁት።ሰነዶቹንም በተመለከተ የፖለቲካ ጉዳዮች ሆነው በመገናኛ ብዙሃን እና በአደባባይ ሲገልጿቸው የነበሩ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።ከዚህ በፊት ከነበረኝ ቀጠሮ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መርመራ ነው የቀረበው፤ አዲስ አልቀረበም በማለት ተጨማሪ ጊዜ ለመርማሪ ፖሊስ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል።
በፈረንጆቹ ነሃሴ 6 የልብ ቀዶ ጥገና ምርመራ ለማድረግ እሁድ ወደ አሜሪካ ለመብረር ትኬት ቆርጠው አርብ እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀው፥ አሁንም የልብ ህክምና ያሰጋኛል የፖሊስ ጣቢያው ውስጥም ማስክ ሳያደርጉ ከመንገድ ላይ የሚያዙ ሰዎች ሳይመረመሩ እየገቡ ናቸው፤ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳልሆን ስጋት አለኝ ሲሉ አቤቱታ አስመዝግበዋል።ከዚህ በፊት የነበረው መንግስት አምስት ጊዜ አስሯቸው ነገር ግን ማስረጃ ስላልተገኘ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ የተናገሩት አቶ ልደቱ፥ አሁንም ማስረጃ ከተገኘብኝ ይጣራ በውጭ ሆኜ ህክምናዬን እንድከታተል ፍርድ ቤቱ የጤናዬን ሁኔታ ከግምት አስገብቶ በዋስ ይልቀቀኝ ሲሉ ጠይቀዋል።
ፖሊስ በበኩሉ ፖለቲካ ሳይሆን የወንጀል ጉዳይ ነው፤ እንደ ሀገር መንግስት ለመገልበጥ በተደረገ ሙከራ በቢሾፍቱ ወጣቶችን አደራጅተው አመፅና ሁከት በመቀስቀስ ነው የተጠረጠሩት፤ በመሆኑም ዋስትና ሊፈቀድ አይገባም ሲል ተቃውሟል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ከዛሬ ጀምሮ አቶ ልደቱ በሀገር ውስጥ የልብ ህክምና ማእከል ህክምና እንዲያገኙ እንዲያደርግ አዟል።የወረርሽኙን ሁኔታ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ እንዲደረግላቸው ያዘዘው ፍርድ ቤቱ፥ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የመጨረሻ ሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዶለታል።
#FBC

በዎላይታ ዞን ትናንት የአመራሮችን መታሰር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ቢያንስ 18 ሰዎች መጎዳታቸውንና ከዚው ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት 2 ሰዎች እንደሞቱ አዲስ ስታንዳርድ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 250 የመተንፈሻ አጋዥ ቬንቲሌተሮችን እያሰራጨሁ ነው አለ፡፡
ተቋሙ ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ ያገኘሁት ነው ያለውን ቬንቲሌተር ለኮሮና ቫይረስ የህክምና መስጫዎች እያሰራጨ መሆኑን ተናግሯል፡፡በጤና ሚኒስቴር ድልድል መሰረት 55 ቬንቲሌተሮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ የጤና ተቋማት እየተሰራጩ ነው ተብሏል፡፡ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 4፣ ለትግራይ ክልል 12፣ ለአማራ ክልል 40፣ ለኦሮሚያ ክልል 62፣ ለደቡብ ክልል 30፣ ለሲዳማ ክልል 7፣ ለሶማሌ ክልል 14፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4፣ ለጋንቤላ ክልል 2፣ ለአፋር ክልል 6፣ ለሐረር ክልል 4 ቬንቲሌተሮችን እንደሚያሰራጭ ኤጀንሲው ተናግሯል።ለመከላከያና ለፖሊስ ሆስፒታሎች ደግሞ5፣ 5 ቬንቲሌተሮች እየተሰራጩ ነው ተብሏል፡፡የመተንፈሻ አጋዥ ቬንቲሌተሮች ለኮሮና ፅኑ ህሙማን በእጅጉ የሚረዱ መሆናቸውን ኤጀንሲው በላከው መረጃ ጠቅሷል፡፡ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ የተሰጡትን ቬንቲሌተሮች የኤጀንሲው ዋና ዳሬይክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በአሜሪካ ኤምባሲ ተገኝተው መረከባቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡
#Sheger