ምርጫ ቦርድ አዲስ ድረ-ገጽ (ዌብ ሳይት) አዘጋጅቶ መጨረሱን አስታውቋል። ድረ-ገጹ የምርጫ ውጤቶች ጭምር የሚገለጹበት በመሆኑ ደህንነቱን ለማስጠበቅ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እና በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገልጿል።
#Ethiopia #Election2012
@YeneTube @Fikerassefa
#Ethiopia #Election2012
@YeneTube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የጥቁር ገበያውን ዶላር ምንዛሬ ቀንሶታል
ከሳምንታት በፊት የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በኢትዮጵያ ህጋዊ ባልሆነው ጥቁር ገበያ 42 ብር ድረስ የሚመነዘር ሲሆን ወደ ቻይና ዶላር ይዘው እቃ ለማምጣት የሚሄዱ ነጋዴዎች ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር ስጋት ስለገባቸውና የሚያደርጉትም ጉዞ በመቀነሱ ምክንያት የዶላር ፍላጎት በተወሰነ መልኩም ቀንሷል። በዚህም ምክንያት የአንድ ዶላር መሸጫ ዋጋ በሁለት ብር ቀንሶ በጥቁር ገበያው አርባ ብር አየተሸጠ እንደሚገኝ ፊደል ፓስት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በባንኮች ደግሞ የዶላር ምንዛሬ ከሁለት ወራት በፊት በየቀኑ አምስት ሳንቲም እየጨመረ ከ32 ብር አልፎ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ዝቅ ብሎ 31. 70 አሰከ 31. 90 ከፍና ዝቅ አያለ ባለፉት ሁለት ሳምንት አየተሸጠ ይገኛል።
Via:- fidelpost

የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከልሶ በቀረበው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የድምፅ መስጫ ቀን #ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሆኗል።
የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
በባለ ድርሻ አካላት ኮንፈረንሱ ላይ የምርጫ ሰሌዳ ማሻሻያውን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አቅርበውታል።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 10 ቀን እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል ።
የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ግንዛቤ ውስጥ ብናስገባም ከህግ አንፃር የድምፅ መስጫ የተከለሰው ቀን ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።
በክረምት መካሄዱ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅእኖ በተመለከተም ከብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ ጋር እየተሰራ መሆኑን ም ተናግረዋል።
#ምርጫ2012

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የ5 ሴት ወጣቶች ህይወት እንዲጠፋ ያደረገው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
የፍርድ ቤቱ ዳኛ አቶ ሐኪም ሲራጅ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት አብዱከሪም ጣሂር አብደላ የተባለው ግለሰብ ነዋሪነታቸው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ ዳይፈርስ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሆኑ ወጣት ሴቶችን በህገ ወጥ መንገድ በማስኮብለል ለህልፈተ ህይወት በመዳረጉ ቅጣቱ ተላልፎበታል ።
“በጎረቤት አገር በኩል ሳውድ አረቢያ ወስጄ በከፍተኛ ደመወዝ ስራ እንድትቀጠሩ አደርጋለሁ ” በሚል ማታለያ በ2010 ዓም በተለያዩ ቀናትና ወራት ከቀያቸው ካስኮበለላቸው 8 ወጣት ሴቶችን ላይ ከእያንዳንዳቸው 3 ሺህ ብር ተቀብሏል ።
ስልክ በመደወልና ዘመድ አዝማድ ሳይሰማ ከአደጉበት ቀዬ ጭለማን ተገን በማድረግ ካስኮበለላቸው 8 ሴት መካከል በጀልባ መስጠም ምክንያት 5ቱ ህይወታቸው ማለፉን ዳኛው ገልፀዋል።በተጨማሪም በደላላ አማካኝነት ቤተሰቦቻቸውን በማስጨነቅ ከእያንዳንዳቸው ቤተሰብ 10 ሺህ ብር መቀበሉን ተናግረዋል።
ከአደጋው የተረፉት ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ ለሟች ዘመዶች በሰጡት ጥቆማ መሰረት የክስ አቤቱታ የደረሰው የጉርሱም ወረዳ ፖሊስ ወንጀለኛውን አብዱከሪም ጣሂር አብደላ በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ ተመስርቶበት የምርመራ መዝገቡ አጣርቶ ለማየት ስልጣን ላለው ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲተላለፍ ተደርጓል።
ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ግለሰቡ ወንጀሉን መፈጸሙ በአቃቢ ህግ፣በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማረጋገጥ የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ከመረመረ በሃላ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት ሲል አምራች ሐይል በሆኑት ወጣት ሴቶቹ ላይ የተፈጸመው ድርጊት አሰቃቂ ወንጀል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጥር 2 ቀን 2012 በዋለው ችሎት ወንጀለኛው አብዱከሪም ጣሂር አብደላን በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተፈፃሚ የሚሆነው ለሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ቀርቦ ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ነው ተብሏል ።
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa

ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶች የተከማቹት ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕቃ ማከማቻ መጋዘን መሆኑን በዛሬው የምርጫ ቦርድ ኮንፍረንስ ላይ ተመልክቷል።ቦርዱ አየር መንገዱን ለዕይታ ባበቃው ቪዲዮ ላይ አመስግኗል።
#ምርጫ2012
@YeneTube @Fikerassefa
#ምርጫ2012
@YeneTube @Fikerassefa
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ለምርጫ "ሰራዊታችንን በአግባቡ እናሰለጥናለን። የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሙ እንዴት መከላከል እንደሚቻል በቂ ዝግጅቶች አድርገናል...በከተማም ሆነ በገጠር ሽፍታ ካለ አንቀበልም።ህግ እናስከብራለን" ብለዋል።
#ምርጫ2012
@Yenetube @Fikerassefa
#ምርጫ2012
@Yenetube @Fikerassefa
በምርጫ ቦርድ ኮንፍረንስ የተሳተፉ የህወሓት ተወካይ፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት በቅርቡ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ የተናገሩትን አንስተው ጥያቄ አቅርበዋል። "ኤርትራ ለእኛ ድጋፍ አላደረገችም" ሲሉ ብርቱካን ሚደቅሳ ምላሽ ሰጥተዋል።
#ምርጫ2012
@YeneTube @Fikerassefa
#ምርጫ2012
@YeneTube @Fikerassefa
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የምርጫ ምዝገባን በተመለከተ "ሎጀስቲክ ላይ ብዙ ወጪ ሳያስወጣ እንዴት መፈጸም እንደምንችል እያየን ነው። እንዴት እንደምንፈጽመው ገና አልወሰንንም" - የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ
#Ethiopia #ምርጫ2012 #Election2020
@YeneTube @Fikerassefa
#Ethiopia #ምርጫ2012 #Election2020
@YeneTube @Fikerassefa
ቻይና የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ግብረኃይል ተቋቋመ!
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የተነገረላቸው ተማሪዎችን ለማስመጣት ግብረኃይል መቋቋሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አርብ የካቲት 6/2012 በወቅታዊ ጉዳይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ፡፡ በቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መንግስት የገንዘብ ድጋፍ መላኩን የገለጹት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው ተማሪዎቹ በቫይረስ እንዳይጠቁ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።
Via Addis Maleda

የሱዳን ገዳሪፍ ክፍለ ግዛት ዋ/አስተዳዳሪ ሜ/ጀኔራል ነስረዲን አብዲ የተመራ ልዑክ ጎንደር ገባ። ልዑኩ በድንበር አካባቢ ፀጥታና በኮንትሮባንድ ንግድ ዙሪያ ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር ነገ በባህርዳር ውይይት እንደሚያካሂድ አምሓራ ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሸባብ አላሕሊ ስቴዲየም በተገኙበት ባስተላለፉት መልዕክት "መብታችሁ ተጠብቆ እንድትሠሩ ለማድረግ መንግሥት ከየሀገራቱ መንግሥታት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት አድርጓል፣ መንግሥት እናንተ ስትከበሩ ሀገራችን እንደምትከበር ስለሚገነዘብ፣ መብታችሁን እና ጥቅማችሁን ለማስከበር የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል" ብለዋል። ጠ/ሚሩ ለተደረገላቸው አቀባበልም ምስጋናን አቅርበዋል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም ጤና ድርጅት በኮረና ቫይረስ ምክንያት የቶኪዮ ኦሎምፒክን መሰረዝ አያስፈልግም አለ።
ዶ/ር ማይክ ራያን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ከአደጋ ዜሮ የሆነ የብዙሀን ስብስብ የለም" ስለሆነም አዘጋጆቹና የአከባቢው የጤና ባለሙያዎች ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ለመስጠት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል።
#AlAln
@YeneTube @Fikerassefa
ዶ/ር ማይክ ራያን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ከአደጋ ዜሮ የሆነ የብዙሀን ስብስብ የለም" ስለሆነም አዘጋጆቹና የአከባቢው የጤና ባለሙያዎች ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ለመስጠት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል።
#AlAln
@YeneTube @Fikerassefa
የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ
የካቲት 6/2012
➡️ በሁሉም የአገሪቷ መግቢያዎች ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ 118 882 መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3 380 በሽታውን ሪፖረት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከ455 በላይ የሚሆኑት ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
➡️ ከጥር 16/2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 47 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡
➡️ ከነዚህም ጥቆማዎች 16ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስላላቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 15ቱ በላቦራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡በትላንትናው እለት ወደ ለይቶ ማቆያ የገባው የጭምጭምታ ግለሰብ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በማዕከሉ እንዲቆይ ተደርጎ የምርመራ ውጤቱ በዛሬው ዕለት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
➡️ የበሽታውን ምልክት ላሳዩ ሰዎች ለይቶ ማቆየት እና መከታተል ይቻል ዘንድ ለየካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ከክልል እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ለሆቴል ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
➡️ ለክልሎች የበሽታውን መከላከል ቅድመ ዝግጁነት ለማጠናከር እንዲረዳ የሕክምና መገልገያዎች በመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል እንዲደርሳቸው የስርጭት ዕቅድ ለኤጀንሲው ተሰጥቷል፡፡
📌ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች
➡️ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከታየባቸው ሀገራት የመጡ መንገደኞች ወይም በዚህ ቫይረስ ከተያዙ ግለሰቦች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች (ትኩሳት፤ ሳል፤ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የመተንፈስ ችግር) ከታዩ፣ ማንኛውም የህብረተሰቡ አካል በአስቸኳይ በ8335 ነጻ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡
➡️ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫቸውን በሶፍት ወይም በክንድእንዲሸፍኑ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍት መክደኛ በለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ወስጥ በመጣል የበሽታውን ስርጭት በጋራ እንከላከል፡፡
➡️ እጃቸውን በሳሙናና በንጹህ ውሃ በመታጠብ የኮሮና /COVID የቫይረስ እና ሌሎችንም መሰል በሽታዎች ስርጭት እንዲከላከሉ እንመክራለን፡፡
➡️ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በሀገራችን እስካአሁን በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አለመኖሩን አውቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ ኢንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን phemdatacenter@gmail.com ወይም ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡
Via Ministry of Health

YeneTube
የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ የካቲት 6/2012 ➡️ በሁሉም የአገሪቷ መግቢያዎች ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ 118 882 መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3 380 በሽታውን ሪፖረት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከ455 በላይ የሚሆኑት ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ➡️…
ከላይ በመግለጫው እንደተቀመጠው የኮቪድ19(ኖቬል ኮሮና ቫይረስ) በሽታ ምልክቶችን ያሳየ ሰው በለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ እንደሚገኝና ናሙናው ለላብራቶሪ ምርመራ መላኩ መገለጹ ይታወሳል። አሁን የምርመራው ውጤት የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ነጻ መሆኑ ተረጋግጧል።
ምንጭ: ጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: ጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ፅህፈት ቤቱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ ሰጥቷል።
በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ከተሞችና ዞኖች በተለይም በኦሮምያ ልዩ ዞን በሰበታ አዋስ፣ለጋጣፎ፣ቡራዩ እና በአጠቃላይ በ26 ከተሞችና በ7 ዞኖች ድርጅቱ ያሰለጠናቸው እና በትክክል የድርጅቱ አባል የሆኑ 350 ሰዎች ታስረውብኛል ሲል ፓርቲው አስታውቋል።
የኦሮምያ መንግሥት በበኩሉ ኦነግ ባነሳቸው ቅሬታ ላይ መልስ ስጥቷል።
Via:- VOA

ኢጄቶ የሲዳማ ክልል ርክክብ እስከ የካቲት 15 እንዲካሄድ ጠየቀ!
እስከ የካቲት 15 ድረስ የስልጣን ርክክብ ተደርጎ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የማይመሰረት ከሆነ ተቃውሞ እንደሚያስነሳ የሲዳማ ወጣቶች ቡድን የሆነው ኢጄቶ አስጠንቅቋል። ሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን የቻለ ክልል መሆኑን በድምፁ ካረጋገጠ 3 ወራቶች የተቆጠሩ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ የሲዳማን ክልል ለመመስረት እያቅማማ እንደሆነ ስማቸው ያልተጠቀሰ የኢጄቶ አመራር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። መንግሥት ከህዝቡ የሚተላለፉ ጥሪዎችን በቸልታ የሚያልፍበት መንገድ የሚመጡትን ችግሮች ከማባባስ በቀር መፍትሄ የሚያመጡ አለመሆናቸውን ጠቅሰው መንግሥት የህዝቡን ውሳኔ ላለማስፈፀም አማራጭ እየፈለገ እንዳለ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በልዩ ልዩ ምክንያት በችግር ውስጥ ከሚገኙ፣ ጥቃት ከደረሰባቸው እና በመጠለያ ውስጥ ከሚገኙ ሴት ኢትዮጵያውያን ጋር በችግሮቻቸው እና በመፍትሄዎች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው። በውይይቱ ችግር ከገጠማቸው ሴቶች በተጨማሪ በልዩ ልዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ስኬትን ያስመዘገቡ ሴቶችም ተገኝተው ልምዳችውን ያጋራሉ።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በ2012ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከዚህ በፊት የነበሩ አስፈፃሚዎች እንደማይሳተፉ ተገለጸ
ቀድሞ በተደረጉ ምርጫዎች የተሳተፉ የምርጫ አስፈፃሚዎች በነሐሴ ወር በሚደረገው በስድተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንደማይሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። እስካሁን የፓርቲዎች የሴቶች ተሳትፎ 10 በመቶ ብቻ መሆኑን አመለከተ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት እንደተገለጸው፤ ከዚህ በፊት አስፈፃሚ የነበሩ ሰዎች ላይ አመኔታ ስለሌለ በምርጫ 2012 እንዳይሳተፉ ተወስኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በመድረኩ እንደገለጹት፤ ከዚህ በፊት አስፈፃሚ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ጥፋተኛ ናቸው ማለት አይደለም፤ እንዳይሳተፉ የተደረገው ግን ጥርጣሬን ለማስወገድ ነው።
Via:- EPA