ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሠማይም_ያለቅሳል

በንፁህ ልብ ኖሮ
በፍቅር ጎን አድሮ
በሠላም ክንፍ በሮ
ፍጥረተ ዘመኑን
ጊዚያተ ዕድሜውን
ጥሩ ሠው የቀረ ዕለት
መልካም ሠው ያለፈ ዕለት
ሠማይም ያለቅሳል
በረጠበ ምድር ወዳጁን ይሸኛል
~~~~~~~~~~~~~~~~
#ተክለ_ዮሀንስ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
#ውሻ_በዘመን

ድሮ

ውሻ በቀደደው ጅብ ነበር እሚሾልከው
ቤተስኪያን ቅጥር ለዐይን ነው የተጠላው

አሁን

ውሻ የሚቀደው አጥቷል
አጥሩም ወድቋል
ጅቡ በቀን ገብቶ ቤቱን አፍርሶታል
ቤተስኪያኑም ውስጥ ውሻው እጥፍ ሆኗል
ፅላት እየሸጠ ምህመን ይነክሳል
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ተክለ_ዮሀንስ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
#እምነት_ተስፋ_ፍቅር_አብረው_ይኖራሉ_ከሁሉም_የሚበልጠው_ፍቅር_ነው!!!

በጋራችን ቤት ውሾች ይጮዋሉ
አትመጥንክም እያሉ
አትመጥናትም እያሉ
ፍቅርን መለካት መመዘን ይሻሉ

የሚመጥን ፍቅር ዋጋው ምን ያህል ነው
የፍቅርስ መለኪያ ሚዛኑ ምንድን ነው
ሃይማኖት የሌለው!
ዘር የማይወክለው!
ፍቅር ብቻውን ሌላ ፕላኔት ነው

እውነት እና ተስፋ ፍቅርን ካልበለጡ
በፍቅር አርማ መንገድ በስሜት ከወጡ
መዋደድ ነው ደስታ
መፋቀር ነው ፌሽታ

ሺ ጊዜ ብለይሽ ውሏችን ባይገጥም
ሃይማኖት እምነትሽ ግርግዳው ቢቆምም
አሻግሬ እያየው ናፍቆቱን አልችልም
ግንቡ ይፍረስና ድልድዩ  ይሰራ
ሂጃብና መስቀል በአንድ ላይ ይጠራ
አራም ይሉ ሃጢያት
ለገደሉ እንጂ ላፈቀሩ ያቁም ቅጣት

ጎጆሽን ቀልሺ መቀነት ልሁንሽ
አላን ከሚፈራው ከሰጋጁ ልብሽ
ነይ አንቺም ግቢ ቀበቶዬ ሆነሽ
ፍቅርን ካስተማረኝ በእየሱስ ልውደድሽ

አጎቴ ሼህ ናቸው ከመስጊድ ያደሩ
አክስትሽ መነኩሴ ገዳም የቆጠሩ
ታዲያ በአንድ ጣራ ሕግ እያሰፉ
ከፍቅር ጎዳና እኛን እየገፉ
አረም ያበቅላሉ ዘሩን እያጠፉ

እናም ፍቅሬ አትገረሚ
ይጮዋሉ ውሾች በአላፊ አግዳሚው
እየጮዉ መብላት ነውና ኑሮዋቸው
አፈቅርሽው ብለው ሲጮዉ አትስሚ
ጆሮሽን ጠርቅመሽ የልብሽን ስሚ

እኔም ወድሻለው መስቀሌን ሳልበጥስ
ሂጃብሽ ይቀመጥ መስገድሽ ይቀደስ
ፍቅርን አስቀድመን ሕግጋቱን እንጣስ

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
:- #ተክለ_ዮሀንስ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
🍊🍊🍊🍊
ከንፁህ ቤት ወለል ቆሻሻዎች ገብተው
ያልተፈጠረውን ጠረን አስንፍጠው
ግርግዳ ጣራውም ፅዳት እየናቁ
ወደ ቤቱ ገብተው መዓዛ ሲያርቁ
ያረፈደችው እምቡጥ አበባ
ብርቱካን ድንቡሼ ወደቤት ብትገባ
ቆሻሻ ብቻ ነው ለሀገሩ የገባ
መሳሪያ ሸክፎ ላይፈታ ያደባ

#ተክለ_ዮሀንስ (ከሰባተኛ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
••••••#ስንሳሳት••••••

ሀበሻ ክፉ ነው ምቀኛ
ጥቁር ደደብ ነው ደበኛ
አፍሪካ ድሃ ነች ክፋተ ቋጥኝ
ብሎ ለሚፅፈው ለብዕረ ለማኝ
ነጫጭባ አምላኪ  ወኔ ቢስ አሊጫም
ከአንተ ዋላ መጥቶ ሲመርጥልህ ቀለም
ይሄንን ተመልከት በነጮቹ ዓለም
በኛ ላብ የቆሙ በደም ወዛችን ፍላጭ
መንበሩን ሰርቀውን ሆነው ፈላጭ ቆራጭ

በአባቶቻችን ሽመና በእናቶቻችን ልቃቂት
እነሱ ሰልጥነው ሲያስተምሩን ስፌት
ምቀኛ አይደሉም ቸር ናቸው አትበሉ
የኛን መውደቅ እንጂ መቆም ይፈራሉ
የጥቁር ንግስ ዕለት ገደል ይምሳሉ
ውል እያሳማሩ ፊርማ ይቀዳሉ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
:- #ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
** #ይሰማኛል *

ይሰማኛል ኮቴ ከፈረስ ሽዎና
ወኔ ከጨበጠ ከጋላቢው ጀግና

ይሰማኛል ዜማ ሽለላ ቀረርቶ
ተደፈርኩኝ የሚል ንጉስ ቀንድ አውጥቶ

ይሰማኛል ፀሎት ከፅላቱ እንፋሎት
መስቀልና ጦርን ከያዙ መናኩስት

ብዙ ነገር ዘመንን ተሻግሮ ሲሰማኝ
ቅኔ ተቃኝቶ
ዜማ ዘምሞ
ደም እየመነጨ ነፃ ወጣ ሲለኝ
እኔ ግን አለውኝ ባርነት ናፋቂ
ባህልና ወጌን ከብራናው ፋቂ

አያቴ ነበረ ወንድሙን ወዳጅ
ተደፈርኩኝ ብሎ ጠላቱን አሳዳጅ
አያቴም ነበረች የወንድ ንፅር ጀግና
በጦሩ አውድማ ፀንታ የምታፀና

ታዲያ የእሳት ልጅ አመድ እኔ
ፍራቻዬ ስር ሰዶ ከወንድነት መቅኔ
ባዶ ድንፋታ አዋቂ ነኝ አዋጅ
ጉራ እየነዛውኝ በጠላት ቤት ሰጋጅ
ቁማር ብቻ! ዘራፍ! አሉባልታ
ሀገር አትሸጥም ትከራይ ጨዋታ

ወይ እኔ ወንዱ የሐበሻው ዘር
ጦር የፈራው እጄ ጋሻ ሲደረድር
ለጠላቴ አፈሙዝ ወንድሜን የምድር
እኔ አዲስ ጀግና ታሪኬን የምሰብር
ምናገባኝ ትላንት የግል ኪሴን እማሰምር
 
ይሰማኛል ትዝብት ደሞ ደግሞ
ሀገር ከቁርበት ላይ በጠናውም ታሞ
ጠባብ ልጆች ወልዶ ሰፊ አሳቢ ጠፍቶ
ሀገራዊ ፍቅሩ በመንደር ተሰፍቶ

ይሄን እንዴት ልየው እንዴት ይግባኝ ሀገር
ተሸንሽኜ እያየው በድንበርና ዘር
አርበኝነት ቅኔው ከየትስ ይሰማኝ
የሀገር ቀሚሷስ ደፋሪ እንዴት ይግባኝ
ወንድም ወንድሙን ገደለው እያሉኝ
እህት በእህቷ ላይ ዶለተች እያሉኝ
የሀገር ደሜ ሞቶ ለብሔር ቆሰልኩኝ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
:- #ተክለ_ዮሀንስ

@getem
@getem
#ጥያቄ

ምንም አልፀልይም
ጥያቄም የለኝም
እንደዛ አደረጉ እንደዚም አልልም
ይሄ የኔ ዕጣ ነው ከቶ አላማርርም

ግን  ፈጣሪ  አንተ ሁሉን አውቃ
ካልጠፋህ ሁሉ ሀብት ካልጠፋህ ሁሉ ዕቃ
ልጅነቴ ምን አረገ ጭራሽ ምን አጠፋ
ለዚች ቡርቲ ዓለም ቁራጭ ተስፋ ጠፋ ?

ጡትም የትአባቱ ወተቱም ይቅርብኝ
እንዴት መሠረቴን እናቴን ነፈከኝ
ጥያቄ እኮ አይደለም አሁን የምነግር
ትዝብት ቢጤ ነው ግርምት የማስጭር
አረ እንዲያው ፈጣሪ የምር ግን እንዲያው
ከስሜ ቀጥሎ የአባቴ ስም ማነው
ድህነት ነው ?
ናፍቆት ነው ?
ብቸኝነትስ ነው ?
ቅናት ቢጤ ቂም ነው ?
ወይስ ተስፉ ቢስ ፅልመት ነው ?

እኔን ግራ የገባኝ
አዲስ ቅኔ አለኝ
ታርዤ ሳለሁኝ ብርዱ የማይደፍረኝ
ቁራሽ የናፈቀኝ ደርሶ የማይርበኝ
መነሻዬስ እንጃ መድረሻም የሌለኝ
ብዬ እንዳልናገር እኔ ባዶ ሠው ነኝ
ምንጩ የማይገባኝ የሆኔ ሙሌት አለኝ

አዲስ ግራ! አዲስ ቀኝ!

ግራዬ ቀኝ ነው
መጥፎ ህልሜ ሁሉ ሠላም ነው መፈቻው
ቀኜም ግራ ነው
ድሎቴ በሙሉ ሚስጥር ነው መነሻው

ግን ፈጣሪ ምንድን ነው የሌለኝ ?
ምንድን ነውስ ያለኝ ?
በባዶ መዳፌ ሺ ነው እሚጠግብብኝ
ቤሳቤስቲ ሳልሰጥ ህልፍ ነው እሚያፈቅረኝ
አጃቢው የበዛው እምባ ሲሆኑ ውሉ
ብቻዬን ሳለሁኝ ማንም ጋር የሌሉ
ብዙ ፈገግታዎች ከኔ ብቻ አሉ

ያም ሆነ ይህ ጠንካራው ፈጣሪ
በአንተ ተስፋ መንገድ በፍቅርህ ስባሪ
ምድረ አዳም የሌለው ባንተ ብቻ ያለው
የኔና አንተ ፍቅር ምክንያቱ ምንድን ነው?
ካጣዋቸው ሁሉ ባዶ ከሚመስሉት
የአንተ ኩርማን ተስፋ ጥሜን የሚያረኩት
እኔ ጋር ያለው ነው ከሁሉ እሚበልጡት ?
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
:- #ተክለ_ዮሀንስ

@getem
@getem
#ቤተ_ጥበብ

ያቺ አዛኝቱ የምጥ ቤቴ ወዳጄ
በሽልም ተብዬ የገባጅ ከእጄ
የሺህዎች ተስፋ የሁላችን እናት
አሀዱ እናቴ #ማርያም እናቴ ናት

ደግሞ ይቀጥላል የእናት ወግ ጥምረቴ
ከነፍስዋ ነፍስ ከስጋዋ እትብቴ
ሀ ግዕዝ ማዕዴ
ሀ ግዕዝ ዘመዴ
የዚች ከንቱ ዓለም አጋሬ ምርኩዜ
የፈጣሪ ጥበብ ሠውኛ አባዜ
የስጋ እናቴ ነች የተስፋ ደሙዜ
የነገ አዲስ ቃና የፍቅራችን ዘዬ
አንዱ ዘለላ ነች ለመኖር #ፋንታዬ

ቀጥሎ ቀጥሎ የሠለሠው ፍቅሬ
ሀገር ይሏት እናት አለችኝ ሠንበሬ
የልቤ ግርፋት ማህተብ ለደምስሬ
እርጅና ያጎበጣት
ወንደሜ ያቆሠላት
ሠካራሙ አባቴ ቤቷን የሚመራው
ለመለኪያው ክብር መቀነቷን የሚዘርፈው
አንጀቷን አቁሱሎ ደሟን የመጠጠው
አንገት የደፋችው ኩሩዋ እመቤት
#ኢትዮጵያ እናቴ ናት

ከነኚህ ከሦስቱ ከውድ እናቶቼ
ጉሎበቴ ጠንክሮ ዕርዳታዬ ቢደርስ
ዕውቀቴ ጎልብቶ ካሻው ቦታ ሲደርስ
ጦቢያ እናቴን ቀና አረጋታለው
ያረጀ ወገቧን ጡረታ የተጠማው
በአዲስ መቀነት ነው ሸብ የማደርገው!!!
__________________________

#ኢትዮጵያ_በእናትነት_ለዘላለም_ትኑር!!!
#ማርያም #ኢትዮጵያ #ፋንትዬ
#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem
@getem
👍1
🕴🕴🕴 #እጠብቅሻለው 🕴🕴🕴

እጠብቅሻለው ጠሀይ እስክትወጣ
የአህዋፍ ዜማ ከቤቴ እስኪመጣ
ጤዛ ተባዝታ እስክትመስል ጎርፍ
የህንቅልፍ አድባራት እስኪወጡብኝ ሠልፍ
ስሜ ተጋግሮ እስኪበስል በሠው አፍ

ለኔስ እንኳ ቢቀር ለስምሽ እዘኚ
አንቺ ስትጠፊ እብደት ጀመሮኚ
መድሃኒት አቅማሺ ጠንቋ እንዳትሰኚ
ጠንቋይስ ይበሉሽ ለአማኝ መላ ሃለው
ሽፍታ ያሉሽ እንደው ልቤ መድረሻ የለው
ወህኒ ያየውሽ ዕለት እኔስ እሞታለው
ያም ሆነ ይህ ግን እጠብቅሻለው!

ንፁህ ልብ ታቅፌ ናፍቆትሽን ይዤ
በኔና አንቺ ዓለም በይሆናል ፈዝዤ
በትላንት ትዝታ ነገሽን አርግዤ
እጠብቅሻለው በፍቅርሽ ተይዤ

እንዲያው በዚህ ጊዜ በበዛበት በሩ
መሄድሽ ምንድን ነው መራቅሽ ሚስጥሩ
ከግለሰብ አልፎ ሕዝቦች ሲፋቀሩ
ለኔና አንቺ ብቻ የት ጠፋ ቀመሩ?

ለጨረቃ ፀልይ እሷ መላ አታጣ
ቢለኝ በፍቅራችን አንቺን ከኔ ያጣ
ተንበርክኬ አደርኩ አሸን ምሽቶችን
ከአልጋዬ ተኳረፍኩ አሸን ለሊቶችን
ስቶጣ እየወጣው ስትገባ እየገባው
ጨረቃን አምኜ እሷን ብቻ እሻለው

እንደኔ እንደኔ ሁሉም መላ ቢስ ነው
በዚ በዛ ቀይስ መካሪው ብዙ ነው
እኔስ ሞኝ ሆንኩ እንጂ ጨረቃ ምን አውቃ
ሚስቴን አምጪ ብዬ መሃልት የምነቃ
እያወኩኝ ኖሮ ለቁራሽ ብርሃን ጠሀይን መጣበቋ
ምንድን ነው ግን ጉዱ አንቺ ያለሽበት
ስሪቱ ምሽግሽ አድራሻውስ ከየት?

ያም ሆነ ይህ እጠብቅሻለው
ትዝታሽም እቴ እንዳቺው ጀግና ነው
የልቤ በራፍ ላይ ጥላውን ያጠላው
ሲያሻው የሚገለኝ
ሲያሻው የሚያኖረኝ
ጠብቃት እያለ ተረት የሚያወራኝ
በባዶ ሜዳ ላይ ጉያሽ የሚከተኝ
ገዳይ ትዝታሽ ነው ጠብቃት የሚለኝ

ባይገባኝም ግን እጠብቅሻለው!
ወረት አልባ ፍቅሬን የት አደርሰዋለው

ባልደርስብሽም ግን እጠብቅሻለው!
ዘመን አልፎኝ ሞቼ ለፍርድ አይሻለው

ባላይሽም ግን እጠብቅሻለው!
ባልሄደው ትዝታሽ ጃጅቼ! አርጅቼ! አንቺን አስባለው

በፈጣሪ ስራ በምፅሃት ዕድሜ
አንቺን ብቻ ብዬ እስኪጠፋኝ ስሜ
ትዝታሽ ብሶበት እሱ እስኪሆነኝ ደሜ

እጠብቅሻለው! እጠብቅሻለው! እጠብቅሻለው!
ጥበቃ እንኳ ቢያልቅ ጥበቃን ጠብቄ እጠብቅሻለው!

=================================

ሠው ብዙ ነገርን ይጠብቃል ተስፋን! ዕድሉን! ቀኑን! ንብረቱን! ብዙ ብዙ ነገር ይጠብቃል ግን ሁሉም በየሆነ ቀን ያበቃሉ እውነተኛ አፍቃሪ ግን መጠበቅ አይደክመውም!!!

#ፍቅር_ለዘላለም_ትኑር!!!

:- #ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)
@Addisumerkato

@getem
@getem
~~☞ #የተገዘተ_ሠማይ ☜~~
ቀንን በፀሀይ ማታን በጨረቃ
ሠማይ እንደዛ ነች ሲያይዋት ምታነቃ
የቸኮለ መሪጌታ ገዝቶ ሳይተዋት
ነካክቶ አደፍርሶ ውበቷን ሳይነጥቃት
.
ሠማያዊ ዐይኗን በጉም የተኳለች
የንጋት ፈገግታዋን በፀሀይ ያደመቀች
የለሊት ኩርፊያዋን በጨረቃ የደበቀች
ማንም ወጥቶ ወርዶ ብሎም አስሮ ፈቶ
በቀኗም ሰርቶባት በለሊቷም ተኝቶ
ባልፈታው ቅኔዋ አፅናፏን ቃኝቶ
ከወዲያ ወዲህ ባዝቶ ዋትቶ
ከሷ በላይ ላሰበው ቀና ብሎ ተሰውቶ
መገዘቷንም ሳያውቅ መፈታትዋን የሚያጋንን
የኔ ቢጤ የተከፋ አንጋጦ የሚለምን
.
ወና ጎጆ ውስጥ ሰፊ ልቡን ያከተመ
በማይገባው ተስፋ ነገውን ያስታመመ
ድሃ የሚባልን ተረት አፏን በዳቦ ሊያብስ
ከተገዘተች ሠማይ ስር ቢቅለሰለስ
ሃብታም ይሉት በራሪ ክንዷ ላይ ቢንተራስ
.
የተፈታ አካሏን አስገዝቶ ቢያቆላልፍ
የታችኛው ድሃ የመሬቱ ሠፈፍ
የተገዘተ ሠማይ ይዞ ለማስፈታት የሚሠለፍ
------------ $ --------
፡-#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem
@getem
🤔🤔🤔 #የገባኝ 🤔🤔🤔

በኖሩኳቸው ትንሽ ዕድሜዎች
ባየዋቸው ጥቂት ሁነቶች
ሁሌም የሚገባኝ
ሁሌም የሚታየኝ
መድረሻዬ ነው ፍቅርሽ
ማብቂያዬ ነው ሴትነትሽ
አየሽ በትላንቴ ሸራ በብሩሼ ቀለም
መልክሽን እንጂ አንቺን መሣል አልችልም
ሠነፍ አትበዩኝ ሠንፌ እኮ አይደለም
የዕውቀቴ መጠን በአንቺ አይለካም
ይለካ እንኳን ቢባል መለኪያ የለውም
ብቻ ምን አለፋሽ ድፍረትን ደፍሬ
ፍቅሬን በትዝታሽ ሚዛን ሠፍሬ
ይሄን አስመሰልኩት ምኞቴን ቀምሬ
ነገን በዛሬ ላይ አዲስ ቀን ጀምሬ
የአዙሪቴ ጥጉ አንቺ ሆነሻል ፍቅሬ

ግን እኮ መድፈሩንስ ልድፈር
ስህተቱም ይሁን በኔ ይጀመር
እኔ የምፈራው እኔ የምሰጋው
በአንቺ እየታሰብኩ
በአንቺ እየታወኩ
የኔ የምለው እኔነቴ ጠፍቶ
አንቺ እንዳልባል ወንድነቴ ቀርቶ
ስር የሌለው ቅፅል መሰረት መስርቶ
አንቺ ላጲስ ሆነሽ እስራስ ሆኜ እኔ
እየሳልኩሽ ኖሬ በአላቂ ዘመኔ
እየሳልኩሽ ልሙት ለፍቅር ስህል ቅኔ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1