ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ዝማሬ ሰብ
።።።።።።።
ከቀፎ ሰገባ ፣ ዋሻ ተሸሽጋ
ከርማ የነበረ ...
ንቢት ይኸው ወጣች ጠሀዩ አማረ
አደይ በመስኩ ላይ ዳግም ተሞሸረ።
ጠል ወጨፉ አልፎ ሰማይ ሲስቅልኝ
ያንተ ቸርነት ነው ሸክሜን የጣለልኝ
እላለሁ! !
እንደጊዜውማ እንደዓመቱ ክፋት
ይህችን አዲስ ጠሀይ ፈክታልኝ ሳላያት
ከአንድ ወጣት ሽመል እግሩ ስር ወድቄ
እንዲህ እንደዛሬው አልታይም ስቄ።
እንደጊዜውማ እንደዓመቱ ጥመት
ወረርሽኝ በሚሉት የደም ውሀ ዥረት
ሳል እያጣደፈ ላብ እያጠመቀኝ
ለአየርህ ርቄ ሞቼ ነበር ምገኝ
ግን ጥላህ ከለለኝ! !
ዛሬ በዓዲስ ተስፋ ...
ሀይቁ ዳር ቆሜ መረቤን ወደርሁት
አፋፉ ላይ ቁሜ ወንጭፌን አሾርሁት
ምድር ከፍሬዋ ዘግና ስትችረኝ
ከአላፊው ርቄ በህላዌ ስገኝ
ያንተ ከለላ ነው እኔን የሚታየኝ ።
እንጂማ እንደ አምናው የመዓት ሰቆቃ
ተስፋና እድሌ በሙቅ ብረት ታንቃ
መራመድ ተስኖኝ እግሬን ሳላነሳ
አንክሼ ነበረ ወቅቱን የማወሳ ።
አሁን ተዚህ ስደርስ.. .
በዓለሟ ሽክርክር ቀናቴን ገርስሼ
ካቀረቀርሁበት
ዳግም ቀና እያልሁኝ ስፍራህን አስሼ
ለአፍ ይምሰል ድርጊት ቃላትን ሳልሰፋ
እንዳለሁ በተስፋ ...
አምላክ የለም ያለኝ የሳይንስ አዋቂ
አንባቢውን አንቂ ...
እመን በሙከራ ...እመን በምርምር ብሎ ሲናገረኝ
ሳልመራመርህ በመረመርከኝ ነው ተገርሜ የምገኝ።
ይልቅ እንካ ውሰድ የድርጎህን ድርሻ
ያንተን ቸርነትን ነው ነገም ላይ የምሻ።
ተመስገን !!

@getem
@getem
@getem

#mikael aschenaki