YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የ2013 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚካሄድበት ጊዜ ተራዘመ!

ህዳር 6 ቀን ሊደረግ የነበረው የ2013 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገልጿል።ድርጅቱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ÷ የ2013 ዓ.ም ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በወረረሽኙ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጿል።ወደ ፊት ምዝገባ የሚጀምርበትን እንዲሁም ሩጫው የሚደረግበትን ቀን በዝርዝር እንደሚያሣውቅም አስታውቋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ሎጂስቲክስ ምክር ቤት ተቋቋመ!

በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ሥርዓትን ለማሻሻል እና ተወዳዳሪ ለማድረግ በዘርፉ ቁልፍ ሚና ያላቸውን ተቋማት በጋራ ማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ ሎጂስቲክስ ምክር ቤት ማቋቋሙን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ምክር ቤቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ጽ/ቤትን ጨምሮ 11 አባላት ያሉት ሆኖ በዛሬው ዕለት ተመሥርቷል። በዛሬው ዕለት የተቋቋመው ምክር ቤት የዕቃ እና የሰነድ ፍሰት፣ የመሠረተ-ልማት አጠቃቀም፣ አሠራር እና የሰው ኃይልን ለመምራት ያስችላል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ውጤታማነት ላይ ግልጽ አመራር ለመስጠት እንዲሁም በዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት እና መፍትሔ በማመላከት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa1
ዓረና በትግራዩ ምርጫ አይሳተፍም!

የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት በትግራይ ክልል በሚካሄደው ምርጫ ኢ- ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት እንደማይሳተፍ ገለፀ።ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ነው ይህ ያለው። መግለጫውን አስመልክቶ ይህን ያሉት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ናቸው።

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
ከኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መስፋፋት ተከትሎ በኬንያ ተጥሎ በቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደረገ!

በኬንያ እ.ኤ.አ. ከጁላይ 07 ቀን 2020 ከንጋቱ 04፡00 ኤኤም ጀምሮ ከናይሮቢ ከተማ፣ ከሞምባሳ እና ማንዴራ ክልሎች ላይ ተጥሎ የቆየው የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን እየጨመረ መጥቷል።ይህንኑ ተከትሎ የኬንያው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. አገሪቷ ለኮሮናቫይረስ የሰጠችውን ምላሽ ለመገምገም ከክልል ገዥዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሀገሪቱ የተስተዋለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን በፍጥነት መስፋፋት ለመግታት እና ዜጎችን ከከፋ አደጋ ለመታደግ ተጥለው የነበሩ እገዳዎች ላይ መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በፊት ተጥሎ የነበረው ከ09፡00 PM እስከ 04፡00 AM የምሽት የሰዓት እላፊ ለተጨማሪ አንድ ወር እንደሚራዘም አስታወቀዋል። በአገሪቱ አጠቃላይ መጠጥ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆነው የሚቆዩ ሲሆን፤ ሬስቶራንቶችም መጠጥ እንዳይሸጡ መታገዳቸውን ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል። የሬስቶራንቶች መዝጊያ ሰዓት ቀድሞ ከነበረው 8 PM ወደ 7 PM ዝቅ እንዲልም ሆኗል።ፕሬዝደንቱ አያይዘውም ይህን ህግ ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ተጠያቂ እነደሚሆን ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የግል ተቋማት አሰሪዎች ሰራተኞቻቸውን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ የሚያደርጉት ድጋፍ ቀንሷል - ኢሰማኮ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የግል ተቋማት አሰሪዎች ቸልተኝነት እየታየባቸው መሆኑን ኢሰማኮ አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለኢዜአ እንደገለጹት የግል ተቋማት አሰሪዎችም ሆነ ሰራተኞች ስለኮሮና ቫይረስ አደገኝነት የክልል ኤፍኤሞች ጨምሮ በተለያዩ የሚድያ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ ነው።ሆኖም በግል ተቋማትም ሆነ በሰራተኞች ዘንድ የቸልተኝነትና የጥንቃቄ ጉድለት በከፍተኛ ደረጃ አንደሚስተዋል ተናግረዋል።

ችግሩ እይተባባሰ ሲመጣ በሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስትር ወደ ሚመራው የሶስትዮሽ የስራ ቦታ ፕሮቶኮል ኮሚቴ ከሰራተኞች ለቀረበው ቅሬታ በማስማማት በርካታ ችግሮች የተፈቱ ቢሆንም በሁሉም ቦታ ግን ተደራሽ አይደለም ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ነገር ግን ይላሉ አቶ ካሳሁን ህጉን አክብረው ለሰራተኞቻቸው የንፅህና መጠበቅያ የሚያቀርቡ ተቋማትና ርቀታቸውን ጠብቀው የሚያሰሩ እንዳሉ ገልፀው አንዳንድ ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ተቋማት ግን ህጉን ቸል በማለትና ለሰራተኞቻቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው ለቫይረሱ እንዲጋለጡ ምክንያት ሆነዋል ብለዋል፡፡በምሳሌነትም አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የውጭ አገር የግል ተቋም ለሰራተኞቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለመደረጉ በርካታ ሰራተኞች በቫይረሱ መያዛቸውን ተናግረዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa1
በዓለማችን ከትቢ በመቀጠል ሁለተኛው ገዳይ የሆነው የጉበት በሽታ ቀን በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ከጉበት በሽታ ነጻ የሆነ ነገን እንፍጠር በሚል መሪ ቃል በአለም ለ10ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡በአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት በአለም ላይ በጥቅሉ ወደ 325 ሚሊየን የሚሆነው ህዝብ በሄፓታይተስ እድሜ ዘለቅ የጉበት ኢንፌክሽን ተጠቂ ሲሆን ወደ 257 ሚሊየን በሄፓታይተስ ቢ እና 71 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ በሄፓታይተስ ሲ ተጠቂ ናቸው፡፡በየአመቱ 1.3 ሚሊየን የሚገመት ህዝብ በሔፓታይተስ ምክንያት ለሞት እንደሚዳረግም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡ይህም ከቲቢ በመቀጠል በአለም ላይ ሁለተኛ ለሞት የሚዳርግ ገዳይ በሽታ ያደርገዋል፡፡

ከኤች አይቪ ጋር ሲወዳደር በኤች አይቪ ከሚያዘው ሰው ይልቅ በሄፓታይተስ የሚያዘው ሰው ቁጥር በዘጠኝ እጥፍ ይበልጣል፡፡ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት እና በኢስያ የሄፓታይተስ በሽታ በስፋት ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡በሀገራችን በፈረንጆቹ 2017 በተሰራ አንድ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በሽታው በስፋት ተሰራጭቶ ከሚገኝባቸው ሀገራት መካከል ስትሆን እስከ 10 ሚሊየን ሰው በሄፓታይተስ ቢ እና 3.5ሚሊየን ሰው ደግሞ በሄፓታይተስ ሲ የተጠቁ ናቸው ተብላል፡፡የሄፓታይተስ ሲን በህክምና ማዳን የሚቻል ሲሆን ሄፓታይተስ ቢን ደግሞ በህክምና ቫይረሱ በመቆጣጠር የኢንፌክሽን ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ማድረግ እንደሚቻል ነው የተነገረው፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
የአማራ ክልል የ2013 በጀት 62 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸድቋል።

24 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ከክልሉ የሚሰበሰብ፣ 38 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እና ዜሮ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ ዕርዳታ የሚገኝ ነው። የፌደራል መንግሥት የሰጠው በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ23 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል።0.2 ቢሊዮን ብሩ ከክልል የሚሰበሰብ ነው። የ2013 በጀት ከ2012 በጀት ጋር ሲነጻጸር በ15 ነጥብ 3 ቢሊዮን (32.4 ከመቶ) ጭማሪ አለው። በጀቱ የተወሰነ ጭማሪ ቢኖረውም የኮሮናቫረስ ወረርሽኝ ከሚያስከትለው ተጽእኖ አንጻር በቂ ነው ለማለት አዳጋች መሆኑን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሐሪ (ዶክተር) ተናግረዋል።

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
የኖቤል ሰላም ሽልማት መልስ!

ሰሞኑን ኖርዌይ ለሚገኘው የኖቤል ሰላም ሽልማት ተቋም በርካታ ኢትዮጵያውያን ደብዳቤ እየላኩ ነበር። እነዚህ ደብዳቤዎች ጠ/ሚሩን የሚደግፉ እንዲሁም ተቃውመው ሽልማቱ እንዲሰረዝ የሚጠይቁ ነበር። የተቋሙ የክርክር ሰሚ እና አጣሪ ቡድን መሪ (እንዲሁም ሽልማቱን በሚድያ ይፋ ያደረጉት) በሪት ሪስ-አንደርሰን ዛሬ በፃፉት ኢሜይል የተቃውሞ ድምፆች ሽልማቱ ይፋ በተደረገ ግዜም፣ አሁንም እንዳሉ ገልፀው ተቋሙ ግን በፍፁም የሰጠውን ሽልማት እንደማይሰርዝ አሳውቀዋል።

ሽልማቱን መሰረዝ ማለት ከኖቤል ፋውንዴሽን መመስረቻ ህግ ጋር የሚጋጭ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።በቅርብ ሳምንታት የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ስዩም መስፍን የኖቤል የሰላም ሽልማትን አስመልክተው "የኖርዌይ የሰላም ሽልማት... እያሰቡበት ነው። ልክ ነበርን ወይ፣ አይደለም ወይ (ብለው) እየታመሱበት ነው" ብለው ተናግረው የነበረ ቢሆንም የሽልማቱ ኮሚቴ ዳይሬክተር ኦላቭ ኖልስታድ በኢሜይል በሰጡኝ መልስ "ይህ መሰረት የሌለው ነገር ነው፣ እውነታ የሌለው አባባል ነው" ብለው ነበር።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa1
የደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ 261 ተማሪዎችን በ2ኛ ዲግሪ ማስመረቁን አስታወቀ!

የደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ በተለያዩ መርሃግብሮች ያስለጠናቸውን 261 ተማሪዎች በ2ኛ ዲግሪ በያሉበት ቦታ ሆነው በዛሬው ዕለት መመረቃቸውን አስታወቀ፡፡በውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው ለምረቃ የበቁትን ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደረጀ አንዳርጌ፤ በቀጣይ የተጣለባቸውን አደራ በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽንና በክረምት መርሃ ግብሮች በ7 ኮሌጆች እና በ21 የትምህርት መስኮች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና በማጠናቀቃቸው መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡ከ261ዱ ተመራቂዎች መካከል 52 ሴቶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa1
የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአዲስ ዐለም ባሌማ የሚመራ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ እንደላከ ማወቃቸውን በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር በየነ ርዕሶም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ልዑኩ የተላከው ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ለመነጋገር እንደሆነም ጠቅሰዋል። ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥትም ሆነ ከትግራይ ክልል መንግሥት ስለመረጃው እውነተኛነት የተሰማ ነገር የለም፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
ካናል ፕላስ ከ50 በላይ ቻናሎችን ይዞ በኢትዮጵያ ገበያ ለመስራት ከኢውቴልሳት ጋር ስምምነት ተፈራረመ!

በጥቅምት 25፣ 1977 ዓ.ም የተመሰረተው የካናል ፕላስ የቴሌቪዥን ቻናል ከኢውቴልሳት ኮሚይኒኬሽን ጋር በመተባበር በቀጥዩ የፈረንጆች አመት ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች በመደበኛና በከፍተኛ ጥራት ደረጃዎች የሚቀርቡ 50 ያህል ቻናሎችን ለማድረስ ዝግጅት መጀመሩን ቢዝነስ ዋየር የተሰኘው መካነድር አስታውቋል። በዘገባው እንደተቀመጠው ከሆነ ቻናሎቹን በኢውቴልሳት 7C ላይ ቻናሎቹንም ለማስተላለፍ በትናንትናው እለት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ስምምነት ተፈርሟል።በመጠነኛ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ይቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁት ከ50 በላይ የሚደርሱት ቻናሎች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኢንዱስትሪን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

በስምምነቱ ወቅት የካናል ፕላስ ሊቀመንበር የሆኑት ዣክ ዱ ፑይ የካናል ፕላስ ቻናሎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ ከስምምነት መድረሳቸው የፈጠረባቸውን ደስታ ከገለፁ በኋላ ወደገበያው በሚገባበት ወቅት ድርጅታቸው ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የተሻለ አማራጭን ይዞ ይመጣል ብለዋል።የኢውቴልሳት ዋና ስራ አስካያጅ ሩዶልፍ ቤልመር በበኩላቸው ስምምነቱ በኢትዮጵያና በፍጥነት እያደገ ባለው የአፍሪካ የሳተላይት ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት የሚያሳይ አጋጣሚ ነው በማለት ከካናል ፕላስ ጋር በደረሱት ስምምነት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 653 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ6503 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 653 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡170 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 15,200፣ ያገገሙት 6526፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 239 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa1
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ትናንት ማታ በተፈጸመ ጥቃት የ14 ንጹሐን ሕይወት አለፈ፡፡

በጉባ ወረዳ አቡጃር ቀበሌ በሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የታጠቁ ኃይሎች ትናንት ሌሊት በድንገት ጥቃት መፈጸማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡በዚህም የንጹኃን ሕይወት ጠፍቷል፤ ለአካል ጉዳትም ተዳርገዋል፡፡ተጎጂዎች የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነም ምንጮች ገልጸዋል፡፡በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ ኩምሳሪ ለአብመድ እንደገለጹት ደግሞ ጥቃት የፈጸሙት የታጠቁ ሽፍቶች ናቸው፡፡ በጥቃቱም የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም አረጋግጠዋል፤ የቆሰሉት ከስድስት በላይ ሰዎችም ወደ ፓዌ ሆስፒታል ለሕክምና እንደተወሰዱ ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል፡፡

ሽፍቶችን ለመያዝም የክልሉ ፀረ ሽምቅ ኃይል ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሽፍቶቹ ከዚህ ቀደምም መኖሪያቸውን ጫካ ውስጥ በማድረግ ሚሊሻ እና የአካባቢ ሽማግሌዎችን ሲያፍኑ፣ ሲያንገላቱ እና መሣሪያም ሲነጥቁ እንደነበሩና በፀጥታ ኃይሎች የሚፈለጉ መሆናቸውን አቶ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡በሌሎች አካባቢዎች ጥቃት እንዳይፈጽሙ ለማድረግም የስጋት ቀጣና ተብለው በተለዩት አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት እንዲሰማራ መደረጉን ተናግረዋል፡፡የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም የተደራጁ እና የጽንፈኛ ኃይሎች አጀንዳ አስፈጻሚ ቡድኖቹ በንጹኃን ዜጎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የ14 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ፣ ከስድስት በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው መረጃ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡‘‘ሽፍቶቹ የተደራጁ እና የብሔር ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ አልመው የጽንፈኛ ኃይሎችን ዓላማ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ያሉ ናቸው’’ ያሉት አቶ ግዛቸው በቁጥጥር ሥር ለማዋል የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና የአካባቢው የፀጥታ አካላት ክትትል እያደረጉ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ አካባቢውን የማረጋጋት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

Via አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa1
የትግራይ ክልል የምርጫ ኮምሽን ምዝገባ ጀመረ!

በቅርቡ በትግራይ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ የተቋቋመው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ ኮምሽን የተባለው ተቋም ዘንድሮ ሊያካሂደው ባቀደው ምርጫ ተሳታፊ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎችን መመዝገብ ጀመረ፡፡የኮምሽኑ አመራሮች ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ ፓርቲዎችን ዳግም በኮምሽኑ መመዝገብ ያስፈለገው የምርጫው ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን ለመለየት፣ ሀሳባቸው ለመቀበልና ለመደገፍ ታቅዶ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
Audio
አቶ ዳውድ ኢብሳ "ቁም እሥር ላይ ነኝ" አሉ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በመንግሥት ፀጥታ ኃይል ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ከተከለከሉ ከ10 ቀናት በላይ እንደሆናቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።ከኦነግ ደምብና ከእርሳቸው እውቅና ውጭ የሆነ ስብሰባም በጉለሌው ፅህፈት ቤታቸው መካሄዱን ገልፀዋል። ስብሰባውን የመሩት አቶ አራርሳ ቢቂላ ስብሰባው የአቶ ዳውድን ሊቀመንበርነት ለመቀማት አይደለም ብለዋል።አቶ ዳውድ ኢብሳ ለምን ቤት ውስጥ እንደታጎሩ ለመጠየቅ ወደ ፌዴራልና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካም ብሏል የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ።

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
ኤችቱ (H2) የቋንቋ ትምህርት ቤት ባለቤት 84 ሚሊዮን ብር “አጭበርብረው” ተሰወሩ!

ኤችቱ(H2) የቋንቋ እና የኮምፒተር ትምህርት ቤት ከ100 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ አጭበርብሮ እንደጠፋባቸው ተበዳዮች ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። የትምህርት ቤቱ ባለቤት የሆኑት ሀፍቶም ኃይሌ ከአንድ ወር በፊት ቁጥራቸው ከ100 በላይ የሆኑ ተበዳዮችን ገንዘብ በብድር እና የድርጅቱ ተጋሪ ትሆናላችሁ በማለት ከግለሰቦች ብር በመቀበል ድንገት አድራሻቸውን አጥፍተው እንደተሰወሩባቸው ተበዳዮች ለጋዜጣው አስረድተዋል።ትምህርት ቤቱ ባለቤት የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ሰርቶብናል በማለት አስካሁን ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሰዎች ቁጥር ከ120 ያለፈ ሲሆን፣ እስካሁን ገንዘብ ተጭበርብረናል ብለው የተሰባሰቡ ሰዎች ብር መጠን በቲንሹ ከ84 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ሰምቻለው ብሏል።ከተበዳዮቹ ውስጥ አንዷ የሆኑት ሚሚ ሳህለ በደላቸውን እንዳስረዱት ከሆነ፣ የኤችቱ ቋንቋ እና ኮምፒተር ትምህርት ቤት ባለቤት ሀፍቶም ኃይሌ“የድርጅቱ ተጋሪ ወይም ባለድርሻ ትሆኛለሽ በማለት አራት ዓመት በውጭ አገር ያፈራሁትን ገንዘብ 180 ሺህ ብር በመቀበል እና በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኛ ሆኜ እንዳገለግል ተስማምተን የ180 ሺህ ብር ደረቅ ቸክ ሰጥቶኝ፣ በእምነት የድርጅቱ ተጋሪ እሆናለሁ ብየ ስለፋ በ180 ሺህ ብሬ እና የአንድ ወር ደምወዜን ቀምቶኝ ተሰውሯል።” ሲሉ የደረሰባቸውን ጉዳት በምሬት አስረድተዋል።ሚሚ አክለውም ሀፍቶም በተሰወሩ ሰሞን በሰልክ ደውለው የቤት ኪራይ ብር እንኳን እንዲልኩላቸው ቢማጸኗቸውም እልክልሻለሁ ብለዋቸው በዚያው ቤተሰባቸውን እና የራሳቸውን ስልክ አጥፍተው እንደጠፉባቸው ተናግረዋል።

Read more👇👇👇👇
https://telegra.ph/H2-Computer-School-07-29
የመአዛ መንግስቴ ዘ ሻዶው ኪንግ የተሰኘው መፅሀፍ በዝነኛው ዘ ቡከርስ ፕራይዝ የ2013 እጩዎች ዝርዝር ተካተተ!

በየአመቱ የሚወጣውና ለሀምሳ አመታት ያክል በብሪታንያና በአየርላንድ በእንግሊዘኛ የታተሙ የልበ ወለድ መፅሀፎችን የመሸለም የሚታወቀው 'The Bookers Prize' በእንግሊዝ ለደራስያን ከሚሰጡ ሽልማቶች አንዱ ሲሆን፣ በመጪው ጥቅምት አሸናፊውን ለማሳወቅ በዝግጅት ላይ የሚገኙት የሽልማቱ አዘጋጆች በትላንትናው እለት የመአዛ መንግስቴን 'The Shadow King' የተሰኘ ልብ ወለድ መፅሀፍ በዘንድሮው ዘ ቡከርስ ፕራይዝ እጩዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቱን ይፋ አድርገዋል።

ይህ በልብ ወለድ ደራስያን ዘንድ ታላቅ ክብር የሚሰጠው ሽልማት ከእጩዎቹ መካከል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ መአዛ መንግስቴ በመካተቷ የተሰማውን ኩራት በእንግሊዝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም በትዊተር ገፁ በትላንትናው እለት ባሰፈረው መልእክት ገልጿል።

በዘ ቡከርስ ፕራይዝ ፋውንዴሽን የሚዘጋጀው ሽልማት በዘርፉ ልምድን ባካበቱ ዳኞች በመታገዝ ሽልማቱን የመጨረሻ እጩዎቹን በመጪው መስከረም 5 2013 ዓ.ም የሚያሳውቅ ሲሆን የዘንድሮ የቡከርስ ፕራይዝ አሸናፊን ደግሞ በጥቅምት 17 2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚያደርግ ከመካነድሩ መረዳት ይቻላል።

መአዛ መንግስቴ በተወዳጅ የልብ ወለድ ድርሰቶቿ ካካበተችው ታላቅ ሙገሳ በተጨማሪ በተለያዩ መፅሀፍቶቿ የኢትዪጵያን ታሪክ በማካተት አገሯን በተለያዩ መድረኮች ማስጠራት በመቻሏ ከብዙ ኢትዮጵያውያንም ሆነ ከቀሪው አለም ሙገሳን አግኝታለች።ለዚህም እንደማሳያነት ከላይ የተጠቀሰው ዘ ሻዶው ኪንግ በተሰኘው መፅሀፍ ደራሲዋ መቼቱን በጣልያን ወረራ ወቅት በማድረግ ለአንባቢው ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ መልኩ ማቅረቧን መግለፅ ይቻላል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa1
Audio
ፖሊስ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ነበር ያላቸውን ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለፀ!

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ነበር ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ሙከራው በመዝናኛ ቦታዎች አካባቢ ቦምብ ከማፈንዳት፤ አድፍጦ ጥቃት እስከመፈጸም የደረሰ ነበር ሲል የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው።

ውይይቱ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።በቀጣይም አገራዊ ምርጫን በሚመለከት ከዚህ በፊት ከተደረው ምክክር የቀጠለ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።በዚህም እስከ ሰባት በሚደርሱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ለማድረግ ስምምነት ተደርሷል፣ በቅድሚያ ግን ውይይት የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎችም ተለይተዋል።በቅድሚያ አገራዊ መግባባት ላይ ውይይት ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን፣ በዚህም ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግ እና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች ተመርጠዋል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa1
ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአረፋ በዓልን ሲያከብር የኮቪድ19 መከላከያ መንገዶችን እና የተቀመጡ ክልከላዎችን በመተግበር ሊሆን ይገባል - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በመግለጫቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ረገድ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው እንደ ቀደሙት አመታት በአንድ ላይ ተሰባስበን ሳይሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በመከወን መሆን ይገባዋልም ነው ያሉት፡፡ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአረፋ በዓል ላይ የተቸገሩትን በመርዳትና የታመሙትን በመጠየቅ ሰብአዊ ተግባር እንዲፈጽምም ጥሪ አቅርበዋል፡፡በተጨማሪም ሰብአዊነትን በተግባር በማሳየት እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በያለበት ቦታ ሁሉ የዱዓ ፀሎት በማድረግ በአሉን እንዲያከብርም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡1 ሺህ 441ኛው የአረፋ በዓል ከነገ በስቲያ አርብ የሚከበር ይሆናል፡፡

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1