ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የራስ_ሃሳብ
.
.
.
ጡት እንዳጣ ህጻን ፣ መራር እንዳጠቡት
እንደተከፋ አንጀት ፣ ከራስ እንዳፋጩት
ሆዷ እንደጮኸ ሴት፣ርሃብ እንደጠናት
ባሏ እንደቀረባት ፣ እንደ ልጅ አልባ እናት
እንደ ወጥመድ አይጥ ፣ እንደ መረብ አሳ
እንደ እረኛ ዋሽንት ፣ እንዳዘለው ገሳ
መውጫ እንዳጣ ትንፋሽ ፣ ውስጤን እንዳመቀ
በ'ምባ ታጥቦ ሆዴ ፣ ላይፈስ በፈለቀ
ቆሻሻው ጸድቶለት ፣ ንጹህ ነገር ቢያጣ
ባር ባር ይለው ጀመር ፣ ወዳጁን እንዳጣ...


ሃገር ምን ይለኛል? ባልተናገረኝ ሰው ባልሰደቡኝ ስድብ
ቁዝም አቅበዝዝዞኝ በሃዘን ድባት ውስጥ ከደስታዬ ሳድብ?
ምንይለኛል ቀየው ባልከፋብኝ ኑሮ ባልተጫነኝ በደል
አይኔ እንባን አርግዞ ለማማጥ ሲታደል ለመውለድ ሲጋደል?

መሃጸነ አፌ እንደ አይኔ ሁሉ ምናለ ቢነጥፍ?
ያረገዘን ሃሳብ በመውለድ እሳቤ ሳይምጥ ከሚለፍፍ?

ፈልቆ ያልፈሰሰ ተምጦ የቀረው የሃሳብ ልጅ ልጄ
ያንተከትከኛል ለሱ ባልኩት እሳት በእንባዬ ምትክ ትኩስ ደሜን ጥጄ

ይተናነቀኛል ህቅ ስቅ እያለ
ወደ ውስጤ ፈሶ ሞልቶ እያጎደለ
ሃሴት ከኔ አርቆ ድባት እያደለ....

አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
የራሴው ሃሳብ ነው ፣ ውስጤን የሚወቅሰው
ቃሌን ማሰልሰሌ ፣ ሆዴን የሚብሰው

አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
ወደፊቴ ያልኩት ፣ ዛሬን የሚያምሰው
ሃሳቤ ቢሰድበኝ ፣ ሽፍን የማለቅሰው

አልበደለኝ በደል አልተናገረኝ ሰው።

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~


የራስ ሃሳብ የጭንቅላት
እየኳለ እያቀላት
ልጇን ወልዳ ልጇ በላት
አይመለስ አይገባላት

እንኳን ሰቡ አዘነለት ሃዘን ልቤን
ይቅር በለኝ ያወጋሁህ ክፉ ሃሳቤን


Tomi


@getem
@getem
@getem
👍1