መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የጉበት_በሽታ ( #ሄፖታይተስ_ቢ )

#ሄፖታይተስ_ምንድን_ነው?

ሄፖታይተስ ማለት ከጉበት መቆጣት ጋር የተያያዘ የጉበት ጉዳት ማለት ሲሆን ይህ የጉበት መቆጣት በሁለት ይከፈላል፡፡

👉የመጀመሪያው ድንገተኛ ሄፖታይተስ (አኪዩት) ይባላል፡፡

👉ሁለተኛው ደግሞ ስር የሰደደ የቆየ የጉበት መቆጣት (ክሮኒክ) ሲባል

የህመሙ ምልክቶች ስድስት ወርና ከእዚያ በላይ ሲቆይ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ድንገተኛው ሄፖታይተስ በቀናት ውስጥ ይጀምርና በሁለት ወይም በሦስት ወራት በዛ ከተባለ በስድስት ወር ውስጥ ህመምተኛው ከበሽታው ያገግማል፡፡ የሄፖታይተስ መንስዔዎች በሁለት ይከፈላሉ።

ተላላፊ (ከኢንፊክሽን) ጋር የተያያዙ እና ከኢንፌክሽን ጋር ያልተያያዙ ናቸው፡፡

በአብዛኛው በሽታው የሚከሰተው ግን ከኢንፊክሽን ጋር በተያያዘው መንስዔ ነው፡፡ ከኢንፊክሽን ጋር በተያያዘ ለሚመጣው በሽታ መንስዔ ከሚሆኑት ውስጥ
👉ከፍተኛ መጠን ያለው የአልኮል መጠጥ
👉መድሐኒቶች፣ የኢንዱስትሪ ኬሚካሎች፣ መርዛማ ነገሮች ይጠቀሳሉ፡፡
አልፎ አልፎ የሰውነታችን የውስጥ መከላከያ (ኢሚዩኒቲ) ሲዛባ የእራሳችን የበሽታ መከላከያ ጉበታችንን ይጎዳውና «አውቶ ኢሚዩን» ሄፖታይተስ የተባለውን የጉበት መቆጣት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ምንም መንስኤው የማይታወቅ የጉበት መቆጣት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም «ክሪብቶጄኒክ» ሄፖታይተስ ይባላል፡፡

#ሄፖታይተስ_ቢ_ምንድንነው

አብዛኛው ሄፖታይተስ የሚከሰተው በአምስት ዋና ዋና የጉበት ቫይረሶች ማለትም ሄፖታይተስ #ኤ #ቤ #ሲ #ዲ እና #ኢ ተብለው በሚጠሩ የቫይረስ ዓይነቶች ሲሆን፤ የእያንዳንዳቸው ባህሪና ምንነት የሚታወቀው በውስጣቸው ባለው ጄኔቲክ ማቴርያል ነው፡፡ ከአምስቱ አራቱ ሄፖታይተስ #ኤ #ሲ #ዲ እና #ኢ አር ኤን ኤ ቫይረስ ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህ ቫይረሶች በውስጣቸው ያለው ጄኔቲክ ማቴርያል ባለ ነጠላ እረድፍ ነው፡፡ ሄፖታይተስ ቢ ባለጥንድ ረድፍ ጄኔቲክ ማቴርያል የያዘ በመሆኑ ዲ ኤን ኤ ቫይረስ ይባላል፡፡ በእዚህም ከላይ ከተጠቀሱት የሄፖታይተስ ቫይረሶች ይለያል፡፡ እነዚህ ቫይረሶች በሽታን የሚያመጡበት መንገድ ይለያያል፡፡ ሄፖታይተስ #ኤ እና #ኢ ከንጽህና ጉድለት ጋር በተያያዘ በተበከለ ውሃና ምግብ አማካኝነት የሚተላለፉ ሲሆን፤ ሄፖታይተስ #ቢ #ሲ እና @ዲ ልክ እንደ ኤች አይ ቪ ቫይረስ ከደምና ከደም ጋር በተያያዙ መንገዶች የሚተላለፉ ናቸው፡፡
እነዚህ ቫይረሶች የሚራቡት ጉበት ውስጥ ሲሆን ፤ከተራቡ በኋላ ወደ ደም ዝውውራችን ይገባሉ። በእዚህ ጊዜ ሰውነታችን ቫይረሱን ለመዋጋት ፀረ ህዋስ (አንቲ ቦዲ) ያመርታል፡፡ ሄፖታይተስ #ኤ #ሲ #ዲ እና #ኢ በተዘዋዋሪ መልኩ በምርመራ የሚገኙ ሲሆን ፤ እነዚህ ፀረ ህዋሶች በደማችን ውስጥ በምርመራ በመለየት የትኛው ቫይረስ እንደያዘን ለማወቅ ይቻላል፡፡ ሄፖታይተስ ቢ ከሌሎች ለየት የሚለው የቫይረሱን አካል (አንቲጅን) በምርመራ ከደም ውስጥ በመለየት ቫይረሱ እንዳለብን በቀጥታ ማወቅ ይቻላል፡፡ በቫይረሱ ሽፋን ላይ ያለው አንቲጅን (ሄፖታይተስ ቢ ሰርፊስ አንቲጅን) በደም ውስጥ ከተገኘ ቫይረሱ እንዳለብን ያሳያል፡፡ ከቫይረሱ ውስጠኛው ክፍል የሚመነጭ አንቲጅን (ሄፖታይተስ ቢ ኢ አንቲጅን) በምርመራ ከተገኘ በደም ውስጥ ያለውን የመራባት መጠንና የማስተላለፍ አቅሙን ከፍተኛነት ያሳያል፡፡
የቫይረሱ መጠን በላቦራቶሪ በደም ውስጥ በዝቶ በአንድ ሲሲ ከአሥር ሚሊዮን እስከ መቶ ሚሊዮን ከተገኘ የህመሙን ደረጃ ከፍተኛነት ያሳያል፡፡ በአጠቃላይ የተለያዩ አንቲጅኖችን በደም ውስጥ በመመርመር የበሽታው ደረጃ ምን ያህል እንደሆነና ዓይነቱን ለማወቅ ይረዳል፡፡
አምስቱም የጉበት ቫይረሶች ድንገተኛ የጉበት መቆጣት ሲያመጡ ተመሳሳይ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡ ሄፖታይተስ #ኤ እና #ኢ ድንገተኛ የጉበት መቆጣት ያስከትሉና ጉበታችን በራሱ ጊዜ አገግሞ ሰውነታችንም ቫይረሶቹን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። ስለዚህም በደም ውስጥ አይቆዩም፡፡ ሄፖታይተስ #ቢ #ሲ እና #ዲ ደግሞ ምንም ምልክት ሳያሳዩ በደም ውስጥ ለረዥም ጊዜ በመቀመጥ እየተራቡ ሄደው ስር የሰደደ የጉበት መቆጣት መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የጉበት በሽታና ካንሰርንም ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
ከአምስቱ ቫይረሶች ሄፖታይተስ #ዲ ስንኩል በመሆኑ ለብቻው ሰውን የማጥቃት አቅም የለውም፡፡ ሰውን የሚያጠቃው ከሄፖታይተስ ቢ ጋር በመዳበል ወይም ሄፖታይተስ ቢ የተያዘን ሰው ነው፡፡ ሁለቱ አብረው ሲከሰቱ የሚያስከትሉት ጉዳትም የከፋ ነው፡፡
ሄፖታይተስ ቢ በአገሪቱ በከፍተኛ የጉበት በሽታና የጉበት ካንሰር መነሻነት በዋነኛነት የሚጠቀስ ቫይረስ ሲሆን ፤ከኤ እስከ ኤች የሚደርሱ ዝርያዎች (ጅኖታይፕስ) አሉት፡፡ እነዚህ ዝርያዎች በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ ሲሆኑ፤ የሚያስከትሉት የህመም መጠን አንዱ ከሌለው ይለያያል፡፡ አንዳንዶቹ በህክምና ቶሎ ሲድኑ አንዳንዶቹ ግን አይድኑም። በእዚህም ምክንያት ሄፖታይተስ ቢን ለህክምና አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

#በሽታው_ከሰው_ወደ_ሰው_ ይተላለፋል

አዎ! በሽታው የሚተላለፈው በቫይረሱ በተበከለ ደም፣ ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ የተበከሉ መርፌዎችና ስለታም ነገሮችን በጋራ በመጠቀም፣ በወሊድ ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ በመሳሰሉት መንገዶች ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
ቫይረሱ በበሽታው በከፍተኛ ደረጃ በተጠቁ ሰዎች ውስጥ መጠኑ ይለያይ እንጂ በማንኛውም ፈሳሽ የሚገኝ በመሆኑ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፍ ያስችለዋል፡፡
የሄፖታይተስ ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ለመግባት ቀዳዳ ይፈልጋል፡፡ ምንም ጉዳት የሌለው ጤነኛ ቆዳ ውስጥ አልፎ አይገባም፡፡ ነገር ግን የዓይናችን የውስጠኛው ሽፋን ያለምንም ችግር ሊያስተላልፈው ስለሚችል ቫይረሱም ያለበት ፈሳሽ ዓይናችን ውስጥ ቢረጭ በበሽታው ለመያዝ መንገድ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በቫይረሱ የተጠቁ ሕሙማንን የሚያስታምሙ የቤተሰብ አባላት የተላጠ ወይንም የተሰነጠቀ ማንኛውም ቁስል እጃቸው ላይ ካለ በፕላስተር መሸፈን አለባቸው፡፡
ማንኛውም ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ (ላብንና ዕንባንም ጨምሮ) በጥንቃቄ መያዝና መወገድ አለበት፡፡ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ሲገባ ከዘጠና እስከ ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሰውነታችን መከላከያ ኃይል ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ አስወግዶ ቋሚ መከላከያ ይፈጥራል፡፡ ቫይረሱን ይዘው የሚቀሩት ከአንድ እስከ አምስት ከመቶ የሚሆኑ ሕመምተኞች ብቻ ናቸው፡፡ ቫይረሱ ካለባቸው ጥቂቶቹ ስር የሰደደ የጉበት መቆጣት ሲይዛቸው አብዛኞቹ ምንም ምልክት አያሳዩም፡፡ በአጠቃላይ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ ሃያ ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ከፍተኛ የጉበት በሽታ (ክሮኒክ ሊቨር ዲዚዝ) ይይዛቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ከዓመታት በኋላ የጉበት ካንሰር ሊይዛቸው ይችላል፡፡
ኢንፌክሽኑ በብዛት የሚታየው ከሃያ እስከ አርባ ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ሲሆን ሕፃናት ላይ እንብዛም አይገኝም፡፡ ከአርባ ዓመት ዕድሜ በላይ ባሉ ሰዎች የበሽታው መጠን የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል፡፡
ቫይረሱ ወደ ሰውነት በሚገባበት ወቅት ድንገተኛ የጉበት መቆጣት የሚያሳየው ምልክት
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉ማቅለሽለሽ
👉የሰውነት መቀነስ
👉ዐይን ቢጫ መሆን
👉በቀኝ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል የህመም ስሜት የሚሰማ ሲሆን፤
ህመምተኛው ህክምና ከወሰደ በሦስት ወር ውስጥ ያገግማል፡፡ ስድስት ወር ከሞላው ግን ስር ወደ ሰደደ የጉበት በሽታ ይቀየራል፡፡

#ህክምናው_ምንድነው
#ሪህ

ሪህ በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል የህመም ዓይነት ነው፡፡ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ንጥረ ቅመም ሲሆን ይህ ንጥረ ቅመም በሰውነት ውስጥ በተወሰነ መጠን መገኘት ያለበትና በሽንት በኩል የሚወገድ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲሆን ሰውነታችን ለማስወገድ አቅም ያጣል፡፡ በዚህን ጊዜ ካልሼም ፎስፊት ወደሚባል ጠጣር ንጥረ ነገርነት ተቀይረው ወደ መገጣጠሚያ ቦታዎች ይሰበሰባሉ፡፡ ከዚህም ሌላ የተከማቸው ዩሪክ አሲድ በኩላሊት ውስጥ እና በሽንት ማመላለሻ መስመሮች ውስጥ በመዝቀጥ የኩላሊት ጠጠር ሊፈጥር ይችላል ፡፡

#መንስኤው_ምንድንነው

ለሪህ የጤና ችግር በመንስኤነት የሚገለፁ የተለያዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

#የዕድሜ_መጨመር

በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው በላይ የንጥረ ነገሮች መፈጠርና መከማቸት
በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አማካኝ
ከቤተሰብ መካከል የጤና ችግሩ ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድል ይኖረዋል
ምክንያታቸው በውል የማይታወቅ ጉዳዮች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች ለሪህ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ቀይ ሥጋ፣ ጉበት ኩላሊትና የጭንቅላት ስጋን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም አልኮል መጠጣት ለሪህ በሽታ ተጋላጭ የመሆን ዕድልን ያሰፋሉ፡፡ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ
👉የሰውነት ክብደት መጨመር፣
👉በቁጥጥር ስር ያልዋለ ደም ግፊት፣
👉ውሃ በብዛት ያለመጠጣት፣
👉የኩላሊት በሽታና ለተለያዩ በሽታዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለሪህ በሽታ ተጋላጭ ያደርጋሉ፡፡

#የህመሙ_ምልክቶች

👉ከትንሽ የጣት ጫፍ እስከ ትላልቆቹ የሰውነት ክፍሎች አካባቢያሉ መገጣጠሚያ ቦታዎች ያብጣሉ
👉የሰውነት ትኩሳት መከሰት
👉 ከቁርጥማት ጀምሮ መላ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በመንካት እስከሚቸግር ድረስ ህመም
👉 ከፍተኛ ስቃይ ያለው ህመም
👉መገጣጠሚያ አካባቢዎች በተለይ መልኩ መቅላት
👉በመገጣጠሚያ አካባቢዎች የማቃጠል ሁኔታ ይከሰታል
👉የጡንቻ መዛል በተለይ ጠዋት ጠዋት እጅና እግርን ለማንቀሳቀስ መቸገር ይኖራል
👉የጤና ችግሩ ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆየ በመገጣጠሚያ ቦታዎች ጠጣርየሆኑ ነገሮች ይፈጠራሉ
👉በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ
👉ቁርጥማት
👉በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ፡፡

#ህክምናው_ምንድነው

አንድ ሰው ለመጀመሪያ ወይም በተደጋጋሚ ጊዜ የሪህ በሽታ ከተከሰተበት ከፍተኛ ስቃይ ይኖረዋል፡፡ የመጀመሪያው የህክምና ስቃዩን ለማስታገስ የሚያስችል መድሃኒቶች ይታዘዛሉ ፡፡ በዚህ ረገድ Non-Steroid Anti-Inflamaty drugs /Nsaids/ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለውጥ ካልመጣ Corticoid Steroids የሚባሉ መድሃኒቶችን በመርፌ ወይም በሚዋጥ መልክ ይሰጣል ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የህመም ስቃይን ከማቃለል በተጨማሪ መገጣጠሚያ ከጥቅም ውጭ እንዳይሆን ለጊዜው ፋታ ይሰጣሉ፡፡
ሌላኛው የህክምና ዘዴ Uric acid ከሰውነት ውስጥ እንዲቀንስ ማድረግ የሚችሉ መድሃኒቶች ነው፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለማከም ጥረት ይደረጋል፡፡ እጅና እግር መንቀሳቀስ ካቆመ በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡

#መልካም_ጤና