ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ‼️

ማርያም ተስፋዬን እንታደግ!

ከላይ በፎቶው የምትመለከቷት ታዳጊ ወጣት #ማርያም_ተስፋዬ ስትባል የሁለተኛ አመት የጥቁር አንበሳ የህክምና ተማሪ ናት። በደረሰባት የልብ በሽታ (Rheumatic Heart Disease) ምክንያት ለአንድ አመት ያህል በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስትረዳ ቆይታ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ ወደ ኤሉዜይር የልብ ህክምና ሪፈር ተፅፎላታል። በመሆኑም ለህክምና የተጠየቀችው 180,000 ብር ከቤተሰቦቿ አቅም በላይ ስለሆነ ለዚህች የነገ ነብስ አድን ሀኪም ሁሉም እጁን እንዲዘረጋ በትህትና እንጠይቃለን ።


የእህቷ የባንክ አካውንት፦
1000199636875 (ሜሪ ተስፋዬ)
አንድ ላይ ስንሆን እንችላለን!
1 ሳምንት ብቻ ነው ያለን

ለበለጠ መረጃ፦
+251910188584
+251926242785

🔹ገንዘቡ በአንድ ሳምንት ውስጥ መገኘት ስላለበት ሁላችንም ርብርብ እናድርግ!

ማርያም 100% ትድኛለሽ‼️

(ሼር ያድርጉት)
@getem
@getem
#ቤተ_ጥበብ

ያቺ አዛኝቱ የምጥ ቤቴ ወዳጄ
በሽልም ተብዬ የገባጅ ከእጄ
የሺህዎች ተስፋ የሁላችን እናት
አሀዱ እናቴ #ማርያም እናቴ ናት

ደግሞ ይቀጥላል የእናት ወግ ጥምረቴ
ከነፍስዋ ነፍስ ከስጋዋ እትብቴ
ሀ ግዕዝ ማዕዴ
ሀ ግዕዝ ዘመዴ
የዚች ከንቱ ዓለም አጋሬ ምርኩዜ
የፈጣሪ ጥበብ ሠውኛ አባዜ
የስጋ እናቴ ነች የተስፋ ደሙዜ
የነገ አዲስ ቃና የፍቅራችን ዘዬ
አንዱ ዘለላ ነች ለመኖር #ፋንታዬ

ቀጥሎ ቀጥሎ የሠለሠው ፍቅሬ
ሀገር ይሏት እናት አለችኝ ሠንበሬ
የልቤ ግርፋት ማህተብ ለደምስሬ
እርጅና ያጎበጣት
ወንደሜ ያቆሠላት
ሠካራሙ አባቴ ቤቷን የሚመራው
ለመለኪያው ክብር መቀነቷን የሚዘርፈው
አንጀቷን አቁሱሎ ደሟን የመጠጠው
አንገት የደፋችው ኩሩዋ እመቤት
#ኢትዮጵያ እናቴ ናት

ከነኚህ ከሦስቱ ከውድ እናቶቼ
ጉሎበቴ ጠንክሮ ዕርዳታዬ ቢደርስ
ዕውቀቴ ጎልብቶ ካሻው ቦታ ሲደርስ
ጦቢያ እናቴን ቀና አረጋታለው
ያረጀ ወገቧን ጡረታ የተጠማው
በአዲስ መቀነት ነው ሸብ የማደርገው!!!
__________________________

#ኢትዮጵያ_በእናትነት_ለዘላለም_ትኑር!!!
#ማርያም #ኢትዮጵያ #ፋንትዬ
#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem
@getem
👍1