ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እርጉም ድብርት ልቤን ሰርጾ፣
በእልፍ ዱካክ ሐዘን ሊግት ...
ንቁ ጅስሜን በ'ሾህ ቀርጾ፤
ጭምት! ፍዝዝ!
ቁዝም! ትክዝ!
አርጎ ሚጥል አካል ነፍሴን ...
በእንባ ለበቅ በአመል ቁጣ፣
ፊትሽ ዳምኖ ያየ ዐይኔ ...
እንደ ሶምሶን ኃይሉን ሲያጣ።

ንጥር ሀሴት ደሜን ሞልቶ፣
በሳቅ ጀንበር ፌሽታ ሊያጭድ ...
ድድር ጥርሴን ፍካት ቀብቶ፤
ፍንትው! ፍንክንክ!
ፍግግ! ፍልቅልቅ!
አርጎ ሚሰድ ጽልመት በሬን ...
በልዝብ ቀልድ በልጅ እብደት፣
ፊትሽ ፈክቶ ያየ ልቤ ...
እንደ ዳንኤል ሲቸር እምነት።

ሀሴት ጎራሽ መፍለቅለቄ
የሚቀየር ... በአዛኝ ፊትሽ!
ድብርት አዛይ መከፋቴ
የሚለወጥ ... በድንቅ ሳቅሽ!

ቢገርምሽ...
ቢደንቅሽ...
ኑረት እርሳስ ፈተና ኩል፣
እንደራሱ ልቤን ሊኩል ...
ጣቱን ቢያረግ ሰበር ሰካ፣
ህይወቴ መልክ የላትም
ባንቺ ገጽ ነው የምትዳምን ...
ባንቺ ገጽ ነው የምትፈካ።

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@paappii
👍309
መምሰል
°°°°°°°°

ከደጇ ቁሚያለሁ
በረከት ለማግኘት ከ'ናቴ ፍልሰታ፣
ማረጓን ያመነ
ይኸው ያሰማል መዝሙርና እልልታ።
"ማርያም አረገች አረገች"

ቀና ብዬ አየሁ የሰማዩን ከፈን፣
ለጠርጣራው ልብሽ ማሳረፊያ 'ሚሆን፥
ከሰጠችሽ ብዬ እንደ ቶማስ ሰበን።

አየሽ ሞኝነቴን
ከፍቅሬ የተነሳ ላንቺ ምህረት ስሻ፣
ከስንት ዘመን በፊት
ያረገች እናቴን
እንዳ'ዲስ ሳሳርግ በምናቤ ዋሻ።

ግን መጥተሽ ይሆን?


ህጻናት በክብር
ስጋ እና ደሙን ቀምሰው ሲመለሱ፣
ቆርበሽ ከሆን ብዬ
እስክትወጭ አያለሁ ከቤተ መቅደሱ።

አየሽ የዋህነቴን
በሴት ግዳጅ ታስረሽ
መግባት እንደማትችይ እያወ'ኩ ጠንቅቄ፣
ትኖሪያለሽ ብዬ
በከንቱ ሳማትር በፍቅርሽ ታንቄ።

ግን መጥተሽ ይሆን?


እልፍ ሆኖ ሳለ
እምነት የተቀባ ነጠላ ያጣፋ፣
ቅጽሩን ሙሉ ብቃኝ
አንችን የሚመስል አንድ ውብ ሴት ጠፋ።

ተመልከች እብደቴን
ተስፋዬ ተሟጦ
ለስግደት ስደፋ ከ'ናቴ ስዕል ፊት፣
ወለል ብሎ ታየኝ ያንቺ መሳይ ውብ ፊት፤
ይኸው ተገፈፈ
ማጣት ያሳወረው
የዓይኔ ላይ ጉድፍ ልክ እንደ ቅርፊት።


ቁጭ እሷን!!
ቁጭ አንችን!!

ሰዓሊ ለነ ቅድስት!!

ለማን ነው የሰገድኩት?

ግን አንቺ ነሽ?


አንቺም አር'ገሻል እንደ እመቤቴ?


አበድኩ መሰለኝ
የማይሆን ጥያቄ ወጣ ካ'ንደበቴ።

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@paappii
32👍16👎3😁2
ይጎምዳል የምላሷ ስለት
ይፋጃል የልቧ ፍም ግለት

መቁረጥ ነው ስራዋ
መጉረድ ነው ሴራዋ
መንደድ ነው እድሏ
ማንደድ ነው አመሏ

ለመቅረብ አትመች ማራቅን አትፈቅድ
ልብን እንደ ጨርቅ አትፈራ ስትቀድድ
አትሸሽ ጨክና አትጠጋ ደፍራ
ጨጓራ እንደ ከሰል ስታፍም አትራራ

ተረተረችኝ
ጣለችኝ ቀርድዳ
መስፋት አያውቅ ጣቷ ተወችኝ ጎራርዳ
አቀጣጠለችኝ
ላዬ ላይ እሳት ሰድዳ
ማጥፋት አያውቅ አፏ ሸሸችኝ አንድዳ

እስቲ አስተምሯት አንጀቷ ይራራ
ልብስ ታድርገኝ ልለፍ በእጇ ስራ
እስትንፋስ ትቸረኝ ልዳን በከንፈሯ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@paappii
24👍16🔥3👎1
ደጇ ተንበርክካ ትሰዳለች ጸሎት
በ'ለምን?' ክር ሰፍታ ምሬት አዘል ብሶት

"ለምን ይኼ በኔ?
ለምን እኔን ብቻ?
አሁንስ አቅቶኛል
ተሸክሞ መጉበጥ የችግር ስልቻ
ወይ መፍትሔ ላክልኝ ወይ እኔን ውሰድ
ሰክኖ መቆም ከብዶኝ
እንደ ሰከረ ሰው አልኑር ስንገዳገድ
በቃኝ!
ከእስራቴ ፍታኝ!
ለምን?
እንዲህ ያለ ፈተና?
ለምን?
ይህ ሁሉ መከራ?
ሰው አይደለሁ ድኩም
ተስፋ መቁረጤ ነው ጠብቂኝ አደራ
ማርያም እመቤቴ
ድንግል እናቴ ..."

ደግማ ደጋግማ ስሟን እየጠራች
የደረሰባትን በእንባዋ እያወራች
ቆየች ስዕሏ ፊት
ሲረግፍላት ታየኝ ሸክሟ እንደቅርፊት

አቤት መታደሏ
ቀናሁ በለቅሶዋ ቀናሁ በመስቀሏ

በእናት እቅፍ ተሸጉጦ
በጫንቃዋ ተቀምጦ
እሹሩሩ መባል ፍም እንባን መታበስ
እንዴት አይፈጥር የመንፈስ መታደስ
ስትፈካ ታየችኝ ስትስቅ ከልቧ
ፀሐይ ቀናች መሰል
ጸዳሏን ልትለምን ቆመች ካጠገቧ

አቤት መታደሏ
ሰላም ውስጧን ሞላ

ጭንቀት ደረመኑን
ሐዘን ክፉ ጦሩን ይዞ ጠፋ ከሷ
በማርያም ውብ መዳፍ
ሲጠረግ እንባዋ ሲታጠብ ስስ ነፍሷ

አቤት መታደሏ
ቀናሁ በአባሿ ቀናሁ በጸዳሏ

#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
82👍25
ስረቅ!
ንጠቅ!
ዝረፍ!
ግረፍ!

ክፉ ሀሳብ
ነፍሴን ሊቀጭ ውስጤን ሲያምስ፣
#ስዕልሽ ፊት
ላፍታ ብቆም ጥፋት እብስ!

ተንኮል ወሮኝ
ቅጥፈት ባህር ሊዘፍቀኝ ሲል፣
#ተአምርሽን
ድንገት ባስብ ጋኔል ቅጥል!

እርጉም ሀሴት
ሊያሳፍሰኝ ከሴት ጭን ስር፣
እርኩስ ስሜት በደል ሲጭር፤
#ውዳሴሽን
ገልጬ ባይ ሰይጣን እርር!

ውድቀት ጠርቶኝ
ክፋት አንቆኝ በኃጢአት ስዋጥ፣
#ማር_ስምሽን
ልክ ስጠራ ዲያቢሎስ ላጥ!

ኃጢአት ጦሩን
ሲሰድ ሰብቆ በጥላቻ፣
#ጋሻዬ ነሽ
#ድንግል_ማርያም
ያጋንንትን መርዝ መግቻ።

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
103👍32🎉3👎2🔥2
ተአምር
"""""""""
ዘንዶ ሳይውጠኝ - ወገቤ ላይ ተጠምጥሞ
ሽቅብ ቢወስደኝ - ወደ ደብረ ዳሞ፤
አንችን ከጎኔ - ፈፅሞ ካላየሁ
ተአምር ነው ብዬ … መች እቀበላለሁ፡፡

ድንገት ተከብቤ - በአንበሳ መንጋ
ሊበሉኝ ሲጥሩ - አፋቸው ቢዘጋ፤
አንችን በዙሪያዬ - ቆመሽ ካላየሁ
የመዳኔን ሚስጥር
ከተአምር ጋር … መች አያይዛለሁ፡፡

ግዙፉ ጎልያድ - ጥሩር ለብሶ
ህይወቴን ሊነጥቅ - ሲመጣ ገስግሶ፤
ወንጭፍ ወንጭፌ - በጠጠር ስጥለው
ከጎኔ ሁነሽ - ስታይኝ ካላየሁ
የድሌን መገኛ
ተአምር ነው ብዬ … መች አስባለሁ፡፡

እመቤቴ
ከድርጊቴ በስተጀርባ - አንችን ካላየሁ በቀር፤
ተአምር አይመስለኝም - የተደረገው ነገር፡፡

በህይወት እያለሁ … ተአምር ምለው እኔ፤
አንችን ማግኘት ነው - ሁልጊዜም ከጎኔ፡፡

(ሌላው ጥንቅር ብሎ ይቅር¡¡¡)

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
53👍37👎2
ሙሾ አውራጅ እንባ አርጋፊ
ምሬት ዘሪ ሞት አቃፊ
ደስታ ማላቅ ሐዘንተኛ
ሁሌ አልቃሽ ብሶተኛ

ግና ዛሬ
ድቅድቅ ጥሼ እንባ ላፈስ
በመንገድ ላይ ስንከላወስ
ድንገት ቆመ
የቅጽሩን ጥግ እግሬ ታኮ
ይጸልያል ምዕመኑ ተንበርክኮ

አሰገግኩ ወደ ውስጥ
አማተርኩ አጮልቄ
ምን ልተንፍስ? ... ምን አውቄ?
ምስጋና እንደው አልለመደኩ
በዝምታ አለቀስኩ

{ለቅሶ አይደል የለት ጉርሴ?
ምሬት አይደል እስትንፋሴ?}

እመቤቴ
በእንባ መሐል አየሁ ምስልሽን
ስታጫውች ውብ ልጅሽን

በዛች ቅጽበት
ተሰለበ ሹል ብሶቴ
ተገፈፈ ጽልመት ፊቴ
ልቤ ጠጣ
ከእቅፍሽ ሀሴት ቀድቶ
እንኳን እኔ
ሐዘን ሳቅ አንቺን አይቶ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
69👍22🤩3😁2😢2🔥1
ጠጥቻለሁ ... መራር ኃጥያት
በልቻለሁ ... እርጉም ክፋት
ወጥቻለሁ ... ከሰው ተራ
ተስያለሁ ... እንደ ካራ

ማረድ ... የጽድቅ አንገት
መቁረጥ ... የጾም አንጀት
መበጠስ ... የጸሎት ክር
መጉረድ ... የምጽዋት ስር

ግብሬ ሆኖ የተጣባኝ
የቁም ሞትን መኖር ቀባኝ

ድንግል ማርያም የለሁም በእውነት
ካንች ተለይቶ መች አለ ህይወት

አጥቢኝ የጾም ወተት ኃጥያትን ማርከሻ
ልጉረስ ከ'ጅሽ ፍቅር ክፋት መደምሰሻ
እናቴ እያልኩኝ ልጥራሽ እንደ ሰው
ውለጅኝ በምልጃሽ ሞቴን ልደምስሰው

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
125👍43👎5🤩2
ስንኩልኩል ተራማጅ በኃጥያት ቦይ ፈሳሽ
ቀና ብዬ ማላይ የህይወቴን ቀያሽ፤
እንደነገሩ ሂያጅ
እንዳሻኝ ወራጅ
ነጥዬ ማላውቅ ጠላት እና ወዳጅ፡
ስንፏቀቅ የምኖር ውድቀት ተንተርሼ
ዘመኔን የበላሁ
ራሴን የጎዳሁ አዳኜን ነክሼ።

የእውር ድንብር ተጓዥ ስንኩልኩል ወልካፋ
እየሄድኩ አልነበር ራሴን ላስጠፋ
ታዲያ እንዴት ተረፍኩ?
እስትንፋስን ታቀፍኩ?
መውደቂያዬን ሚያቆም መጥፊያዬን ሚያድን
ምን ነበር እኔጋ ፈዋሽ የቁም በድን?
ምንም!
ማንም!

እንዴ...
ወይ ጉዴ
ረስቼህ አልነበር ... እንዴት አስታወስከኝ
ንቀት ግፌን ትተህ እንደምን ታደግከኝ
ጥል ምርኩዝ ሲጥለኝ እንደምን ደገፍከኝ።
እንዴት ታዘዘልህ ክንፍህ እኔን ሊጋርድ
ገፍትሬህ አይደለ እንዲህ ምንገዳገድ።

ሚካኤል አባቴ
ጉዞዬ ወደ ምሬት መንገዴ ወደ ሞት
የት አግኝተህ ቀየርክ የኔን ስብር ህይወት

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
37👍25👎1
ተጋፈጥኩ መከራዬን
ተፋላምኩ ፈተናዬን
ኃይሌን ጨረስኩ እንጂ መች አገኙሁ ውጤት
እኔ አለቅኩ እንጂ መች በቃሁ ለስኬት
ሩጫዬን ገታሁ አቆምኩ ትግሌን ላፍታ
ቃኘሁ ድክመቴን የሽንፈቴን ቃታ
ለካ
ብቻዬን ነው ምጓዝ እርቃኔን ወጥቼ
መከታ ጋሻዬን ረዳቴን ትቼ
ለካ
ውልክፍክፍ ስንኩልኩል ነበር አሯሯጤ
እውር ድንብር ነበር ሚወነጨፍ ውስጤ
ለካ
በዜሮ ተባዝቷል ሙከራ ጥረቴ
አንቺን ሳልይዝ ሂጄ ድንግል እመቤቴ

አፈገፈግኩ ወደ ኋላ
ተመለስኩ ወደ ቀልቤ
ሰአሊ ለነ እያልኩ ታጠቅኩሽ በልቤ

ይኸው ነጻ ጥርጊያው
ይኸው ቀና መንገዱ
ገና ሳልጠጋው
ሲያዘቀዝቅ አየሁ  የመከራ ቀንዱ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
96👍37👎1
ባፈቀርኩት ሰው ስለተጎዳሁ
ባፈቀረኝ ሰው ስለተከዳሁ
ፍቅር ሚባል ቃል በሰማሁ ቁጥር
ሳጥናኤል ነው በአእምሮዬ ቋት ቀድሞ ሚሰፍር

አትፍረጅ ብስቅም
አይግረምሽ ባፌዝም
አፈቅርኃለው መባል
የልቤን ቅንጣት ስጋ ቆንጥጦ አይዝም

ትወጂኛለሽ!
እና ምን አገባኝ?
መልስ ሲፈልግ ነው
ፍቅር መስቀል አጥቶ መቀመቅ ያስገባኝ

ትጠብቂኛለሽ!
አቦ ተንቀሳቀሽ!
መከተል አይሻም
የተፈቃሪ ልብ አፍቃሪ ሳይሸሽ

ትጸልይኛለሽ!
አትሞኝ አንች ሴት
የተመኙት ዕለት
እንደዋዛ አይገኝ ሞት እና ሀሴት

ይደቁስሻል
ያበራይሻል
በፍቅር ተገን ሰይጣን ለምድ ለብሶ
ጠልተሽኝ ኑሪ
ልብሽ ይቸንከር ደም እንባ አልቅሶ

ባልጠበቀው ነው ጋኔል ሚረታ
ወደድኩህ ሳትይ
ፍቅርሽን ግለጭ ልክ እንደ ጌታ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
👍4312😢12😱6🔥3👎1
ቢፍለቀለቅ ንፍር ውኃ
... ... ... ቢግለበለብ እቶን እሳት
ልጣል ብያዝ በአጥፊ እጆች
... ... ... ብወረወር ተብሎ ቅጣት
ይከፈታል ለምስጋና
... ... ... ቢሸበብም አፍ መዳፌ
መቀዝቀዙ ከቶም አይቀር
... ... ... ነዶ ቢታይ መጥፊያ ሰይፌ
አይወረኝም አንዳች ፍርሃት
... ... ... አይችልም ውስጤን ሊንድ
አቅፌ የለ ገብርኤልን
... ... ... ለዘላለም በልቤ ክንድ

የተራቡ አናብስቶች
... ... ... እንዲበሉኝ ብጣል ጉድጓድ
ግፍ እንድጋት ቢፈርዱብኝ
... ... ... አምላክህን እያሉኝ ካድ
ስቄ አልፋለሁ በፊታቸው
... ... ... ሺ ቢያዛጋም ሞት ሊውጠኝ
መዘጋቱ ከቶም አይቀር
... ... ... እንድቆይ አምላክ ካጨኝ
አልናወጽም ብቦጫጨቅ
... ... ... አልሰጋም ላፍታ ቅንጣት
ይዤ የለ መልአኩን
... ... ... ለዘላለም በልቤ ጣት

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
70👍31👎2🔥2🎉1
አፍ አውጥቶ ሐኪም ሚጠራው
... ... ... እልፍ ገንዘብ የአሸን ብር
ከታማሚው ስቃይ በላይ
... ... ... አስታማሚን የሚያሸብር፤
አስታማሚን ሚያስደነግጥ
ብርታት ወኔን ሚሰለቅጥ
የሰናፍጭ ቅንጣት ተስፋን
... ... ... አሽቀንጥሮ ወዲያ ሚጥል
ምሬት ብሶት አስዘንቦ
... ... ... በእንባ ገመድ ሚያንጠለጥል።



እንደ ስምኦን ቄሬናዊው
... ... ... ተጋራኹ የልጄን መስቀል
እስኪላጥ ስስ ጫንቃዬ
... ... ... ተሸከምኩም ስጋት ቀንበር።
ትድን ይሆን?
ትሞት ይሆን?
ተፍረከረኩ
ተንኮታኮትኩ፤
ተስፋ አዝዬ
በጭንቀት ዝዬ
እኔን ገበርኩ
ያለኝን ሸጥኩ።
ጨረስኩ!

አየሁት ቤቴን
ዳበስኩት ኪሴን
ካንቺ ምስል በቀር ምንም የለም በእጄ፤
ሁሉን ሽጨዋለሁ ትድን ብዬ ልጄ።
እመቤቴ ማርያም አልሸጥሽ እንደ እቃ፤
ነይ አብረን እናልቅስ ነይ እንዘን በቃ።

ምናለኝ ካንቺ ውጭ
... ... ... ማን አለኝ ካንቺ በቀር
ነይ መድኃኒት ሁኛት
... ... ... የልጄ ልብ ሳይሰበር
ነይ ዳብሻት በመዳፍሽ
... ... ... ነይ እቀፊያት እንደጌታ
አንቺ ነሽ ማር ሐኪሟ
... ... ... አንቺ ነሽ የነፍሷ አለኝታ


እኔማ አቅም የለኝ
እኔማ እጅ አጠረኝ
እንባ እንጂ ምን ቀረኝ!

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
👍4919😢2🤩1
መምሰል
°°°°°°°°

ከደጇ ቁሚያለሁ
በረከት ለማግኘት ከ'ናቴ ፍልሰታ፣
ማረጓን ያመነ
ይኸው ያሰማል መዝሙርና እልልታ።
"ማርያም አረገች አረገች"

ቀና ብዬ አየሁ የሰማዩን ከፈን፣
ለጠርጣራው ልብሽ ማሳረፊያ 'ሚሆን፥
ከሰጠችሽ ብዬ እንደ ቶማስ ሰበን።

አየሽ ሞኝነቴን
ከፍቅሬ የተነሳ ላንቺ ምህረት ስሻ፣
ከስንት ዘመን በፊት
ያረገች እናቴን
እንዳ'ዲስ ሳሳርግ በምናቤ ዋሻ።

ግን መጥተሽ ይሆን?


ህጻናት በክብር
ስጋ እና ደሙን ቀምሰው ሲመለሱ፣
ቆርበሽ ከሆን ብዬ
እስክትወጭ አያለሁ ከቤተ መቅደሱ።

አየሽ የዋህነቴን
በሴት ግዳጅ ታስረሽ
መግባት እንደማትችይ እያወ'ኩ ጠንቅቄ፣
ትኖሪያለሽ ብዬ
በከንቱ ሳማትር በፍቅርሽ ታንቄ።

ግን መጥተሽ ይሆን?


እልፍ ሆኖ ሳለ
እምነት የተቀባ ነጠላ ያጣፋ፣
ቅጽሩን ሙሉ ብቃኝ
አንችን የሚመስል አንድ ውብ ሴት ጠፋ።

ተመልከች እብደቴን
ተስፋዬ ተሟጦ
ለስግደት ስደፋ ከ'ናቴ ስዕል ፊት፣
ወለል ብሎ ታየኝ ያንቺ መሳይ ውብ ፊት፤
ይኸው ተገፈፈ
ማጣት ያሳወረው
የዓይኔ ላይ ጉድፍ ልክ እንደ ቅርፊት።


ቁጭ እሷን!!
ቁጭ አንችን!!

ሰዓሊ ለነ ቅድስት!!

ለማን ነው የሰገድኩት?

ግን አንቺ ነሽ?


አንቺም አር'ገሻል እንደ እመቤቴ?


አበድኩ መሰለኝ
የማይሆን ጥያቄ ወጣ ካ'ንደበቴ።

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
35👍31👎14🤩10
ይመስለኝ ነበር
ፍቅር አዳልጦት ውድቀት ያነቀው
መቼም የማይስቅ ሞትም ቢንቀው
ይመስለኝ ነበር
ሚወደውን ያጣ ትንፋሹ የሚርቅ
እንባ ሲቀለብ ማግኘትን 'ሚንቅ
ይመስለኝ ነበር
ዳግም ማያብብ አንዴ የረገፈ
እምነት ተስፋውን ቆሞ ያሰየፈ
ተሳስቻለሁ
ተጸጽቻለሁ
መምሰል መሆን ላይሆን ባ'ጉል ስጋት ቀንበር
መክሰምን ፍራቻ ወድቄ ለካ ነበር

ይለይልኝ ዘንድ
ትተሽኝ ስትቀዝፊ
ጥለሽኝ ስትከንፊ

ጽልመት ሳቅ አንጣፊ
ፍም እንባ አርጋፊ
እልህ ዘር አብቃይ
ሰው ሸሽቶ ጣይ
ልሆን ለዘላለም ራሴን ሳሰለጥን
አንሽዬ አንሺ ላከ ውድቀቴን የሚጥል
ተነሳሁ ተራግፌ
ተስፋን ታቅፌ

እንኳን ተውሽኝ እንኳን ጣልሽኝ
ጥሩ እጅ ላይ ገፍተሽ አኖርሽኝ

#ኤልዳን
tiktok ... ldan291

@getem
@getem
@getem
19👍8🔥1🤩1
እልልታ
ጭብጨባ
ከአውደ ምህረቱ ተነስቶ ይነፍሳል፤
የሰማእቷ ታ'ምር እንደ ጉድ ይወሳል።

"ሰምታኛለች እናቴ..."
"ታውቃለች አርሴማ..."
ክብሯን የሚመጥን
ይገባል ስለት - ጧፍ፣ ጥላ፣ ብር፣ ሻማ።

ሰው ይጸልያል
ሰው ይለምናል ክፍተቱን አይቶ፣
እኔ ከንቱ ግን
የጎደለኝን አላውቅም ከቶ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፣
ደጅሽን ስረግጥ እታደሳለሁ።

እዪኣት ያቺን ሴት
ከአትሮንሱ ጀርባ የምትዘምረው
ስምሽን ደጋግማ የምታነሳው፤
እኔ እስከማውቃት
ፊደል የሚያንቃት
ኩልትፍ አንደበት - ነው የነበራት።

ምን ጸልያ ነው አፏ የተፈታ?
ምን ብላሽ ይሆን
ቃል አቅሙን አጥቶ ለእሷ የተረታ?
የእኔማ ምላስ አግድም ለፋፊ
ለ'ንቶ ፈንቶ እንጂ ለጸሎት ታጣፊ።

እይው ያንን ሰው
ኑሮ የደቆሰው
የደስታን እንባ ሞልቶ ሚያፈሰው፤
እኔ እስከማውቀው
ሞት 'ሚናፍቀው
ማጣት በዝቶበት ገዳይ ሚፈልግ
ተስፋን ተነጥቆ
አለመኖርን የሚያነበንብ።
ምን ሰጥተሽው ነው ፊቱ የፈካ?
ምን አግኝቶ ነው
የደስታው መጠን ጣሪያ የነካ?
እኔ ሳቅ አላውቅ እንባም አይገደኝ
መኖርም መሞት ትርጉም አይሰጠኝ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፤
ደጅሽን ስረግጥ ነፍስ እገዛለሁ።

#ኤልዳን
tiktok - ldan291

@getem
@getem
@getem
53👍34🔥3
ከዳመናው መሀል ይፈልቃል ኃያል ጢስ
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ

ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ

ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)

አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ

እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር

በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)

ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
20👍17🔥2
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
38👍32🔥6😢1
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
45👍22🔥4👎3
አብሮ መጥፋት

በፍቅር ሰንሰለት እኔን ላንቺ ድሮ፣
ያለፈ ታሪክሽን
የኀጢአቴን ግርሻት ሊያጠፋ ቀን ቀጥሮ፤
"ወደ ኋላ መዞር ላ'ፍታ ሳትመኙ፣
ወደ ፊት ተጓዙ ነጋችሁን ቃኙ!
ለፍቅር ታመኑ ለፍቅር ተቀኙ!"
የሚል ትእዛዝ ሰጥቶን
ትናንትናችን ላይ እቶን እሳት ቢለቅ፣
ወላዋይ መንፈስሽ
ልክ እንደ ሎጥ ሚስት ታየ ሲፍረከረክ፡፡

የቀድሞ ፍቅረኛሽ…
ያ ሁሉ ትዝታ
መጥፋት አብከንክኖሽ በድንገት ስትዞሪ፣
የጨው ሐውልት ግግር
አድርጎ ቢያስቀርሽ የፍጥረት ፈጣሪ፤
ሎጥን ልምሰል ብዬ…
የፍቅርሽ እርምጃ
ከኋላዬ ሲቀር ወደ ፊት አልሄድም፣
አይቼሽ ለማልቀስ
አይቼሽ ለመድረቅ
ያ'ምላኬን ቃል ሽሬ መዞሬ አይቀርም፡፡

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
22🔥3🤩2