ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ጥያቄ

ምንም አልፀልይም
ጥያቄም የለኝም
እንደዛ አደረጉ እንደዚም አልልም
ይሄ የኔ ዕጣ ነው ከቶ አላማርርም

ግን  ፈጣሪ  አንተ ሁሉን አውቃ
ካልጠፋህ ሁሉ ሀብት ካልጠፋህ ሁሉ ዕቃ
ልጅነቴ ምን አረገ ጭራሽ ምን አጠፋ
ለዚች ቡርቲ ዓለም ቁራጭ ተስፋ ጠፋ ?

ጡትም የትአባቱ ወተቱም ይቅርብኝ
እንዴት መሠረቴን እናቴን ነፈከኝ
ጥያቄ እኮ አይደለም አሁን የምነግር
ትዝብት ቢጤ ነው ግርምት የማስጭር
አረ እንዲያው ፈጣሪ የምር ግን እንዲያው
ከስሜ ቀጥሎ የአባቴ ስም ማነው
ድህነት ነው ?
ናፍቆት ነው ?
ብቸኝነትስ ነው ?
ቅናት ቢጤ ቂም ነው ?
ወይስ ተስፉ ቢስ ፅልመት ነው ?

እኔን ግራ የገባኝ
አዲስ ቅኔ አለኝ
ታርዤ ሳለሁኝ ብርዱ የማይደፍረኝ
ቁራሽ የናፈቀኝ ደርሶ የማይርበኝ
መነሻዬስ እንጃ መድረሻም የሌለኝ
ብዬ እንዳልናገር እኔ ባዶ ሠው ነኝ
ምንጩ የማይገባኝ የሆኔ ሙሌት አለኝ

አዲስ ግራ! አዲስ ቀኝ!

ግራዬ ቀኝ ነው
መጥፎ ህልሜ ሁሉ ሠላም ነው መፈቻው
ቀኜም ግራ ነው
ድሎቴ በሙሉ ሚስጥር ነው መነሻው

ግን ፈጣሪ ምንድን ነው የሌለኝ ?
ምንድን ነውስ ያለኝ ?
በባዶ መዳፌ ሺ ነው እሚጠግብብኝ
ቤሳቤስቲ ሳልሰጥ ህልፍ ነው እሚያፈቅረኝ
አጃቢው የበዛው እምባ ሲሆኑ ውሉ
ብቻዬን ሳለሁኝ ማንም ጋር የሌሉ
ብዙ ፈገግታዎች ከኔ ብቻ አሉ

ያም ሆነ ይህ ጠንካራው ፈጣሪ
በአንተ ተስፋ መንገድ በፍቅርህ ስባሪ
ምድረ አዳም የሌለው ባንተ ብቻ ያለው
የኔና አንተ ፍቅር ምክንያቱ ምንድን ነው?
ካጣዋቸው ሁሉ ባዶ ከሚመስሉት
የአንተ ኩርማን ተስፋ ጥሜን የሚያረኩት
እኔ ጋር ያለው ነው ከሁሉ እሚበልጡት ?
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
:- #ተክለ_ዮሀንስ

@getem
@getem
#የመልስሽ #ጥያቄ

#እኔ #ምልሽ
የእንባችን ገንቦ ~ ሳይሰበር በፊት
ይፈስ ነበር አይደል ~ በሳቃችን ግፊት
የተፈጥሮስ ሂደት ~ እንዲህ ሳይጓደል
ከልብ እየሳቁ ~ ማልቀስ ነበር አይደል ?

#እኮ
#እኛ #እኮ #ነን
ሀዘንን በደስታ _ እያነሳን ልንጥል
ስሜታችን ቆርጠን _ ስሌት ልንቀጥል
በአንድ ወገን ስለነው ~የተፈጥሮን መቀስ
በየተራ ሆኗል ~ መሳቅና ማልቀስ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@getem
(አዳም ሳተ
ከገነትም ተጎተተ
አዳም ከገነት ሲባረር
እነሆ እርቃኑን ነበር
በዕውቀቱ ስዩም)

ክፍል 4 #ጥያቄ_ምልክት

ሰይጣን አሳሳተኝ ይላል
ከክፉ ሲውል ሰው
በሌላ ዓይን ደሞ
ራሱን ሳይዳኘው
ሰው ሰውን ወቀሰው።

ሰው ሲያጠፋ
ሰው ሲቆሽሽ ሰይጣን ከተባለ
በዚች ምድር
ፃድቅ እንጂ ሃፅያን መች ኖረ
የሰው ጥፋት ሳይሆን
የሰይጣን ከተባለ።

እንዲያው እግዜር ፈቅዶ ቢሰጣችሁ ስልጣን
ጥፋተኛው ማነው
ሰው ነው ወይስ ሰይጣን?

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍294