መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ቢጫ_ወባ (Yellow Fever)

#ቢጫ_ወባ_በሽታ_ምንድነው?

የሎው ፊቨር ወይም ቢጫ ወባ የሚባለው በሽታ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣና የመድማት ችግር የሚያስከትል በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፍ የትኩሳት በሽታ ነው፡፡

👉ትንኟ በበሽታው ከተያዘ ሰው ደም በምትመጥበት ጊዜ በተህዋሲያኑ ትያዛለች፤የተህዋሲያኑ ተሸካሚ የሆነች የወባ ትንኝ ከጤነኛ ሰው ደም ለመምጠጥ ቆዳውን በምትበሳበት ጊዜ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
👉በሞቃታማ ስፍራ በሚገኙ ጥቅጥቅ ባሉ ደኖች፣ በስራ ወይም መኖሪያ ቦታ ረግረጋማና የአቆረ ውሃ፤ በየቦታው የተጣሉ ውሃ የሚያቁሩ ቁሳቁሶች፣ በማይከደኑ የውሃ ማጠራቀሚያ እቃዎች ለትንኞች መራቢያነት ምቹ ስፍራዎች ናቸው፡፡

#የቢጫ_ወባ_በሽታ_ምልክቶች

የመጀመሪያ 3 እና 4 ቀናት የሚከሰቱ

👉በድንገት የሚከሰት ትኩሳት
👉ብርድ ብርድ የሚል ስሜት፣
👉 ራስ ምታትና አጠቃላይ የሰውነት ህመም፣
👉 የጀርባና የጡንቻ ህመም፣
👉 ማቅለሽለሽና ትውከት ዋናዎቹ ናቸው

#በሁለተኛ_ደረጃ_የሚከሰቱት

👉የትኩሳት ማገርሸት፤
👉የሰውነት ወይም የዓይን ቢጫ መሆን (juandice)፤
👉የሰውነት (ከዓይን፣ አፍ፣ አፍንጫ፣ ወ.ዘ.ተ.) መድማትና
👉ደም የተቀላቀለበት ትውከት ናቸው፡፡

የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በአስቸኳይ ሕክምና እርዳታ በጤና ተቋማት ካላገኙ ራስን መሳትና ብሎም ሞት ያስከትላል፡፡

#የቢጫ_ወባ_በሽታ_መከላከያ #መንገዶች

👉በሽታው እጅግ አስተማማኝ የሆነ ምንም ጉዳት የማያስከትል፣ በአንድ ጊዜ የሚወሰድና ለበሽታው የዕድሜ ልክ የሰውነት መከላከያ የሚፈጥር ክትባት ስላለው ክትባቱ በሚሰጥበት ወቅት በመገኘት በነፃ መከተብ በሽታውን፡ መከላከልም ሆነ በሕክምና ሙሉ በሙሉ ማዳን ይቻላል፡፡

👉ትንኟ እንዳትራባ መቆጣጠር

፦ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ቁሳቁሶችን ማስወገድ፣
፦ውሃ ያቆሩ ስፍራዎችን ማጠንፈፍ ማድረቅ
፦ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ስፍራዎችን ፀረ-ተባይ ማስርጨት፣
፦በቤት ውስጥ የወባ መግደያ ፊሊት መርጨት፡፡

እንዴት_የትንኟን_ንክሻ_እንከላከል

፦እጀ ሙሉና ረጂም ልብሶችን መልበስ
ትንኝ ማባራሪያ የሰውንተ ቅባት መጠቀም፤
፦በማንኛውም ስዓት የአልጋ አጎበር በመጠቀምና መተኛት፤
፦መኖሪያ ቤትን የትንኝ መግደያ ፍሊት በመርጨት ትንኞችን ማስወገድ፤

#የበሽታው_ምልክቶች_ሲታዩ

በአስቸኳይ በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ ሪፖርት ማድረግና ሕክምና ማግኘት ከበሽታው ለመዳን ስኬታማ ለውጥና ፈውስ ለማግኘት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡

#መልካም_ጤና

Like and share