YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከልሶ በቀረበው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የድምፅ መስጫ ቀን #ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሆኗል።

የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በባለ ድርሻ አካላት ኮንፈረንሱ ላይ የምርጫ ሰሌዳ ማሻሻያውን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አቅርበውታል።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 10 ቀን እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል ።

የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ግንዛቤ ውስጥ ብናስገባም ከህግ አንፃር የድምፅ መስጫ የተከለሰው ቀን ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።

በክረምት መካሄዱ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅእኖ በተመለከተም ከብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ ጋር እየተሰራ መሆኑን ም ተናግረዋል።

#ምርጫ2012
@YeneTube @Fikerassefa